• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ደሞዝ የከፈለ ማዘዝ ይችላል” የሚለው አባባል በፖለቲካ ይሰራል

January 1, 2016 07:19 am by Editor Leave a Comment

እንደ ሰላማዊ ትግል ተማሪ ከህዳር ወር መጀመሪያ ግድም አንስቶ እስከ ታህሳስ ወር አጋማሽ 2008 ድረስ የተካሄደውን የኦሮሚያ ተማሪዎች ሰላማዊ ትግል በቅርብ ስከታተል ነበር። የሰላማዊ ትግሉ መልዕክት “የኦሮሚያን መሬት አስመልክቶ የፌደራል እና የክልል መንግስት የወጠናችሁትን እቅድ እናውቃለን ። እኛ ለእቅዳችሁ ትብብር አንሰጠውም፣ አናጸድቀውም፣ እንቃወመዋለን። እኛን እንደ ተመልካች ማየታችሁን አቁማችሁ አዳምጡን። የመሪታችን ባለቤቶች እኛ መሆናችን ተገንዝባችሁ አነጋግሩን፣ በውሳኔ መስጠቱ ሂደት አሳትፉን። የመሪታችን ተጠቃሚነት መብታችንን እወቁ።” የሚል ነበር። ካለምንም  ጥርጣሬ፣ ንቀት እና እብሪት ሰልፈኞቹ የሚናገሩትን ላደመጠ እና ያነገቡዋቸውን ጽሑፎች ላነበበ ሰው የሰልፈኞቹ መልዕክት ግልጽ ነበር። ጥያቄው እጅግ በጣም ቀላል ነበር። ምንም ውስብስብነት አልነበረውም። መንግስት ግን እጅግ በሚያሳዝን አኳን ውስብስብ አደረገው።

ይህ ሰሞኑን በኦሮምያ እንደ አበባ ፈክቶ ያየነው ሰላማዊ ትግል በታሪካችን አይተነው አናውቅም። የኦሮሚያ ወጣት ህይወቱን ከፍሎ ለኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል ባህል እድገት ፍጹም የማይረሳ አስተዋጽኦ አድርጓል ብሎ አፍ ሞልቶ መናገር ይቻላል። ይሁን እንጂ የዛሬውም ገዢ እንደ ቀድሞቹ የኢትዮጵያ ገዢዎች ሰላማዊ ሰልፈኞችን ገድሏል። ደብድቧል። አስሯል። የተጀመረው ሰላማዊ ትግል የሚቆመው ሰላማዊ ምላሽ ሲያገኝ እንጂ በግድያ እንዳልሆነ አምባገነኖች የሚገባቸው ጉዳይ አይደለም። የዚህ ጽሁፍ ግብ ሰላማዊ ትግሉን ከውድመት ጠብቀን አንድ እርምጃ ሽቅብ ከፍ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ አንድ ሁለት የአኪያሄድ ምክሮች መለገስ ነው።

በስልጣን ላይ የሚገኝ አምባገነን ቡድን (አምባገነን መንግስት) የፖለቲካ ኃይል (አቅም) የሚፈስለት ከሰማይ ሳይሆን በምድር ላይ ከሚገኙት ስድስት (6) የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ነው። ከእነዚህ ምንጮች የሚፈስለትን አቅም እየጠጣ መንግስት ይፋፋል። ወዛም ይሆናል። የፖለቲካ አቅሙም ይጎለብታል። ይኽን አቅም ተጠቅሞ ተቃዋሚዎቹን ይመታል። ተቀዳሚ ግቡ የሆነውን የስልጣን ዘመን ያራዝማል። ስለዚህ በመንግስት የፖለቲካ ኃይል ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ለመፈጸም ሰላማዊ ትግል የመንግስትን የፖለቲካ ኃይል ምንጮቹን በዝርዝር ማወቅ ይኖርበታል። የመንግስትን የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ማወቅ ለሰላማዊ ትግል ስኬት ጠቃሚ ነው።

ከስድስቱ የፖለትካ ኃይል ምንጮች ውስጥ አንዱ ምንጭ “የመንግስት የአገር ኢኮኖሚ፣ የግብር፣ የመሬት እና የተፈጥሮ ሃብት ባለቤትነት” መሆኑ ነው። በኢትዮጵያ መንግስት የዚህ አብይ የፖለቲካ ኃይል ምንጭ ባለቤት መሆኑ “ደሞዝ ከፋይ” አድርጎታል። በኢትዮጵያ ትልቁ ደሞዝ ከፋይ መንግስት ሊሆን የቻለበት ምክንያትም የዚህ ትልቅ የፖለቲካ ኃይል ምንጭ ባለቤት መሆኑ ነው። ስለዚህ ለፖሊስ ከፋዩ መንግስት ነው። ለደህንነቶች ይከፍላል። ለእስር ቤቶች ሰራተኞች ደሞዝ ከፋይ ነው። ለመንግስት ሚዲያ ሰራተኞች ደሞዝ ከፋይም እሱ ነው። ለመለዮ ለባሹ ደሞዝ ከፋይ እሱ ነው። ለካድሬዎችም ይከፍላል። ሁልጊዜም ባይሆን አስተዳደሩን ለማጠናከር እና የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም ደሞዝ የከፈላቸውን ሁሉ ያዛል። ሁሉም ይታዘዛሉ። ሁልጊዜ ባይሆንም።

ማን የዚህ ቁልፍ የፖለቲካ ኃይል ምንጭ ባለቤት አደረገው ? ህዝብ ዴሞክራሲያዊ በሆነ ስርዓት ፈቅዶ የለገሰው እንዳልሆነ ይታወቃል። ከዚህ የፖለቲካ ኃይል ምንጭ የሚፈስለት አቅም እንዲዳከም ከተደረገ መንግስት ደሞዝ የመክፈል አቅሙ እንደሚዳከም ግልጽ ነው። እንደቀድሞው ደሞዝ መክፈል አይችልም። ደሞዝ ያልተከፈላቸው አብዛኛው ካድሬ፣ ፖሊስ፣ ደህንነት፣ የእስር ቤት አስተዳዳሪ፣ ቢሮክራሲው (የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኛ) እንደቀድሞ መታዘዝ አይፈልጉም። “ደሞዝ ያልከፈለ” ማዘዝ አይችልም ማለት ነው። ስለዚህ መንግስት ደሞዝ ሳይከፍ እንደቀድሞው ማስተዳደር እንደማይችል ግልጽ ነው።

ደሞዝ እስካልከፈለ ድረስ የሚታዘዝለት ስለማይኖር መንግስት እንደቀድሞው ተቃዋሚውንም መምታት አይችልም። በዚህ አይነት ቀደም ሲል በመንግስት እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የነበረው የበላይነት እና የበታችነት ግንኙነት የፖለቲካ አቅም ሚዛን ይቀየራል። በመጨረሻም የመንግስት ደሞዝ መክፈል አቅም መዳከም ቀጣይነት እንዲኖረው ከተደረገ በመንግስት እና በተቃዋሚዎች መካከል የነበረው የፖለቲካ ኃይል ሚዛን ግንኙነት ከበላይ እና ከበታች ግንኙነት ወደ አቻነት እንደሚሸጋሸግ ግልጽ ነው።

ከአገር ውስጥ እና ከውጭ ወደ መንግስት የሚፈሰው የገንዘብ መጠን ከቀነሰ ደሞዝ የመክፈል አቅሙ እንደሚቀንስ ግልጽ ነው። ይኽ ጉዳይ እንግዲህ ሰላማዊ ትግሉን ቀስ በቀስ በኢኮኖሚ ግንባር ትብብር ማሸጋገርን የግድ ይላል።

በመጨረሻ በኢትዮጵያ በመደረግ ላይ የሚገኘውን ሰላማዊ ትግል በሚመለከት ሁላችንንም ሊያሳስቡን እና ጥንቃቄ ልናደርግባቸው የሚገቡ ሶስት ማስጠንቀቂያ መሰል ነገሮች ልናገር እና ልሰናበታችሁ።  እነሱም አንደኛው ግብታዊነትንት (Spontaneity)፣ ሁለተኛው ብክለት (Contamination) የሚለው ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ ህብረት ወይንም ለነፃነት የሚደረግ ሰላማዊ ትግል ትግግዝ (ሽርክና) የሚለው ነው።

ግብታዊነት፥

 (1) ግብታዊ ሰላማዊ ትግል አምባገነኖች ሊወስዱዋቸው የሚችሉትን አረመኔያዊ እርምጃዎች በቅድሚያ የመገመት እና የመዘጋጀት ጊዜ ስለሌለው ግብታዊነትን ልናስወግድ ይገባል።

(2) ግብታዊ ሰላማዊ ትግል ሊገጥሙት የሚችሉትን ወሳኝነት ያላቸው እንቅፋቶች በቅድሚያ አንስቶ ተገቢ ፕላን ስለማያሰላ ውጤቱ ውድመት ሊሆን ስለሚችል ግብታዊነት ሊወገድ ይገባል።

(3) ግብታዊ ሰላማዊ ትግል በስልጣን ላይ የሚገኘውን አምባገነን መንግስት ማውረድ ቢችልም ቀደም ብሎ የተሰላ ህዝብን የመንግስት ስልጣን ባለቤት የሚያደርግ እና ምናልባትም በሽግግር ወቅት ለከሰት የሚችልን በመፈንቅለ መንግስት ወይንም በራሱ ከስልጣን በወረደው ቡድን የሚፈጸመን ቅልበሳ የሚከላከል ፕላን ስላማይኖረው አገሪቱን ወደ ነፃ ምርጫ እና ወደ ዲሞክራሲ ማሸጋገር ስለሚሳነው ህዝብን የድል ባለቤት ማድረግ አይችልም። አዲስ አምባገነን የድል ፍሬ ሰብሳቢ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ግብታዊነትን እናስወግድ።

ስለዚህ አንድን ሰላማዊ ትግል ግብታዊ ነው ከሚያሰኙት መስፈርቶች ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ግብታዊ ሰላማዊ ትግሎች ሊነሱ ከሚችሉባቸው ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ፥

(1) በተለያዩ የመንግስት ስልጣን እርከን የሚገኙ ሙስና የተጠናወታቸው አምባገነኖች በቃኝ የማይለውን የግል ፍላጎታቸውን ለማሙዋላት በህዝብ ላይ የሚፈጽሟቸው አይን ያወጡ አስገዳጅ ዘረፋዎች እና ጨቋኝ ተግባራት ህዝብ ሊሸከም ከሚችለው መጠን ሲያልፉ፣

(2) በተለያዩ የመንግስት ስልጣን እርከን ላይ የሚገኙ አምባገነን አለቆቻቸውን በማስደሰት ተሿሚ እና ተሸላሚ ከመሆን በስተቀር ሌላ የማይታያቸው እውር ሹመኞች በህዝብ እና በታዋቂ ግለሰቦች ላይ የሚወስዱዋቸው አረመኔ እርምጃዎች ህዝቡን ሲያስቆጡ፣

እንደሚታወቀው ለተጀመረው ግብታዊ ሰላማዊ ህዝባዊ አመጽ መንግስት ፍትሃዊ ምላሽ ካልሰጠ ሰላማዊውን አመጽ አባብሶ ገዢውንም ሆነ ተቃዋሚውን (ሁለቱንም) ሊያሰምጥ የሚችል ሁኔታ ለፈጠር ይችላል።

ብክለት፥

ሰላማዊ ትግሉን ከብክለት መጠበቅ ሌላው የሰላማዊ ትግል የደህንነት ስራ ነው። ጀብዱኛ ግለሰቦች ወይንም ሌሎች ሰላማዊ ትግሉን ተቀላቅለው የሶሪያ አይነት ሁኔታ በኢትዮጵያችን እንዳይደገም ማድረግ አለበን። ሰላማዊ ትግሉ በፕላን የሚመራ እና በሰላማዊ ትግል ድስፕሊን እየታነጸ እንዲያድግ ማድረግ አለብን። ሰላማዊ ሰልፈኞች መካከል ሆኖ ፖሊስ ላይ ድንጊያ መወርወር ወይንም ጥይት መተኮስ ሰላማዊ ትግል አለመሆኑ በግልጽ መታወቅ አለበት።

ህብረት/ሽርክና፥

ይህ ማለት የድርጅት ውህደት ሳይሆን በተጨባጭ መንግስት በሰላማዊ ትግሉ ላይ የሚፈጽመው እና የአገሪቱ የሰላማዊ ትግል ሰራዊት በአንድ ጥላ ስር መሰባሰብን አስተውሎ አዎንታዊ ምላሽ የሚሰጥ በጋራ ግብ ዙሪያ መሰባሰብ ማለት ነው። የአይዲዮሎጂ እና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ከተፈጠረ በኋላ የዴሞክራሲ ኃይሎች በመነጋገር ወይንም በድርድር ወይንም ህዝቡ በምርጫ ፖሊሲ ልዩነቶች ላይ በሚሰጠው ድምጽ ሊወሰኑ የሚችሉ ጉዳዮችን አለጊዜያቸው አንስቶ አለመራኮት ማለት ነው። ውህደትም ቢሆን ለረጅም ጊዜ በትናንሽ ጉዳዮች ላይ ተጋግዞ በመስራት የሚፈጠር ትውውቅን ቅድሚያ ይላል። በጋራ መስራት በጋራ መስራት የሚቻሉ ነገሮችን ለይቶ አውጥቶ በእነሱ ላይ ተጋግዞ አብሮ የመስራት ባህልን መገንባት መጀመርን የግድ ይላል። በተፈጥሮው የትጥቅ ትግል በመግደል አሸናፊ ፓርቲ መፍጠርን የግድ ስለሚል የተቃዋሚ ፓርቲዎችን አብሮ መስራት አዳጋች ያደርጋል። ሰላማዊ ትግል ግን በተፈጥሮው ያን አይነት ችግር የለውም። በዚህ ረገድ በአሁኑ ሰዓት ጉልህ የሆነ የህዝብ ድጋፍ ያላቸው ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ አብረው መስራት የማይችሉበት ምክንያት ፍጹም አይታየኝም። እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች አብረው በመስራት የህዝባቸውን ጥም ማርካት አለባቸው። አብረው በመስራት ብስለታቸውን ለህዝባቸው ማሳየት አለባቸው። ይህን በማድረግ የህዝባቸውን ክብር እና ምስጋና ማግኘት ይገባቸዋል። በአጭሩ በርቀት ማስተዋል የሚችሉ መሪዎች መሆናቸውን ሊያሳዩን ይገባል።

ከሰላምታ ጋር

ግርማ ሞገስ

girmamoges1@gmail.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule