• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጉቦ በመቀበል እስረኞችን የለቀቁ ታሰሩ!

December 16, 2013 06:24 am by Editor 2 Comments

ከ300 እስከ 500 ሺህ ብር እየተቀበሉ በሀሰተኛ ሰነድ ታራሚዎችን ከማረሚያ እንዲወጡ አስደርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሶስት የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የስራ ሀላፊዎችና አምስት ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ተጠርጣሪዎቹ ኦፊሰር ገብረመድህን አረጋ፣ ረዳት ኦፊሰር ኢሳያስ ከበደና ዋርደር ኢብራሂም መሀመድ ሲሆኑ፥ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የእስረኞች አስተዳደር የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ናቸው።

ከእነዚህ የስራ ሃላፊዎች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት የተቀሩት ግለሰቦች ደግሞ ፥ በንግድ ስራ ይተዳደር የነበረው አቶ ሰለሞን ገለታ፣ አቶ ብሩክ ሀይሌ፣ ወይዘሪት ሳባ ገብረሚካኤል፣ አቶ ናታን ዘላለምና አቶ ቴዎድሮስ ግደይ ናቸው።

የፌደራሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን  መርማሪ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ የወንጀል ችሎት ባቀረበው የጊዜ ቀጠሮ ማመልከቻ ላይ እንደተመለከተው፥ ከሳባ ገብረሚካኤል ውጪ እነዚህ በንግድ ስራ ይተዳደሩ የነበሩ ግለሰቦች ቀደም ሲል በተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸውና በማረሚያ ቤት የእስራት ጊዜያቸውን ጨርሰው የወጡ ናቸው።

እንደ መርማሪው ማመልከቻ ሳባ ገብረሚካኤል በኮምፒውተር ፅሁፍ እያገዘቻቸው፥ በንግድ ስራ የሚተዳደሩት ግለሰቦችም ከፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ታራሚዎች ከእስር የሚፈቱበትን ትዕዛዝ በሀሰተኛ መንገድ በማዘጋጀት እንዲሁም በሀሰተኛ ፊርማ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ማህተም በማስመሰል አዘጋጅተዋል።

በማረሚያ ቤት የሚገኙና ቅጣታቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆነ 300 ሺህ ብር ከዚያ በላይ ከሆነ ደግሞ 500 ሺህ ብር እየተቀበሉ ፥ ከ11 በላይ ታራሚዎችን በዚህ ሀሰተኛ ሰነድ ከእስር እንዲለቀቁ አድርገዋል ይላል።

የሚያገኙትንም ገንዘብ ለኦፊሰር ገብረመድህን አረጋ፣ ረዳት ኦፊሰር ኢሳያስ ከበደና ዋርደር ኢብራሂም መሀመድ ለተባሉት የማረሚያ ቤቱ የስራ ሀላፊዎች በመስጠታቸው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

በመርማሪው ማመልከቻ መሰረት እነዚህ የስራ ሃላፊዎች የነበሩ ተጠርጣሪዎች የእስር መፍቻ ደብዳቤው በሀሰተኛ መንገድ የተዘጋጀ እንደሆነ እያወቁ ታራሚዎች እንዲፈቱ በማድረጋቸው ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከሶስቱ የስራ ሀላፊዎች ውስጥ ኦፊሰር ገብረመድህን አረጋ ሀሰተኛ የእስር መፍቻ ካቀረበ አንድ ታራሚ 40 ሺህ ብር መቀበሉ ተመልክቷል።

የጊዜ ቀጠሮ ማመልከቻውን የተቀበለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ የወንጀል ችሎት ተጠርጣሪዎቹ ያቀረቡት የዋስትና መብት ጥያቄ ቢለቀቁ መረጃ ያጠፋሉ የሚለውን የመርማሪውን ተቃውሞ በመቀበል ፥ ጉዳያቸውን ማረሚያ ሆነው ይከታተሉ ብሏል። (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. በለው! says

    December 17, 2013 09:31 pm at 9:31 pm

    << በአድሃሪውና ባላባቱ ሥርዓት ፩ ጆንያ ከሰል፣ ፩ስልቻ ጥሬ እህልና ፭ ክንድ ጋቢ አጅ መንሻ ፩ ቀይ አወራዶሮን ጨምሮ ፤ በደረግ ዘመነ መንግስት ግን ተሻሽሎ በወጣው ስም የማዛወር ሥልጣንና ኀላፊነት ማናቸውም ከ፳ሺህ ብር የሚደርሱ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ሁሉ " ጉቦ "ተብለው እንዲጠሩ ከዚያ በላይ የሚቀበሉና የሚያቀባብሉ ግን የፓርቲ አባላትና ከፍተኛ ጋዶች የሚነጋገሩበት ተብሎ ይጠቀስ ነበር።

    *አሁንማ 'በአብዮታዊ ዴሞክራሲ' 'ልማታዊ መንገስት' ማናቸውም ከ፩ሚሊየን ብር በታች የሆኑ የጉዳይ ማስፈፀሚያ ድጎማዎች ሁሉ የቀድሞ ሥማቸውን 'ጉቦ' ሆኖ እንዲቀጥሉ። ከ፩ሚሊየንና ከዚያም በላይ የማይንቀሳቀስ ንበረትን ጨምሮ የሚሰጡ የአጅም የእግርም ማንሻዎች ሁሉ "ሙስና" ተብለው እንዲንቆለጳጰሱ በመወጣው መመሪያ መሠረት… የቀድሞውን ሥርዓት ናቀፈቂዎች በሚያደርጉት ሴራ ሙስናን በጉቦ በማሸበርና ህገ መንግስቱንና(የህወአት ማኒፌስቶ) ህገመንግሰታዊ የሙና ሥርዓቱን ለመናድ፣ የሚያደርጉትን ጥረት ከምንጩ ለማድረቅ በተደረገው የሙሰኞች ያላሰለሰ ትብብርና እርዳታ ከ፫፻እስከ ፭፻ሺህ ብር የተቀበሉ ፫ አሸባሪ ጉቦኞች የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የስራ ሀላፊዎችና ፭ ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ።ከእነዚህ የስራ ሃላፊዎች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት የተቀሩት ግለሰቦች ደግሞ ፥ በንግድ ስራ ይተዳደር የነበረው አቶ ሰለሞን ገለታ፣ አቶ ብሩክ ሀይሌ፣ ወይዘሪት ሳባ ገብረሚካኤል፣ አቶ ናታን ዘላለምና አቶ ቴዎድሮስ ግደይ ናቸው።

    * ከሳባ ገብረሚካኤል ውጪ እነዚህ በንግድ ስራ ይተዳደሩ የነበሩ ግለሰቦች ቀደም ሲል በተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸውና በማረሚያ ቤት የእስራት ጊዜያቸውን ጨርሰው የወጡ ናቸው። ታላቅ የሥራ ልምድ ያካበቱ…ድሮስ ድልድይ አፍረሽ ልማታዊ መንግስት ሲል ምን ማለት ነበር በለው!
    *ሳባ ገብረሚካኤል በኮምፒውተር ፅሁፍ እያገዘቻቸው፥ በንግድ ስራ የሚተዳደሩት ግለሰቦችም ከፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ታራሚዎች ከእስር የሚፈቱበትን ትዕዛዝ በሀሰተኛ መንገድ በማዘጋጀት እንዲሁም በሀሰተኛ ፊርማ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ማህተም በማስመሰል አዘጋጅተዋል።(ሥራ ክፈቱ ብለዋቸ አፋቸውን ይክፈቱ? ከሶስቱ የስራ ሀላፊዎች ውስጥ ኦፊሰር ገብረመድህን አረጋ ሀሰተኛ የእስር መፍቻ ካቀረበ አንድ ታራሚ ፵ ሺህ ብር መቀበሉ! ምን አላት?ይህ የወ/ሮ ታጋይ አዜብ በአሜሪካ የተሰራላቸው ቤት ውሃና መበራት ክፍያ ናት። በሕግ አመላክ የእስር መፍቻ ደብዳቤ ይዘጋጅለትና በነፃ ይፈታ! ! ለነገሩ ፵ሺህ በ፷፻፪፻ ሲሰላ የአቶ መለስ የ፮ ወር ያልተጣራ ገቢ ማለት አደለምን!
    **፪፱፻፲፭ እንዲሁ ከአደጉ ሀገሮች ጎን መሰለፍ አለን? ምነው ሸዋ ተስካር ነው ሠረግ? እራሱ ህወአተሻቢያ ቀበሮ ጉድጋድ ሆኖ ሲሰራበት የኖረው አደለምን እነዚህስ ሥልጠና ወስደው የለምን?ባንክ መዝረፍ ፣ጎተራ መገልበጥ፣ የገበሬ ሚስት መድፈር በህወአጠሻቢያ የተጀመረ በፋውንዴሽኑ ከተውልድ ተውልድ እንዲተላላፍ ለምርምርና ጥናት ተቀብሮ የለምን!? ሀገር፣ ዳርድንበር፣ ወደብ፣ ሰንደቅ፣ መስደብና ማዋረድ መሸጥ የተጀመረው " በሰጥቶ መቀበል ማኒፌስቶ" ለም መሬት ለጎረቤት ሀገራት የሚቸረው "በታላቁ የሙስና ራዕይ" አደለምን!?
    "አልተናገርኩም ወይ እዚሁ ብቅ ብዬ
    የሙስና ሥርዓት ሻቢያህወአት ወሮ በላዬ !?
    ኢትዮጵያ ፡ ነጋዴው ፣ፖለቲከኛው፣ አድርባይ ምሁር፣ ካድሬ፣መከላከያው፣ብሄርተኛው፣ ኢንቨስተርና ዲያስፖራ በመኖፖል የጠረነፋት ክልል ነች።!እናንት በመጠላላፍ በመፈቃቀርና በመቻቻል ተጠርንፋችሁ የድሃ ደም የምትመጠምጡ፣ ጣታችሁን ወደ ሻቢያህወአት ቀስረችሁ እጃችሁ ድሃው ሕዝብ ንብረትና ገንዘብ ላይ የተጫነ፣እዳይጽፍ፣ እንዳይናገር፣ እንዳይሰባሰብ ለገቢ ምንጫችሁ ያዘናችሁ፣ ከመሀል ሆናችሁ የምትበትኑ ሹምባሾች፣ የቁራ ጩኸት የአዞ እንባ እያነባችሁ ዘረኝነትን ጎጠኝነትን የምትሰብኩ፣ ስንጨቆንና ተረስተን ነበር እያላችሁ… አሁን የራሳችሁን ብሔራችሁን የረሳችሁ አድርባዮች ሁሉ እባካችሁ አታወናብዱ ተነሱ!!የሙሰኞች ወታቦ(ሞኖፖሊው) ይፍረስ! ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ከህዝቦቿ ጋር ለዘለዓለም ትኑር!!

    Reply
  2. Shaleka Kebede says

    December 19, 2013 06:37 am at 6:37 am

    ኦፊሰር ገብረመድህን አረጋ፣ ረዳት ኦፊሰር ኢሳያስ ከበደና ዋርደር ኢብራሂም መሀመድ ; አቶ ብሩክ ሀይሌ፣ ወይዘሪት ሳባ ገብረሚካኤል፣ አቶ ናታን ዘላለምና አቶ ቴዎድሮስ ግደይ
    Anything in commen here … Or is it just me ? Weyne Wegen , Weyne Ager, both have ended up being a playgroung for the ” ድልድይ አፍረሽ ልማታዊ መንግስት ” . !!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
Copyright © 2026 · Goolgule