የኢትዮጵያን ለም መሬት ከተቀራመቱት ኢንቨስተሮች መካካል አንዱ የሆነው የህንዱ ካሩቱሪ ከኢትዮጵያ ለቅቆ የሚወጣበት ጊዜ መቃረቡን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል አስታወቁ። አበዳሪዎችና ባለ አክሲዮኖች ፊታቸውን እንዳዞሩበትም ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ባዶ ዋይታ የሚያሰማው ኢህአዴግ የያዘው አዲስ አቋም ድርጅቱንና ከድርጅቱ ጋር የቀረበ ግንኙነት አላቸው የሚባሉትን ሃሳብ ላይ ጥሏል። በምናምንቴ ዋጋ የኢትዮጵያ ድንግል መሬት ባለቤት የሆነው ካሩቱሪ ለጊዜው በገንዘብ ሊተመን የማይችል የተፈጥሮ ደን ሲያወድም የከለከለው አልነበረም። ለጊዜው ማልማት ከሚችለው አቅም በላይ መሬት ወስዶ የተፈጥሮ ደን የጨፈጨፈው ካሩቱሪ ተቃውሞ የገጠመው ገና ከጅምሩ ነበር። በቦታው ሆነው መረጃ ሲያቀብሉ የነበሩ ወገኖችና ለድርጅቱ ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት በጋምቤላ መሬት … [Read more...] about ካሩቱሪ በኪሳራ ለ“በቃኝ” እያቅማማ ነው!
Archives for August 2013
የ“አምላካችሁ ባሮች” የሆናችሁ “ሰላማዊ ሰልፈኞች” ቅድሚ የምትሰጡት ለማን ነው?
እርቅን፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ መቻቻልን ለማውረድ የሃይማኖት አባቶችና ሽማግሌዎች ቁልፍ ሚና አላቸው። በር ዘግተው ይጸልያሉ። ያስታርቃሉ። ይገስጻሉ። ያስጠነቅቃሉ። እንዲህ አይነት ለሌሎች ብርሃን ለመሆን የሚቃጠሉ የሃይማኖት አባቶች ያሏቸው ምንኛ የታደሉ ናቸው? በተቃራኒው የአምላክ ባሪያዎች፣ የየእምነታቸው ባሪያዎች፣ የምዕመናን መንፈስ መጋቢዎችና ጠባቂዎች፣ ወዘተ አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚወጡ በይፋ ተነገረን። "በተገንጣይ ነጻ አውጪ" ስም እየተጠራጠረና እየተጸየፈ አገራችንን ከሚመራ ከሃዲ ድርጅት ጎን ለመቆም የሃይማኖት መሪዎች መነሳታቸው ለፈረደባት ኢትዮጵያና ለህዝቧ ከዚህ በላይ ሃፍረት የለም!! ችግሩ በውስጥም በውጭም ያለውን ይመለከታል። ይህንን ስንል ምክንያታችንን ህዝብ ይረዳዋል ብለን እናምናለን። በሰማያዊውም ሆነ በምድራዊው ዓለም “መተፋት” አለ። የሃይማኖት አባቶችና … [Read more...] about የ“አምላካችሁ ባሮች” የሆናችሁ “ሰላማዊ ሰልፈኞች” ቅድሚ የምትሰጡት ለማን ነው?
ህዝበ-ሙስሊሙን ያለአግባብ በስጋት መፈረጅ፤ ማዋከብና መግደል በአፋጣኝ ይቁም!!
የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት አንቀጽ 11 ቁጥር 3 ”መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ ሀይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ” ይላል፡፡በሀገራችን ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ በወታደራዊው ደርግ እንዲሁም አሁን ስልጣን ላይ ባለው ወያኔን ጨምሮ ሁሉም ሀይማኖቶች ከመንግስት ጣልቃገብነት ነፃ ሆነው አያውቁም። ፍትህ፣ ነጻነት፣ እኩልነት እና አንድነት ለብዙ ሀይማኖቶች መሰረታዊ እሴቶች ናቸው፡፡ እነዚህ እሴቶች ላለፉት 22 ዓመታት በዘረኛው የወያኔ መንግስት እየተሸረሸሩ እና እየተመናመኑ ዛሬ ከነአካቴውም ለመጥፋት ተቃርበዋል፡፡ ስለመሰረታዊ የሰው ልጅ መብት እና ነጻነት እንዳይወራ የወያኔ የጥይት አፈሙዞች በእያንዳንዱ ሰው እና የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ተደቅኗል፡፡የእምነት ቦታዎችንም ሳይቀር በመድፈር ህዝበ-ምዕመኑ የኔ የራሴ የሚለው የአምልኮ ቦታ እና የአምልኮ ስርዓት … [Read more...] about ህዝበ-ሙስሊሙን ያለአግባብ በስጋት መፈረጅ፤ ማዋከብና መግደል በአፋጣኝ ይቁም!!
ተመስገን እላለሁም ፣ አልልምም !
በሰላም አውሎ ላሳደረኝ ፈጣሪ ስተኛም ሆነ ስነሳ " ተመስገን ፈጣሪየ! " የምትለዋን ምስጋና ከማቅረብ ተቆጥቤ አላውቅም ። ቸርነቱ የማያልቅበት ፈጣሪ አምላኬ አጉድሎብኝ አያውቅም! ጤና ስጠኝ ስለው ጤናውን ፣ ጥበብ መላ ላጣሁለት መላ ስጠኝ ስለው መላ ብልሃቱን ፣ ጉልበቴን አበርታው ስለው ብርታቱን ፣ ቅን ልቦና ስጠኝ ስለው ርህራሔውን እና የፈለግኩትን ሁሉ አያጓድልብኝም! እናም ዘወትር ተመስገን እለዋለሁ ! ገና ከአልጋየ ሳልነሳ ከአፊ ውስጥ አንድ ቃል ይመላለሳል ፣ ቃሉ ወደ አረፍተ ነገር ሺር በሎ ተቀየረ ! በጨለማ የማያይ አይኔን ወደ ድቅድቁ ጨለማ የመኝታ ክፍል ጣራ አፍጥጦ በምናብ አነበንበዋለሁ ... በጀርባየ ተኝቸ ወደ ጣራ ካፈጠጥኩበት ወደ ጎን ግልበጥ እልና እጆቸን ጭንቅላቴ ስር ወሸቅ አድርጌ ከአፊ የማወጣውን አረፍተ ነገር ደጋገምኩ " ተመስገን ተመስገን ተመስገን … [Read more...] about ተመስገን እላለሁም ፣ አልልምም !
ሰማያዊ ፓርቲ በሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ላይ ተቃውሞ አቀረበ
በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. የመጀመሪያውን የተቃውሞ ሠልፍ ያካሄደው ሰማያዊ ፓርቲ፣ በመጪው እሑድ በሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በተዘጋጀው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ ተቃውሞ አቀረበ፡፡ ሁለተኛውንና በርካታ ሰዎች እንዳሚሳተፉበት ሲገልጽ የከረመውን ሰላማዊ ሠልፍ የሚያካሄደው ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. እንደነበር ፓርቲው አስታውቆ፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በተደራቢነት በዕለቱ ሠልፍ እንደሚያደርግ ያስተላለፈው ጥሪ ትክክል አይደለም ብሏል፡፡ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም. ያስተላለፈውን፣ ‹‹አክራሪነትና ጽንፈኝነትን እናውግዝ›› የሚል የሠልፍ ጥሪ የተቃወመው ሰማያዊ ፓርቲ፣ ከአንድ ወር በላይ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ሲያስተዋውቅና ጥሪ ሲያደርግ መክረሙን ገልጿል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርግ ቀድሞ ማሳወቅ ለሚገባው … [Read more...] about ሰማያዊ ፓርቲ በሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ላይ ተቃውሞ አቀረበ
The Secret (ሚስጢሩ…)
ስለተከሰተው ሚስጢርና የሚስጢሩን ቀላል መደረግ አሁን የሚጠይቁኝ አይመስለኝም።ይልቁንም አጠቃቀሙ እንዴት ነው? ይሉኝ ይሆናል።ለዚህ በክፍል ሶስት ጽሁፌ መልስ ይዣለሁ።ከዛ በፊት ግን ታላቁ መጽሐፍ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይላል?የሚስጢሩ ተጠቃሚዎችስ ምን ይነግሩናል?ይሄን አንብበው ወደ ሚስጢሩ አጠቃቀም ይሻገሩ። "አምናችሁም፤ በፀሎት፤ የምትለምኑትን፤ ሁሉ ትቀበላላችሁ።" ማቴዎስ፤ ፳፩-፳፪ "የፀለያችሁትን፤ የለመናችሁትንም፤ እንዳገኛችሁት እመኑ። ይሆንላችሁማል።” ማርቆስ፤ ፲፩-፳፬ "ነገሮች ሁሉ፤ ይለወጡልህ ዘንድ ዓለም እንደገና ራሷን ታዘጋጃለች።” ዶ/ር ጆ ቫይታል "የመጀመሪያው መነሻህ ታማኒነት ይሁን።የደረጃውን መጨረሻ አጠቃለህ ማየት አያስፈልግህም።ዝም ብለህ ወደ መጀመሪያው ደረጃ ውጣ።" ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የሚስጢሩ አጠቃቀም የምትፈልገውን ለመፍጠር … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)
Tigray Republic flaunting her wealth at glittering TDA functions across the globe.
Created by the dead enclave hero Meles Zenawi and officially known as the regional state of Tigray, state within a state and the birthplace of the current ruling party in Ethiopia, Tigre People Liberation Front/TPLF; Tigray republic is holding its glittering annual Tigray Development Association/TDA functions around the world with tyrannized and indigent Ethiopian taxpayers footing the huge bill. After a week long music and dance spectacle in various US cities, where scrumptious meals and … [Read more...] about Tigray Republic flaunting her wealth at glittering TDA functions across the globe.
ትዞራለች … ትዞራለች … ሲደክማት ታርፈና አሁንም ትዞራለች!
አንድ ወዳጄ መሃመድያ ተብሎ በሚጠራው የጅዳ ከፍል ከኢትዮጵያ አለም አቀፍ ትምህር ቤት አካባቢ ይህችን በፎቶው ላይ የምታዩዋትን እህት አግኝቶ ሊያነጋግራት ቢሞክርም ፈቃደኛ አልነበረችም። ከየት ነው የመጣሽው? ስትባል"ከመቀለ" ከማለት ባለፈ ስሟንና የሆነችውን አትናገርም። ብዙ ሊያግባባት ሞክሮ ያልተሳካለት ይህ ወዳጀ ይህች እህት ያደፈና የተቀደደ ጥቁር "አባያ" ለብሳና መናኛ ነጠላ ጫማ የተጫማችው እህት የአዕምሮ ሁከት እንዳለባት የተረዳው ብዙ ለማነጋገር ሞክሮ በሰጠችው አንዳንድ ምላሽ እንደሆነ ገልጾልኛል! ልጁን ትምህርት ቤት ሊያስመዘግብ በሔደበት አጋጣሚ በጠራራው ሜዳ ስትንከራተት በማየቱና ምንም መርዳት ባለመቻሉ ያዘነው ወዳጄን መረጃ ይዤ የጅዳን ቆንስል ሃላፊዎች ስልክ በመደወል ይህችን እህት በመጠለያው አምጥተው ሌላው ቢቀር ካሉት የአዕምሮ በሽተኞች ጋር ቀላቅለው ከመኪና እና … [Read more...] about ትዞራለች … ትዞራለች … ሲደክማት ታርፈና አሁንም ትዞራለች!
የአንድነቶች ሰላማዊነት ጽናት በባሌ ሮቤ እና በፍቼ ኦሮሚያ!
“አንድነት ፓርቲ ሳይገድል እየሞተ ህገ-መንግስቱን የማስከበር ሰላማዊ ትግሉን አጠንክሮ ዛሬም ወደፊትም ይቀጥላል፡፡” የሚለውን መርሃቸውን አንድነቶች ካስተዋወቁን ከርመዋል። ባለፈው ሳምንት በባሌ ሮቤ እና በፍቼ ኦሮምያ የተተከሉት መረን የለቀቁ አምባገነን አስተዳደሮች እና ደህንነቶች የፈጸሙባቸውን ወደር የለሽ የአንደበት፣ የሳይኮሎጂ እና የአካል ጥቃት በፈገግታ በመቀበል እየሞቱ ሳይገድሉ በሰላማዊ ትግል ህገ-መንግስቱን ለማስከበር ያላቸውን ጽናት ደግመው አሳይተውናል አንድነቶች። አንድነቶች የሚሰብኩትን የሚፈጽሙ መሆናቸውን ኢትዮጵያ እንደገና ባለፈው ሳምንት ተመልክታለች። የባሌ ሮቤ እና የፍቼ አምባገነን አስተዳዳሪዎች እና ደህንነቶች አረመኔነት አሳፋሪ ነበር። በፍጹም የስልጣኔ አየር የነፈሰባቸው አይመስሉም። ዘመናዊ አስተሳሰብ ለአንድ ቀንም የጎበኛቸው አይመስሉም። ይባስ ብሎ የባሌ ሮቢ … [Read more...] about የአንድነቶች ሰላማዊነት ጽናት በባሌ ሮቤ እና በፍቼ ኦሮሚያ!
The Totolamo-Kofele blood bath victims named, death toll still climbing.
“Wolahi, Wolahi…” swears 85 year old Totolamo village barley farmer and cattle herder Hajji Abdinur Shifa when a reporter asked him if he know any terrorist hiding in his village. His face looks like a paint of sorrow and grief. His wife affectionately called by the villagers, Adiyo, was too fragile to talk about the August 3 2013 blood bath that turned their agriculture and livestock rich village into an inferno. “My son took three bullets and died a day later at Sashemene general hospital. … [Read more...] about The Totolamo-Kofele blood bath victims named, death toll still climbing.