ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ ሶሻል ፓርቲና የደቡብ ህብረት ፓርቲ መሪ ናቸው። በግል የመድረክ መስራች ሲሆኑ፣ የሚመሩት ድርጅትም በመድረክ ጥላ ስር ከተሰባሰቡት ፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ይገኝበታል። ፕ/ር በየነን ጨምሮ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ኢህአዴግን በመቃወም የሚታወቁ ፖለቲከኞች ተተኪ ፖለቲከኞች አላዘጋጁም በሚል ይወቀሳሉ። በዚህ ጉዳይ ስማቸው ከሚነሱት መካከል አንዱ ፕ/ር በየነ ናቸው። ፕ/ር በየነ አሜሪካ ለሥራ መምጣታቸውን ተከትሎ የጎልጉል ዘጋቢ ቃለ ምልልስ አድርጎላቸዋል። ፕ/ር በየነ በቃለ ምልልሳቸው ወቅት በተደጋጋሚ "እኔ የምናገረው ሰክነው ማዳመጥ ለሚችሉት ነው" በማለት ያሳስባሉ። ለምን? ጎልጉል፡- ስለ መንግሥትና ተቃዋሚዎች እርቅ ጉዳይ ወሬ ይወራል የሰሙት ነገር አለ? ፕ/ር በየነ፡- የለም። ምንም አልሰማሁም። ጎልጉል፡- እርስዎ የሚመሩት ፓርቲ ጥያቄው … [Read more...] about ፕሮፌሰሩ – ሰክነው ማዳመጥ ለሚችሉ መናገር ያስደስታቸዋል
Archives for January 2014
ርዕዮት አለሙ ጋዜጠኛ እንጅ አሸባሪ ናት ብየ አላምንም!
የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን ስራዎች በቅርብ ተከታትያለሁ! ውንጀላ እስራቷን ፣ ህክምና እንድታገኝ መደረጓን እና የቤተሰብ እና የወዳጆችዋ ጉብኝት እንዳታገኝ መከልከሏን ሰምቻለሁ ! ይህ ሁሉ በዚህች የመናገር የመጻፍ ነጻነቷን ተጠቅማ ህገ መንግስታዊ መብቷን በተጠቀመች ወጣት ጋዜጠኛ ላይ የሚከፈል መስዋዕትነት ቢሆንም ስቃይ መከራዋ ፣ በደል መገፋቷ ያንገበግበኛል!እናም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ተተገፈፈቸው መብቷ ይመለስ ዘንድ በሚደረገው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ደጋፊ ነኝ ! ርዕዮት አሸባሪ አይደለችም ብየ አምናለሁና ፊርማየን ለድጋፍ ሳስቀምጥ ኩራት ይሰማኛል ! ፍትህ ለጋዜጠኛ ርዕዮትና ለመሰሎቿ ስመኝ ለኢትዮጵያስ እንኳንም ተወለድሽ የምላት አሁንም በኩራት ነው! ግጥሙን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about ርዕዮት አለሙ ጋዜጠኛ እንጅ አሸባሪ ናት ብየ አላምንም!
