• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሀገር የማያድስ አዲስ ዓመት ለእኔ ምኔ ነው?!

August 27, 2015 12:26 am by Editor 2 Comments

ዛሬ ላይ የጊዜ ዑደት ተፈጥሮአዊ ልማድ አጃቢና አድማቂ ከመሆን በቀር ዘመን ተሸኝቶ ዘመን ሲተካ አላፊውን ዘመን በመልካምና በበጎ የምንዘክርበት መጪውንም ተስፋ የምናደርግበት አንዳች ተጨባጭና በቂ አመክንዮ (ምክንያት) ያለን መስሎ አይሰማኝም!! ይህን ስል ግን ከእያንዳንዱ ግለሰብ አሊያም ቡድን አንፃር ሳይሆን አንደሀገር ማለቴ ነው፡፡

እነሆ ዳር ላይ ቆመን እንቀበለው ዘንድ የምናሰፈስፍለት የ2008 ዓ.ም በተዳፈነ ዲሞክራሲ የአማራጭ እሳቤ አልባ ወደሆነ የፓርላማ እና የክልል ምክር ቤቶች አስተዳደር ስር የሚዘፍቀን ከዛም ባለፈ ምንአልባትም ሳንሰማና ሳናይ፤ መስማማትና አለመስማማታችንም ሳይታወቅልን በሚደነገጉ የሕግ፣ የደንብ እና የፖሊሲ ድንጋጌዎች የምንዋጥበት ወቅት ጅማሬ ነው ማለት ይቻላል! ለመጠናቀቅና የዘመኑን መቁጠሪያ ወደ 2008 ለመቀየር ጥቂት ቀናት የቀሩት ይህ የ2007ዓ.ም በመሪዎቻችን አጅግ አሳዛኝ፣ አሣፋሪና አስቂኝ ድርጊቶች አንዲሁም ወደር በማይገኝለት ሐሰት የተጨማለቀ ነበር ብዬ ብል ከግነት ይቆጠርብኛል የሚል ግምት የለኝም! ምክንያቱም ሁሉንም እያየንና እየታዘብን ያለፍነው ሐቅ ነውና!

ሕሊናቸውን ሽጠው ሆዳቸውን እየሞሉ ካሉ፤ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ጥምቀት የልማታዊ ዲሞክራሲ ማህተብ ካነገቱ ካድሬዎች በቀርስ ማን አጋነንክ ወይም ሐሰት ተናገርክ ብሎ ይከሰኛል??!!

1. አሳዛኞቹ ተግባራት፡- ነገ ላይ በአዲሱ ዘመን አሮጌው ሊሰኝ የሚጣደፈውና ጉደኞች ጉደኛ ያሰኙት 2007ዓ.ም የሰላሳ ወገኖቻችን ደም በሊቢያ በረሐ በአረመኔዎች እጅ በከንቱ መፍሰስን የተመለከትንበትና የሰማንበት መንግሰታችንም ዜጎቹ መሆናቸውን አስኪያጣራ ዓለም ኢትዮያዊያን አንደሆኑ አኛም ወንድሞቻችን መሆናቸውን ቀድመን ያወቅንበትን ሂደት አሳልፈናል፣ የሳሙኤል አወቀ ሰለእውነት የመጮህ ትግል ፍሬ በሐሰተኞች በግፍ የመገደል እጣ ፈንታ መሆኑን ተረድተንበታል፣ በሐይማኖት ነፃነት መብት ለጥያቄዎቻቸው መልስን ለችግሮቻቸው መፈትሔዎቸን ይፈልግ ዘንድ የተቋቋመ ኮሚቴ አባላት የነበሩ የሙስሊም ወገኖቻችን ላይ በተመሰረተ የሽብር ክስ ከ7 እስከ 22 ዓመት የሚደርስ የእስር ፍርድን ተመልክተናል፣ በዩ.ኤስ.ኤ ካሊፎርኒያና በአውስትራሊያ የተከሰተው ዓይነት ድርቅ (ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ለተናገሩት አኔ አፍራለሁ!!) በተወሰነው የሀገራችን አካባቢዎች መከሰቱን አይተናል፤ በእነዚህ ሁሉ 2007 ዓ.ም ሁላችንን አሳዝኖ ወደማለፉ ነው፡፡

2. ወደር አልባው ሐሰትና አስቂኙ ክንውን፡- ከ1987ዓ.ም ጀምሮ አምስት ዓመታትን እየጠበቀ በ2 እና በ7 በሚጨርሱ የዘመን አድሜ ቁጥሮች የሚደረገው ጠቅላላ ምርጫ 2007ዓ.ም ላይ ሲደረስ ለየለትና በማሩ ፈንታ እሬቱን እና ምሬቱን የጋገረች ንብ መቶ በመቶ ተመርጣለች የሚል ለጆሮ የሚከበድ ትልቅ ሐሰት ተሰማበት፤ ይህን ውሸት የነገረን ምርጫ ቦርዱ ደግሞ የዚህ አስቂኝ የሀሰት ክንውን የስራ ሂደት ባለቤት መሆኑን በቁርጠኝነት አስመሰከረ!

3. የዓመቱ ዘመን ተሻጋሪ አስቂኝ ትውስታዎች፡- መቼም 2007ዓ.ም እድለኛ ዓመት ነበር ከተባለ ለመጀመሪያ ጊዜ በስልጣን ላይ የሚገኝ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሀገራችንን ለመጎብኘት የመጣበት ዘመን ተብሎ ሊጠራ መቻሉ ብቻ ይሆናል፡፡ እናም ይህን ተከትሎ መሪዎቻችን የቀለዷት ቀልድ ዘመን ዓለሜን ስስቅባት የምኖር አቻ የለሽ ቀልድ ናት፡፡ ይህቺውም ምንድንናት ብትሉኝ ባራክ ኦባማ ወደ ናይሮቢ ከዛም ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት እየተሰናዳ ባለበት ወቅት ያለምንም ኮሽታ ሌላው ቀርቶ ክሳቸውን የያዘው ፍርድ ቤት እንዃን ስለሁኔታው ሳይሰማና ሣያውቅ በክስ መቋረጥ ሰበብ የተወሰኑ የዞን9 ጦማሪያንና ጋዜጠኞችን ከእስር የለቀቁባት ኩምክና ናት እላችኋለሁ!!

እንደው ይቺ ቀልድ መቶ ዓመት የመኖር እድል ቢገኝ መቶውንም ዓመት ጥርስ ታስከድናለች ትላላችሁ? በዚህም ብቻ ያልበቃው ቀልድ ፕሬዝዳንቱ ከተሸኑና ሰንበትበት ካልንም በኋላ በቅርቡ የተወሰኑ ፖለቲከኞችን በነፃ በመልቀቅ ቀጥሏል!! ሲፈልግ ያለበደልህ ያስርሀል፤ ሲያሻው በነፃ ይለቅሀል!! ታድያ ይህን የመሰለ ቀልደኛ ከወዴት ይገኛል?!

የቀልዱ ጨዋታ የገባቸው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማም ጨዋታውን ተቀላቅለው የኛውን ቀላጅ በኢዮቤልዩ ቤተመንግሰት ከፍ ከፍ አደረጉና በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በዝረራ አፈርጠውልኝ ሔዱ’አ!!

ዘመን ሲቀየር አስተሳሰብ አብሮ ላይቀየር፣ ስርአትም ከዘመን ኋሊት ለፈፀመው በደልና ስህተት ከዘመን ፊት ቀርቦ ላይታረምበትና እና ላይጠየቅበት የአዲስ ዓመት ለውጥ የቁጥር መቀየር እና የወቅት ሽግግር አንጂ የዘመን መታደስ ሊሰኝ አንዴት ይቻለዋል?! አሳዛኙ ድርጊት፣ ሐሰቱና አስቂኙ ክንውን አንዲሁም ቀልዱ ለከርሞ አብሮን ሲሻገር እያየን! እውነት እላችኋለሁ አዲስ ዓመት የሚባል የለም አሁንም ነገም አሮጌው ላይ ነን!!


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Tigestu Firew says

    August 27, 2015 07:28 pm at 7:28 pm

    የዚህ ፅሑፍ ፀሐፊ እይታዎች ሁሌም ይገርሙኛል!! የተለያዩ ፅሑፎቹን በፌስቡክ ገፁ ላይ አንብበያለሁ በጣም ይመቹኛል! ጎለጉል ጋዜጣም ይህ ፅሑፍ ለብዙኀን ተደራሽ ይሆን ዘንድ በጋዜጣው ላይ ማውጣቱ አስደስቶኛል!!

    Reply
  2. አክሊለ says

    September 1, 2015 05:26 pm at 5:26 pm

    ውድ ጎልጉል፣ ይህን ግጥም በዚህ ሊንክ ላይ አንብቤ ስለወደድኩት ልኬላችኋለሁ። የነገ ሰው ይበለን። http://ethiopianchurch.org/en/poems_shorts/242-%E1%88%98%E1%88%B5%E1%8A%A8%E1%88%A8%E1%88%9D%E1%8A%95-%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB.html

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule