
በትግራይ፥ “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” የሚለው በግነት የተሞላ ትርክት ከራሱ ከትርክቱ መነሻ ጋር ሦስት ትውልድ በልቷል። አያት፣ አባትና ልጅን የሕይወት ዘመን የአካል ጉዳተኛ አድርጓቸዋል።
በትጥቅ ትግሉ፣ በባድመ ጦርነት እና በአሁኑ ጦርነት አያት፣ አባትና ልጅ አካለ ጎደሎ የሆኑበት የትግራይ ፖለቲካ ሙሉ ትራጀዲ ለኢትዮጵያም የተረፈ መሆኑ ይሰመርበት።
ዛሬ በትግራይ ያለ አካለ ጎደሎ ‘የጉዳት መቼት’ ለማወቅ ‘የደርጉ ነው ወይስ የብልጽግናው?’ እንዲህ ያደረገህ ብሎ መጠየቅ ግድ የሚልበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
አያት፣ አባትና ልጅ አካለ ጎደሎ ለመሆን ያበቃቸውን፤ ከአማራ፣ አፋርና ኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አፋሳሽ ቅራኔ ውስጥ የከተታቸውን የእብደት ፖለቲካቸውን መርምሮ ለመከለስ/ለማረም ከመነሳሳት ይልቅ ዛሬም ለአራተኛ ዙር ጦርነት ምልመላ፣ ልምምድና ስልጠና ላይ ናቸው። (Mulualem G. Medhin)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
የቅርብ ጊዜው የወንድማማቾች ጦርነት በሁለቱ ክልሎች መሪነት የተሠራ ሌላ ትራጀዲ ነበር የሚተዋወቁት አብረው የኖሩት መንግስት ነን ባዮች በጠመዱት ፈንኝ የማይተዋወቁ ሀገር ወዳድ ዜጎች የተቃጠሉበት ሌላው አራተኛ ትውልድ የበላ ሤራ