• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኦባማ “ልማታዊ” ጎብኚ?!

August 31, 2015 09:19 am by Editor 3 Comments

ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንትና አጃቢዎቻቸው ለሁለት ቀን አዳር ለሆቴል ያወጡት ወጪ ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ እንደነበር ተገለጸ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት በአንድ ሆቴል ብቻ እንደሚደረግ አስቀድሞ የተነገረ ቢሆንም የአስተዳደራቸው ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ አጃቢዎቻቸውና ሌሎች የደኅንነት ሠራተኞች በአራት ሆቴሎች ውስጥ አርፈው እንደነበር Weekly Standard የክፍያ ሰነዶችን በማስደገፍ ይፋ አድርጓል፡፡ አስቀድሞ የተለቀቀው መረጃ እንደሚያመለክተው የኦባማ ቡድን በሒልተን ሆቴል ቆይታ እንደሚያደርግና ወጪውም ብር 8,491,127.81 ወይም በግምት ዶላር $ 412,390.86 መሆኑን የሚያሳይ የኮንትራት ውል መፈረሙን ነበር፡፡

hotels

ከአሜሪካ መንግሥት የተጠያቂነት ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የፕሬዚዳንቱ ቡድን ለሁለት ቀናት ያረፉት በአንድ ሆቴል ሳይሆን በአራት የተለያዩ ሆቴሎች ነበር፡፡ በዚህም መሠረት ከላይ ለተጠቀሰው የሒልተን ሆቴል ወጪ 1,280 የመኝታ ክፍል ምሽቶች ተከራይተዋል፡፡ 22 ማዞሪያ ከዋሪት ህንጻ ፊትለፊት በሚገኘው ካፒታል ሆቴልና ስፓ (Capital Hotel and Spa) ለ1,000 ክፍል ምሽቶች ብር 3,673,950 ወይም በዶላር $178,433.71፤ ካዛንቺስ በሚገኘው ኢሊሊ (Elilly) ሆቴል ለ120 የመኝታ ክፍሎች ብር 5,100,480 ወይም በዶላር $246,877.06፤ እንዲሁም በሸራተን አዲስ ለ1,236 የመኝታ ክፍል ምሽቶች ብር 10,050,826.13 ወይም በዶላር ግምት $488,141.14 ወጪ መደረጉ ተዘግቧል፡፡ ይህም ለአራቱ ሆቴሎች በድምሩ በዶላር ግምት 1,325,841 ወይም በብር 27,771,383.94 መሆኑ ጨምሮ ተገልጾዋል፡፡ ክፍያው አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አስፈጻሚነት በውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) መከናወኑ መረጃው በግልጽ ያስረዳል፡፡

hilton elilly capital sheraton

ከፕሬዚዳንቱ ቡድን ጋር አብረው የተጓዙ በፍሎሪዳ ጠቅላይግዛት የሚገኙ ነጋዴ ለWeekly Standard እንዳሉት “(በአዲስ አበባ) አብሬአቸው ስሰራ የነበሩ በከተማዋ የሚገኙ አሜሪካውያን እንደነገሩኝ ኦባማ አዲስ አበባ በነበሩበት ጊዜ የአሜሪካ መንግሥት ሸራተንን እንዳለ ገዝቶት ነበር”፡፡ ኦባማ በሸራተን ለመቆየታቸው ደግሞ አብሯቸው የተጓዘው ፎቶ አንሺ Pete Souza የምስል ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡

ይህ የሆቴል ወጪ ብቻ ሲሆን ከዚህ ሌላ ለእጅ ስልክ ቀፎዎች ግዢ $7,540 ዶላር ወጪcell መደረጉን አብሮ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡ ስልኮቹ የተገዙት በአሜሪካ ኤምባሲ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ኩባንያ ከውጪ ድርጅት ጋር ባደረገው ኮንትራት መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡ ስልኮቹን የሸጠው ኩባንያ ማንነት ተጠይቆ ቤተመንግሥቱ (ኋይት ሃውስ) መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡ ስልኮቹን ማን እንደተጠቀመባቸው ከጉብኝቱ በኋላ ደግሞ የት እንደደረሱ አይታወቅም፡፡

ኦባማ ኢትዮጵያን በጎበኙ ወቅት የወጣው ይህ ወጪ የሆቴል ኪራይና የስልክ ብቻ ሲሆን ሌላ እጅግ በርካታ የሆነ ከጉብኝቱ ጋር የተደረገ የደኅንነት፣ የጉዞ፣ የግንኙነት፣ የሚሊታሪ፣ ወዘተ ወጪዎችን የሚጠቀልል አይደለም፡፡

በሆቴሉ ወጪ ዙሪያ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ እንዳሉት “ካንበት ሁኔታ አኳያ ስተረጉመው ኦባማ ልማታዊ ጎብኚ ናቸው፤ ሥልጣናቸውን ከመልቀቃቸው አንድ ሁለቴ ጉብኝታቸውን ቢደግሙ የባንክ ዕዳችንን ከፍለን ጨርሰን ትርፋማ እንሆን ነበር፤ ሕገመንግሥታቸውን ቀይረው ለሦስተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ቢወዳደሩ መቶ በመቶ እደግፋቸዋለሁ፤ መቶ በመቶ እንደሚያሸንፉም እርግጠኛ ነኝ” ብለዋል፡፡ (የገጽ ፎቶ: Pete Souza)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Politics Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. rasdejen says

    August 31, 2015 12:43 pm at 12:43 pm

    So what? America is ever since the 1980s lier, destructive and arrogant?

    Reply
  2. ketma jifar says

    September 1, 2015 01:21 am at 1:21 am

    የዚህ አይነት ሀገራችንን የሚመለከት ጽሁፍ እንዳለ ክውጭ ጋዜጣ ገልብጠን መጻፍ ያለብን አይመስለኝም። እንኳንስ 1000 ክፍሎች 300 ክፍሎች ያሉት ሆቴል እንኳ በአዲስ አባ የልም ። ይታረም።

    Reply
    • Editor says

      September 2, 2015 07:20 am at 7:20 am

      ketma jifar

      ዜናውን ከውጭ ጋዜጣ እንዳገኘነው ብንጠቅስም መረጃው ግን የተገኘው በፈጠራ ወይም በግምት አይደለም:: ለነገሩ እንዲህ ያለው ዜና የሚገኘው ህወሃት ከሚመራት ኢትዮጵያ ሊሆን እንደማይችል ግልጽ በመሆኑ ለርስዎም የተሰወረ አይደለም::

      በዜናው ላይ እንዳሰፈርነው የአሜሪካ መንግሥት ለሆቴሎቹ የከፈለውን ወጪ ያደረገበት መረጃ በግልጽ ተቀምጦዋል:: ሆቴሎቹ ያንን ያህል ክፍል ይኑራቸው አይኑራቸው ማጣራቱ ሳይሆን የተከፈለው ወጪ መጠን የዜናው ቀዳሚ ዓላማ በመሆኑ የክፍሎቹ ብዛት ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ አልነበረም:: ከዚህ ሌላ ክፍያውን የፈጸመው ያሜሪካ መንግሥት ይፋ ባደረገው መሠረት የተከራየውንና የከፈለውን በገልጽ አስቀምጦዋል:: ዋናው ዜና ለሁለት ቀናት አዳር ይህንን ያህል ወጪ ለሆቴል መደረጉ ነው::

      በእኛ በኩል የተፈጸመው ግድፈት በእንግሊዝኛው በሦስት አገላለጽ ማለትም – sleeping rooms, room nights and sleeping room nights – የሚሉትን በአንድ የአማርኛ አገላለጽ መጻፋችን ነው – ለዚህም እርምት ወስደናል::

      ከዚህ በተረፈ የአሜሪካ መንግሥት ለሆቴሎቹ ወጪ ክፍያ ማድረጉ ይበልጥ ለመረዳት በየስሞቻቸው ላይ ከዚህ በታች ያሉትን ማጣቀሻዎች በመመልከት ማስረጃ እንዲያገኙ አስፍረናቸዋል::

      ሸራተን አዲስ

      ሒልተን

      ካፒታል

      ኢሊሊ

      ከምስጋና ጋር

      አርታኢ/Editor
      ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
      http://www.goolgule.com
      editor@goolgule.com

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule