ኢህአዴግ እመራበታለሁ በሚለው ህገ መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን እንደ ዴሞክራሲያዊ መብት በመውሰድ የትኛውም ወገን በሚፈልገው ጉዳይ አቋሙን ለመግለጽ ሰልፍ ለማድረግ ‹‹ማሳወቅ››ብቻ እንደሚጠበቅበት ቢደነግግም መሬት ላይ ያለው እውነታ ከዚህ እጅጉን ያፈነገጠ በመሆኑ የጎንደሩ ደማቅ ሰልፍ የተከናወነው ከእውቅናው ውጪ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡
‹‹እውቅናውን ››ባልቸረው ሰላማዊ ሰልፍ የታየውን የህዝብ ጨዋ ድርጊት በመንተራስ ‹‹ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግስታዊ መብት ነው››ወዘተ በማለት ሰልፉን ‹‹እውቅና በመስጠቱ የተደረገ ››ለማስመሰል ካድሬዎቹ በሶሻል ሚዲያዎች የሚያደርጉትን መንፈራገጥ እውነታውን በመግለጽ ማስቆም ይገባናል፡፡
ሰልፉ ከኢህአዴግ እውቅና ውጪ መደረጉ በራሱ በአገር ውስጥ ለሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትልቅ ትምህርት ሊሰጥ እንደሚገባው ይሰማኛል፡፡ህዝብን ከጀርባው ማሳተፍ የቻለ ማንኛውም አይነት ንቅናቄ በየትኛውም መንገድ ሊታፈን እንደማይችል ጎንደር ምስክር ተደርጋ ልትጠቀስ ትችላለች፡፡ (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply