• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮጵያን ለማየት ፣ ጥምቀት በጎንደር ማክበር…!

January 18, 2014 04:53 am by Editor Leave a Comment

የከተራው በአል

ከተራ ምንድን ነው? ከሚለው ትርጓሜ እንነሳ … በየዓመቱ የጥምቀት በዓል በድመቀት ይከበራል፡፡ ከበዓሉ በፊት የከተራ በዓል የሚከበርበትን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ገለጻ ከተራ ከበበ ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡ የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥል ይውላል፡፡ የምንጮች ውኃ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል ፣ ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ ይገደባል፡፡

ከተራ በዓል  በየዓመቱ በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ይውላል ።  የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታይ ምእመናን ሲወርድ ሲዋረድ ይዘው በመጡት ሃይማኔታዊና ባህላዊ እሴት መሰረት በጥምቀትን በዓል ዋዜማ ወንዝ ምንጭ ውሃው ይገደባል ፣ ይከተራል። ውኃው የሚከተረው በማግሥቱ ጥር 11 ቀን የጥምቀት በዓል ስለሚከበር ለሕዝቡ መጠመቂያ እንዲሆን ነው። ይህ በጥምቀት ዋዜማ የሚደረገው ውኃውን መከተርና መገደብ ስርአትም ” ከተራ ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

የከተራው በዓል ሲከበር

ታቦተ ሕጉን ተሸክመው ዮርዳኖስን እንደ ተሻገሩት ካህናተ ኦሪት፤ ካህናቱ የማይለወጠውን ታቦተ ሕጉን በራሳቸው ተሸክመው የብሉዩን ሥርዓት ከሐዲስ ኪዳን ጋር አንድ አድርገው የሐዲስ ኪዳን መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስን እያሰቡ፤ ካህናተ ሐዲስም ወደ ከተራ (ዮርዳኖስ) ይጓዛሉ፡፡ ሊቃውንቱም እንዲሁ ለበዓሉ የሚስማማውን ቃለ እግዚአብሔር እያደረሱ እንደሚያድሩ የሃይማኖት ልሂቃን አባቶች ያስረዳሉ።timqet bahir

የከተራ ዕለት ጥር 10 ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ የሄደበትን ለማዘከር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን “ኃዳፌ ነፍስ ለጻድቃን” የሚለውን ዋዜማ ይቆማሉ፡፡ የዋዜማው ቀለም ከቀኑ በአራት ሰዓት በመላው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ይጀመራል ። ከዚያም የዋዜማው ሥርዐት ቅዱስ ተብሎ እስከ ሰላም ያለው ቀለም ይደርሳል፡፡ በዕለቱም ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ ታቦተ ሕጉን የሚያነሡት ሰሞነኛ ካህን ከምግበ ሥጋ ተከልክለው ለዕለቱ የሚገባውን ጸሎት ያደርሳሉ፡፡

በከተራው ዕለት ድንኳን ተተክሎ፣ ዳሱ ተጥሎና ውኃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ታቦተ ሕጉ የሚንቀሳቀስበት ሰዓት ሲደርስ የየቤተ መቅደሱ ታቦታት በወርቅና በብር መጎናጸፊያ እየተሸፈኑ በተለያየ ኅብር በተሸለሙ የክህነት አልባሳት በደመቁ ካህናትና የመጾር መስቀል በያዙ ዲያቆናት ከብረው፣ ከቤተ መቅደስ ወደ አብሕርት /ምጥማቃት/ ለመሄድ ሲነሡ መላው አብያተ ክርስቲያናት የደወል ድምፅ ያሰማሉ፡፡ ምእመናን ከልጅ እስከ ዐዋቂ በዐጸደ ቤተ ክርስቲንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው ህዝበ ክርስትያኑ ያጅቧቸዋል።  በአማሩ አልባሳት ተውበውም መንገዶች በእልልታ በሆታና በጭፈራ በማድመቅ ታቦቶችን በክብር ወደ ተዘጋጀው የበዓሉ ቦታ አጅበው ይደርሳሉ!

በዓለ ጥምቀት እና ኢትዮጵያ

ታላቁ የከተራ እና የጥምቀት በዓል ሲነሳ ኢትዮጵያውያን ሩቅ ዘመንን ተሻግረን ቅዱሳን ሰማዕት አባቶችን ሊቃውንት አባቶችን አስተምሮት እናዘክራለን።  በቅዱስ ላልይበላ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር እየተመላለሱ በብሕትውና እና በስብከተ ወንጌል ያገለግሉ የነበሩት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በመቐለና በመርጡለ ማርያም እየተዘዋወሩ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል፡፡ በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት (1260-1275 ዓ.ም) በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (1203-1204 ዓ.ም) አሳሳቢነት የተጀመረው ሥርዐተ በዓል ተጠናክሮ እንዲቀጥል በዐዋጅ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ ታቦታቱም በሕዝብ ጥበቃና ክብካቤ ተደርጎላቸው በየጥምቀተ ባሕሩ እንዲያድሩ ወስነዋል፡፡ የበዓሉ አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና አድማሱ ብሔራዊነትን እየያዘ መጣ፡፡

ከዐፄ ገብረ መስቀል ጀምሮ የአደባባይ በዓል የሆነው የጥምቀት በዓል በ15ኛው ክ/ዘመን በደገኛው ኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ(1426-1460 ዓ.ም) አማካኝነት ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው ዕለቱን እንዳይመለሱ፣ በዚያ ፈንታ በጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርደው እንዲያድሩ፣ አገሩን በኪደተ እግር ይባርኩም ዘንድ በሄዱበት መንገድ እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ፡፡ ይህን ታሪክ በመከተል ዐፄ ናዖድ (1486-1500) ዓ.ም) ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመን ታቦተ ሕጉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በሚወርድበት እና ከባሕረ ጥምቀቱ ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ አጅቦ አውርዶ፣ አጅቦ መመለስ እንዳለበት timqet celebrationበዐዋጅ አስነግረው ነበር፡፡ ሕዝቡም ታቦታተ ሕጉን በሆታና በእልልታ ከቤተ መቅደስ አጅቦ ከአወጣ በኋላ በባሕረ ጥምቀት ከትሞ ማደር ጀመረ ። …

ኢትዮጵያ ዜና ጥምቀተ ክርስቶስን ከሰማችበት ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አንሥቶ በተለይም ከአጤ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (6ኛው መ/ክ/ዘ) ወዲህ የጥምቀትን በዓል ዛሬ በሚታየው አኳኋን ስታከበር እንደ ቆየች ይታመናል፡፡ በክብረ በዓሉ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት የሚወርዱት ታቦታት በካህናቱ ሃሌታ፣ በምእመናኑ እልልታ እና በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያኑ በተቋቋሙ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች መዝሙሮች ታጅበው በተመሳሳይ አኳኋን እንደሚመለሱ ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያን ለማየት ፣ ጥምቀት በጎንደር ማክበር  …

በአርባ አራቱ ታቦት መናህሪያ በጎንደር ከልጅነት እስከ እውቀት የማውቀው ታላቅ ህዝባዊ በአል ቢኖር የጥምቀት በአል ነው . . . የጎንደር አባቶችና እናቶች ባማረ የባህል ልብሶቻቸው ተውበው ደምቀው ጎንደርና ጥምቀትን ያደምቋታል። ጥምቀት ገና ከጥንት ከጠዋቱ  የውጭ ሃገር ጎብኝዎችን ቀልብ ከሚስቡት በአላት ቀዳሚ መሆኑንም አውቃለሁ ።  አባቶች ጥንግ ድርብ እና አልፎ አልፎም ቀደምቱን ያማራ በርኖስ የባህል ልብሳቸውን ለብሰው ጥምቀትን ደምቀው ሲያደምቁት ፣ የቀረው ነዋሪም “ለጥምቀት ያልሆነ ልብስ ይበጣጠስ” ሆነና  አቅሙ የፈቀደ አዲስ ልብስ አስገቶ ይለብሳል። ያጡ የነጡት ደግሞ ያላቸውን መላብስ አጣጥበውና በወግ በወጉ ጠቅመው በአደባባይ የሚታዩት በጥምቀት ነው፡፡ በጥምቀት የጎንደር ስመ ጥሩ የአርባ አራቱ ታቦት ፣ ሊቃውንት፤ ስመጥር የደብር አለቆችና ካህናት በሚያምረው ልብሰ ተክህኖ አምረውና ደምቀው ይታያሉ . . .  በነጭ የባህል ልብሳቸው ላይ ጣል ከሚያደርጉት ጥቁር ካባቸውንና በራሳቸው ጥምጣም  የሚታወቁት በጎንደር የቅኔ ፤ የመወድስና የአቋቋም ዝማሬ ሊቃውንት ባማረው አንደበታቸው የውዳሴ መዝሙር ጣዕመ ዜማ፣ ወርብና ሽብሸባውን በአደባባይ የሚያሰሙበት ልዩ አጋጣሚ ቢኖር ይህ የጥምቀት በአል ነው . . . ዘመን በዘመን ሲተካ ጥምቀት በጎንደር  እንዲህ እያደመቀ እዚህ ደርሰናል . . . !

ዛሬም ጎንደር በጥምቀት በቱሪስት መናህሪያ ሆና ዘመንን የኢትዮጵያ መገለጫ ሆና አይን እንደሳበች ትገኛለች ! ከዛሬ አራት ከፍለ ዘመን (400 አመት ) በፊት የተሰሩት የጎንደር ቤተ መንግስቶች አስገራሚ ጥበብ ዛሬ ድረስ ውበትና ግርማ ሞገስ ይታይባቸዋል፡፡  የዚያን ዘመን ሰማይ ጠቀስ ቤተ መንግስቶችን አስገንብተው የጎንደርን ከተማ በመቆርቆራቸው የሚታወቁት አጼ ፋሲል ሱስንዮስ ጥምቀት መዋኛ ገንዳንም ከቀሃ ወንዝ ዳረወቻ ገንብተዋል። አጼ ፋሲለደስ ሃገሬ በአሉን የሚያከብርበትን የመዋኛ ቅጽግ ግቢ ከልለው ያሰሩ ብልህ መሪ ነበሩ ! ይህም የያኔው ብልህ መሪ ለጥምቀት የሰጠውን ልዩ ክብር አመልካች ለመሆኑ ጥርጥር የለኝም ፡፡  አጼ ፋሲል በቀሃ ወንዝ ዳርቻ ያሰሩት የመዋኛ ገንዳ ዛሬ ድረስ ለጎንደር ጥምቀት መድመቅ ፈርጥ ሆኖ ዘመን ሲነጉድ የዚያ ዘመን የስልጣኔ አሻራችን ያስቃኘናል፡፡  ከመዋመኛው አንድ ጫፍ ታቦተ ጽላቱ በክብር የሚያርፍበት መቅደስ አሰርተዋል፡፡ በዚያ የጸሎት ቤት ስርአተ ቅዳሴ ፤ ማህሌት ሽብሸባው ጥምቀት በመጣ በሄደ ቁጥር ይከወንበታል፡፡ ግራማ የተላበሰውን ይህን መዋኛ  ሶስት ፎቅ ህንጻ በአስገራሚ ጥበብን ይታይበታል።

ጥምቀት በጥንታዊዋ መዲና በጎንደር ሲከበር የጥበብና የስልጣኔ አሻራ ሲከበር ለበአል አክባሪዎቹ ብዙ መልዕክትን ማጫሩ አይቀርም ! የአጼ ፋሲል የቀደመ ስልጣኔ ቅሪት ውብ ህንጻዎች የጥንቱን ማንነታችን እያወሱ ካወቅንበት ከዛሬ የኢሊ ጉዞዋችን እንድንነቃም እያደመቀ እያዋዛ ያዘክሩናል …

ጥምቀትን ታኮ የተመረቀው የመይሳው ካሳ ሃውልት ፣ የማይረሳኝ የመኪና አደጋ … ትዝታ

timqet tewodrosዛሬ ዛሬ የጥምቀት በአል በአብዛኛው በወጣቱ  ሙሉ ተነሳሽነት በልዩ ስሜትና ዝግጂት በልዩ ስሜት እንደሚከበር በስልክ ያጫወተችኝ  እድሜዋ ከ80 የዘለለው የእድሜ ባለጸጋ እመሆይ እናቴ ነበረች ። ዛሬን አያድርገውና ድሮ በልጅነት ካህን አባቴንና እናቴን ተከትየ በፋሲል ውቅር ከተማ በጎንደር በአሉ አከባበር ደምቄ አድጌበታለሁና  የጥምቀትና ጎንደር ትዝታ አብረውኝ ይኖራሉ …፡

ከሁለት አመት በፊት ጥምቀትን በጎንደር ለማክበር ባደግኩበት ቀየ ተገኝቸ ነበር ።  በከተራው በአል በጥምቀት ዋዜማም በጉጉት ይጠበቅ የነበረው  የአጼ ቴዎድሮስ ሃውልት ምረቃ ላይ ተገኝቸም ኢትዮጵያን በጎንደር አይቻታለሁ ፡፡ በተወለዱ ባደጉበት ምድር ለአንድ ክፍለ ዘመን ጥርኝ አፈር ለመታሰቢያቸው የተነፈጋቸው የኢትዮጵያ አንድነት ተምሳሌት የአጼ ቴዎድሮስ ሃውልት በጎንደር ከተማ እምብርት በፒያሳ መሃል አደባባይ ተሰርቶ የምረቃውን ስነ ስርአት ሲካሔድም ተመልክቻለሁ  ።  ካች አምና በተከበረው ጥምቀት በጎንደር ደመና አሳዛኝ ትዕይንት ሲስተናገድም እማኝ ነበርኩ !

የአባይ በርሃው የመኪና አደጋ

የጎንደር ጥምቀት ክብረ በአል ጋር የቴዎድሮስ ሃውልት ምረቃ ሊከበር በዝግጅት ላይ እያለ ከወደ አባይ በርሃ የተሰማው መርዶ የከፋ ነበር። መርዶው በመይሳው ካሳ ሃውልት ምረቃና በጥምቀቱ የደመቀ ዋዜማ ስሜታቸው በደስታ ላይ የነበርነውን በአል አክባሪ ሁሉ ቅስም የሰበረ ነበር። በአሉን ለማክበር አስበው ወደ ጎንደር ሲገሰግሱ በአባይ በርሃ በተከሰተው የመኪና አደጋ ህይዎታቸው ያጡበት ወገኖች ቁጥርም ከፍ ያለ ነበር ። በርሃው ወገኖቹን በልቶታልና ጎንደሬውን አንገቱን በሃዘን ደፍቶ ማቅ ያለበሰው ቀን ቢኖር ይህ ቀን ነበር። ደስታቸውን ለመግለጽ ሳግ እየተናነቃቸው ለቴዎድሮስና ለሚናፍቋት አንድነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያ ያላቸውን ፍቅር በመግለጽ ላይ የነበረው ኢትዮየጵያዊ ከትንሽ እስከ ትልቅ በርሃው በበላቸው ወገኖቹ በሃዘን ቅስሙ መሰበሩና ስሜቱ መጎዳቱን በእያንዳንዱን ፊት ይነበብ እንደነበር አይረሳኝም …

በአባይ በርሃ ገደል ገብቶ ሰው የጨረሰው አውቶቡስ እኔ ልጆቸና እህቴ በአንድ ሆነን በተሳፈርንበት አውቶቡስ እኩል  ከአዲስ አበባ ነበር የተነሳው። ከአዲስ አበባ እስከ አባይ በርሃ ድረስ ከበስተኋላችን ይጓዝ ነበር ። በአባይ በርሃ ደልደል ባለ መንገድ ዳር በአንድነት ለደቂቃዎች እረፍት አድርገንም ነበር ። እኛ ቀድመን አቀበቱን ወጠን ደጅን እንደደረስን የማይታመነውን አደጋ መርዶ ሰማን… ይከተለን የነበረው አውቶቡስ ከሃምሳ በላይ አብዛኛው እንደኛ ጥምቀትን በጎንደር ሊያከብር የተሳፈረው ወገን ገደል ገብቶ ሰው አንዳለቀ በቀትሩ የራዲዮ ዜና እወጃ ሰማን!  ያ ቀን. ለእኔ የሚረሳ እና የሚዘነጋ አይደለም ! በአባይ አፋፍ አንድ ጫፍ  እረፍት ባደረግንባት ደቂቃ ሰላምታ የተለዋወጥኳቸውን ወገኖች በሰአታት ልዩነት የማለቃቸውን አሰቃቂ ዜና የሰማሁባት እለት ሆዴን ያላወሰኝና ያስደነገጠኝ ስሜት ትዝታው አሁን ድረስ ያውከኛል …ነፍሳቸውን ይማር !

ኢትዮጵያ የምትከብርበት የጎንደር ጥምቀት …

ከአካባቢ የወረዳ የዞንና የገጠር ከተሞች የመጣው ኮበሌ ባለጀንፎ ሽመል ከዘራውን ወልውሎ ለሆታና ጭፈራው ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል፡፡ ከሁሉም ቀልብን የሚስቡት የከተማ ጎረምሶች በህብረት ተሰባስበው በዘመነኛና በባህላዊው ዘፈን ጥምቀቱን ሲያደምቁት ፣ ወጣት አርሶ አደሮች በበኩላችው የሚያምር  አረንጓዴና ሰማያዊ በቁልፍ የተንቆጠቆጠ ቂምጣና ጨሸሞዞቻቸው በተጨማሪ የሚያምር ገናባሌ አድርገው በአልባሳት ደምቀዋል፡፡ ኮበሌዎች ጠባብቡን ቁምጣ ፣ ሸሚዝና ገንባሌ ለብሰውና ከጎፈሬያቸው ላይ ሚዷቸውን ሻጥ በማድረግ በአሉን ለማድመቅ የበኩላቸው በማድረግ ላይ ናቸው ፡፡ አልፎ አልፎም ቢሆን ኮረዳ ሴቶች ጭምር በቅባት የጠገበ ጸጉራቸውን ቁንዳላ ተሰርተው አረንጓዴ ቀሚስ አሰፍተውና በነጩ ቁልፍ አሽቆጥቁጠው ከመቸውም ጊዜ በላይ ለጎንደር ጥምቀት ህብረ ባህላዊ ድምቀትን ሰጥተው አድማቂዎች ናቸው። ወጣቶች ፣ ሃገር ቤት ከመጣው ቢጤያቸው ጋር ሲላቸው ሰይ ሰይ ተብሎ የሚታወቀውን ባህላዊ የዱላ ጫወታ እየተጫወቱ ባአሉን ያደምቁታል። እንዲያው በአጠቃላይ ከህጻናት ጀምሮ ኮበሌው፣ ኮረዳው ፣ እና እድሜ ጠገብ አባቶችና እናቶች የጎንደር ጥምቀትን በአል ልዩ ውበት ናቸው  . . .

አንተ የት መጣህ አይባልም …ማን የማንን ይጫወት አይባልም!   ኦሮሞው ፤ከንባታው ፤ ጉራጌው፤ ሃረሪው ፤ትግሬው ፤ አማራው ፤ ሱማሌው ይዘፈናል ፣ የደለቃል ፣ ጃሎ ይባላል! ኢትዮጵያዊ በጎንደር የጥምቀት በአል አንድ ሆኖ ባንድ ክብረ በአሉን ይታደማል ! አገር ጎብኝው ፈርንጅና ጥቁሩ ከሃገረ አሜሪካ ፤ ከአውሮፓን ከሩቅ ምስራቅና ከአውስትራልያና ከተለያዩ አለማት የመጡት ሀገር ጎብኝዎች በካሜራቸው እያጠመዱ ጥምቀትን በጎንደር ሲያከብሩ የኢትዮጵያን በጎንደር እያዩ ነው!  የእረፍት ጊዜያችውን በዓለ ጥምቀትን ተጠግተው ጎንደርን ሲጎበኙ በጨዋታው ደምቀው ተውበው፣  የዚያን ዘመን የእነ አጼ ፋሲልን ቤተ መንግስቶች ፣ የቅድመ አያቶቻችን ድንቅና ውብ ባህልና ያለፈ መልካም ስራ እየተደነቁ የሚያልፉበት ትዕይንት በመሆኑ ኢትዮጵያን ለማየት ጎንደርን በጥምቀት ማየት ያሰኝዎታል!  በሀገሬው ሆታ ጭፈራ ተደምመው የደስታ የፌስታ ቀንወትን እያሳመሩ ኢትዮጵያን በጎንደር እያዩ ጥምቀትን ያከብራሉ ! . . . የካች አምናው ትዝታ ራሴን ቢያነሆልለው በከተራው በአል በትዝታ ተጉዠ በማለዳ ወጋዎጌ ይህችን ያህል ላስቃኛችሁ ወደድኩ . . .

መልካም የከተራና  የጥምቀት በአል!

ነቢዩ ሲራክ

የግርጌ ማስታዎሻ : ስለከተራና ጥምቀት ብዙን መረጃ ያገኘሁት ከሐመር መጽሔት ሲሆን ለወዳጆች እንዲስማማ አድርጌ ማቅረቤን ሳልጠቁም አላልፍም።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Social

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule