ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ውሀ በዮሐንስ እጅ እንደተጠመቀ እንኳን ክርስቲያን ከክርስትና እምነት ውጭ የሆነ ሁሉ ያውቀዋል። ክርስቲያን ነኝ የሚል ሁሉ ይሰብከዋል። በተለይ እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህናት የጥንት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አበው በሰሩልን ስርአት ከዓለም ልዩ በሆነ መንገድ እናንጸባርቀዋለን። በውስጡ ያዘለው ለወዳጅ ለጠላት የተሸከመው የመልእክቱ ይዘት እና ጥልቀት ምን ያህል እንደገባን እራሳችንን እንጠይቅ። ምክንያቱም ይህች ጦማር የተሸከመችውን ያባቶቻችንን ስሜት ለመናገር ለመመስከርና ትውልዱን ለማስተምር
የሚጠይቅና የሚፈትን ከዚህ ዘመን የከፋ የለም።
ስለ ጥምቀት በዓል ሁሉም የሚሰብከውን ሁሉም የሚያውቀውን በዚህች ጦማር ገልብጨና መልሸ በመናገር አንባቢን ማድከም አልፈልግም። ሲነገር ብሰማ ኖሮ ሰአቴን ባላጠፋሁ እኔም ባልደከምኩ ነበር። ይህ አባቶች በውስጤ ያስቀመጡት ዛሬ በኢትዮጵያ ላይ ሲደረግ ከማየውና ከምሰማው ጋራ በመጋጨት ስሜቴን የጦር ሜዳ አድርጎ ገንፍሎ የወጣ ነው። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply