• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የስብሃት ነጋ ወንድም በሌብነት ተያዘ

July 7, 2020 09:47 pm by Editor 3 Comments

አቤሴሎም ነጋ የተባለውና ነዋሪነቱ በአውስትራሊያ የሆነው ስብሃት ነጋ ወንድም 4 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር (2.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር) በማጭበርበርና በመስረቅ መከሰሱን Herald Sun ዘገበ።

እኤአ ከ2008 – 2019 ባሉት ዓመታት የ54 ዓመቱ አቤሴሎም ነጋ የተለያዩ የፋይናንስ ወንጀሎችን በመፈጸም ነው 4.2 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ወደ ግል የባንክ ሒሳቡና iEmpower በሚል ለሚመራው የግል ድርጅቱ ሒሳብ እንዲገባ ያደረገው። ወንጀሉ ስርቆት ብቻ ሳይሆን በኑሯቸው ዝቅተኛ ለሆኑ የሚሰጠውን (የዌልፌር) ገንዘብን አጭበርብሮ መውሰድም የሚጨምር ነው።  

አቤሴሎም ከዘረፈው ገንዘብ ውስጥ $25,300 የሚሆነውን ያጭበረበረው ከሕግ ጋር ችግር ያለባቸውን የአፍሪካ ወጣቶችን ለመርዳት ከተቋቋመ ድርጅት በመስረቅ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ አቤሴሎም የቪክቶሪያ ጠቅላይ ግዛት የእኩል ተጠቃሚነትና የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የቦርድ አባል ለመሆን ብሎ ባቀረበው ሰነድ ማጭበርበሩና መዋሸቱ ተደርሶበታል። በዚሁ ጠቅላይ ግዛት ታዋቂ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ ተወካይ ሆኖ ይጠቀስ የነበረውን አቤሴሎም፤ ፖሊስ ለሁለት ዓመታት ሲከታተለው እንደነበር የዜና ዘገባው ያስረዳል። ክሱ እስካሁን ሊዘገይ የቻለው በየጊዜው ሲለዋወጣቸው የነበሩትን የስልክ ንግግሮች ለማስተርጎም ጊዜ በመውሰዱ ነው።

የመርማሪዎቹ መረጃ እንደሚጠቁመው አቤሴሎም የሃሰት ሰነዶችን በማቅረብ iEmpower ለተባለው ድርጅቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ጥሬ ገንዘብ “ባፋጣኝ ገንዘብ ያስፈልጋል” በሚል እያምታታ ሲወስድ መኖሩን ያመለክታል። ይህንን ወንጀሉን ለመደበቅ በየዓመቱ በሚያወጣው የፋይናንስ ዘገባ መረጃ በመደበቅ ሪፖርት ያደርግ እንደነበር ተደርሶበታል።

በሌብነት የተከሰሰው አቤሴሎም ወሳኝ ከሆኑ የጠቅላይ ግዛቱና የፌዴራል መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ትሥሥር በመፍጠር ለመታወቅ የበቃ ሲሆን ኅብረባህላዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በሚዲያ አስተያየት በመስጠት የሚታወቅም ነበር። ከዚህ በፊትም የቪክቶሪያ ግዛት ኅብረባሕላዊ ኮሚሽነር እንደነበር ለመታወቅ ተችሏል።

አቤሴሎም የሃሰት ማስረጃ በማቅረብ ከጥቅምት 2012 እስከ ነሐሴ 2018 የቪክቶሪያ ጠቅላይ ግዛት የእኩል ተጠቃሚነትና የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የቦርድ አባል በመሆን 21,578 ዶላር በማምታታት ለራሱ ያደረገ ሲሆን ለቃልና ጽሁፍ ተርጓሚዎች ዕውቅና የሚሰጠው ባለሥልጣን የቦርድ አባል እንደነበር የወጣው ዘገባ ይጠቁማል።

አቤሴሎም፣ ዳንኤል ነጋ ከተባለ ጋር በማሤር የ iEmpower የኦፐሬሽን መምሪያ ኃላፊ በሆነው ሪቻርድ ራያን ላይ የከፋ ጉዳት ለማድረስ በሚል ተጨማሪ ክስ ቀርቦበታል።

ይህ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዝርፊ፣ ማጭበርበርና ሌብነት በጠቅላይ ግዛቱ ከፍተኛ የድንጋጤ ንዝረት ፈጥሯል። አቤሴሎም በዋስ የተፈታ ሲሆን ፍርድ ቤት ሴፕቴምበር 23 በድጋሚ ይቀርባል።

ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም ሲገዛ የነበረው ህወሃት የተባለው የበረሃ ወንበዴዎች ቡድን በሥልጣን ለረጅም ዓመታት የቆየው እንደ አቤሴሎም ዓይነቶች በሚደጉሙት እንደሆነ ይህ አንድ ማሳያ ነው። ስብሃት ነጋ የተባለው ቀንደኛ የወንበዴ በረኸኞቹ አባት ከሌሎቹ ወንበዴዎች ጋር በመሆን መቀሌ መሽጎ የወንድሙን ዓይነት “ዕድል” እየተጠባበቀ የሚገኝ ይመስላል።

ይህ ወንጀለኞችን ለፍርድ የማቅረብ ሒደት በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥልና በተለይ በፖለቲካው ዓለም በየዕለቱ የዓመጽ ተግባራትን ከሚሰብኩት አንደ ጸጋዬ አራርሳ ዓይነቱ የአቤሴሎም ዕጣ እንዲደርሳቸው ለማድረግ በርትተን መታገል አለብን በማለት ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ ተናግረዋል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News, Social Tagged With: abeselom nega, sebhat nega

Reader Interactions

Comments

  1. Welelaye ke stockholm says

    July 8, 2020 01:38 pm at 1:38 pm

    Hey!

    Thanks … !

    leba zerafi .. derome yetaweke new .. hagerachenene asebdate .. HODAME !!

    “be enkulalu gezya shebtahte nega bekonetetewe noro … mene lengeru esume yawe new ..! ke ayeha yewelache gider ..,. teram temetalche new … !

    ke kelle wede hager kezaem alem akefe lebawe .. werdete new …

    chenkilatchewn dengayi argo fetrowachew ,, torenete ena lebente yewatalchewale .. ewekte keyete yemta engdi .. yemyakute yehane new .

    Reply
  2. T says

    July 8, 2020 10:55 pm at 10:55 pm

    I think this fraud thing must be hereditary.

    Reply
  3. Tesfa says

    July 20, 2020 02:17 am at 2:17 am

    ትዕይንት – በሃረር የኦሮሞ የጅምላ አሳቢዎች ለራስ መኮነን የቆመውን የመታሰቢያ ሃውልት ወረውታል። አንዳንዶች ወደ ላይ እየወጡ ነው። በዙሪያቸው ቆንጨራ፤ በትርና ሌላም ነገር የያዙ ወጣቶች ከደስታ ብዛት የተነሳ ይፈነጥዛሉ። ራቅ ራቅ ብለው የክልል ፓሊሶችና ሌሎችም የጸጥታ ሃይሎች በዝምታ ያያሉ። ፈረሰኛው ተገፍትረው ሲወድቁ መቧረቅ ተጀመረ እልልታው ቀለጠ። የቄሮ ልጆች ጀግንነታቸው ተመሰከረ። የቆመን በማውደም ቀዳሚ ናቸው። መንገድ በመዝጋት የሚስተካከላቸው የለም። የሰው አንገት ለመቅላት፤ ቤትና ንብረት ለማቃጠል፤ ቤ/ክርስቲያን ለማውደም ለኦሮሚያ ነጻነት ታጥቀው ተነስተዋል። የሚገርመው ይህኑ ቪዲዪ እየቀረጽ ሶሻል ሚዲያ ላይ በመለጠፍ ገንዘብ ለማግኘት መጣራቸው ነው። የእንስሳት ክምችት። ይህ ሁሉ ገመና ግን የመጣው ወያኔ ለራሱ ጥቅም ሲል ባሰመረው የአፓርታይድ የክልል ፓለቲካ ነው። አሁን ራሱን በመቀሌ አስጠልሎ ተንኮልን በርቀት ከትግራይ ተወላጅ ከሆኑ ነጋዴዎች፤ ሹፌሮች፤ ወታደሮች፤ ጋዜጠኞችና ሌሎችም ጋር የአብይን መንግሥት ለማፍረስ ሌት ተቀን የሚሰራው ወያኔ የኦሮሞን ጽንፈኞችን ለራሱ መልሶ ሲጠቀምባቸው ማየትና መስማት ልብን ያማል።
    ወያኔ ከጅምሩ ሌባ ነው። ይህ የእኔ የፈጠራና የስም ማጥፋት ወሬ አይደለም። አብረው የታገሉና ዛሬ በህይወት ያሉ የሚመሰክሩት እውነት ነው። ይህ የሌብነት ተግባራቸው ተላላፊ ነው። የተጠጋቸው ሁሉ ሌባና ደም አፍሳሽ ነው የሚሆነው። እኔ የሃበሻው ነገር ግርም ይለኛል። ከወያኔ ጋር ሆነው ሲገድሉ፤ ሲዘርፉ፤ ሲያዘርፉ የነበሩ በውጭ ሃገር ራሳቸውን በሰረቁትና አስቀድመው ባሸሹት የህዝብ ሃብት ሲንደላቀቁ እየተመለከተ ለሚኖርበት ሃገር ሚዲያና ባለስልጣን መ/ቤት ማሳወቅ ለምን እንደሚከብድ አይገባኝም። አሰፋ ማሩን የገደለው የወያኔ ተኳሽ በለንደን ሲጎራደድ ማየት ኦ ሰላም በስምሽ ስንት ግፍ ተሰራ ያስብላል።
    አሁን እንሆ የአቦይ ስብሃት ወንድም በስርቆት መጠርጠርና መያዙ የሚያስገርም አይሆንም። ህይወታቸው ኑሮአቸው ሁሉ በማታለልና በመቀማት በመግደልና በማፈን ላይ የተመሰረተ የደም ሰዎች ናቸው። እሱ ብቻ አይደለም። መቀሌና አዲስ አበባ ላይ የተንጣለለ ቤት ሰርተው እያከራዪና እየኖሩበት፤ በዘመድና አዝማድ ስም ንግድ ቤቶችና ሆቴሎችን ከፍተው እየተንፈላሰሱ ለትግራይ ህዝብ አሁን በጭልፋ ጥሬ ሰፋሪዎች መሆናቸው የቱን ያህል የጭፍን ፓለቲካ አራማጆች እንደሆኑ ያመላክታል። የኢህአዴግ (የወያኔ) የቁልቁለት ጉዞ ጸሃፊ በማሃከላቸው የነበረውን የፓለቲካ መሸራገድና የልጆች ጫዋታ ያየውን የአምስት አመት ገመና አስነብቦናል። የገባኝ እንዴት በህዝባችን ላይ ሲያላግጡ እንደነበረ ነው። ዛሬም የትግራይን ህዝብ ተከበሃል፤ ታጠቅ፤ ወደ ሃገርህ ተመለስ የሚሉት ፈንጅ ማጥመዳቸውን ስለሚያውቁና እሳትም እየጫሩ ስለሆነ ከሞትን አንድ ላይ እንሙት አይነት ጥሪ ነው እንጂ ለትግራይ ህዝብ አይገዳቸውም። በአዲስ አበባ ከካዝና በብዙ ቶን ቡና ሲዘረፍ አቶ መለስ ያሉት “የሚሰርቁትን እጃቸውን እንቆርጣለን” ነበር። አይ እንዴት ተደርጎ የራስ እጅ በራስ ይቆረጣል። ለፓለቲካ ፍጆታ ግን እንዲያ ነበር የደነፉት። የወያኔ ሌብነት ሃገርና መርከብ እስከ መሸጥ ድረስ ነው።
    ለፍላፊው ጌታቸው ረዳ በቅርቡ ወደ ሃውዜን ብቅ ብሎ ታጠቁ፤ ተዘጋጅ ምሽግ ቆፍሩ ወዘተ ያለው በሃውዜን ላይ የሰሩት ግፍ ተረስቷቸው ይሆን? አይደለም። ግን ለወያኔ የሰው ህይወት የዝምብ ያህል ነው። የሃውዜን ገቢያ በደርግ ያስደበደቡት ራሳቸው አሽልከው ባስገቧቸው ሰዎች የተሳሳተ መረጃ ለደርግ አቀብለው እንደሆነ ታሪክ ይመሰክራል። ጭፍኑ ደርግም ወያኔ ገቢያ ውስጥ ይኖራል በማለት ህዝባችን ጨፈጨፈው! አይ ጊዜ በሰው ህይወት ላይ ትላንትም ዛሬም ቀልድ! ከወደ መቀሌ ወደ ሌሎች የሃገሪቱ አካባቢ የሚሄደው ስሚንቶ የጠፋው ምሽግ እየሰሩበት ይሆን? የአንደኛው ዓለም አይነት የጦርነት ስልት በ 21ኛው ዘመን። ከማን ጋር ይሆን የሚዋጉት? ከኤርትራ፤ ከዶ/ር አብይ አይደለም ከራሳቸው ጋር እንጂ!
    የአቶ ስብሃት ነጋ ወንድም በዝርፊያ መያዙ እግዚኦ አያሰኝም። ሙያው ነውና! የሌብነት ካባን የለበሰ ሰው ምን ጊዜም አጣም ኖረውም መስረቁ አይቀርም። ልምድ ነውና። ጠለቅ ያለ ምርመራ ቢደረግ ምን አልባት ከአቶ ስብሃት ጋር የሚያይዘው ሌሎችም የስርቆት ወንጀሎች ይኖራሉ ባይ ነኝ። ያው ስብሃት ነጋ ደግሞ የወያኔ የነፍስ አባት ስለሆነ ዘረፋው ሃገራዊና ዓለም አቀፋዊ መልክ ይዞ ወያኒያዊ በመሆኑ እልፍ ጉድ ሊወጣ ይችላል። የጉድጓዱ ሚስጢር የሚለው መጽሃፍ ታወሰኝ። ገጣሚው እንዳለው ነው።
    እውነትን ፍለጋ በቆፈርነው ጉድጓድ
    እህል ዘራንበት በልተን እንድናድር።
    እውነት ቢዚህ ምድር ላይ አለች? የት ናት። እነማን ጋ? ለምን ትላንት ያለቀሱ አይኖች ዛሬም ያለቅሳሉ? ለምን መሞት ያለባቸው ቆመው እየሳቁ ረጅም አስበው ሌት ተቀን እየሰሩ ለመኖር የሚታገሉት አፈር ይመለስባቸዋል? አለም አንቺ አለም ምኑ ጋ ቢነኩሽ አቤት ብለሽ ለዚህ ሁሉ ጥያቄ ምላሽ ትሰጭ ይሆን? አላውቅም። ግን ሌባውም ስርቆቱን ይቀጥል። ዘረኛውም የቆመውን ያፍርስ፤ ያቃጥል። ግን የነገር ሁሉ ማክተሚያ አለው። ምን አልባትም እንዲህ ያቅበዘበዛቸው ኮቪድ 19 ዲዲቲ እንደተነፋበት ተባይ ሊያንጠባጥባቸው ይሆናል። ቆይቶ ማየት ነው። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am
  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule