• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል!

December 25, 2013 09:39 am by Editor 1 Comment

በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ አንምሳደር ዘነበ ከበደ የሚመሩ የመንግስት ሹማምንቶች ጅዳ ከተማ ውስጥ መሽገዋል ያሏቸው 80 ሺህ ኢትዮጵያውያን እጃቸውን በሰላም ካልሰጡ የመንፉሃው አይነት እልቂት እንደሚጠብቃቸው ሲያሙዋርቱ! ሪያድ በኢትዮጵያው አንምሳደር መሃመድ ሃሰን የሚመራው ቡድን የሚያሰማው «ጅብ ከሄድ ውሻ ጮህ ጥሪ» ድብቅ አጀንዳ ያለው መሆኑ ተገለጸ !

ከ9 ሚሊዮን በላይ የተለያዩ የውጭ ሃገር ዜጎች በጥገኝ ነት እንደሚኖሩባት የምትታወቀው ሳውዲ አረቢያ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሃገር ዜጎች የመኖሪያ ፈቃዶቻቸውን እንዲያስተካከሉ የተሰጠ የ 7 ወር የግዜ ገደብ መጠናቀቅን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች ከ 3 መቶ ሺህ በማይበልጡ ኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ ባነጣጠረው እርምጃ እስካሁን ቁጥሩ በወል ለማይታወቅ ወገናችን አሰቃቂ ህልፈተ ህይወት ስቃይ እና መከራ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል። በተለይ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራ ሰፈር ሃገራቸው ለመግባት ጥያቄ ባቀረቡ ወገኖቻችን እና በሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች መሃከል በተነሳ ግጭት አያሌ እህቶቻችን በአረብ ጎረምሶች «ሸባብ» ተደፍረዋል ከዚህም በላይ እህቶቻቸውን እና ሚስቶቻቸውን ከአስገዶ መደፈር ጾታዊ ጥቃት ለመከላከል ጩሀታቸውን ያሰሙ ንጹሃን ወገኖች በአሰቃቂ ሁኔታ በሳንጃ እና በጓራዴ ተገድለዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻች ከዚህ ስበእና ከጎደለው ጥቃት እርሳቸውን ለመታደግ ከዳር እስከዳር «ሆ»ብለው አደባባይ በመውጣት እና የሳውዲ አረቢያ አውራጎዳናዎችን በማጨናነቅ የአለምን መገናኛ ብዙን ሽፋን ማግኘታቸውን ተከትሎ በሳውዲ አረቢያ በጠራራ ፀሃይ እና በሌሊት በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸም የነበረው ጭፍጨፋ ስቃይ እና በደል በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚገኙ ወገኖቻቸውን ዘንድ የቀሰቀሰው ቁጣ በሳውዲ መንግስት ላይ ባሳረፈው ተጸዕኖ በማን አለብኝነት በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸም የነረውን ኢሰባዊ ድርጊት ለግዜውም ቢሆን ጋብ እንዲል አስችሏል።

የኢትዮጵያኑ አለማቀፍዊ ቁጣ ያስደነገጠው የሳውዲ አረቢያን መንግስት በሚልዮን ለሚቆጠሩ የውጭ፡ሃገር ዜጎች ያወጣውን ህግ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ ለማተኮር አስገድዶታል። ይህ በዚህ እንዳለ እስካሁን በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያ ውያን ስደተኞች የስውዲ አረቢያን ምድር በሰላም ለቀው ለሃገራቸው እንደብቁ የሚናገሩ ምንጮች አሁንም 80 ሺህ ህገወጥ ኢትዮጵያውያን ጅዳ ጣይፈ መካ መዲና በሚባሉ ከተሞች ውስጥ መሸገዋል ተብሎ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት እየተሰጠ ያለው መግለጫ ቅንነት የጎደለው መሆኑንን ይገልጻሉ። በሃጂ እና ኡምራ አሊያም በባህር ወደ ሳውዲ ምድር ድንበር አቅርጠው ህገወጥ፡በሆነ መንገድ ገብተውል ተብለው የሚነገርላቸው ኢትዮጵያውያን ያሉበትን ሁኔታ የማይዘረዘርው በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት የመንግስት ሹማምንቶች መግለጫ ህገወጥ የተባሉት ወገኖች በጊዜ እጃቸውን ሰጠተው ወደ ሃገር ካልተመልሱ በሪያድ መንፉሃ የተከስተው አይነት አልቂት እንደሚከተላቸው አስጠንቅቀዋል።

ይህ በጅዳው ቆንስል ዘነበ ከበደ የሚመራው ጽ/ቤት ሰሞኑንን እያሰማን ያለው ጩህት ወገናዊነት የጎደለው እና ሳውዲያኖቹ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ በማነጣጠር መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ጭምር ከሳውዲ ምድር ጠራርጎ ለማስወጣት የተያዘ እቅድ አንዱ አካል መሆኑንን የሚናገሩ የጅዳ ነዋሪዎች የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ወገኖች በሳውዲ ምድር በሰላም ሰርቶ የመኖር ህልውናቸው አስተማማኝ ባልሆነበት አጋጣሚ እንደዚህ አይነት መግለጫ ማውጣት ሃላፊነት የጎደለው መሆኑንን አክለው ይገልጻሉ። እንዚህ ወገኖች የጅዳው ቆንስላ ጽ/ቤት እንደዚህ አይነት አስገራሚ መረጃ በአረብኛ እና በአማርኛ ቋንቋ በተዘጋጁ በራሪ ወረቅቶች ቅስቀሳ ማካሄዱ ትላንት ሪያድ ከተማ መንፉሃ ውስጥ፡ቆጨራ እና ሳንጃ ታጥቀዋል የሚል የተሳስተ መለዕክት በማስተላለፍ የገዛ ወገኖቻቸውን ካስፈጁት በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አንባሳደር መሃመድ ሃሰን ስህተት የማይለይ መሆኑንን ይናገራሉ።

በሌላ በኩል ሰሞኑንን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ በየጥጋጥጉ ማስታወቂያዎችን በመለጠፍ እና በራሪ ወረቀቶች በመበትን ስራ ተጠምዶ የከረመው ቡድን እያሰማ ያለው የተለመደ የአዞ እንባ «ጅብ ከሄደ ውሻ ጮህ» መሆኑንን የሚገልጹ የሪያድ ነዋሪዎች የምህረቱን አዋጅ ተከትሎ ጉዳዮቻቸውን እስካሁን ማስፈጸም ተስኗቸው በሳውዲ አረቢያ ውስጥ ለመኖር የሚያስችሏቸውን ማመዘኛ ያላሞሉ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ እየቀረቡ ምዝገባ እንዲያካሂዱ የሚለው መለዕክት ለኢትዮጵያውያኑ ታስቦ ሳይሆን ዲፕሎማቱ የተለመደውን ድብቅ አጀንዳቸውን በቀሪው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ላይ ለማስፈጸም እንደሆነ ይገልጻሉ።eth embassy saudi

የገበያ ግርግር ለምን ያመቻል እንዲሉ በተለያዩ አቅጣጫዎች ያለደረስኝ በወገኖቻችን ስም በመቶሺ የሚቆጠሩ ሪያሎችን በመሰብሰብ ላይ የሚገኙት በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች አሁንም ለመዝገብ ከሚመጡ ወገኖች ኪስ ለተለያዩ ገዳዮች ማስፈጸሚ የሚውል ገንዘብ ለመሰብሰብ እቀድ እንዳላቸው ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል። የኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክቡር ቴድሮስ አድሃኖም በወገኖቻችን ላይ ለተፈጸመው አስቃቂ ግድያ ግፍ እና በደል ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ የገቡትን ቃል ከፖለቲካ ግበአትነት እንደማያልፍ የሚናገሩ ወገኖች የኢትዮጵያ መንግስት በሳውዲ አረቢያ መንግስት ላይ ያሳረፈው ምንም አይነት ዲፕሎማሲያዊ ተጸኖ ባለመኖሩ ሳውዲያኑ ለኢትዮጵያውያኑ ያላቸው ጥላቻ አገርሽቶ በሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን «በስፖንሰሮቻቸው» የመኖሪያ ፈቃዳቻቸው በመሰረዙ አያሌ ወገኖች ለህገወጥነት እይተዳረጉ መሆናቸው ይናገራሉ።

ይህ በዚህ እንዳለ ይህን ዜና ከተጠናከረ በኃላ ቀደም ሲል በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ባወጣው ማስታወቂያ መስረት ሰሞኑንን ሲመዘገቡ የነበሩ ወገኖቻችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ሃገራቸው መግባት እንዳለባቸው ኤንባሲው ያስታወቀ መሆኑንን የሪያድ ምንጮች ገልጸዋል። ለዚህም ኤንባሲው በስሩ በሚገኙ የልማት ማህበራት ህዝበ ነዋሪውን በየጎጡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ፡በማስጠራት የመኖሪያ ፈቃድ ያለው ኢትዮጵያዊ ጭምር ከሶስት ወር በፊት ሀገሪቱን ለቆ መወጣት እንደሚጠበቅበት ለማግባባት ያደረገው ሙከራ ከፈተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው የሚናገሩ ወገኖች የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ካርታ አሲዘው አሊያም ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቻቸውን በመሸጥ እስከ 60 እና 70 ሺህ ሪያል አውጥተው የገዙትን መኖሪያ ፈቃዶቻቸውን ሰርዘው ሃገር እንዲገቡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ እያሰማ ያለው ጩኽት በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን መቀስቀሱን አክለው ገልጸዋል።

Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ የላኩት

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. adnankedir says

    December 27, 2013 06:20 pm at 6:20 pm

    ዉድ፣በለቤቴ:ወ/ሮ:ነጃቴ:አመን:ኡማር:ግንቦት:26/2005አ/ም:ነብሰቸዉን:የለወቁ3ልጆቿወንጥለብኝ፤ወደ:ጅደሄደ:የሰረች:በሰረዋ:አህመድእብረህምነበቤተሰቦቹበደረሰበትጨነ:ወደ:ሀገሬሸኙኝሰትልአሰሬወ፡በዝቦረቴን፡በመሰጠት፡ለፖልስ:አስረክቦት፡ጅደ:የምገኘዉ:ጎተመለ:የሚበለዉ:ትልቁ:እስር:ቤት:ከመሰሎቼ:ገረ:ተስሬ:ተምሜ:እየተሰቀዬሁኝነዉ፡ብለ:የዘሬ:ሁለት:ወረ:አከበቢ፡ከደወለችልኝ:ቦሀለ:አድረሸዋ:ጠፍቶብኛል፡ስለዝህ:ጉደዩን:አጠርተቸሁ:በዝህአድረሸ፡እንድተሰዉቁኝ:እጠይቀለሁኝ::

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule