• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

«ችግሩን ለማስወገድ፣ ግለሰብ ወይም ቡድን መወገድ አለበት» ዐባይ ፀሐዬ

April 10, 2017 05:54 am by Editor 1 Comment

የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) አጠቃላይ ግብ፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው። የዚህ ግብ መዳረሻ ደግሞ በኢትዮጵያዊነታቸው በጽኑ የሚያምኑ ኢትዮጵያውያን እና ከሁሉም በላይ፣ የዐማራውን ነገድ ማጥፋት ሲቻል እንደሆነ በማመኑ፣ ላለፉት 43 ዓመታት የኢትዮጵያዊነት የወል ዕሴቶችን፣ ነባር ሃይማኖቶችን፣ የአገራዊነት መገለጫ የሆነችውን ሰንደቅ ዓላማችንን፣ በሕዝቡ መሀል የአንድነት መገለጫ የሆኑ ተቋሞችንና አሠራሮችን፣ ግንኙነቶችን በአዋጅ አጥፍቷል። በዐማራው ነገድ ላይ የተቀነባበረ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጽሟል። የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዐማሮች ከምድረ-ገጽ እንዲጠፉ ተደርጓል።

የትግሬ-ወያኔ ለዚህ ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና የዐማራውን ነገድ ለማጥፋት ላለመው ዓላማው ወደ ግቡ መዳረስ የረዳው አደረጃጀቱ ወታደራዊ መሆኑ፣ ወታደሩ ካንድ አናሳ ነገድ የወጣና በኢትዮጵያዊነትና በዐማራ ነገድ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ይዞ የተደራጀና አድርግ ያሉትን የጥፋት ርምጃ ሁሉ ለመፈጸም ወደ ኋላ የማይል ዘረኛ መሆኑ አንዱና ዋናው ምክንያት ነው።

ሁለተኛው ምክንያት የትግራይን ሕዝብ በነቂስ በወታደራዊ ሥልትና ጠገግ አደራጅቶ የጥፋት ተግባሩ ተባባሪ ማድረግ መቻሉ ነው።

ሦስተኛው ምክንያት፣ አገሪቱን በነገድ ሸንሽኖ፣ ሁሉም ነገዶች ዐማራውን በጠላትነት ፈርጀው የርሱ አጋር እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉ ነው። ከሁሉም በላይ በዐማራውና በኦሮሞው ነገዶች መካከል ነባር የአንድነት ስሜታቸውን አውልቀው፣ በጠላትነት እንዲተያዩ፣ የሀሰት ድርሳኖችን በመድረስ ዓይንና ናጫ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉ እንደሆነ በግልጽ ይስተዋላል።

አራተኛው ምክንያቱ ለአበዳሪና ለጋሽ መንግሥታትና ድርጅቶች ዲሞክራት መስሎ መታየት የሚችልበት የተለያዩ ጭንብሎች ማጥለቅ መቻሉ ነው።

አምስተኛውና ብቸኛ መተማመኛው፣ በየትኛው መልኩ ይሁን የትግሬ-ወያኔ ከሥልጣን ከወረደ በአገር ክሕደትና በሕዝብ ጭፍጨፋ ወንጀል ተጠያቂ እንደሚሆን ስለሚያምን፣ ከየትኛውም አቅጣጫ ሊነሳ የሚችልበትን ተቃውሞ በኃይል ማፈን የሚል ሥልት አንግቦ የሚንቀሳቀስ መሆኑ ነው።

ስድስተኛውና አይቀሬ ግቡ፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ለመቶ ዓመታት ለመቆየት ያለመው ዓላማው  በተለዋዋጭነት የሚከተላቸው መንገዶች አላዋጣ ሲሉት፣ ትግራይን በሁለመናዋ ሀብታም በማድረግ፣ ትግራይን ገንጥሎ ከኤርትራ ጋር በመዋሐድ «ትግራይ ትግርኚ» የሚለውን የጣሊያን የወደቀ ፕላን ዕውን ማድረግ የሚለው ነው። ለዚህ ዓላማ ተፈፃሚነትም ባለፉት 26 ዓመታት ትግራይ በኢትዮጵያ ሕዝብ አንጡራ ሀብት በኢንዱስትሪ፣ በእርሻ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በትራንስፖርት፣ በመገናኛ፣ በመንገዶች ግንባታ፣ የአፍሪካ ታይዋን ለማድረግ ብዙ መሠራቱ ይታወቃል። የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን አፍርሶ ወደ ጉሬው ሲገባ፣ ከመሀል አገር ጥቃት እንዳይሰነዘርበት፣ የአገሪቱን የመከላከያ ኃይል ማለትም፣ የአየርና የምድር ጦር ወደ ትግራይ አጉዟል። የአገሪቱን የመረጃ ማዕከል መቀሌ ወስዷል። በትግራይ ውስጥ ሦስት ታላላቅ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያዎች ገንብቷል። ከጂቡቲ መቀሌና ከመቀሌ ሱዳን የሚያገናኝ የባቡር ሐዲድ እያስገነባ ነው። የአገሪቱን ተንቀሳቃሽ ቅርሶች በሙሉ ሰብስቦ አክሱም አስገብቷል። የትግሬን ትውልድ በዕውቀት የበለጸገ ለማድረግ በገፍ በሕዝብ ሀብት ትግሬዎች ብቻ የውጭ ትምህርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል።

የትግሬ-ወያኔ በዚህ ሁሉ ጥረቱ ለመቶ ዓመታት በኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ እንፈነጫለን ብለው የተከተሏቸው ስልቶች አዋጭ አልሆኑም። ሕዝቡን በነገድና በቋንቋ ከፋፍሎ የርሱ ተከታይ ለማድረግ ያጠመደው ወጥመድ እራሱን በመጥለፍ አላላውስ እያለው ነው። በዐማራና በኦሮሞ መካከል የገነባው የጥላቻ ግንብ፣ ጀግኖቹ የጎንደር ዐማራ ልጆች፣ በሐምሌ ወር 2008 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ባደረጉት ከፍተኛ የተቃውሞ ሕዝባዊ ሰልፍ፣ «የኦሮሞ ደም የእኛ ደም ነው!» በማለት ያሰሙት ድምፅ፣ የኦሮሞ ብሔርተኞችን ፍላጎት አሽቀንጥሮ ጥሎ «የዐማራው ደም የኦሮሞ ደም ነው!» በማለት የጥላቻ ግንቡን ደረማምሰውታል።

ዲሞክራት ለመምሰል የዓለም ለጋሽና አበዳሪ መንግሥታትን ያታልልበት የነበረው ጭንብል፣ በ1997 ዓ.ም. ምርጫ የትግሬ-ወያኔን ዕውነተኛ ማንነት ፍንትው አድርጎ ያሳየ በመሆኑ፣ ከምዕራባውያን መንግሥታት ያገኝ የነበረውን ድጋፍ በብዙ እጁ እንዲያጣ ሆኗል። ከሁሉም በላይ የትግሬ-ወያኔ አስተሳሰብ አውራ የነበረው መለስ ዜናዊ በተፈጥሮ ከዚህ ዓለም መለየት፣ ወያኔን አውራ የሌለውን ንብ አድርጎታል። እንደተለመደው ሕዝብ ሊያጭበረብርሩበት የሚያስችል ሀሳብና አሠራር የሚያመነጭ አውራ መሪ የትግሬ-ወያኔ መፍጠር አልቻለም። በመሆኑም ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ የወያኔ ጉዞ የዳበሳ እና የዕውር የድንብሱን ሆኗል።

«እስከ መጨረሻው ከወያኔ ጋር ይቆማል»፣ የሚባለውና የወያኔ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መሠረት የሆነው የትግራይ ሕዝብ በበኩሉ፣ የትግሬ-ወያኔ የአብራኩ ክፋይ የሆነ፣ በስሙ የተደራጀና በዛም አነሰም ትግራይን ከሌሎች ነጥሎ ተጠቃሚ ያደረገ እንደሆነ ቢገነዘብም፣ «የትግሬ-ወያኔ እየሄደበት ያለው መንገድ የኋላ ኋላ የትግራይን ትውልድ ለጥፋት የሚዳርግ ነው» በማለት፣ በትግሬ-ወያኔ የጉዞ አቅጣጫ ላይ ጥያቄ ማንሳት ጀምሯል። ይህም የትግሬ-ወያኔን ትውልድ አመለካከት  በአራት ከፍሎት ይገኛል።

