የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) ወይም ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ተብሎ በሚጠራው የወንበዴ ቡድን ስም አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት የቀረበውን ውሳኔ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳይ ክርክር ችሎት በምርጫ ቦርድና እነ’ገ/ሚካኤል ተስፋዬ መካከል የተደረገው ክርክር ውሣኔ አግኝቷል። በህወሓት ስም የሚጠራ ለረጅም ዓመታት የሚታወቅ ፓርቲ የነበረ በመሆኑ በዚሁ ስም አዲስ ፓርቲ ማቋቋም መራጩን ያደናግራል ተብሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ስም ክልላዊ ፓርቲ ለመመሥረት የቀረበለትን የቅድመ ዕውቅና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ያቀና ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በእነ’ገ/ሚካኤል ተስፋዬ መካከል … [Read more...] about ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ
Archives for August 2023
“ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት
አሁናዊ የመከላከያ ሠራዊቱን ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የሠራዊቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ፣ መግለጫው በተለያዩ አካላት በሠራዊቱ ላይ እየተናፈሱ ያሉ ብዥታዎችን ለማጥራት የተሰጠ ነው ብለዋል። ሠራዊቱ ካለፉት ዓመታት በነበረበት ቁመና ላይ እንዳለ የሚያስቡ አካላት ካሉ የቆሙት እነርሱ እንጂ ሠራዊቱ ተራማጅ ነው ያሉት ኮሎኔል ጌትነት፣ ሠራዊቱ ዘርፈ ብዙ ግዳጁን እየተወጣ ነው ብለዋል። "ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ" የሚል አካል ላይ ሠራዊቱ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል። ሠራዊቱን መቋቋም ያልቻሉ አካላት በሠራዊቱ ላይ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ ላይ ይገኛሉም ነው ያሉት ኮሎኔል ጌትነት። በተለይ አሁን ላይ … [Read more...] about “ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት