• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

Opinions
የኔ ሃሳብ

በባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ በትግሬ-ወያኔ ግፍ የተጨፈጨፉትን እንድናውቃቸውና እንድንዘክራቸው!

August 19, 2016 11:20 pm by Editor Leave a Comment

በባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ በትግሬ-ወያኔ ግፍ የተጨፈጨፉትን እንድናውቃቸውና እንድንዘክራቸው!

ዘረኛው የትግሬ ወያኔ የወልቃይት ጠገዴን የማንነት ጥያቄ ደግፈው በወጡ የባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ በግፍ የገደላቸው ወገኖቻችን ዝርዝር በከፊል። «የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ፣ የእኛም የዐማራነት ጥያቄ ነው፣» ብለው እሑድ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓም ላይ በባሕርዳር ከተማ፣ በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ለማሰማት በወጡ ዐማሮች ላይ፣ የትግሬ ወያኔ ዘረኛ ቡድን በርካታ፣ ሩቅ አሳቢ፣ ለሥራ የጓጉ፣ ላገርና ለወገን ታላቅ ተስፋ ሰንቅው የነበሩ የአያሌ ወጣቶችን ሕይዎት በግፍ ነጥቋል። በባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ወያኔ ከገደላቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች መካከል ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን የከፊሎቹን አገኝቷል። ከሰንጠረዡ ለመረዳት እንደሚቻለው፣ በግፍ ከተገደሉትና ዝርዝራቸውን ማወቅ ከተቻለው አርባ ዘጠኝ(49) ሰዎች ውስጥ፣ ዕድሜአቸው ሰላሳና ከዚያም … [Read more...] about በባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ በትግሬ-ወያኔ ግፍ የተጨፈጨፉትን እንድናውቃቸውና እንድንዘክራቸው!

Filed Under: Opinions Tagged With: Bahir Dar Massacre, Right Column - Primary Sidebar

በስደት ላይ ያለው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ

August 19, 2016 09:15 am by Editor 1 Comment

በስደት ላይ ያለው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ

በስደት ላይ ያለው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አንድነት ማህበር የአቋም መግለጫ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን። በስደት ላይ ያለው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ዙሪያ የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት መነሻ በማድረግ ያወጣውን መግለጫ በመደገፍ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አንድነት ማህበር የተሰባሰብን ተወካዮች ባካሄድነው አስቸኳይ ጉባኤ በሀገራችን ኢትዮጵያ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በሰፊው ተመልክተን የጋራ የአቋም መግለጫ አውጥተናል። ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ምዕ. ፪ ከቁ. ፲፰ ጀምሮ “ልጆቼ ሆይ ይህቺ የመጨረሻዋ ሰዓት ናት እኛም የመጨረሻዋ ሰዓት እንደሆነች አውቀን በአንድነት እንቁም” ብሎ ባስተማረን መንፈሳዊ መሪ ቃል መሠረት … [Read more...] about በስደት ላይ ያለው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

ለመሆኑ አማራ ማነው?

August 19, 2016 02:33 am by Editor Leave a Comment

ለመሆኑ አማራ ማነው?

ዛሬ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግሥት ዐማራ በተባለው ኅብረተ-ሰብ ላይ ብዙ ግፍና ዐመፅ እንደፈጸመና እንዳስፈጸመ በገፍ ይነገራል። በኅብረተሰቡ ላይ ተፈጸሙ ከተባሉት ድርጊቶች አብዛኞቹ በሥዕል የተቀረጹ፣ ለሰው መብት በቆሙ ባስተማማኝ ብሔራዊና ዓለም-ዐቀፍ ድርጅቶች ከነማስረጃቸው የተጠናቀሩ፣ እሙን በሆኑ ያይን ምስክሮች የተደገፉ ስለሆኑ ማስተባበሉ ከመደናቈርና የአተካራ ግብግብ ከመግጠም ውጭ ሌላ ፋይዳ ያለው አይመስለኝም። የግፎቹ ኢሰብኣዊነትና የፈጻሚዎቻቸውም አውሬነት ለሚሰማ ሁሉ ከመዘግነን አልፎ፣ ሰው ሁኖ መፈጠሩን ራሱን የሚያስጠላ ከመሆኑ የተነሣ፣ ልቦና ያለው ተመልካችም ሆነ ሰሚ፣ መንግሥት ነን ባዮቹ የወያኔ ገዢዎች በጀርመንና በኢጣሊያን ምድር ከታዩት ከናዚና ከፋሽስት መንግሥታት መሪዎች በምን ይለያሉ ብሎ ለመጠየቅ ይገደዳል። በበኩሌ ጥላቻው ከየት መጣ ብዬ አውጥቼ … [Read more...] about ለመሆኑ አማራ ማነው?

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

የአማራውን ሕዝብ ሁለገብ የሕልውና ትግል ለማገዝ መደራጀት ያስፈልጋል!

August 19, 2016 02:02 am by Editor Leave a Comment

የአማራውን ሕዝብ ሁለገብ የሕልውና ትግል ለማገዝ መደራጀት ያስፈልጋል!

ከኃይለገብርኤል አያሌው የቀድሞው የመዐሕድ አመራር አባል ለአመታት በሕዝባችን ላይ ተከማችቶ የቆየው የጭቆና አገዛዝ የፈጠረው ምሬትና ቁጣ በመላው ሃገሪቱ መፈንዳት ጀምሮል። በተለይም በኦሮምያ ባለፉት ተከታታይ ወራት የቀጠለው ሰላማዊ ተቃውሞ የአያሌ ወገኖቻችንን ህይወት እየቀጠፈ ቀጥሏል። ይህም ትግል የኦሮሞ ህዝብ ትግል ተብሎ በሃገር ወስጥና በውጭ ሚድያዎች እውቅና አግኝቷል። በተለያዩ ልዩነቶች ተብታትኖ የኖረውን የኦሮሞ ፖለቲካ ሃይሎችና ሊህቃንን አቀናጅቶ ሃገር ውስጥ ያለውን ትግል ማዕክል ያደረገ እንቅስቃሴ ሲደረግ ይታያል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የአማራውን ሕዝብ ሁለገብ የሕልውና ትግል ለማገዝ መደራጀት ያስፈልጋል!

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

ወልቃይትን በኢትዮጵያዊነት መነፅር

August 19, 2016 12:14 am by Editor 4 Comments

ወልቃይትን በኢትዮጵያዊነት መነፅር

ምሁርን መተቸት ይቻላል? ይቻላል እንደምትሉ በማመን መቀጠሌ ነው። አዎ ደሞም የሚቻል ይመስለኛል። በኛ ሀገር ነውር ሆኖ የሚያስቀጣው መንግስትን መተቸት እንጂ በሌላው ማንኛውም ሰው ሃሳብ ላይ ሃሳብ ቢሰጡ ክፋት የለውም። እርግጥ ከፖለቲካ ውጭም ቢሆን መተቻቸት የለመድነው ባህል ስላልሆነ ሲተች የሚወድ ብዙ ሰው የለም። ለነገሩማ የብልሹ ፖለቲካ ባህላችን ምንጭ ይኼው አሳዛኝ ማህበራዊ አስተሳሰባችን አይደል? ብቻ ፕሮፌሰር በክርክር የሚያምኑ በሳል ምሁር እንደሆኑ ስለማምን ያለስጋት በሃሳባቸው ላይ ሃሳብ ልሰነዝር ደፈርኩ። ፕሮፌሰር፥ወልቃይት የማነው? የማይረባ ጥያቄ፥ በሚል ርእስ በብሎጋቸው ያወጡትን በጎልጉል ድረገፅ ላይ ካነበብኩ በኋላ የሚደገፍም የሚነቀፍም ነጥብ አገኘሁበት። በአንድ በኩል ጥያቄው በዘር ሳይሆን ባገር መነፅር ሊታይ ይገባል። ወልቃይት የትግራይም ያማራም ሳይሆን … [Read more...] about ወልቃይትን በኢትዮጵያዊነት መነፅር

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን

August 18, 2016 11:34 pm by Editor Leave a Comment

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን

ኦገስት 26  የሰልፉ አዘጋጆች:- ዲኚሀር ኢንተርቴይመንት በጀመርን የኢትዮጵያ፡ የሙዚቃና  የባህል ማዕከል  እና በጀርመን የኢትዮጵያውያን የስደተኞች ምክር ቤት እና ለበለጠ መረጃ +49 15785114566 +49 61032904352 +49 15218504056 ይደውሉ:: ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር … [Read more...] about ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

ጉ፣ የአቶ ዠ ልጅ ወይም “ጉማሬው” ዋናተኛ

August 18, 2016 12:01 pm by Editor Leave a Comment

ጉ፣ የአቶ ዠ ልጅ ወይም “ጉማሬው” ዋናተኛ

አቶ ዠ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ከተጫነባቸው በኋላ በUN ኢትዮጵያን ወክሎ የመቀመጥ ስልጣናቸው ቀረና ወደ ሌላ ሥልጣን ተሻገሩ። እድገት ወይም ውርደት (promotion ወይም demotion) ሳንል፣ ወደ ሌላ ሥልጣን ተሻገሩ እንላለን። አቶ ዠ የሃገሪቱ የዋና ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ሆነው ተሾሙ። እንግዲህ “ፕሬዚደንት” የሚለው ቃል እስካለ ድረስ፣ ሹመቱ፣ ማዕረጉ ትልቅ ነው ተብሎ እንዲታሰብ የአቶ ዠ መልካም ፈቃድ ነው እንላለን። የዋና ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ሆነው የተሾሙበት ጊዜ ደግሞ እንዳጋጣሚ ሆኑ የኦሎምፒክ ውድድር የተቃረበበት ጊዜ ነበር። ዠ አዲሱ ቢሮአቸው ሆነው አንድ ሃሳብ ብልጭ አለላቸው። ሃገራቸውን በኦሎምፒክ መወከል። የሃገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ በኦሎምፒክ መክፈቻ ላይ ተገኝቶ ማውለብለብ...። እንዴት ያለ ድንቅ ሃሳብ ሲሉ አሰቡ አቶ ዠ። እንግዲህ መሰደብ፣ መዋረድ፣ መሰደድ፣ … [Read more...] about ጉ፣ የአቶ ዠ ልጅ ወይም “ጉማሬው” ዋናተኛ

Filed Under: Literature, Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

የህዝባችንን የትግል ፈር እንከተል!!

August 18, 2016 12:02 am by Editor Leave a Comment

የህዝባችንን የትግል ፈር እንከተል!!

ለወራት በኦሮሞ ወጣቶች ሲካሄድ የቆየው ለዴሞክራሲ የሚደረገው ህዝባዊ ትግል ሳያቋርጥና እየሰፋም እየሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እየደጋገሙ ሲታገሉለት የቆየው የህዝቦች ወንድማማችነትና የትግል አንድነት ጥያቄም ባለፉት ሳምንታት በአማራውና በኦሮሞ ክልሎች በሚካሄዱት ሰላማዊና ህዝባዊ ትግሎች አማካኝነት ስር እየሰደደ መሆኑን እየታዘብን ነው፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ በትግሉ ማየልና መስፋት ብርክ የያዛቸው የወያኔ/ ኢህአዴግ መሪዎች ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ለሚያቀርባቸው ጥያቄዎች ለመስጠት የሚሞክሩት አጸፋ በለየለት ጸረ ህዝብ አመጽ መሰማራት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ መልክ ባለፉት ወራት በኦሮሞ ታጋዮች ላይ ያወረዱትና በመቶ የሚቆጠሩ ንጹህ ዜጎችን መግደልና በሽህ የሚቆጠሩ ሌሎችን ለእስር መዳረግ ሳይበቃቸው አሁን ደግሞ በኦሮሞም በአማራም ታጋዮች ላይ ይህንኑ … [Read more...] about የህዝባችንን የትግል ፈር እንከተል!!

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

የትግሬዎች መንግሥት አወዳደቁና ክፋቱ!

August 18, 2016 12:00 am by Editor Leave a Comment

የትግሬዎች መንግሥት አወዳደቁና ክፋቱ!

ባሁን ሰዓት፤ በገዥነት ሕልሙ እየተንሳፈፈ ካለው የትግሬዎች ቡድን በስተቀር፤ ኢትዮጵያን አደጋ ላይ የጣላት ይሄው ቡድን፤ የውድቀት አፋፉ ላይ መሆኑ ለሁላችን ግልጽ ነው። አሁን ካለንበት ሰዓት እስከመጨረሻው ውድቀቱ ያለው ጊዜ ግን፤ በጣም የከፋና የተመሰቃቀለ ነው። ይህ የሚሆነው፤ ከፊል በዚህ ወራሪ ቡድን ተግባር ሲሆን፤ ከፊሉ ደግሞ በኛው በታጋዩ ክፍል ያለነው ለዚህ ውድቀት በማድረግና ባለማድረግ ላይባለው ሂደታችን ነው። በተጨማሪ ደግሞ፤ የሃያ አምስት ዓመት የዚህ ቡድን ፀረ-ኢትዮጵያ አገዛዝ፤ ሀገራችንን ለከፋ ወደፊት አዘጋጅቷታል። ሀቁን ተቀብለን ከአሁኑ መደረግ ያለበትን ካላደረግን፤ በኋላ ይሄን ብናደርግ ኖሮ ብለን የመቆጫ ሰዓት አናገኝም፤ ያኔ ሁኔታውን አንገዛውምና! ይህ ወራሪ ቡድን፤ የመጨረሻ እስትንፋሱን የሚያወጣው በቃሬዛ ነው።ሕዝቡ አቸናፊ ሆኖ እንደሚወጣ ምንም ዓይነት … [Read more...] about የትግሬዎች መንግሥት አወዳደቁና ክፋቱ!

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

የትግሬ-ወያኔ የዐማራ እና የኦሮሞ ነገዶችን ሕዝብ ጨርሶ ለማጥፋት ያቀደው ሚስጢራዊ አዲስ ሤራ

August 17, 2016 01:11 am by Editor 2 Comments

የትግሬ-ወያኔ የዐማራ እና የኦሮሞ ነገዶችን ሕዝብ ጨርሶ ለማጥፋት ያቀደው ሚስጢራዊ አዲስ ሤራ

ላለፉት 25 ዓመታት የትግሬ-ወያኔ በሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ከመጠን በላይ በመሆኑ፣ ሕዝቡን ለእምቢተኝነት አነሳስቷል። ይህ ግፍና በደል መጠን የለሽ በመሆኑ፣ በአገሪቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች፣ በተለይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎ፣ በሐረርጌ፣ በአርሲና በወለጋ ክፍለ-ሀገሮች የሚኖረው ሕዝብ፣ የትግሬ-ወያኔ «ለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ዕኩልነት» ሲል «አመጣሁት» ያለውን «ሕገ-መንግሥት» የማይቀበለው መሆኑንና፣ የዚሁ  «ሕገ-መንግሥት» ተብየ መገለጫ የሆነውን ሠንደቅ ከተሰቀለበት በማውረድ፣ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፣ የነፃነት ቀንዲል የሆነችው ሠንደቅ ከፍ-ብላ እንድትውለበልብ እያደረገ መሆኑ በግልጽ ተስተውሏል። ይህም የትግሬ-ወያኔ አመጣሁት ያለው ዕኩልነትና የነገዶች አንድነት ውሸት መሆኑን፣ ባንፃሩ ግን የትግሬ-ወያኔ የውስጥ ቅኝ ገዥ ኃይል … [Read more...] about የትግሬ-ወያኔ የዐማራ እና የኦሮሞ ነገዶችን ሕዝብ ጨርሶ ለማጥፋት ያቀደው ሚስጢራዊ አዲስ ሤራ

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

  • « Previous Page
  • Page 1
  • …
  • Page 59
  • Page 60
  • Page 61
  • Page 62
  • Page 63
  • …
  • Page 166
  • Next Page »

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule