• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

Opinions
የኔ ሃሳብ

ተደናቂ ለሆነ የፍትሕ አገልግሎት ስለ ተሰጠ ሽልማት

April 25, 2017 06:06 am by Editor Leave a Comment

ተደናቂ ለሆነ የፍትሕ አገልግሎት ስለ ተሰጠ ሽልማት

ጋዜጣዊ መግለጫ ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ - የኢትዮጵያ ጉዳይ ተደናቂ የሆነ የፍትሕ አገልግሎት በመፈጸማቸው ከዚህ ቀጥሎ ስማቸው ለተዘረዘሩት ሽልማት ያበረከተ መሆኑን ይገልጻል፤ ቀሲስ/ዶር. ምክረ-ሥላሴ ገብረ አማኑኤል፤በፋሺሽት ኢጣልያ የኢትዮጵያ ወረራ ዘመን ስለነበረው የቫቲካን ሚና ግንዛቤ እንዲገኝ በደረሱት መጽሐፋቸው አማካኝነት ስላበረከቱት አስተዋጽኦ፤ ሚር. ኢያን ካምፕቤል፤ ፋሺሽቶች በኢትዮጵያ ላይ ስለ ፈጸሙዋቸው የጦር ወንጀሎች በደረሱዋቸው መጽሐፎች ስላበረከቱት አስተዋጽኦ፤ ሚር. ቫሌሪዮ ቺሪያቺ፤ ፋሺሽት ኢጣልያኖች፤ በኢትዮጵያ ላይ ስለ ፈጸሙት የጦር ወንጀልና ባሁኑ ወቅት በመኪያሔድ ላይ ስላለው የፍትሕ ጥረት ግንዛቤ እንዲገኝ ፊልም በማዘጋጀት ስላበረከተቱት አስተዋጽኦ፤ አቶ ከባዱ በላቸው፤ ፋሺሽት ኢጣልያኖች፤ በቫቲካን የትብብር ድጋፍ፤ … [Read more...] about ተደናቂ ለሆነ የፍትሕ አገልግሎት ስለ ተሰጠ ሽልማት

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም የዘመን ዕንቁ! የትውልድ ዋርካ!! 87ኛ ዓመት

April 23, 2017 09:32 am by Editor 5 Comments

የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም  የዘመን ዕንቁ! የትውልድ ዋርካ!! 87ኛ ዓመት

መግባቢያ! የሀገረ-ኢትዮጵያ የእውቀት አደባባይ በአስፈሪ ዝምታ ተውጧል። ምሁራኖቻችን ከህዝባዊ ተዋፅኦ አፈግፍገዋል። የአደባባይ ምሁራን ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት በመናመን ላይ ባሉ ብርቅዬ የዱር እንሰሳት መመሰል ከጀመረ ዓመታት አልፈዋል። ቁጥራቸው የበዛ ምሁራን አገዛዙ በፈጠረው የጥቅመኝነት ፖለቲካ ጥላ ስር መጠለል ምርጫቸው ሆኗል። ጥቂት የማይባሉት ደግሞ የባዕድ አገር ስደትን መርጠዋል። ሕዝባዊ መድረኮቻችንን ፋይዳ ቢስ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮችና በተዛቡ የታሪክ ትርክቶች፤ በዘውጋዊ አጥርና አገራዊ ከፍታን መፍጠር በማይችሉ ሙግቶች ተውጠዋል። ዕድሮችና የመረዳጃ ማህበራት ሳይቀር ዘውጋዊ ቅርጽ (አጥር) ሰርተዋል። አገሪቱ ለገባችበት የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ቅርቃርና ለማህበራዊ ችግሮቻችን መፍትሔ ይሰጣሉ ተብለው ተስፋ የተጣለባቸው የፖለቲካ ልሂቃን አገሪቱን ለአራት አስር ዓመታት ክፉኛ … [Read more...] about የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም የዘመን ዕንቁ! የትውልድ ዋርካ!! 87ኛ ዓመት

Filed Under: Opinions, Politics, Social Tagged With: Full Width Top, Middle Column

የእግዚአብሔር መልእክት በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል

April 21, 2017 04:01 am by Editor 4 Comments

የእግዚአብሔር መልእክት በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል

"ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደአለላ ብትሆን እንደአመዳይ ትጸዳለች እንደደምም ብትቀላ እንደባዘቶ ትጠራለች፤ እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እንቢ ብትሉ ግን ብታምጹም ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናገሮአልና፡፡" ኢሳ. 1/18. በእግዚአብሔር ለሚያምን ሰው፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜም፣ ለዘለዓለም ሙሉና የማይወዳደሩት ኃይል እንዳለው ለሚያምን ሰው፣ ለእግዚአብሔር ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም አሁን መሆኑን ለሚያምን ሰው "ኑና እንዋቀስ" (በእንግሊዝኛው "come now let us reason together") ማለት ለእግዚአብሔር ምን ያህል መውረድ እንደሆነ መገንዘብ የሚዳግት አይመስለኝም፤ የእንግሊዝኛው ትንሽ ሻል ያለ መስሎ "ኑና እንከራከር" የሚል ቢሆንም ከመጨረሻው የላይኛው ዳኛ ጋር መከራከር የሚችለው ማን ነው? እግዚአብሔር … [Read more...] about የእግዚአብሔር መልእክት በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል

Filed Under: Opinions, Social Tagged With: Left Column

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይና ዋልድባ ገዳም

April 18, 2017 07:07 am by Editor Leave a Comment

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይና ዋልድባ ገዳም

የዋልድባ ገዳም በህዋሓት መሪዎች በዓይነ ቁራኛ የወደቀው ገና ትግሉ እንደተጀመረ ነው። የዋልድባ ገዳም የህወሓት መሪዎች እንዲወድም ሃሳብ ያቀረቡት በ1973 መጨረሻ አካባቢ ሲሆን፣ አቅማራ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በወቅቱ የህወሓት መናኸሪያ ነበር። በተመቤን ውስጥ የሚገኘው ቦታ በፕሮፓጋንዳ ጽ/ቤት ተሰብስበው ወሰኑ፤ በስብሰባ የነበሩት አመራር ፖሊት ቢሮው በሙሉ ነበር። እነሱም፣ ስብሃት ነጋ፣ አረጋዊ በርሄ፣ ገደይ ዘርአጽዮን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን እና መለስ ዜናዊ ነበር። በወቅቱ ማ/ኮሚቴ የነበሩ ናቸው። በዚህ ስብሰባቸው የዋልድባን ገዳም እጣ ፈንታ ወሰኑ። ዋልድባ እንዲወደም! የዋልድባ ገዳም ለብዙ መቶ ዘመናት የቅዱሳን፣ ብፁአን፣ ባህታውያን፣ ቀሳውስት፣ አባቶች፣ ደናግል፣ ዲያቆናት ወዘተ ሰፈር በመሆን በኢትዮጵያ ቅዱስና በታሪክ ትልቅ ምእራፍ የያዘ ገዳም ነው። ይህ ቅዱስ ገዳም … [Read more...] about ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይና ዋልድባ ገዳም

Filed Under: Opinions, Social Tagged With: Left Column

ለዴሞክራሲ አርበኞች ተባብሮ ለመታገል የሚያስችል ቀላልና ጠቃሚ ሃሳብ

April 14, 2017 05:16 am by Editor 2 Comments

ለዴሞክራሲ አርበኞች ተባብሮ ለመታገል የሚያስችል ቀላልና ጠቃሚ ሃሳብ

አስቀድሞ የከበረ ሰላምታ ይድረሳችሁ፤ በዚህ ማስታወሻ የቀረበውን ሃሳብ ጠቃሚ ነው የምትሉ ስለጠቀሚነቱ፤ ጎጂ ነው የምትሉም ስለጎጅነቱ የሚታያችሁን ምክንያቶች ጨምራችሁ መልስ እንድትሰጡ ትጠየቃላችሁ፤ ሌሎች ይህ ሃሳብ ከተላለፈበት ዕለት ቀደም ብሎ ተደራጅታችሁ እንቅስቃሴ የጀመራችሁና በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያልገባችሁ ካላችሁ ተቀላቅላችሁ ድምጻችሁን ማሰማት ትችላላችሁ። በጉዳዩ ላይ ድምጽ ለማሰማት ግለሰቦችም መብታችሁ የተጠበቀ ነው። መልስ ስትሰጡ ግን አድራሻችሁን ማኖር አትርሱ።  የመልሱ ውጤት ከታየ በዃላ ቀጣይ ሂደት ይኖራ ተብሎ ተስፋ ይደረጋል። ለዚህ ጽሁፍ መነሻ፤- ከወራት በፊት አቶ ዘውዴ ጉደታ የተባሉ ወንድም "የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ እና የአገር አንድነትን "ያገቱት" ሦስት ተጻራሪ ሃይሎች" በሚል ርዕስ አንድ ሰፋ ያለ ጽሁፍ አስነብበው ነበር። ከዚያም በላይ የጸሃፍያን … [Read more...] about ለዴሞክራሲ አርበኞች ተባብሮ ለመታገል የሚያስችል ቀላልና ጠቃሚ ሃሳብ

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

የበጋው መብረቅ (ሌፍተንት ጀነራል ጃጋማ ኬሎ)

April 13, 2017 07:00 pm by Editor Leave a Comment

የበጋው መብረቅ (ሌፍተንት ጀነራል ጃጋማ ኬሎ)

. . . ጃጋማ በውጊያ ብቻ አልነበረም ብስለቱ በአስተዳደርም የተደነቀ ነበር።ለምሳሌ፤ከአምቦ መንገድ በላይ ያሉት ነዋሪዎች ጥራጥሬ እያዋጡ ቆሎ እየቆሉ ለአርበኛው ይረዳሉ፤ከአምቦ መንገድ በታች ያሉት ግን የጃገማ አርበኞች ሙጀሌ የወረሳቸው ሰለሆኑ ይህን የተሰነጣጠቀ እግራቸው ችሎ መራመድ አይችሉም፤ስለዚህ እንኳን እኛን ከኢጣሊያ ስራዊት ሊጠብቁን እና ሊከላከልሉን ቀርቶ ለራሳቸውም ሰለማይሆኑ በምንም ነገር አንረዳቸውም ማለታቸውን ጃጋማ ሰማ። ለሰራዊቱም ትእዛዝ ሰጥቶ ወደ ሃያ ሺህ ከብቶቻቸውን አስነዳባቸው፤ ህዝቡም በጣም ተደናግጦ ምነው ምላሳችንን በቆረጠው በሚል በጣም ተደናገጡ።ቀንበራቸውን ተሸክመው የጃጋማ ጦር የሰፈረበት ቦታ ድረስ በመሄድ እግዚኦ አሉ። ወጣቱ መሪ ጃጋማ እንዲህ አላቸው (እኛ ከእናንተ የወጣን የእናንተ ልጆች ነን፤ጠላት የሚንቀን አንሶ ለሐገራችንና ለእናንተ በባዶ … [Read more...] about የበጋው መብረቅ (ሌፍተንት ጀነራል ጃጋማ ኬሎ)

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ ተስፋና ሥጋት!

April 12, 2017 07:26 am by Editor 1 Comment

የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ ተስፋና ሥጋት!

ላለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት በዘረኛው የትግሬ ነፃ አውጪ የአገዛዝ መዳፍ ሥር የታፈነውን ሕዝባችንን ወደ ነፃነትና የዴሞክራሲ ምዕራፍ ለማሸጋገር የጋራ ትግል ለማድረግ ሲሞከር ቆይቷል። ሆኖም በእነዚህ ዘመናት ውስጥ የተፈጠሩት የፖለቲካ ኃይሎች ትብብር፣ ቅንጅት፣ ኅብረት እና ውህደት አንዱም ከዳር ሳይደርስ እንዲሁ ሲሰበሰብና ሲበተን ከርሟል። እንደ አባባልም እንደ መታወሻም “ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ” የሚለው የዶ/ር መረራ ጉዲና መፈክር አንዱም ገቢራዊ ሳይሆን አብዛኞቹ የፖለቲካ ተቋማት በአገዛዙ ጫናና በራሳቸው ደካማ አደረጃጀት ህልውናቸው እየጠፋ ለሐገር የሚተርፍና ትውልድ የሚረከበው አንድም አግባቢ የጋራ ማዕከል ሳይመሰረት በኪሳራ የታጀቡ ዓመታትን አሳልፈናል። ትብብር የጉልበት ምንጭ ነው።ትብብር ድልን ማቅረቢያ ዘለቄታዊና ሠላማዊ ሽግግርን ማሳለጫ መሳርያ ነው።ትብብር ከሚከሰረው … [Read more...] about የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ ተስፋና ሥጋት!

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

ከኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ-ምልልስ በስተጀርባ

April 12, 2017 06:15 am by Editor Leave a Comment

ከኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ-ምልልስ በስተጀርባ

ጠንቋይና ፖለቲከኛ የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር አለ። ሁለቱም ተገልጋያቸውን ለማምታታት የትኩረት አቅጣጫ ማስቀየርን ተክነውበታል። ኢሳያስ አፈወርቂ በዚህኛው - የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ - ገለጻቸው ራሳቸውን ሳይቀይሩ ሌላውን ለመቀየር የተነሱ ግብዝ ነው የሆኑት። ይህ "ቃለ-ምልልስም" አንድ አላማ አለው። አላማውን ለማወቅ ቃላቶችን መሰንጠቅም አያስፈልግም። ግልጽ ነው። 'ብዙ ስላልተሰራበት' መልዕክቱ የተጠበቀውን አላማ የመታ አይመስልም። ቃለ-ምልልሱ የተደረገበት ወቅት፣ የተመረጠበት ሰዓት የሚሰጠን ግልጽ የሆነ ግን የተለየ ትርጉም አለ። ጠያቂዎቹ በሻዕቢያ ላይ የነበራቸው የፖለቲካ አቋም ከመቅጽበት መቀየሩ በራሱ የሂደቱን ግራጫ ምስል ያሳየናል። "ሁሉን ቢናገሩ ሆድ ባዶ ይቀራል" ይላሉ አበው።  እነዚህ ጉዳዮች ውስጥ ገብቶ መላ-ምቶችን መዘርዘሩ አስፈላጊ ባይሆንም (አንዱ መላ ምት … [Read more...] about ከኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ-ምልልስ በስተጀርባ

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: Left Column

«ችግሩን ለማስወገድ፣ ግለሰብ ወይም ቡድን መወገድ አለበት» ዐባይ ፀሐዬ

April 10, 2017 05:54 am by Editor 1 Comment

«ችግሩን ለማስወገድ፣ ግለሰብ ወይም ቡድን መወገድ አለበት» ዐባይ ፀሐዬ

የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) አጠቃላይ ግብ፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው። የዚህ ግብ መዳረሻ ደግሞ በኢትዮጵያዊነታቸው በጽኑ የሚያምኑ ኢትዮጵያውያን እና ከሁሉም በላይ፣ የዐማራውን ነገድ ማጥፋት ሲቻል እንደሆነ በማመኑ፣ ላለፉት 43 ዓመታት የኢትዮጵያዊነት የወል ዕሴቶችን፣ ነባር ሃይማኖቶችን፣ የአገራዊነት መገለጫ የሆነችውን ሰንደቅ ዓላማችንን፣ በሕዝቡ መሀል የአንድነት መገለጫ የሆኑ ተቋሞችንና አሠራሮችን፣ ግንኙነቶችን በአዋጅ አጥፍቷል። በዐማራው ነገድ ላይ የተቀነባበረ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጽሟል። የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዐማሮች ከምድረ-ገጽ እንዲጠፉ ተደርጓል። የትግሬ-ወያኔ ለዚህ ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና የዐማራውን ነገድ ለማጥፋት ላለመው ዓላማው ወደ ግቡ መዳረስ … [Read more...] about «ችግሩን ለማስወገድ፣ ግለሰብ ወይም ቡድን መወገድ አለበት» ዐባይ ፀሐዬ

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ የፖለቲካ ትግል፤ ወይንስ የተበታተነ ተቃውሞ?

April 7, 2017 05:40 am by Editor Leave a Comment

ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ የፖለቲካ ትግል፤ ወይንስ የተበታተነ ተቃውሞ?

የያዝነውን እናጢን! ምን እያደረግን ነው? የትግሬዎቹ ገዢ ቡድን በሚያደርገው የዕለት ተዕለት አውዳሚ ተግባሩ በመቆጣት፤ ለተቃውሞ መነሳትና፤ ይህን አካል በተግባሩ ወንጅሎ፤ በደሎቹን መዘርዘሩ አንድ ነገር ነው። ይህ ተቃውሞ ነው። በመቃወምና ይህ መደረግ የለበትም ብሎ በመጮህ፤ የተወሰነ ግብን ማስገኘት ይቻላል። ተግባሩ ግን ይቀጥላል። ቢበዛ ቢበዛ፤ በተግባሩ ሂደት ላይ ትንሽ ማስተካከያ ማስከተል ይቻላል። ከዚያ በተረፈ ግን፤ ይህ በመፈጸም ያለ በደል፤ በድጋሚ እንዳይከሰት የሚያቆመው ነገር የለም። ይሄን በማድረግ የሚረካ ሊኖር ይችላል። እንደገና፤ ይህ ተቃውሞ ነው። በታቃራኒው ደግሞ፤ የተፈጸሙትና በመፈጸም ላይ ያሉት በደሎች፤“መደረግ የለባቸውም!” ብሎ መነሳት ብቻ ሳይሆን፤ “የዚህ ሁሉ ምንጩ፤ አንድ አካል ነው። ይህ አካል መንግሥታዊ ሥልጣኑን ባንድ መንገድ ወይንም በሌላ፤ በጁ … [Read more...] about ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ የፖለቲካ ትግል፤ ወይንስ የተበታተነ ተቃውሞ?

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

  • « Previous Page
  • Page 1
  • …
  • Page 37
  • Page 38
  • Page 39
  • Page 40
  • Page 41
  • …
  • Page 167
  • Next Page »

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በፋኖ ስም ከአማራ ገበሬና ከዳያስፖራ የሚሰበሰበው በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የጥቂት አመራሮች መበልጸጊያ ሆኗል November 20, 2026 08:54 am
  • የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው! November 17, 2026 11:54 pm
  • “የጫካ ቱጃሮች!”— የፋኖ አመራሮች ስለተሰማሩበት የገንዘብ ዝርፊያ አስደንጋጭ መረጃ November 17, 2026 05:43 pm
  • በየወሩ 4 ሚሊዮን ብር እየተከፈለው ሀገር ሲያፈርስ የነበረው ሪፖርተር November 16, 2026 01:17 am
  • ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት November 14, 2026 12:42 am
  • የመለስ ዜናዊን ጭንብል የገፈፈው የትህነግ ሚዲያ (EMF) ምስክርነት November 13, 2026 03:32 pm
  • ትህነግ በወታደራዊና በፖለቲካዊ መስክ እንደሞተ ሁሉ በሪፖርተር በኩል የሚዲያ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል November 13, 2026 01:13 am
  • በከባድ ታክስ ማጭበርበር የሚፈለጉት አቶ አበባው ደስታ፣ አማራጭ የቴሌኮም ጌትዌይ ፕሮጀክትን ሊጠቀልሉ ነው November 12, 2026 03:50 am
  • “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ሕዝብ እየገደለ ነው” የኦነግ ሸኔ (OLF/OLA) ተወካይ ጃል ጅረኛ November 10, 2026 05:12 pm
  • ከትህነግ የተማረኩና ከውጭ ሀገራት የገቡ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በቃሊቲ ለእይታ ቀረቡ November 6, 2026 03:36 pm
  • የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ሁርሶ የተወሰዱበት ምሥጢር November 5, 2026 12:43 pm
  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
  • ዜግነት ሊያሰርዝ በሚችለው የኢልሃን ዑመር ምርመራ ላይ አዳዲስ መረጃ ተገኝቷል October 19, 2026 04:45 pm
  • በትግራይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ስም በአስቸኳይ ሊቀየር ይገባል! October 19, 2026 02:55 am
Copyright © 2026 · Goolgule