• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሶስት ነገር ያጣችው ሳልዋ – አሜሪካ

January 19, 2014 03:46 am by Editor Leave a Comment

አሜሪካ የመጣችው ከ27 አመት በፊት ነበር። ሁለት ልጆች የወለደችለት ባለቤትዋ በሞት ሲለያት ታዳጊ ህጻናት ልጆቿን ይዛ በሱዳን በኩል አድርጋ አሜሪካ መጣች። ሳልዋ ትባላለች፤ የጠይም ቆንጆ ናት። በአሜሪካ ዲሲ ከተማ ብዙዎች የሚያውቋት በታታሪ ሰራተኛነቷ፣ በሳቅ ጨዋታዋ፣ እንዲሁም በመልካም ባህርይዋ ነው። ጥሩ ስራና ገቢ የነበራት ሳልዋ በፍቅር ከቀረበችው ሃበሻ ጋር በአብሮነት መኖር ይጀምራሉ። ለረጅም አመት ብዙዎችን የሚያስቀና ፍቅር እንደነበራቸው የሚያውቋቸው ይናገራሉ።

በድንገት የሳልዋን ልብ የሚሰብር ሁኔታ ይፈጠራል፤ የምትወደውና ልጅ ያልወለደችለት ፍቅረኛዋ በድንገት በሞት ይለያታል። ሃዘኑን መቋቋም የተሳናት ሳልዋ ይባስ ብሎ ሁለቱ ልጆቿ ጥለዋት ወደ ሌላ ከተማ ሄዱ። ለ17አመታት ገደማ ጠይቀዋት አያውቁም፤ እሷም ልጆቿ የት እንዳሉ አታውቅም። ሶስት ነገር ያጣችው ሳልዋ ጤናዋ ተቃወሰ። አእምሮዋ ተነካ። ህይወት ፊቷን አዞረችባት። ለጎዳና ኑሮ ተጋለጠች። ሃበሻ በሚበዛበት መንገድ ከአንድ ሬስቶራንት salwaጥግ ኩርምት ብላ ታሳልፋለች። ያገኘችውን ሃበሻ « ነፍሴ..ወገኔ..ኑርልኝ!» እያለች በጣፋጭ አንደበቷ ሰላምታና መልካም ምኞቷን ትገልፃለች። ለመጀመሪያ ግዜ ካገኘኋት ከአምስት ወር በኋላ ዳግም ሳገኛት አልረሳችኝም ነበር።

የማስታወስ ችሎታዋን አደነቅኩላት። ኑሯዋ ግን እጅግ አሳዛኝ ነው። ስትናገር ቀልጠፍ የምትለው ሳልዋ እንዲህ አለች፥ « በእኔ የደረሰው በማንም አይድረስ። ወላድ ይፍረደኝ!! ሁለት ጊዜ ትዳር ብመሰርትም ፈጣሪ ነጠቀኝና ብቸኛ አደረገኝ። እንደገና የወላድ መካን ሆንኩ። እብድ እናት ስለሆንኩ አፍረውብኝ ይሆናላ!? ምን አደርግላቸዋለሁ!?..እስቲ ንገረኝ?…እ..እ…ንገረኝ ነፍሴ!?..» ቅዝዝ ብላ አተኩራ እየተመለከተችኝ። … በዲሲ ለ35 አመት የኖረ አንድ ሃበሻ ስለሳልዋ ሲናገር፥« እንዴት አይነት መልካም ሰው መሰለችህ!! ስራ በነበራት ጊዜ ሃበሻ እንዲህ ችግር ደረሰበት ሲባል ገንዘብ ቀድማ የምትሰጥ ደግ ሴት ናት።

እኔን ጨምሮ ለብዙ ሰዎች ገንዘብ ታበድረን ነበር። አንዳንዱ ሳይመልስላት ሲቀር ምንም አትልም። ሳልዋ እንዲህ መሆኗ..» ሳግ እየተናነቀው ሳይጨርስ ተወው። ሳልዋ አዘውትራ ከማትጠፋበት ጎዳና በ30ሜትር ርቀት የኮሚኒቲ ቢሮ አለ። ግን እሷን የሚያይ “አይን” የላቸውም።…

አርአያ ተስፋማሪያም

ምንጭ: ECADForum

Filed Under: Social Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule