ዘረኛው የትግሬ ወያኔ የወልቃይት ጠገዴን የማንነት ጥያቄ ደግፈው በወጡ የባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ በግፍ የገደላቸው ወገኖቻችን ዝርዝር በከፊል።
«የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ፣ የእኛም የዐማራነት ጥያቄ ነው፣» ብለው እሑድ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓም ላይ በባሕርዳር ከተማ፣ በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ለማሰማት በወጡ ዐማሮች ላይ፣ የትግሬ ወያኔ ዘረኛ ቡድን በርካታ፣ ሩቅ አሳቢ፣ ለሥራ የጓጉ፣ ላገርና ለወገን ታላቅ ተስፋ ሰንቅው የነበሩ የአያሌ ወጣቶችን ሕይዎት በግፍ ነጥቋል። በባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ወያኔ ከገደላቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች መካከል ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን የከፊሎቹን አገኝቷል።
ከሰንጠረዡ ለመረዳት እንደሚቻለው፣ በግፍ ከተገደሉትና ዝርዝራቸውን ማወቅ ከተቻለው አርባ ዘጠኝ(49) ሰዎች ውስጥ፣ ዕድሜአቸው ሰላሳና ከዚያም በላይ የሆኑት ስምንት ( 8) ብቻ ነው። አርባ አንዱ (41) በወያኔ የግፍ አገዛዝ የተወለዱና ወያኔ ሲገባ ከአምስት ዓመት ዕድሜ የማይበልጡ መሆኑ በግልጽ ይታያል። በመሆኑም ያለፈውን ሥርዓት የማያውቁ፣ ያልኖሩበት፣ በትህምርትም ያልተማሩት በመሆኑ የሚናፍቁት አንዳች ነገር ይኖራ ተብሎ አይታሰብም። ወጣቶቹ ሰዎች ናቸው እና እንደማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር መልካም ነገርን፣ እንደሰው ዕኩል መታየትን፣ ጥሩና መልክ ነገሮችን የመመኘት፣ ራሳቸውን ከሌሎች አቻዎቻቸው ጋር አመዛዝኖ ለእኛ ለምን ሰብአዊ መብቶቻችን፣ ተዘዋውሮ የመሥራትና ያመኑበትን በግልጽ የመናገር፣ የመደራጀት፣ ወዘት መብትና ነፃነት እንነጠቃለን፣ ከዚህ ሁሉ በላይ ማንነታቸውን ለምን ይካዳል ብለው መጠየቃቸው ሰው ሆኖ በመፈጠራቸው ብቻ የተሰጣቸው መብት እንጂ፣ ያለፈ ሥርዓት የመናፈቅ ወይም ትምክህተኛ የመሆን ውጤት አይደለም።
በሌላም በኩል እነዚህ በወያኔ ዘመን ተወልደው፣ በርሱ የትምህርት ሥርዓት ያለፉ ወጣቶች ያነሱት የማንነት ጥያቄ ሥርዓቱ ገነባሁት ያለው «የነገዶች ዕኩልነትና ሰላም» አስገኘሁት እያለ የሚለፍፈው «ልማት» ውሸት መሆኑን ገላጭ ነው። የዘረኝነት ሥርዓቱ፣ ዐማራውን በጠላትነት ፈርጆ ያወጀበት የዘር ጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል፣ እየከፋ መምጣቱን፣ የዐማራው ወጣት ትውልድ ማንነታችን እናስከብር ብሎ በቁርጠኝነት መነሳቱን የሚያመለክት ነው። ባጭሩ ወያኔ የወልቃይት ጠገዴን የማንነት ዕውነተኛ ጥያቄ «ያለፈው ሥርዓት ናፋቂዎች፣ ትምክህተኞች፣ ነፍጠኞች» እያለ ያልሆነ ስም የሚለጥፍባቸው ንፁሐን ዜጎች የራሱ ከፋፋይ፣ አጥፊና ዘረኛ ሥርዓት ውጤቶች፣ የዘረኛና ብልሹ አስተዳደሩ ውጤት መሆኑን፤ ይህንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያልተቀበለው እንደሆነ የሚያሳይ አጉሊ መነፀር ነው።
በወያኔ አጋዚ ጦርና ከሕዝቡ መሀል ለዘመናት በኖሩና የባሕርዳር ሕዝብ እንደወገን በሚያያቸው፣ እነርሱ ግን እንደጠላት ቆጥረው ለገዳዩ ቡድን መረጃ በማቀበል በተሰማሩት የትግሬ ነገድ አባሎች የተጨፈጨፉት ሰላማዊ ዜጎች፣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ስማቸውን ለማግኘት የቻላቸው የሚከተሉት ናቸው። ለወራት ያህል በዘለቀው ሕዝባዊ እንቢተኝነት ሕይዎታቸውን ያጡ ወገኖቻችን ስምና ማንነት እየተከታተልን የማሳወቅ ተግባራችንን በንቃት ለመወጣት የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን።
ተራ ቁጥር |
የተገዳይ ሙሉ ስም |
ዕድሜ |
መኖሪያ አድራሻ |
1 | ዕድሜዓለም ዘውዱ | 27 | ባሕር ዳር |
2 | ገረመው አበባው | 25 | ባሕር ዳር |
3 | ተፈሪ ባዩ | 16 | ባሕር ዳር |
4 | ሰሎሞን አስቻለ | 25 | ባሕር ዳር |
5 | ሙሉቀን ተፈራ | 27 | ባሕር ዳር |
6 | አደራጀው ኃይሉ | 19 | ባሕር ዳር |
7 | አስማማው በየነ | 22 | ባሕር ዳር |
8 | ታዘበው ጫኔ | 21 | ባሕር ዳር |
9 | አሥራት ካሣሁን | 24 | ባሕር ዳር |
10 | የሽዋስ ወርቁ | 20 | ባሕር ዳር |
11 | ብርሃን አቡሃይ | 29 | ባሕር ዳር |
12 | ሽመልስ ታዬ | 22 | ባሕር ዳር |
13 | አዛናው ማሙ | 20 | ባሕር ዳር |
14 | ሢሣይ አማረ | 24 | ባሕር ዳር |
15 | ሞላልኝ አታላይ | 21 | ባሕር ዳር |
16 | መሣፍንት አማራ | 22 | እስቴ |
17 | እንግዳው ዘሩ | 20 | ባሕር ዳር |
18 | ዝናው ተሰማ | 19 | ባሕር ዳር |
19 | ዋለልኝ ታደሰ | 24 | ባሕር ዳር |
20 | ይታያል ካሤ | 25 | ባሕር ዳር |
21 | እሸቴ ብርቁ | 37 | ባሕር ዳር |
22 | ሞገስ | 40 | ባሕር ዳር |
23 | አደራጀው ደሣለኝ | 30 | ባሕር ዳር |
24 | አበበ ገረመው | 27 | ጢስ ዐባይ |
25 | ማኅሌት | 23 | ባሕር ዳር |
26 | ተስፋዬ ብርሃኑ | 58 | ባሕር ዳር |
27 | ፈንታሁን | 30 | ባሕር ዳር |
28 | ሰጠኝ ካሤ | 28 | ባሕር ዳር |
29 | ባበይ ግርማ | 26 | ባሕር ዳር |
30 | አለበል ዓይናለም | 28 | ደብረማርቆስ |
31 | አብዮት ዘሪሁን | 20 | ባሕር ዳር |
32 | አበጀ ተዘራ | 28 | ወረታ |
33 | ደመቀ ዘለቀ | 22 | ወረታ |
34 | አለበል ሃይማኖት | 24 | ወረታ |
35 | ሰሎሞን ጥበቡ | 30 | ቻግኒ |
36 | ፍሥሃ ጥላሁን | 25 | አዲስ አበባ |
37 | ቅዱስ ሀብታሙ | 16 | አዲስ አበባ |
38 | በረከት ዓለማየሁ | 28 | ዳንግላ |
39 | ያየህ በላቸው | 30 | ዳንግላ |
40 | ዓለማየሁ ይበልጣል | 27 | ዳንግላ |
41 | በለጠ ካሤ | 32 | ደብረታቦር |
42 | ይህነው ሽመልስ | 30 | ደብረታቦር |
43 | ይበልጣል ዕውነቱ | 24 | ጢስ ዐባይ |
44 | ሀብታሙ ታምራት | 27 | ባሕር ዳር |
45 | ታደሰ ዘመኑ | 26 | አዴት |
46 | ሽመልስ ወንድሙ | 28 | ቡሬ |
47 | ዓይንአዲስ ለዓለም | 24 | ደብረወርቅ |
48 | እስቲበል አስረስ | 19 | አዴት |
49 | ሞገስ ሞላ | 23 | ባሕር ዳር |
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፭
ሐሙስ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም.
Leave a Reply