“ወደው አይስቁ”
የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም። የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ። "የምኒሊክ ወንጀል በጡት መቁረጥ ብቻ አያበቃም። ... የወንዶች ብልትም ተቆርጧል።..." በአኖሌ ሃውልት የምትገረሙ ነፍጠኞች ካላችሁ። በዚህ ብዙም አትደነቁ። ገና የወንድ ልጅ ሃፍረተ-ስጋ በሃውልት መልክ በአደባባይ ይቆምላችኋል። "የባሰ አታምጣ!" ነው ነገሩ። ሜንጫዎቹ ሰክረዋል። አእምሮዋቸውም ስቷል። የሚናገሩትን … [Read more...] about “ወደው አይስቁ”
ሶስት ነገር ያጣችው ሳልዋ – አሜሪካ
አሜሪካ የመጣችው ከ27 አመት በፊት ነበር። ሁለት ልጆች የወለደችለት ባለቤትዋ በሞት ሲለያት ታዳጊ ህጻናት ልጆቿን ይዛ በሱዳን በኩል አድርጋ አሜሪካ መጣች። ሳልዋ ትባላለች፤ የጠይም ቆንጆ ናት። በአሜሪካ ዲሲ ከተማ ብዙዎች የሚያውቋት በታታሪ ሰራተኛነቷ፣ በሳቅ ጨዋታዋ፣ እንዲሁም በመልካም ባህርይዋ ነው። ጥሩ ስራና ገቢ የነበራት ሳልዋ በፍቅር ከቀረበችው ሃበሻ ጋር በአብሮነት መኖር ይጀምራሉ። ለረጅም አመት ብዙዎችን የሚያስቀና ፍቅር እንደነበራቸው የሚያውቋቸው ይናገራሉ። በድንገት የሳልዋን ልብ የሚሰብር ሁኔታ ይፈጠራል፤ የምትወደውና ልጅ ያልወለደችለት ፍቅረኛዋ በድንገት በሞት ይለያታል። ሃዘኑን መቋቋም የተሳናት ሳልዋ ይባስ ብሎ ሁለቱ ልጆቿ ጥለዋት ወደ ሌላ ከተማ ሄዱ። ለ17አመታት ገደማ ጠይቀዋት አያውቁም፤ እሷም ልጆቿ የት እንዳሉ አታውቅም። ሶስት ነገር ያጣችው ሳልዋ ጤናዋ … [Read more...] about ሶስት ነገር ያጣችው ሳልዋ – አሜሪካ
ግራና ቀኝ ጠፋን!
በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ወያኔ-ኢሕአዴግ የሚወቀስበት ሥራ በጣም ቢያመዝንም የሚመሰገንበት ሥራ የጽሑፍ ቁጥጥርን ማስቀረቱ ብቻ ነው፤ ሁልጊዜም አንድ ጥሩ ነገር የሚያስከትለው አብዛኛውን ጊዜ የማይጠበቅ ነገር ሊኖር ይችላል፤ ለምሳሌ አጠቃላይ ነጻነት ሲመጣ ወንጀለኛነት ይጨምራል፤ እንዲሁም የጽሑፍ ቁጥጥር ሲነሣ ጸሐፊዎች ይበዛሉ፤ ትምህርት በተስፋፈበትና ማንም እንደፈለገ ለመጻፍና ለማሳተም ችሎታውም ዕድሉም በማይገኝበት፣ ሳያበጥርና ሳይሰልቅ አሰር-ገሰሩን ጽፎ በአደባባይ የሚወጣውን ጥምብ-እርኩሱን አውጥተው ሁለተኛ እንዳይለምደው የሚያደርጉ የታወቁና የሰላ አእምሮና ብዕር ያላቸው አርታእያንና ሐያስያን (ገምጋሚዎች) ባሉበት ብዕሩን የሚያባልግ ጸሐፊ አይወጣም፤ ይህ ሁሉ ባልተሟላበት እንደኛ ባለ አገር ውስጥ ብዕርን ማባለግ እንደመብት ወይም እንደነጻነት እየታየ ነው፡፡ በአደባባይ … [Read more...] about ግራና ቀኝ ጠፋን!
የጥምቀት በዓል
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ውሀ በዮሐንስ እጅ እንደተጠመቀ እንኳን ክርስቲያን ከክርስትና እምነት ውጭ የሆነ ሁሉ ያውቀዋል። ክርስቲያን ነኝ የሚል ሁሉ ይሰብከዋል። በተለይ እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህናት የጥንት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አበው በሰሩልን ስርአት ከዓለም ልዩ በሆነ መንገድ እናንጸባርቀዋለን። በውስጡ ያዘለው ለወዳጅ ለጠላት የተሸከመው የመልእክቱ ይዘት እና ጥልቀት ምን ያህል እንደገባን እራሳችንን እንጠይቅ። ምክንያቱም ይህች ጦማር የተሸከመችውን ያባቶቻችንን ስሜት ለመናገር ለመመስከርና ትውልዱን ለማስተምር የሚጠይቅና የሚፈትን ከዚህ ዘመን የከፋ የለም። ስለ ጥምቀት በዓል ሁሉም የሚሰብከውን ሁሉም የሚያውቀውን በዚህች ጦማር ገልብጨና መልሸ በመናገር አንባቢን ማድከም አልፈልግም። ሲነገር ብሰማ ኖሮ ሰአቴን ባላጠፋሁ እኔም ባልደከምኩ ነበር። ይህ … [Read more...] about የጥምቀት በዓል
“በሴቶች ላይ የሚደረግ አካላዊ ጥቃትና ትንኮሳ ይቅር!”
ነገ ከተራ፣ ከነገ በስቲያ ጥምቀት ስለሚከበር ቢሮ ውስጥ ያለን ኢትዮጵያውያን ጥምቀትን አይተው ለማያውቁ ፈረንጅ ባልደረቦቻችን ስለ በአሉ ዘርዘር አድርገን እያወራን ነበር፡፡ ወሬው ሲሟሟቅ አንዱ ልጅ "the best part is throwing lemon (lime) on the girls!" አለ፡፡ ‹‹ከሁሉ ከሁሉ ደስ የሚለኝ ግን ልጃገረዶች ላይ ሎሚ መወርወር ነው›› እንደማለት ፡፡ ፈረንጆቹ ግራ ተጋቡ፡፡ ‹‹በበአል ምድር ምን ይሁን ብላችሁ ነው ሴቶች ላይ ሎሚ የምትወረውሩት?›› ብሎ ጠየቀ አንዱ፡፡ ‹‹ለፍቅር ለመጠየቅ ነዋ!...ሎሚ የተወረወረባት ሴት ደስ ይላታል፡፡ እንደውም ልጃገረዶች ወደ ጥምቀት ሲሄዱ አዲስ ልብስ ወይ ያላቸውን አጥበውና ተኩሰው ለብሰው፣ ተኳኩለው ነው የሚሄዱት፡፡ ያውም፤ ‹‹ እንደው ቀንቶኝ ሎሚ የሚወረውርብኝ አገኝ ይሆን!›› ብለው አልኩት፡፡ ይባስ ግራ … [Read more...] about “በሴቶች ላይ የሚደረግ አካላዊ ጥቃትና ትንኮሳ ይቅር!”
ኢትዮጵያን ለማየት ፣ ጥምቀት በጎንደር ማክበር…!
የከተራው በአል ከተራ ምንድን ነው? ከሚለው ትርጓሜ እንነሳ ... በየዓመቱ የጥምቀት በዓል በድመቀት ይከበራል፡፡ ከበዓሉ በፊት የከተራ በዓል የሚከበርበትን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ገለጻ ከተራ ከበበ ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡ የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥል ይውላል፡፡ የምንጮች ውኃ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል ፣ ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ ይገደባል፡፡ ከተራ በዓል በየዓመቱ በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ይውላል ። የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታይ ምእመናን ሲወርድ ሲዋረድ ይዘው በመጡት ሃይማኔታዊና ባህላዊ እሴት መሰረት በጥምቀትን በዓል ዋዜማ … [Read more...] about ኢትዮጵያን ለማየት ፣ ጥምቀት በጎንደር ማክበር…!
ይመቻችሁ ጌቶቼ
ኩርዳዊ ነኝ ከኢራን - ኢማን አባስ እባላለሁ በቋንቋዬ እንዳልቀኝ - እንዳልከትብም ሁኛለሁ፤ የኔ ጌቶች ያሻቸውን - እሆን ዘንዳ ቢያስጨንቁኝ ግዳይ ጣልኩኝ እራሴን - ጭካኔያቸው ቢብሰኝ፤ ያውላችሁ ያሻችሁት - እንዳልሆን እሆን ፍርዳቸሁ አንደበቴን ተቆልፌ - ዐይኖቼን ተለጉሜ ይመቻችሁ እላለሁ - ጆሮቼን አስከርችሜ፤ ብእሬን ወርውሬ - ቀለሙን ደፍቼ ፍረዱኝ እላለሁ - እናንት ወገኖቼ፤ (ለምሥራቅ ኩርድ ባለቅኔው ለኢማን አባስ አመጽ መታሰቢያ) … [Read more...] about ይመቻችሁ ጌቶቼ
Terror plot to turn Ethiopian Epiphany celebration into an inferno uncovered
According to our well-placed sources in the inner circle of the ruling minority junta’s powerful and complex security apparatus, the regime has already assigned several well-trained and craven secret service agents dressed as Muslims to carry out massive bombing campaign during the Ethiopian Orthodox Tewahido Church’s Epiphany commemoration feast (Timket) on the 19th and 20 January 2014. The distinctly unpopular and even more feared government of Ethiopia, the godfather of terror and wanton … [Read more...] about Terror plot to turn Ethiopian Epiphany celebration into an inferno uncovered