የሩስያ ኮሚኒስት አምባገነኖች ሕዝቡን ሰንገው በሚገዙበት ዘመን፤ አንድ ስመጥር ፈረንሳዊ ደራሲ ወደ ሞስኮ ጎራ ይላል፡፡ በጊዜው የመንግሥት ታጣቂዎች ተቃዋሚዎችን በማፈንና በመግደል ተጠምደው በማየቱ አዝኖ ቅሬታውን ላንድ ካድሬ ገለጸ፡፡ ካድሬው ቅሬታውን ከሰማ በኋላ “እንቁላል ፍርፍር ለመሥራት ከፈለግህ እንቁላሉን መስበር አለብህ” ብሎ ተፈላሰፈ፡፡ ደራሲው የዋዛ ስላልነበረ እንዲህ ብሎ መለሰት፤ “እዚህም እዚያም የእንቁላል ስብርባሪ ይታየኛል፡፡ ግን ፍርፍሩ የታል?” እስከቅርብ ጊዜ ስንሰማው የነበረው፤ “ዲሞክራሲን ቸል ያልነው ቅድሚያ ሕዝቡን ዳቦ ለመመገብ ነው” የሚለው መከራከርያ ውሃ በልቶታል፡፡ ዳቦውም ሆነ ዲሞክራሲውም ገደል ገብቷል፡፡ የምለው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ በሀገሪቱ በየቦታው እየተፈጸመ ያለውን ግድያ በጊዜ አቁሙ! ገባሩ ህዝብ የሚላችሁን ስሙ፡፡ ስለ “ዘለቄታዊ … [Read more...] about “ሕዝብ ከሸፈተ ሠራዊት አያቆመውም” መለስ ዜናዊ
Archives for December 2015
ወያኔ በራሱ ወጥመድ
ራስን ሳያታልሉ ሌላውን ማታለል አይቻልም፤ ለራስ ካልዋሹ ለሌላ ሰው መዋሸት አይቻልም፤ ዞሮ ዞሮ ወደቤት እንደሚባለው ዞሮ ዞሮ ማታለልም ሆነ ውሸት ማደሪያ ሲያጡ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፤ ያኔ ፈጣሪና ፍጡር ይፋጠጣሉ፤ ፍጡር የማታለያ ልብሱን አውልቆ በዓለም ፊት ራቁቱን ይቆማል፤ በከመረው ውሸት መጠን ነቀፌታ ተሸክሞ ያቃስታል፡፡ የታወሩት ዓይኖቹ ይከፈቱና ሕይወት ነጠላ አለመሆኑን፣ በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ውጣ-ውረድ መኖሩን፣ ጥላቻና ፍቅር፣ ጤንነትና ሕመም፣ ደስታና ሐዘን መፈራረቃቸውን፣ የግለሰብ ሕይወት በሞት ተሸንፎ መሻሩን፣ ገንዘብ የማይገዛው ነገር መኖሩን፣ ገንዘብ በከበደ መጠን ማቅለሉን አለማወቅ፣ ገንዘብ የማይመክተው ጦርና በገንዘብ ሊታጠቀው የማይችል መሣሪያ መኖሩን አለማወቅ፣ የደከመ እንደሚያይልና ያየለ እንደሚደክም፣ ዓለማችን በጣም የተያያዘና የተቆራኘ በመሆኑ አንዱን … [Read more...] about ወያኔ በራሱ ወጥመድ
የሞረሽ የአቋም መግለጫ
እኛ የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት እሑድ ኅዳር ፳፮ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. (Sunday December 6, 2015) ባደረግነው የማዕከላዊ ምክር ቤቱ ሰባተኛ መደበኛ ስብሰባ ፣ በማዕከላዊ ምክር ቤቱ ስድስተኛ መደበኛ ስብሰባ በጸደቁት የ፮(ስድስት) ወራት የሥራ ዕቅዶች አፈጻጸም ምዘና ሪፖርት፣ በድርጅቱ የቁጥጥርና ፍተሻ የአካላትና የአባላት የሥራ እንቅስቃሴና የገንዘብ አሰባሰብና አጠቃቀም ሪፖርት በአንክሮ አዳምጠን አስፈላጊውን ውይይት በማድረግ ሪፖርቶቹ ከምክር ቤቱ አባሎች የቀረቡትን ገንቢ ሀሳቦችን አካትቶ የድርጅቱ ቋሚ ሰነድ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ ወስነናል። ከሁሉም በላይ በዚህ መደበኛ ስብሰባ ምክር ቤቱ አጽንዖት ሰጥቶ ሠፊ ጊዜ ወስዶ የተወያየበት «የድርጅቱን ዓላማና ተልዕኮ በተሻለ መንገድ እንዴት ማከናወን ይቻላል?» ለሚለው ጥያቄ ተገቢና ሁነኛ መልስ … [Read more...] about የሞረሽ የአቋም መግለጫ
ተቃውሞ በዝምታ
* እስካሁን አምስት ሰዎች ሞተዋል ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) ጋዜጠኝነት “አሸባሪነት” በመሆኑ መረጃ እንደልብ ባይገኝም ከተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች የተገኘው ዜና እንደሚያመለክተው የተማሪዎች ሰላማዊ የዝምታ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ እንደሚነገረው ዘገባ ከሆነ ስማቸውና የመኖሪያ ስፍራቸው የአንዳንዶቹም ከነፎቶዋቸው ይፋ የተደረገው መረጃ ላይ እንደሰፈረው የተማሪዎች ንቅናቄ ከተጀመረ እስካሁን የአምስት ወገኖች ህይወት በህወሃት ታጣቂዎች አልፏል፡፡ ዛሬ የተደረገው ተቃውሞ በበርካታ የተለያዩ ከተሞች መቀጠሉ ሲሰማ በእንቅስቃሴው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች እና ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ በተለይ በአዲ አበባ ዩኒቨርሲቲና በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ … [Read more...] about ተቃውሞ በዝምታ
ጋምቤላ: የፌደራሊዝሙ ክሽፈት ማሳያ?
ሐሙስ 20 – 01 – 2003፣ ጋምቤላ ከተማ፡ የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዲሱን የስራ ዘመኑን የመጀመሪያውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ በማጽደቅ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ በመዝጊያው ስነ ስርዓት ላይ በጊዜው የክልሉ ፕሬዝደንት የነበሩት ኡሞት ኡባንግ ባደረጉት ንግግር፡ ‹‹ጋምቤላን ወደ ቀድሞው ክብሯ እንመልሳታለን፡፡ ያችን አኙዋዎች፣ ኑዌሮች፣ መዠንገሮች፣ ኦፖዎች፣ ኮሞዎችና ደገኞች አንድ ላይ በሕብረት የሚኖሩባትን - ጋምቤላ፡፡ ሁላችንም አፍሪካዊያኖች ነን፡፡ ጥላቻና ልዩነት ለማናችንም አይበጁንም…›› በማለት የሁሉንም ተሰብሳቢዎች ልብ የሚነካ ሃሳብ አቀረቡ፡፡ 156 መቀመጫዎች ያሉት የክልሉ ምክር ቤትም በጭብጨባ ተናጋ፡፡ ኡሞት ይሄን ታሪካዊ ንግግር ሲያደርጉ ከኡሞት ጎን የተቀመጡት የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ እንዲሁም የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አሽኔ … [Read more...] about ጋምቤላ: የፌደራሊዝሙ ክሽፈት ማሳያ?
“ትግራይ ወረዳ ውስጥ ያለ የመንግሥት አሰራር በኦሮሚያ ውስጥ … ይገኛል”
* "የአዲስ አበባ መሬት በማለቁ ወደ ኦሮሚያ መሬት እጃቸውን መዘርጋት ጀመሩ" * "ማስተር ፕላኑ መሰሪ ነው" በቀለ ገርባ የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላንን በተመለከተ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ያለውን ዝርዝር አቋም በተመለከተ የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባን አዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ በፅ/ቤታቸው ተገኝቶ አነጋግሯቸዋል፡፡ መንግሥት ማስተር ፕላኑ ከተሞችን በመሰረተ ልማት በማስተሳሰር እድገትን ለማምጣት ከፍተኛ ጥቅም አለው ይላል፡፡ ፓርቲያችሁ ደግሞ ማስተር ፕላኑን አልቀበልም ብሏል፡፡ በምን ምክንያት ነው የማትቀበሉት? እኛ ማስተር ፕላኑን የማንቀበለው በትክክል የህዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የተዘጋጀ ነው የሚል እምነት ስለሌለን ነው፡፡ መንግሥት በዚህ አሳቦ ወደ ኦሮሚያ አጎራባች ከተሞች ዘልቆ እየገባ … [Read more...] about “ትግራይ ወረዳ ውስጥ ያለ የመንግሥት አሰራር በኦሮሚያ ውስጥ … ይገኛል”
የአቶ ዠ የልማታዊ አርቲስትነት ደብዳቤ
አቶ ዠ ደብዳቤ ጻፉ። 40 አመት ሙሉ መፈክር ሲጽፉ ኖረው፣ ኖረው፣ ኖረው አሁን አርቲስት ለመሆን የሚያበቃውን ዝግጅት የጨረሱ መስሎ ተሰማቸው። ሰሞኑን ለወጣው ማስታወቂያ “ብቁ ነኝ” ብለው አሰቡ። ይድረሥ፣ ለ“ኢሃዲግ ፍቅር” ቴአትር ቤት “ሥራ አስቀማጭ”፣ ይቅርታ በቀድሞ ሥሙ የሃገር ፍቅር ቴአትር ቤት በመባል ለሚታወቀው ... ሥራ አስኪያጅ፣ ጉዳዩ፣ በ 23/2/2008 የወጣውን ማስታወቂያ አስመልክቶ፣ ከታች እንደሚታየው፣ የተለያዩ ኪነጥበባዊ ሥራዎችን ለማቅረብ “ልማታዊ” ፍላጎትን ሥለመግለጽ። የወጣውን ማስታወቂያ አስታኮ የተለያዩ ልማታዊ ኪነጥበባዊ ሥራዎችን ለማቅረብ 40 አመታት ሙሉ ተዘጋጅቻለሁ፣ ብቃት ያለኝም ነኝ። ከዚህ ኪነጥበባዊ ሥራ የሚገኘው ገቢም በከፊል ለታላቁ “ውዳሴ” ግድብ ቦንዳ (ይቅርታ “ቦንድ”) መግዣ እንዲውል ለመስማማት በገዛ ፍላጎቴ እገደዳለሁ። ይቅርታ … [Read more...] about የአቶ ዠ የልማታዊ አርቲስትነት ደብዳቤ
ፈረንሳይ እስከ 160 የሚሆኑ መስጊዶችን ልትዘጋ ነው!
በመጪው ጥቂት ወራቶች ፈረንሳይ እስከ 160 የሚጠጉ መስጊዶችን ለመዝጋት መወሰኗ ተሰማ፡፡ የአገሪቱ ከፍተኛ ኢማም እንዳሉት በሥራ ላይ በዋለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት ጽንፈኛ አመለካከት የሚያራምዱ የእምነት ቦታዎች መዘጋት አለባቸው፡፡ በኅዳር ወር መጀመሪያ አካባቢ በፓሪስ የተከሰተውን ጥቃት ተከትሎ እስካሁን ጽንፈኛ አቋም አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሦስት መስጊዶች መዘጋታቸውን የአገር አቀፍና የአካባቢ ኢማሞች ለመምረጥ ኃላፊነት የተሰጣቸው ኢማም ሃሰን ኤል-አላዊ ለአልጃዚራ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት በቀጣይ ወራቶች በርካታ መስጊዶች እንደሚዘጉ አስረድተዋል፡፡ “ከአገር ውስጥ ሚኒስቴር ጋር በምናደርገው ውይይት እና ይፋ በሆኑት መረጃዎች መሠረት ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው፣ ጥላቻን የሚሰብኩ፣ ታክፊሪ ንግግር የሚደረግባቸው ከ100 እስከ 160 መስጊዶች ይዘጋሉ” … [Read more...] about ፈረንሳይ እስከ 160 የሚሆኑ መስጊዶችን ልትዘጋ ነው!
የተቆለፈበት ቁልፍ!
ከዶ/ር ምህረት ደበበ፣ የአዕምሮ ህክምና ስፔሺያሊስት፣ እ.አ በ2005 ዓ.ም የተጻፈ መጽሀፍ፣ 438 ገጽ ትችት! በዶ/ር ፈቃዱ በቀለ፣ የስልጣኔ ተመራማሪና የኢኮኖሚ ዕድገት ባለሙያ! ይህን መጽሀፍ አግኝቴ ለማንበብ እድል ያጋጠመኝ ከሁለት ሳምንት በፊት ባለቤቴ ወደ ኢትዮጵያ ሄዳ ስትመለስ ይዛልኝ ከመጣች በኋላ ነው። በዶ/ር ምህረት ደበበ የተጻፉ ሁለት ወፈፍራም መጽሀፎች ሲሆኑ፣ አንደኛው መጽሀፍና በቅርብ የወጣውን የሽፋኑ ሰዕል ደስ ስላለኝ እንደ አጋጣሚ አንስቼ ካገላበጥኩኝ በኋላ፣ እስቲ ብዬ ደግሞ ሌላውን ሳገላብጥ አቀራረቡ ደስ ስላለኝ ሃሳቡን ይበልጥ ለመረዳትና ለመገምገም ሆነ ወይም ለመተቸት እንዲያመቸኝ በሚል በመጀመሪያ ያገላበጥኩትን በመተው ቀደም ብሎ የታተመውን ማንበብ ጀመርኩኝ። እንደ ዕውነቱ ከሆነ አንዳንድ ጊዜ ከኢትዮጵያ የሚመጡ በአማርኛ ቁንቋ የተጻፉ መጽሀፎችን … [Read more...] about የተቆለፈበት ቁልፍ!
የመለስ ሬሣ በህይወት ያሉትን ዜጎች እያፈናቀለ ነው
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባርን በራሳቸው ልክ አሰፍተው፤ ተቃዋሚዎቻቸውን አስገድለው፤ ሌሎችን ደግሞ እንዲሰደዱ አድርገው አገር በነጻ አውጪ ስም ለዓመታት የገዙት መለስ ሞተውም ሬሳቸውን እና በሕዝብ ደም የጨቀየውን “ሌጋሲያቸውን” ለመጠበቅ ዜጎች ከመኖሪያቸው ይፈናቀላሉ፤ እምቢ ያሉ ደግሞ ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡ ለመለስ መዘከሪያ ቦታ ለማስቀቅ የተፈቀደበት ደብዳቤ ለዝግጅት ክፍላችን በፌስቡክ በኩል በሰነድነት ደርሶናል፡፡ ደብዳቤው እንደሚያስዳው ሬሣ ለማክበር ሕያዋን እንዲገደሉ፤ እንዲፈናቀሉ ይደረጋል፡፡ ሬሣ ሕያዋንን ለሞት ሲዳርግ! ህወሃት በኃይል በሚገዛት ኢትዮጵያ የማይሰማ ጉድ የለም፡፡ (ጎልጉል) … [Read more...] about የመለስ ሬሣ በህይወት ያሉትን ዜጎች እያፈናቀለ ነው