ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንትና አጃቢዎቻቸው ለሁለት ቀን አዳር ለሆቴል ያወጡት ወጪ ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ እንደነበር ተገለጸ፡፡ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት በአንድ ሆቴል ብቻ እንደሚደረግ አስቀድሞ የተነገረ ቢሆንም የአስተዳደራቸው ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ አጃቢዎቻቸውና ሌሎች የደኅንነት ሠራተኞች በአራት ሆቴሎች ውስጥ አርፈው እንደነበር Weekly Standard የክፍያ ሰነዶችን በማስደገፍ ይፋ አድርጓል፡፡ አስቀድሞ የተለቀቀው መረጃ እንደሚያመለክተው የኦባማ ቡድን በሒልተን ሆቴል ቆይታ እንደሚያደርግና ወጪውም ብር 8,491,127.81 ወይም በግምት ዶላር $ 412,390.86 መሆኑን የሚያሳይ የኮንትራት ውል መፈረሙን ነበር፡፡ ከአሜሪካ መንግሥት የተጠያቂነት ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የፕሬዚዳንቱ ቡድን ለሁለት ቀናት … [Read more...] about ኦባማ “ልማታዊ” ጎብኚ?!
Archives for August 2015
ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ
ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። አዎ! ማተቡን ላጠበቀና በአምላኩ ለሚታመን በእርግጥ ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። ሰዉ ነኝና እንደ ፈጣሪ ቃሌ ሁሉ እዉነት ነዉ ብዬ አለተፈጥሮዬ አላብጥም። ግን ሰዉ ብሆንም ፈጣሪዬን የምፈራ ሰዉ ነኝና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ስል ልቦናዬ እያወቀዉ እንደነ ጋሼ እንደልቡ ዉሸት ደርድሬ ለአንባቢ የማቀርብበት ምንም ምክንያት የለም። ከዚህ ቀጥሎ የማስነብባችሁ እያንዳንዱ ቃል እንደ ዳያስፖራ ተረተኞች የምተርተዉ ‘ሰዉ ሰዉ’ የማይሸተት ተረት ሳይሆን ኢትዮጵያ ድንበር ላይ በየግንባሩ የተሰለፉትንና በስልጠና ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አርበኞች ስጎበኝ በአይኔ ያየሁትንና በጆሮዬ የሰማሁትን ቃል ነዉ። ቨርጂኒያ ወደሚገኘዉ “Dulles” አዉሮፕላን ማረፊያ የሄድኩት ከልጄ ጋር ነበር። ከቤቴ Dulles የግማሽ ሰዐት መንገድ ነዉ። ያቺን ግማሽ ሰዐትና አዉሮፕላን ማረፊያ ደርሼ … [Read more...] about ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ
ጎሳን ለይቶ የሚደረግ ጥቃትን ለማስወገድ መሰረታዊ ለውጥ ያሻል
አንድ መንግስት ልማታዊ ሊባል የሚችለው የሚመራውን ሕዝብ ከዃላ ቀርነትና ከድህነት ኣሮንቓ መንጥቆ ሲያወጣ፣ የህዝቡን ኣንድነትና መልካም ግንኙነት ሲያጠናክር፣ የኣገርን ብሔራዊ ጥቅምና ዳር ድንበር ሲያስከብር ነው። ሕዝብ በኑሮ ክብደት የሚሰቃይበትና የበይ ተመልካች በሆነበት፣ ወጣቱ ተስፋ ቆርጦ ለስደት ሲዳረግና እግረመንገዱን ለተለያዩ ኣደጋዎች የሚጋለጥበት፣ የጎሳ ስሜት ነግሶ ኣንዱ ሌላውን እንዲጠላና ሰላም እንዲናጋ፣ ዜጋ ለዘመናት ከኖረበት ቦታና መሬት በሃይል እየተፈናቀለ እንዲበታተን የሚያደርግ ስርዓት ያሰፈነ ቡድን የሚመራው መንግስት ጥፋታዊ እንጂ ልማታዊ ተብሎ ሊጠራ አይገባውም። የሕዝቡን መብት ገፎ፣ የአገሩን ሃብትና ንብረት፣ ለም መሬት ጭምር ለባእዳን አሳልፎ እየሰጠ፣ እየሸጠና ተባብሮ እየመዘበረ በውጭ አገር ባንክ የሚያካብት ቡድን ስልጣን ላይ ባለበት አገር ውስጥ ልማታዊ … [Read more...] about ጎሳን ለይቶ የሚደረግ ጥቃትን ለማስወገድ መሰረታዊ ለውጥ ያሻል
በቤንሻንጉል-ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በሚኖሩ ዐማሮች ላይ የተፈፀመ የዘር ማጥፋት ወንጀል
መግቢያ ሞረሽ-ወገኔ ይህ አስደንጋጭ ዜና እንደደረሰው የድርጊቱን ዘግናኝነት እና ፍፁም ኢሰብዓዊነት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ ከዚያም አልፎ ያለአግባብ ግለሰቦችንም ሆነ ድርጅቶችን ላለመወንጀል፣ ስለሁኔታው ከሥር መሠረቱ መረጃዎችን ለማጣራት ሙከራ አድርጓል። ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እና ሰብዓዊነት የሚሰማችሁ ግለሰቦች ሁሉ እንድትገነዘቡልን የምንፈልገው፣ በእንዲህ ዓይነት እጅግ የሚሠቀጥጥ ድርጊት ላይ ዘገባ ለማዘጋጀት ምን ያህል ከባድ የኅሊና ፈተና እንደሚደቅን ንፁሕ ኅሊና እና አስተዋይ አዕምሮ ያለው ሰው ይስተዋል አልባልም። አንዳንድ ጊዜ «ቋንቋ ኃሣብን በትክክል ለመግለጽ ያስቸግራል» ይባላል። ዕውነት ነው፣ እንደዚህ ያለ ለመስማትም ሆነ ለመናገርም የሚቀፍ እና የሚከብድን ድርጊት፣ ድርጊቱን ባየው ሰው፣ በተረዳው እና በገባው መልክ ለሁለተኛ እና ለሦስተኛ ወገን ለመግለጽ … [Read more...] about በቤንሻንጉል-ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በሚኖሩ ዐማሮች ላይ የተፈፀመ የዘር ማጥፋት ወንጀል
ትረገም ሆነብኝ!!
ልጇ ነፍሰ ገዳይ - ስለሆነ እርጉም እሱን የወለደች - እናቱ ትረገም ብለው ሲናገሩ እያሉ ሲያወሩ ... አትረገም ብዬ - ልጽፍ አሰብኩና ትረገም ሆነብኝ - “አ” እረሳሁና! … [Read more...] about ትረገም ሆነብኝ!!
ሀገር የማያድስ አዲስ ዓመት ለእኔ ምኔ ነው?!
ዛሬ ላይ የጊዜ ዑደት ተፈጥሮአዊ ልማድ አጃቢና አድማቂ ከመሆን በቀር ዘመን ተሸኝቶ ዘመን ሲተካ አላፊውን ዘመን በመልካምና በበጎ የምንዘክርበት መጪውንም ተስፋ የምናደርግበት አንዳች ተጨባጭና በቂ አመክንዮ (ምክንያት) ያለን መስሎ አይሰማኝም!! ይህን ስል ግን ከእያንዳንዱ ግለሰብ አሊያም ቡድን አንፃር ሳይሆን አንደሀገር ማለቴ ነው፡፡ እነሆ ዳር ላይ ቆመን እንቀበለው ዘንድ የምናሰፈስፍለት የ2008 ዓ.ም በተዳፈነ ዲሞክራሲ የአማራጭ እሳቤ አልባ ወደሆነ የፓርላማ እና የክልል ምክር ቤቶች አስተዳደር ስር የሚዘፍቀን ከዛም ባለፈ ምንአልባትም ሳንሰማና ሳናይ፤ መስማማትና አለመስማማታችንም ሳይታወቅልን በሚደነገጉ የሕግ፣ የደንብ እና የፖሊሲ ድንጋጌዎች የምንዋጥበት ወቅት ጅማሬ ነው ማለት ይቻላል! ለመጠናቀቅና የዘመኑን መቁጠሪያ ወደ 2008 ለመቀየር ጥቂት ቀናት የቀሩት ይህ … [Read more...] about ሀገር የማያድስ አዲስ ዓመት ለእኔ ምኔ ነው?!
ሃሰት ነገሰ፤ ዳቢሎስ ነገሰ ነው
ክርስቶስ በደሙ የዋጀን እኛ ክርስቲያኖችና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃሰትና ቅጥፈት የሚናኝበት እየሆንን ነውና ይህንን ክርስቲያናዊ ያልሆነ ከፋፋይ የሃጢአት ሥራ ለማስቆምና ለማስወገድ የምንጥር እንጂ የሃስትና የቅጥፈት መሣሪያ በመሆን ከክርስቲያን ወገኖቻችን ጋር የምንናቆር አንሁን። ዛሬ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ሕዝብን ከሕዝብ የሚከፋፍልና የሚያናቁር ሃሰትና የቅጥፈት ስራ ብቻ መሆንኑን ሁሉም ይረዳ። ሃስትና ቅጥፈትን የደገፈና የተከተለ ክርስቲያን ሁሉ ከሃሰተኞቹና ከቀጣፊዎቹ ያነሰ ሃሰተኛና ኅጢዓተኛ ሊሆን እንደማይችል በሚገባ ሊረዳው ይገባናል። አዕምሮውን የሰይጣን ማደሪያ ካላደረገና የሰው ልጅ ጤና ካልነሳው በስተቀር ውሸትንና ቅጥፈትን መተዳደሪያዬ ብሎ ሊይዝ አይችልም። በተለይም ደግሞ፤ በፈጣሪው አምኖ በክርስትና የተጠመቀና እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ከሃሰትና ከውሸት ሁሉ … [Read more...] about ሃሰት ነገሰ፤ ዳቢሎስ ነገሰ ነው
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፱
ከአዘጋጆቹ፤ የጎልጉል ወዳጅ ወለላዬ “እኚህ ሰው ማናቸው?” በሚል ዓምድ ሥር ለአገራቸው የለፉና የደከሙ ኢትዮጵያውያንን እንዲነሱ፣ እንዲወደሱ፣ እንዲከበሩ፣ … በማድረግ ግሩም ሥራ ሲሰሩ መቆየታቸውን ባለፈው ጠቅሰን ነበር፡፡ እርሳቸው ባለባቸው በርካታ ኃላፊነቶች ለተወሰኑ ጊዜያት ሳይመቻቸው ቢቀርም አሁንም ግን “እኒህ ሰው ማናቸው” ዓምድ በልባቸው ነው ያለው፡፡ በመሆኑም ሰሞኑን ከቀድሞ ፎቶዎች መካከል የሆነውን ይህንን በመላክ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን የካቢኔ አባላት የነበሩትን በቁጥር በማድረግ እነማን እንደሆኑ እንደተለመደው ቢቻል በግጥም አንባቢያን በማቅረብ እንዲሳተፉ በግጥም ጥሪ አድርገዋል፡፡ በጃንሆይ ዘመን የካቢኔ አባላት በመሆን ሰርተዋል እኒህ የሚታዩት እስቲ እነማናቸው ግለጹ በዝርዝር በፎቷቸው አንጻር በተሰጠው ቁጥር፡፡ … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፱
Is Africa really rising?
Introduction President Barack Obama praised Africa’s economic performance in his speech on the 2015 Global entrepreneurship summit which was held in Nairobi from July 25-26, 2015. He stressed that Africa is “on the move and the continent is one of the fastest growing region in the world.” Further, he emphasized that “the people are being lifted out of poverty, and income is growing.” In his words, “the middle class is growing and young people are harnessing technology to change the way Africa … [Read more...] about Is Africa really rising?
የድህረ-መለሱ ኢሕአዴግ አሰላለፍና የ“አዲሱ” ሥራ አስፈጻሚ የቢሆን ዕድል
የአራት ድርጅቶች ስብሰብ የሆነው ኢሕአዴግ፤ በሕወሓታዊ የድርጅት መንፈስ እየተመራ የስልጣን ቆይታ ዘመኑን ከአመታት ልኬት ወደ አስርታት ያሻገረ በመሆኑ፣ ከእንግዲህ የአገዛዝ ዘመኑን በክፍለ ዘመን ክፋይ አገላለጽ መጥራቱ ተራዛሚ የስልጣን ቆይታውን ይበልጥ የሚገልፀው ይሆናል፡፡ እናም ሩብ ክፍለ ዘመን ያህል በስልጣን ላይ ያለው ኢሕአዴግ በሰሜን ኢትዮጵያ የፖለቲካ ተዋረድ አገሪቱን “እየመራ” እዚህ ደርሷል፡፡ ግንባሩ ከፊት ለፊቱ አንደ “ትልቅ” ድርጅታዊ ጉባኤ ይጠብቀዋል፡፡ ነሐሴ 20/2007 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ የድርጅቱ አስረኛ ጉባኤ መካሄድ ይጀምራል፡፡ የመቀሌው ጉባኤ ከመካሄዱ ከቀናት በፊት፣ አራቱም ድርጅቶች በየክልል ርዕስ ከተማቸዉ የየራሳቸውን ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ የድርጅታችዉን ሊቀ-መንበርና ም/ሊቀመንበር የሚመርጡ ይሆናል፡፡ ዛሬ ላይ እየታየ ካለው የግንባሩ ከፍተኛ … [Read more...] about የድህረ-መለሱ ኢሕአዴግ አሰላለፍና የ“አዲሱ” ሥራ አስፈጻሚ የቢሆን ዕድል