አንደኛው አመለካከት «የትግሬ-ወያኔን የበላይነት አስጠብቆ ለመጓዝ፣ እስከ ዛሬ በኢትዮጵያዊነትና በዐማራው ነገድ ላይ ያራመድነውን በተግባር የታገዘ ፕሮፓጋንዳ አቁመን፣ ኢትዮጵያዊነትን ከዐማራው ምሑራን አመለካከት ነጥቀን፣ ብዙኃኑን የዐማራ ነገድ አስከትለን በኢትዮጵያ አንድነት ጥላ ሥር መጓዝ» የሚለው ነው። ይህን ሀሳብ በማቀንቀን ከሚታወቁት አንዱ ስየ አብርሃ ነው። በስየ ትንታኔ፣ ዐማራ ኢትዮጵያዊነትና አንድነት የሚሉትን ጽንሰ ሀሳቦች ካራመድንለት፣ ባለፉት በተፈጸሙ ችግሮች ወደ ኋላ ሂዶ አይከሰንም፤ ከእኛ ጋር ይቆማል፤ ዐማራው ከእኛ ጋር ከቆመ ደግሞ ሥልጣናችን ነቅናቂ የለውም ብሎ ያምናል።

ሁለተኛው አስተሳሰብ፣ «ኦሮሞና ዐማራው እንዳይገናኙ በማድረግና፣ ልዩነታቸውን በማስፋት፣ እነርሱን በማፋጀት እኛ አስታራቂና ገላጋይ በመሆን የኃይል ሚዛን በመጠበቅ መዝለቅ አለብን» የሚል ነው። የዚህ አመለካከት ተከታይ ከሆኑት መካከል አቶ ገብሩ አሥራት አንዱና ዋናው ነው። ይህ አስተሳሰብ እንደ ተስፋየ ገብረአብ የመሳሰሉትን የሀሰት ድርሳን ደራሾችን በማበረታታት፣ በዐማራውና በኦሮሞው መካከል ምንም ዓይነት የአንድነት ስሜት እንዳይፈጠር ተግቶ መሥራት የሚል ነው። ግቡም ወያኔ ነቅናቂ የሌለው የሥልጣን ባለቤት በማድረግ የመቶ ዓመቱን የቤት ሥራ ዕውን ማድረግ ነው።

ሦስተኛው አስተሳሰብ «ከኢትዮጵያ ማዕከላዊ ሥልጣን በኃይል ወይም በሌላ ዘዴ እስከምንባረር ድረስ፣ የአገሪቱን ሁለንተናዊ ሀብት ወደ ትግራይ በማጓዝ፣ የትግራይን ትውልድ የዕውቀት ባለቤት በማድረግ፣ ከኢትዮጵያ ለቀን ስንወጣ ተከታታይ ጥቃት ሊደርስብን እንዳይችል የሚያደርግ የመከፋፈልና የማዳከም ሥራዎች በመሥራት፣ እኛ ከኤርትራ ጋር በመዋሐድ የትግራይ-ትግርኚን መንግሥት መመሥረት» የሚል ነው። ለዚህ ግብም እንዲረዳ ዛሬ በአገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኤርትራውያን እንዲማሩ በሩ በሠፊው ተከፍቶላቸዋል። የአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ ተቋሞች በግማሽ ትግሬና ኤርትራውያን እንዲመሩ ተደርጓል።

የወያኔ ባለሥልጣኖች በተለያየ ደረጃ የነደፏቸው የትግራይን የበላይነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ሁሉም ስልቶች  ተሞክረው ግን፣ የትግራይን ዘላቂ የበላይነት ለማረጋገጥ ዋስትና የሚሰጡ ሆነው አልተገኙም። ከዋስትናቸው ይልቅ፣ የትግሬ-ወያኔዎች በኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያዊነትና በዐማራ ላይ ያላቸውን ጥላቻ የበለጠ እያጎሉት በመምጣታቸው፣ ለራሳቸው ለወያኔዎች በሥልጣን መቆየት ሳይሆን፣ በሕይዎት ለመቆየት የማይችሉበት ሁኔታ እየተፋጠነ መምጣቱን የሚያሳዩ ሆነዋል። በመሆኑም የወያኔው ትውልድ በአንድ ሰው የበላይነት፣ በአንድ ሰው ቅንጭላት ተመርተው፣ በአንድ ጆሮ ይሰሙት የነበሩትና ያን እንደ አንድ ሠራዊት ተግባራዊ ያደርጉ የነበሩት፣ ከፍ ሲል በተጠቀሱት አመለካከቶች ተከፋፍለው ገመድ ጉተታ ውስጥ ገብተዋል። ይህ ያሳሰባቸው የትግራይ የበላይነት ዓላማ አራማጆች፣ በአካሄድ የገጠማቸውን ልዩነት አስወግደው፣ ሁሉም የሚስማሙበትን የትግራይ የበላይነት ዕውን ለማድረግ አንድ ቁርጠኛ ውሣኔ ላይ ደርሰዋል።

ይህም ውሣኔ ሆን ተብሎ ሾልኮ እንደወጣ አስመስለው፣ በአቶ ዐባይ ፀሐዬ አማካኝነት ለሕዝብ ጆሮ እንዲደርስ የተነገረው ነገር ነው። አቶ አባይ ፀሐዬ የፓርላማውን፣ የካቢኔውንና «የኢሕአዴግን»፣ ከሁሉም በላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ተብየውን ድክመት ዘርዝሮ ከመናገር አልፎ፣ «ችግሩን ለማስወገድ፣ ግለሰብ ወይም ቡድን መወገድ አለበት» ሲል በማን አለብኝነት አውጇል። ይህ በዐባይ ፀሐዬ በኩል የተነገረ፣ በመረሩ ቃሎች የታጀበ ማስፈራሪያ፣ ከማስፈራሪያነት ባሻገር ወያኔ በአቶ ኃይለማርያም ደሣለኝና በካቢኔው ላይ የትግሬ-ወያኔ ወታደራዊ ባለሥልጣኖች መፈንቅለ-አገዛዝ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ነው። ማንም እንደሚያውቀው፣ ዐባይ ፀሐዬ፣ ከመለስ ሞት በኋላ የወያኔ ዐውራ ባለሥልጣን መሆኑ ይታወቃል። እርሱ ያለው ሁሉ ያላንዳች ችግር ተግባራዊ ሲሆን ዐይተናል፣ ሰምተናል። ስለሆነም፣ የጊዜ ጉዳይ እንጂ፣ የኃይለማርያም ደሣለኝ የወግ ዕቃነት አክትሞ፣ ሁሉም ነገር  በትግሬ-ወያኔዎች እጅ እንደሚገባ የዐባይ ፀሐዬ ንግግር ከማሳበቅ አልፎ፣ ሐቁን ይናገራል። የዚህ ዕውን መሆን፣ የትግሬ-ወያኔ ትግራይን በመገንጠል ከኤርትራ ጋር ለሚፈጥረው የትግራይ-ትግርኚ መንግሥት ከወዲሁ መንገድ ጠራጊ ሊሆን እንደሚችል መናገር ነቢይ መሆንን አይጠይቅም።

ይህ ዕውን ሆነ ማለት፣ የተጀመረው ወታደራዊ አገዛዝ ሥር በመስደድ፣ በዐማራው ነገድ ላይ የተከፈተው ሁለገብ ጥቃት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። በመሆኑም ዐማራው የተደገሰለትን የጥፋት መጠን ከወዲሁ አውቆ፣ የተጀመረውን ሕዝባዊ እንቢተኝነት በማጠናከር፣ ለምሣ ወይም ለራት ያሰቡንን ቁርስ በማድረግ፣ የዐማራውን ኅልውና አስጠብቀን የኢትዮጵያን አንድነት ለማረጋገጥ በሁሉም ረገድ ዝግጁ መሆን ይጠብቅብናል።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

የዐማራው  ኅልውና መጠበቅ፣ ለኢትዮጵያ አንድነት መጠበቅ ዋስትና ነው!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

እሑድ ሚያዚያ ፩ ቀን ፪ሺህ ፱ ዓ.ም.

ቅፅ ፭፣ ቁጥር  ፲፫

 

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    April 22, 2017 02:43 am at 2:43 am

    Guys!!! Abbay Tsehaye is an alcoholic person. A person who is addictive with alcohol couldn’t work research in a better way. He had done wrong things several times. Now he is sitting beside the PM office as researcher. Do you think he can do it well??? I doubt!!!! No one listens to me but I point out his mistakes. We are building our country; by criticizing or supporting or avoiding or telling the truth or the most accepting ideas would be making constructive critics to those who are working or sitting on the chairs. These lead us to the right path or road. Abbay Tsehaye is not normal He drinks too much!!! That means he is abnormal!!! But the PM gave him a key post to the guy!!! It is not correct!!! This position should be given to Finfinnee University president. University is a center of research!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule