ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በግሌ አላውቀውም፤ ነገር ግን እስከሚበቃኝ ድረስ አውቀዋለሁ። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እኔን አያውቀኝም፤ ነገርግን እኔና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ጠበቆቹ እንዳለን ያውቃል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጎንደር ውስጥ አንገረብ እስርቤት ባሁኗሰዓት - ምሽት፣ ረቡዕ ሐምሌ ፳፯ ቀን ፳፻፰ ዓመተ ምህረት - ለጊዜው አለ። እዚያ እንዲቆይ ያደረገው ወገኑ ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው፤ በእስርቤት ያለ ግለሰብ፤ በትክክል ይሁን በድፍረት በመታሰሩ ብቻ፤ ጠበቃ ያስፈልገዋል። እናም ጠበቃው ነኝ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ለኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጥብቅና!
Opinions
የኔ ሃሳብ
የነፍጠኞች ፖሊቲካ
ነፍጠኛነት ባህላችን ነው፤ ፖሊቲከኛነት አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤ ፖሊቲከኛነትና ነፍጠኛነት ተቃራኒ ተግባሮችን ያመለክታሉ፤ ተቃራኒ ተግባሮች አብዛኛውን ጊዜ ተቃራኒ ዘዴዎች ያስፈልጋቸዋል፤ ለምሳሌ መፍጨትና መቡካት ተቃራኒ ተግባሮች ናቸው፤ መፍጨት ሲበታትን፣ ማቡካት ሰብስቦ ያያይዛል፤ የሚፈጭ ሰው ማቡካት ይችላል፤ እንዲሁም ማቡካት የሚችል ሰው መፍጨት ይችላል፤ ፈጪ አቡኪ መሆን የሚችለውን ይህል ወይም አቡኪ ፈጪ መሆን የሚችለውን ያህል ነፍጠኛ ፖሊቲከኛ ወይም ፖሊቲከኛ ነፍጠኛ መሆን ይችላል ወይ? መልሱ ግልጽ ነው፤ አይችልም፤ የነፍጠኛ ትግል በጠመንጃ ነው፤ የፖሊቲከኛው ትግል በቃላት፣ በንግግር ነው፤ በሌላ አነጋገር የነፍጠኛ በዱላ፣ የፖሊቲከኛ ትግሉ በመላ ነው፡፡ የፖሊቲካ ሥልጣንን ነክሶ ይዞ ሕዝብን በሕዝብ በዱላ እያደባደቡ በማሸነፍም ሆነ በመሸነፍ የሥልጣንን ክብር ማግኘት … [Read more...] about የነፍጠኞች ፖሊቲካ
ታሪካዊው የጎንደር ሰልፍ እና እንድምታው
በሰሞነኛው የአዲስ አቤ ቀልድ ልጀምር። ወጣቱ፣ ሱሪ ለመግዛት ወጥቶ አንድ የልብስ ሱቅ ወስጥ ገባ። ባለ ሱቁ ጠየቀው። “የቻይና ይሁንልህ ወይንስ የአውሮፓ ሱሪ?” ወጣቱም መለሰ። “የለም የለም... የጎንደሩን ሱሪ ነው የምፈልገው።” እስረኞችን የማስፈታቱ ሰላማዊ ጥያቄ የእብሪት መልስ ሲያገኝ፤ ጨዋታውም ተቀየረ። “እንዲያውም አናውቅህም። ከህዝብ ጫንቃ ላይ ወረድ” ሲል ነበር የጎንደር ሕዝብ ብረትን ሰብሮ ዙፋኑን የነቀነቀው። “ወንዱን በምርቃና ሴቱን በቃና አደንዝዘን ይዘነዋል!” ያሉት ሕዝብ ከቶውንም እንዳልተዘናጋ አሳየን.... የመናገር እና ሃሳብን ያለፍርሃት የመግለጽ መብትን ህወሃት ሲፈልግ የሚሰጥ ሲያሻው ደግሞ የሚነፍገው የግል ሃብቱ አድርጎ ለ25 አመታት ሰንብቶ ነበር። ይህ መብት በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አሸብርቆ ጎንደር ላይ ተከበረ። በባህርዳር፣ በደሴ፣ በኦሮምያ፣ … [Read more...] about ታሪካዊው የጎንደር ሰልፍ እና እንድምታው
ሕዝብን አፍኖና በኃይል ረግጦ መግዛት ያብቃ!
ባለፈው እሁድ ትንሽ ትልቅ፣ ወንድ ሴት፣ ከተሜ ገጠሬ፣ ሳይል የጎንደር ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር በነቂስ ወጥቶ ከተማዋን ባጨናነቀ መልኩ የህወሓት አገዛዝ የፈጠረውን የሽብርና የፍርሃት አጥር ሰብሮ በመውጣት የተቃውሞ ድምጹን በሰላማዊ መንገድ አሰምቶ ወደቤቱ ተመልሷል። ምንም እንኳን አገዛዙ የተቃውሞ ሰልፉ እንዳይካሄድ ማናቸውንም እርምጃዎች ቢወስድም፣ ግፍ የበዛበት፣ የቆረጠና የተባበረን ሕዝባዊ ማዕበል የሚመክተው አንዳችም ምድራዊ ኃይል የለምና ከፍተኛ ጨዋነት በተሞላው መልክ ሕዝቡ ተቃውሞውን አሰምቷል። በዕለቱ ካስተጋባቸው መፈክሮች ውስጥ "በኦሮሚያ የሚደረገው የወገኖቻችን ግድያ ይቁም" የሚለው የጎንደር ሕዝብ ምንጊዜም በኢትዮጵያዊነትና በሀገር አንድነት ላይ ያለው የሚታወቀውን ጠንካራ አቋሙን ያሳየበትና የትግል አጋርነቱን በግልጽ ያንጸባረቀበት ነው። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የሕዝብ … [Read more...] about ሕዝብን አፍኖና በኃይል ረግጦ መግዛት ያብቃ!
ከሰልፉ በኋላስ ….?
ኢህአዴግ እመራበታለሁ በሚለው ህገ መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን እንደ ዴሞክራሲያዊ መብት በመውሰድ የትኛውም ወገን በሚፈልገው ጉዳይ አቋሙን ለመግለጽ ሰልፍ ለማድረግ ‹‹ማሳወቅ››ብቻ እንደሚጠበቅበት ቢደነግግም መሬት ላይ ያለው እውነታ ከዚህ እጅጉን ያፈነገጠ በመሆኑ የጎንደሩ ደማቅ ሰልፍ የተከናወነው ከእውቅናው ውጪ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ‹‹እውቅናውን ››ባልቸረው ሰላማዊ ሰልፍ የታየውን የህዝብ ጨዋ ድርጊት በመንተራስ ‹‹ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግስታዊ መብት ነው››ወዘተ በማለት ሰልፉን ‹‹እውቅና በመስጠቱ የተደረገ ››ለማስመሰል ካድሬዎቹ በሶሻል ሚዲያዎች የሚያደርጉትን መንፈራገጥ እውነታውን በመግለጽ ማስቆም ይገባናል፡፡ ሰልፉ ከኢህአዴግ እውቅና ውጪ መደረጉ በራሱ በአገር ውስጥ ለሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትልቅ ትምህርት ሊሰጥ እንደሚገባው ይሰማኛል፡፡ህዝብን ከጀርባው … [Read more...] about ከሰልፉ በኋላስ ….?
The Necessity of Cultural Reform: Working with time, not against
In my recent article entitled “The Power of Culture: Why we couldn’t make lasting transformations”, I argued that reforming our culture is critical to experience lasting and sustainable change but, at the same time,very challenging. As promised, in the coming couple of articles, I’d like to propose just a few of the cultural attributes we may consider reforming. Let me begin this journey by suggesting a change that may not draw serious controversies since, compared to my upcoming reform … [Read more...] about The Necessity of Cultural Reform: Working with time, not against
አንድ ህዝብ አንድ ሀገር!
ሰው ነፃነት ይፈልጋል። ነፃነት ላለመፈለግ ራሱ ነፃነት ይጠይቃል። ስለዚህ ነፃነቱን የሚቃወም አይኖርም። ምክንያቱም ነፃነትን በራስ መቃወም በራሱ ነፃነት ነው። ሰው ነፃ ለመሆንም ላለመሆንም ነፃ መሆን አለበት። ሰው ነፃ ላለመሆን የመወሰን ነፃነት አለው። ዋናው ጉዳይ ዉሳኔው የራስ መሆን አለበት፤ የሌላ አካል ጣልቃ ገብነት ሊኖረው አይገባም። ነፃነት የሰው ነው፤ የራሳችን ሃብት ነው። በሌሎች ጣልቃ ገብነት ሊገደብ ግን ይችላል። ስለዚህ ነፃነታትችን ከፈለግን መጠበቅ ይኖርብናል። ነፃነታችንን ለመጠበቅ ፈፃሚ ተቋም ያስፈልጋል። ፈፃሚ ተቋም ወይ ስርዓት የሚኖረው መንግስት ሲኖር ነው። መንግስት የሚኖረው ሀገር ሲኖር ነው። ሀገር የሚኖረው ህዝብ ሲኖር ነው። የምንፈልገው ነፃ ህዝብ ነው። ነፃ ህዝብ የሚኖረው ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሲኖር ነው። ዴሞክራሲያዊ መንግስት የሚኖረው የዴሞክራሲ … [Read more...] about አንድ ህዝብ አንድ ሀገር!
የአቶ ዠ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ጉዳይ
አቶ ዠ፣ ከ Fast Lane ዩኒቨርስቲ በተልዕኮ በአራት ወራት እድሜ የዶክትሬት ድግሪ የተጫነባቸው የክብር ዶክትሬት እንደሚጫንባቸው ጭምጭምታ ተሰማ። ጭምጭምታው ደግሞ ከሁነኛ ምንጮች ነው። በ“ተልዕኮ” ማለት ለ Fast Lane ዩኒቨርሲቲ ደብዳቤ መጻፍና ገንዘብ መላክ ነው ተብሎ ይታማል። ይህን ሃሜት እኔ ጭምጭታ ነው የሰማሁት። ጭምጭምታው ግን ከሁነኛ (አስተማማኝ) ሰው ነው። አቶዠ፣ቀድሞ በደርግ ጊዜ መፈክር ጸሃፊ፣ በኋላም በኢሃዲግ ጊዜ ልማታዊ ጸሃፌ ተውኔት፣ቀድሞ የኢሃዲግ ፍቅር ቤት ሥራ አስቀማጭ፣ ይቅርታ ሥራ አስኪያጅ፣ በዩናይትድ ኔሽንስ የኢትዮጵያ ተወካይ፣ ለዩናይትድ ኔሽንስ ዋና ጸሃፊነት በራስ አነሳሽነት ተወዳዳሪ፣ ወዘተርፈ...ወዘተርፈ....ወዘተርፈ....እንዳልኩት የክብር ዶክትሬት እንደሚጫንባቸው ጭምጭምታ ተሰማ። ጭምጭምታው ደግሞ ከሁነኛ ምንጮች ነው። ሆኖም ችግር … [Read more...] about የአቶ ዠ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ጉዳይ
“የኢትዮጵያን ችግር በኢህአዴግ መዋቅሮች ታጥረን መፍታት አንችልም” ጻድቃን ገ/ትንሳኤ
ህወሃት አገር የመገንጠል ዓላማውን አንግቦ የትጥቅ ትግል በጀመረበት ጊዜ ከተጋዳላይነት ተነስተው በአጭር ጊዜ ውስጥ የሌፍተናንት ጄኔራል ማዕረግ ለመጎናጸፍ የበቁት የቀድሞው ኤታማዦር ሹም ጻድቃን ገ/ትንሣዔ “የሃገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሃሳቦች” በሚል ርዕስ “Horn Affairs” ላይ ለወቅቱ የአገራችን ችግር ይበጃል ያሉትን የመፍትሔ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡ እነ ስየ አብርሃን ወደ ወኅኒ የጣለው ህንፍሽፍሽ በተከሰተ ጊዜ የመለስ ወገን ከመሆን ይልቅ ከውህዳኑ እነተወልደ ጋር በመወገናቸው በሳሞራ የተተኩት ጻድቃን አሁን እንደመፍትሔ ያቀረቡትን ሃሳብ አንዳንድ ወገኖች መልካምና የሰከነ አስተሳሰብ በማለት ሊደገፍ እንደሚገባ ሃሳብ ይሰጣሉ፡፡ በህወሃት ግፈኝነት የተማረሩና ህወሃት ካልተወገደ ሰላም አይኖርም የሚሉ ደግሞ የጻድቃንን ሃሳብ “ከዝንብ ማር አይጠበቅም” ብለው በመፈረጅ … [Read more...] about “የኢትዮጵያን ችግር በኢህአዴግ መዋቅሮች ታጥረን መፍታት አንችልም” ጻድቃን ገ/ትንሳኤ
በወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች ላይ ክስ ተመሠረተ
* ዐማራ ነኝ ማለታቸው እና በአውሮፕላን የተጓዙበት ቲኬትም በወንጀል ማስረጃነት ቀርቧል የትግራይ ክልል የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት አስተባባሪ ኮሚቴዎችና የማኅበረሰብ አባላት ላይ የመሠረተው ክስ ዛሬ ሐምሌ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ይፋ ሆኗል፡፡ የትግራይ መንግሥት በ34 የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች ላይ የመሠረተው ክስና ማስረጃ ብሎ ያቀረበው ባለ 250 ገጽ የትግርኛ ድርሰት በግልጽ እንደሚያሳየው የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች ‹‹እኔ ዐማራ ነኝ›› ማለታቸው፣ የተለያየ ጊዜ ለሚመለከታቸው አካላት ማመልከቻዎችን ማስገባታቸው፤ በባንክ ገንዘብ ማንቀሳቀሳቸው ብሎም አንደኛው ተከሳሽ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ በአውሮፕላን መጓዙ በወንጅል ከተከሰሱባቸውን የወንጀለኛነታቸው ማስረጃ ሆነው ቀረበዋል፡፡ በምስክርነት በዳንሻና በአካባቢው በሠፈራ የመጡ ትግሬዎችና የሕወሓት አመራሮች ተዘርዝረዋል፡፡ … [Read more...] about በወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች ላይ ክስ ተመሠረተ










