በኦሮሞ ወጣቶች የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተጀመረውና በደርዘን ለሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት ማለፍ ምክንያት የሆነው እንቅስቃሴ አሁን ባለው አዲስ ሁኔታ በአጀንዳውም በተሳትፎውም እየሰፋ ሲሄድ እየታዘብን ነው፡፡ ለዚህ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በወያኔ/ኢህአዴግ ግፈኛ አገዛዝ በተሰጠው የጭፍጨፋ ምላሽ የተነሳ ንቅናቄው በአጠቃላይ ቁጣን በተላበሰ መልክ ለዴሞክራሲ ወደሚለው ጥያቄ እየተቀየረ ነው፡፡ እንደዚህ በመሆኑም በአንድ በኩል በዚያው በኦሮምያ ክልል ከተማሪዎቹ ባሻገር ገበሬዎች፣ ሰራተኞች፣ ሴቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከትግሉ እየተቀላቀሉ ሲሄዱ በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ከኦሮሞ ወጣቶች አንድነት ለማሳየት ብቻ ሳይሆን ፍትህና ዴሞክራሲ ለሚለው ለዚህ የጋራ የሆነ አጀንዳ የመንቀሳቀስ አዝማሚያ እያሳዩ ነው፡፡ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply