• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ታሰሩ

October 18, 2023 04:29 pm by Editor Leave a Comment


የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ታምሩ ገምበታን ጨምሮ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ሰዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰሞኑን መሆኑንና አቶ ታምሩ ገምበታ ግን ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. መሆኑ ተገልጿል።

የምክትል ዳይሬክተሩ ቤት በፍርድ ቤት የብርበራ ፈቃድ መበርበሩንና ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

የመንግሥት አስተዳደር ለውጥ ከተደረገ ጀምሮ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ አገልግሎት ተቋም ውስጥ የተለያዩ ለውጦች (ሪፎርም) የተደረገ ቢሆንም፣ አንዳንድ የተቋሙ ሠራተኞች በድለላ ሥራ የተሰማሩ አካላት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በቁጥጥር ሥር ውለው በምርመራ ላይ እንዳሉም ተመላክቷል።

አገልግሎቱን በዋና ዳይሬክተርነት ይመሩ የነበሩት አቶ ብሩህተስፋ ሙሉጌታ፣ ምክትል ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ፍራኦል ጣፋና አቶ ታምሩ ገምበታን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከ3 ወራት በፊት ሐምሌ መጀመሪያ ሳምንት አካባቢ ከኃላፊነት ማንሳታቸው ይታወሳል፡፡

ተቋሙ ከፓስፖርትና መሰል አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ቅሬታ ሲቀርብበት መቆየቱ ይታወቃል።

በተጨማሪ ከዜጎች ከፍተኛ ገንዘብ በመቀበል በሕወጥ መንገድ ወደ ውጭ አገር ሲልኩ ነበር የተባሉ 16 የተቋሙ ሠራተኞች፣ እንዲሁም 5 በአሠሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ስም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎችም ከዚህ ቀደም በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

በተያዘው ሳምንት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የተሰማው ምክትል ዳይሬክተሩን ጨምሮ ሌሎች ሰዎችም ከሙስና ጋር በተያያዘ መጠርጠራቸው ተገልጿል፡፡ (ሪፖርተር ጋዜጣ)

ከዚህ የሪፖርተር ዘገባ በኋላ የተጠርጣሪዎቹ ፎቶና ስም ዝርዝር ወጥቷል፤

42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች መታሰራቸው ተገለፀ

እነዚህ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት ፦
– ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣
– ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ
– ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተውጣጣ ግብረ-ኃይል ከሙስናና ሕገወጥ ተግባር ጋር በተያያዘ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ ከቆየ በኃላ ነው ተብሏል።

ተጠርጣሪዎቹ ፤ ተገልጋዮች በመደበኛ የመንግሥት ስርዓት የሚፈልጉትን የፓስፖርትና መሰል አገልግሎቶችን በአፋጣኝና በአነስተኛ ዋጋ ማግኘት ሲችሉ የፈጠሯቸው የተንዛዙና እና የተወሳሰቡ አሠራሮች ዜጎችን ለከፋ እንግልት ዳርገዋል ተብሏል። በተጨማሪ ላልተገባ ወጪ እንደዳረጉ ተመላክቷል።

ከፍተኛ ገንዘብ በመጠየቅ በሙስና ተግባር ተሰማርተው የግል ጥቅማቸውን ሲያሳድዱ ነበር ተብሏል።

የተሰጣቸውን ስልጣንና ኃላፊነት በመተው  ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ፦

– በዜግነት ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ የውጭ ሀገራት ዜጎች፣
– በወንጀል ተከሰው የጉዞ ሰነዳቸው ለታገደባቸውና ሐሰተኛ የማንነት መገለጫ ላላቸው ሕገወጦች ጭምር የፓስፖርት፣ ሊሴፓሴና ቪዛ አየር በአየር በመሸጥና በማስተላለፍ መንገደኞች በሌሉበት ጉዞ እንዳላቸው በማስመሰል እንዲሁም የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀት ወደ ተለያዩ ሀገራት እንደተዘዋወሩ የሚገለፅ ማሕተም በማዘጋጀት ተግባር ተሰማርተው መገኘታቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ተመልምለው ያለፉ እንደሆኑ በማስመሰል ግለሰቦች ባልተገባ መንገድ ለሥራ ወደ ተለያዩ የዓረብ ሀገራት እንዲወጡ በማድረግ እንዲሁም የሕጋዊ ግለሰብን ፓስፖርት ፎቶግራፍ በመቀየር ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽሙ ተደርሶባቸዋል ተብሏል።

እነዚህ ወንጀለኞች ከአዲስ አበባ እስከ ክልሎች የጥቅም ትስስር  በመዘርጋት ሙስና  ሲፈጽሙ እንደቆዩ ተገልጿል።

ሐሰተኛ የማንነት መታወቂያዎችን በማዘጋጀትም ተግባር ላይ ተሰማርተው ከነበሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ጋርም ግንኙነት በመፍጠር ወንጀሉን ሲፈፅሙ ቆይተዋል።

ይህን ተከትሎም በተደረገ ክትትል ከ200 በላይ የሚሆኑ በሕገወጥ መንገድ የተዘጋጁ #ፓስፖርቶች እንዲመክኑ መደረጉና የወንጀል ድርጊቱም መንግሥትን በሚሊየን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ እንዳሳጣው ተገልጿል።

በዚህም ፦
– በአዲስ አበባ ከተማ፣
– ኦሮሚያ፣
– አማራ፣
– ሲዳማ፣
– ሶማሌ፣
– ጋምቤላ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በወንጀሉ የተሳተፉ  በኢሚግሬሽንና ዜግነት  አገልግሎት ሲያገለግሉ የነበሩ ከከፍተኛ አመራርነት እስከ ባለሙያ ያሉ 42 ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

በወንጀል ድርጊቱ ተሰማርተው ከተገኙና በሕግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ ተጠርጣሪዎች መካከል ፦

– የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ታምሩ ግንበቶ አዋልሶ
– ዘመድኩን ጌታቸው፣
– ከድር ሰዒድ ስሩር፣
– አስቻለው እዘዘው፣
– አብዱላሂ አሊ መሀመድ (አብዱላሂ ጃርሶ)፣
– ቴዎድሮስ ቦጋለ፣
– ጌትነት አየለ፣
–  ጀማል ገዳ፣
– ሙላት ደስታ፣
– ጅላሎ በድሩ፣
– ገነት ኃ/ማርያም፣
– ደገፋ ቤኩማ ፣
– ወንድይፍራው ሽመልስ ገ/ሰንበት እና ሌሎችም ይገኙበታል።

በተያዙት ተጠርጣሪዎች ዙሪያ ምርመራ ይቀጥላል የተባለ ሲሆን  በግለሰቦቹ ዙሪያ ተጨማሪ  መረጃ ያላቸው ዜጎች ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ #ጥቆማ_መስጠት ይችላሉ ተብሏል። (@tikvahethiopia)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: ethiopian terrorists, ICS, Immigration and Citizenship Service, operation dismantle tplf, tplf terrorist, ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ አገልግሎት

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule