ኢትዮጵያ በአፍሪካና አለም ታሪክ አኩሪ ስም ይዛ የኖረች ታላቅ ሀገር ናት። ልጆቿ ጎሳና ቋንቋ ሳይለያቸው ለሃገራቸውና ለክብራቸው በቆራጥነት በከፈሉት የጋራ መስዋእትነት ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለአህጉራቸው ህዝብ ጭምር ክብር ያጎናፀፉ ጀግኖች መሆናቸውን ያስመሰከሩባት የአበሻ ምድር ናት። ኢትዮጵያ በሽታ ድህነትና ማይምነት ሳይበግረው የውጪ ጠላትን ያንበረከከ ጀግና ህዝብ ያላት ታምረኛ ሃገር ናት። ኢትዮጵያ የራሳቸውን ያገር አንድነት በሚያስደንቅ ወኔ ህይወታቸውን በመገበር ለአፍሪካ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው አለኝታነታቸውን ያረጋገጡ ኩሩ ህዝብ ሃገር ናት። ኢትዮጵያ ከራሷም አልፋ ላለም ሰላምና ደህንነት የታገለችና በጥቁር ህዝብ አኩሪ ታሪክ ተምሳሌነቷ ለትውልድ ልእልና ያጎናጸፈች የጀግና ህዝብ ምድር ናት። እንዳለመታደል ሆኖ ያቺ ስመገናና ሃገር ያች በህዝ ያገር ፍቅር ወኔና ጀግንነት … [Read more...] about ሰላም ወዳድነት አሸናፊነት ነው
Archives for January 2016
የኢትዮጵያ ፈርስ–ት ባለቤትን ይተዋወቁት!
ቤን እባላለሁ። EthiopiaFirst የሚባል ለሕወሓት/ኢሕአዴግ ጭፍን ወገንተኛ ሆኖ የሚሠራ “የሚዲያ” ተቋም አለኝ። EthiopiaFirst የሚለው ያው ደርግ ‘ኢትዮጵያ ትቅደም’ እንዳለው ወይም ናዚዎች ‘ጀርመን ትቅደም’ እንዳሉት ሰው ማባበያ ስያሜ ነው። ኢትዮጵያ ፈርስት እያልኩ የምጠራውን የሚዲያ ተቋምን ተጠቅሜ ኢሕአዴግ የጠላውን ጠልቻለሁ፣ ኢሕአዴግ የወደደውን ወድጃለሁ። ለምሳሌ የዞን፱ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ሲታሰሩ “እሰይ! አገር ሊያተራምሱ ሲሉ ተያዙ” እያልኩ፣ እየማልኩ እና እየተገዘትኩ ፕሮግራም ሠርቼ ተመልካች ለማሳሳት ጥሬ ነበር። በዜግነቴ ካናዳዊ ነኝ፤ ቢሆንም ግን ለውጭ ዜጎች የማይሰጠው ዕድል የሕወሓት/ኢሕአዴግ ወዳጅ ስለሆንኩ ተሰጥቶኝ አንዳንዴ በየወሩ የሚታተም «ኅብረ–ብዕር» የተባለ መጽሔት ባለቤትና አዘጋጅ ሆኛለሁ። በመጽሔቴ ላይ ‘አብይ ጉዳይ’ የሚባል አምድ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ፈርስ–ት ባለቤትን ይተዋወቁት!
ካለፉት ድርጊቶች መማር ያልቻለ ትውልድ፣ ለገጠሙት ችግሮች መፍትሔ ማግኘት አይቻለውም!
የአንድ አገር ችግሮች የዛሬ ሁኔታዎች የፈጠሩዋቸው ብቻ አይደሉም። እንዳውም የአብዛኞቹ ችግሮች መነሻ መሠረታቸው ዛሬ ሳይሆን፣ ትናንትና ከትናንት ወዲያ ነው። የወቅቱን ችግሮቹ አስቸጋሪና ውስብስም የሚያደርጋቸውም ይኸው ምንጫቸው ካለፉ ትውልዶች ተያይዘው መምጣታቸው ነው። የዛሬውን የአገራችን ፖለቲከኞች አብሮ ለመሥራት ቀርቶ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ማሰብ ያቃታቸው የለውጥ አራማጅ ነኝ የሚለው ትውልድ ዘርቶት የሄደው «ኢትዮጵያ አገር አይደለችም፤ እንዳውም የብሔረሰቦች እስር ቤት ናት፤» የሚለው አስተሳሰብ ተሸካሚ በመሆኑ ነው። በመሆኑም ዛሬ ትውልዱ ለገጠመው ሁለንተናዊ ችግር መፍትሔ ለመሻት ከልቡ ካሰበና ለዚህም ቆርጦ ከተነሳ፣ ያለፉት ትውልዶች የተከተሉትን ሕዝብን በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በማንነት የመከፋፈል አስተሳሰብና አመለካከት አውልቆ መጣልና ኢትዮጵያዊ ማንነትን መቀበል ይጠበቅበታል። … [Read more...] about ካለፉት ድርጊቶች መማር ያልቻለ ትውልድ፣ ለገጠሙት ችግሮች መፍትሔ ማግኘት አይቻለውም!
በውጥረት ላይ ውጥረት መደራረብ ይቁም!
ሰሞኑን በኦሮሚያ እና በሰሜን ጎንደር የተከሰተው የተቃውሞ ንቅናቄ ሀገሪቱን ውጥረት ውስጥ ከትቷታል፡፡ አመጹ እየተጋጋለ መሄድ እንጂ የመቀዛቀዝ ባህሪ አላሳይ ብሏል፡፡ አሁንም በልዩ ልዩ አካባቢዎች ቀጥሏል፡፡ በአራቱም አቅጣጫዎች ውጥረት ሰፍኗል፡፡ በህይወት ዘመኔ ይህንን ያህል ዘላቂ ሆኖ የቆየ አመጽ አይቼ አላውቅም፡፡ በዚህ አመጽ ለጠፋው ህይወትና ንብረት እናዝናለን፡፡ በየትኛውም ወገን ሆኖ በትርኢቱ ውስጥ የተሳተፈው የኛው ዜጋ በመሆኑ ነፍሱና አካሉ ታሳዝነናለች፡፡ ታዲያ አመጹ የተከተሰው በመንግሥት ሚዲያ እንደሚነገረው “ኪራይ ሰብሳቢዎች፣ ግንቦት ሰባቶችና ኦነጎች በወጠኑት ሴራ ነው” የሚለው ምክንያት መሰረት የለውም፡፡ እንደዚህ ማለት “ህዝቡ አያገናዝብም፤ በማንም ይታለላል” የማለትን ያህል ነው፡፡ በኤርትራ የመሸጉት ድርጅቶችም ሆኑ “ኪራይ ሰብሳቢ” የሚባሉት የማይታወቁ ሃይሎች … [Read more...] about በውጥረት ላይ ውጥረት መደራረብ ይቁም!
የሰሞኑ “የኦሮምያ ግርግር” ግራ ገብቶኛል
በሁለት ደረጃ የሚቀርቡ ጥያቄዎች አሉኝ፤-- አንድ፡-- ግርግሩ የኦሮምያ ነው? ወይስ የኢትዮጵያ? ወይስ ኦሮምያ ከኢትዮጵያ ተለይቷል? ሁለት፡-- የኢትዮጵያ የመሬት ጉዳይ ኦሮሞዎችን ብቻ የሚመለከት ነው? ወይስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ? አንደኛ፣ ግልጽ ከሆነው እውነት እንነሣ፤ ኦሮምያ ከኢትዮጵያ አልተለየም፤ ስለዚህም ግርግሩ የኢትዮጵያ ነው እንጂ የኦሮምያ አይደለም፤ ጥንቱኑ ለማጋጨት የተሰጠውን ስያሜ በስምነቱ ከማጽደቅ በላይ ለታቀደው ዓላማ አመቺ መሣሪያ ማድረግ ነው፤ ይህ ደግሞ በቅድሚያ መሸነፍን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ከወያኔ በቀር ደጋፊ ያለው አይመስለኝም፤ ቁርጠኛ ትግል ቁርጠኛ ዓለማና ቁርጠኛ ስልት ያስፈልገዋል፤ ስለዚህም ቁርጠኛ መሪ ያስፈልገዋል፤ የሕመሙን መርዝ እየተጎነጩ ከሕመሙ ፈውስ ለማግኘት አይቻልም፤ ግርግሩ የኦሮሞ ከተባለ ሁለት ውጤቶች ይከተላሉ፤ አንዱ ውጤት … [Read more...] about የሰሞኑ “የኦሮምያ ግርግር” ግራ ገብቶኛል
መሬት ለአራሹ!
በኣስራ ዘጠኝ ስልሳዎቹ ኢትዮጵያ ደምቃ ነበር። የለውጥ ጥም ይዟት ትጮህ ነበር። መቼም በየሃገሩ ኣገራዊ ችግሮችን መልክ ኣስይዞ፣ መሪቃል ወይም መፈክር ኣውጥቶ ለውጡን የሚመራውና የለውጥ ሃይል የሆነው ወጣቱ ሲሆን በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሁሌም ቀዳሚዎች ናቸው። ታዲያ በዚያ የለውጥ ወራት ጊዜ ከነበረው ኣንዱና ትልቁ ጥያቄ የመሬት ላራሹ ጉዳይ ነበር ኣሉ። መሬት ላራሹ! መሬት ላራሹ! መሬት ላራሹ!……… ወጣቱ ድምጹን ኣሰማ ። ኣራሹ ማን ነው? ያውጭሰኛውና መሬት የለሹ ዜጋ ነዋ። በጥቂት የመሬት ከበርቴዎች እየተጨቆነ የሚኖረው የሰፊው ድሃ ህዝብ ግፍ ይብቃ፣ ኣዲስ ዘመን መጥቷልና እናንተ የመሬት ከበርቴዎች ሆይ በቃችሁ። ኣራሹ ገበሬ እጣው በሆነችው በዚህች ኣገር ውስጥ፣ የርስቱ ገመድ በወደቀባት በዚህች ምድር ላይ መሬት ይኑረው ነው ጥያቄው። በርግጥ ይህ ጥያቄ በጥሩና ሳይንሳዊ … [Read more...] about መሬት ለአራሹ!
ለጋራ አላማ ለጋራ ትግል
በኦሮሞ ወጣቶች የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተጀመረውና በደርዘን ለሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት ማለፍ ምክንያት የሆነው እንቅስቃሴ አሁን ባለው አዲስ ሁኔታ በአጀንዳውም በተሳትፎውም እየሰፋ ሲሄድ እየታዘብን ነው፡፡ ለዚህ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በወያኔ/ኢህአዴግ ግፈኛ አገዛዝ በተሰጠው የጭፍጨፋ ምላሽ የተነሳ ንቅናቄው በአጠቃላይ ቁጣን በተላበሰ መልክ ለዴሞክራሲ ወደሚለው ጥያቄ እየተቀየረ ነው፡፡ እንደዚህ በመሆኑም በአንድ በኩል በዚያው በኦሮምያ ክልል ከተማሪዎቹ ባሻገር ገበሬዎች፣ ሰራተኞች፣ ሴቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከትግሉ እየተቀላቀሉ ሲሄዱ በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ከኦሮሞ ወጣቶች አንድነት ለማሳየት ብቻ ሳይሆን ፍትህና ዴሞክራሲ ለሚለው ለዚህ የጋራ የሆነ አጀንዳ የመንቀሳቀስ አዝማሚያ እያሳዩ ነው፡፡ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ለጋራ አላማ ለጋራ ትግል
“ደሞዝ የከፈለ ማዘዝ ይችላል” የሚለው አባባል በፖለቲካ ይሰራል
እንደ ሰላማዊ ትግል ተማሪ ከህዳር ወር መጀመሪያ ግድም አንስቶ እስከ ታህሳስ ወር አጋማሽ 2008 ድረስ የተካሄደውን የኦሮሚያ ተማሪዎች ሰላማዊ ትግል በቅርብ ስከታተል ነበር። የሰላማዊ ትግሉ መልዕክት “የኦሮሚያን መሬት አስመልክቶ የፌደራል እና የክልል መንግስት የወጠናችሁትን እቅድ እናውቃለን ። እኛ ለእቅዳችሁ ትብብር አንሰጠውም፣ አናጸድቀውም፣ እንቃወመዋለን። እኛን እንደ ተመልካች ማየታችሁን አቁማችሁ አዳምጡን። የመሪታችን ባለቤቶች እኛ መሆናችን ተገንዝባችሁ አነጋግሩን፣ በውሳኔ መስጠቱ ሂደት አሳትፉን። የመሪታችን ተጠቃሚነት መብታችንን እወቁ።” የሚል ነበር። ካለምንም ጥርጣሬ፣ ንቀት እና እብሪት ሰልፈኞቹ የሚናገሩትን ላደመጠ እና ያነገቡዋቸውን ጽሑፎች ላነበበ ሰው የሰልፈኞቹ መልዕክት ግልጽ ነበር። ጥያቄው እጅግ በጣም ቀላል ነበር። ምንም ውስብስብነት አልነበረውም። መንግስት … [Read more...] about “ደሞዝ የከፈለ ማዘዝ ይችላል” የሚለው አባባል በፖለቲካ ይሰራል