• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ የፖለቲካ ትግል፤ ወይንስ የተበታተነ ተቃውሞ?

April 7, 2017 05:40 am by Editor Leave a Comment

የያዝነውን እናጢን!

ምን እያደረግን ነው?

የትግሬዎቹ ገዢ ቡድን በሚያደርገው የዕለት ተዕለት አውዳሚ ተግባሩ በመቆጣት፤ ለተቃውሞ መነሳትና፤ ይህን አካል በተግባሩ ወንጅሎ፤ በደሎቹን መዘርዘሩ አንድ ነገር ነው። ይህ ተቃውሞ ነው። በመቃወምና ይህ መደረግ የለበትም ብሎ በመጮህ፤ የተወሰነ ግብን ማስገኘት ይቻላል። ተግባሩ ግን ይቀጥላል። ቢበዛ ቢበዛ፤ በተግባሩ ሂደት ላይ ትንሽ ማስተካከያ ማስከተል ይቻላል። ከዚያ በተረፈ ግን፤ ይህ በመፈጸም ያለ በደል፤ በድጋሚ እንዳይከሰት የሚያቆመው ነገር የለም። ይሄን በማድረግ የሚረካ ሊኖር ይችላል። እንደገና፤ ይህ ተቃውሞ ነው።

በታቃራኒው ደግሞ፤ የተፈጸሙትና በመፈጸም ላይ ያሉት በደሎች፤“መደረግ የለባቸውም!” ብሎ መነሳት ብቻ ሳይሆን፤ “የዚህ ሁሉ ምንጩ፤ አንድ አካል ነው። ይህ አካል መንግሥታዊ ሥልጣኑን ባንድ መንገድ ወይንም በሌላ፤ በጁ ጨብጧል። ይህ አካል ይህን በደል መፈጸሙ፤ ስነ ፍጥረቱ ነው። ከዚያ የተለየ ሌላ ሊያደርግ አይችልም። እናም ይህ አካል መወገድ አለበት!” ማለትና፤ ይህን አካል የሕዝቡ በሆነ አካል ለመተካት መነሳት፤ ሌላ ነው። ይህ ሥርዓትን ለመለወጥ የሚደረግ፤ የፖለቲካ ትግል ነው።

በኒህ ሁለቱ መካከል ያለውን መሠረታዊ ልዩነት ሁላችን እናውቃለን። እስኪ ከዚህ አንጻር የያዝነውን ሂደት፤ ምን እያደረግን እንደሆነ እንመለክት። የእስልምና ተከታዮች ተቃውሞ፣ የአኝዋክን መጨፍጨፍ ተቃውሞ፣ በጉራፈርዳ የአማራዎችን መፈናቀል ተቃውሞ፣ ለሱዳን ደንበር ተቆርሶ መሠጠቱን ተቃውሞ፣ የሀገሪቱን ወደብ አልባ መሆን ተቃውሞ፣ የወልቃይትን አላግባብ ወደ ትግራይ መጠቅለል ተቃውሞ፣ የኦሮሞዎችን በገፍ ወደ እስር ቤት መነዳት ተቃውሞ፣ የኦጋዴኖችን ሆን ብሎ ማስራብ ተቃውሞ፣ የሠራተኞች፣ የመምሀራን፣ የተማሪዎች፣ የሴቶችና የጋዜጠኞች ማኅበራትን መፍረስና የመሪዎቹን መታሰርና መሰደድ ተቃውሞ፣ የወጣቶችን በገፍ መጨፍጨፍ ተቃውሞ፣ መምህራን ያለአግባበ ከሥራቸው ስለተባረሩ ተቃውሞ፣ የሕዝብ ድምጽ በመሰረቁ ተቃውሞ፣ ሌሎችን በማራቆት የትግሬዎችን በተለይ ተጠቃሚነት ተቃውሞ፣ የአማራዎችን በፖለቲካ ፍልስፍናና በመንግስታዊ አስተዳደር፤ አልፎ ተርፎም በዘር አጥፊ ሂደት መጠቃት ተቃውሞ፣ የአማራዎች በገደል መወርወር፣ በየቦታው መገደልና መታሰር፣ እንደ እንሰሳት ሥጋቸው ታርዶ መበላት ተቃውሞ፣ መንግሥታዊ አካላት ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጸድተው፤ በትግሬዎች ብቻ በመሞላት፤ ትግሬዎችና የትግራይ ክልል፤ ከተመጣጣኝ ተገቢ ድርሻቸው በላይ፤ የሀገሪቱን ንብረትና የመበልጸግ ዕድል ማግኘት ተቃውሞ፤ . . . መዘርዘሩ የሚያቆም አይደለም። ይህን ማንም ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያውቀዋል። ታዲያ ይሄ ሁሉ ተቃውሞ ምን ሊያስከትል ይችላል? ይሄን እያደረግን መሆናችንን ማንም የሚክደው አይደለም። ተቃውሞ ነው የያዝነው ብል፤ ተሳስተሃል የሚለኝ ካለ፤ልማር ዝግጁ ነኝ።

“ታዲያ ይሄ አይሰራም ካልክ፤ አንተ ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ የፖለቲካ ትግል ስትል፤ ምን ማለትህ ነው?” የሚል ጠያቂ አይጠፋም። ተገቢ ነው። ትክክለኛ ጥያቄም ነው። መልስ መሥጠትም ግዴታዬ ነው።

ከላይ የተዘረዘሩትን ሁሉ የፈጸመው አንድ የትግሬዎች ገዥ ቡድን ነው። ይህ የትግሬዎች ገዥ ቡድን፤ ከላይ የተዘረዘሩትን በደሎች ሲፈጽም፤ እያንዳንዳቸውን በተናጠልና የማይገናኙ አድርጎ አይደለም። ስለዚህ፤ መገንዘብ የሚያስፈልገው፤ እኒህ ድርጊቶች የአንድ አጥፊ ቡድን፤ መሠረታዊ እምነቶችና፤ የተለያየ ግብ ያላቸው፤ ነገር ግን የተሳሰሩና ወደ አንድ አቅጣጫ የሚያመሩ የፖለቲካ እርምጃዎች ናቸው። አንደኛውን ከሌላኛው የሚያስተሳስረው ገመዱ፤ ሌሎችን በማውደም፣ ታሪክን በመጠምዘዝ፣ አንድ አዲስ ሕልውና ለማምጣት የተሴረ መሆኑና፤ ይህን ሁሉ ደግሞ የትግሬዎቹ ገዥ ክፍል የፈጸማቸው መሆናቸውነው። አንድ ኅብረተሰብ፤ በሂደት ይቀየራል፤ያድጋል። ማደጉም ተገቢ ነው። የሰው ልጅ የሥልጣኔ ግስጋሴ ግድ የሚለው፤ የነበረውን እየፈተሸ፣ በሂደቱ አዲስ ግኝቶችን እያካተተ፤ ለውጦችን እያስከተለ፤ ያለፈው ትውልድ ለወደፊቱ ትውልድ ማስረከቡን ነው። ባለበት የቆመ ኅብረተሰብ፤ የሕልውና ጊዜው ውስን ነው።

ይህ ገዢ ቡድን፤ አሁንም ራሱን፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ ይጠራል። ነገር ግን፤ ራሳቸው ትግሬዎች ገዥ በሆኑበት አገር፤ ትግሬዎቹን ከማንና ከምን ነው ነፃ የሚያወጣቸው? አንድ በሉ። ሕግ ማለት የትግሬዎቹ ገዥዎች የሚፈልጉት ማለት በሆነበት አገር፤ ሕግና ሥርዓት ፍለጋ መውጣት የዋኅነት ነው። ሁለት በሉ። ማንነትሽንም እኔ ነኝ የምነግርሽ፤ የሚል ገዥ ቡድን ባለበት አገር፤ አገር አለኝ ብሎ ማለት አይቻልም። ሶስት በሉ። የምትኖርበትን ቦታ የምሠጥህና የምነጥቅህ እኔ ነኝ ያለን ገዥ፤ ትግሬው ላልሆነ ሁሉ፤ የኔ ገዥ ነው ብሎ ማለት አይቻልም። አራት በሉ። ይሄን ሁሉ በመደመር ነው፤ አስፈላጊ የሚሆነው፤ ሥርዓትን የሚለውጥ የፖለቲካ ትግል ነው፤ የምለው።

የትግሬዎቹ ገዥ ቡድን በሥልጣን ላይ በቆየበት ሃያ አምስት ዓመታት፤ በጣም መሰረታዊ የሆኑና አስቸጋሪ ለውጦችን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሕይወት ላይ ጭኗል። ጊዜ በወሰዱ ቁጥር፤ እኒህ ለውጦች፤ ሥር እያበጁ ተተክለው፤ አዲሱን ትውልድ በክለው፤በሕዝቡ ስነ ልቦና ውስጥ እየተጋገሩ፤ የወደፊቱን መንገድ ውስብስብ እያደረጉት እንደሆነ ግልጽ ነው። እኒህን መቅረፉ የጊዜ ጉዳይ ነው። ላሁን ግን፤ እኒህን ሀቅ ብሎ ወስዶ፤ በኒህ ዙርያ፤ የፖለቲካ ትግሉን ማድረጉ፤ የኛ ኃላፊነት ነው። እንግዲህ ዛሬ ለተያዘው የትግላችን መነሻ የሚሆነው፤ የትናንት ወይንም የነገ የፖለቲካ ሀቅ አይደለም። አሁን ያለንበት የዛሬው የፖለቲካ ሀቅ ነው ገዥያችን። ትግሉ የዛሬ፤ የዛሬውን ትግል ገዥ ደግሞ፤ የዛሬው የፖለቲካ ሀቅ ነው።

እስኪ የዛሬውን የፖለቲካ ሀቅ እንመለከት።

የትግሬዎቹ ገዥ ቡድን ከጠዋቱ ሲነሳ፤ “ትግሬዎች የራሳችን መንግሥት መመሥረት አለብን!” ብሎ ነው። ይህን በተግባር ለማዋል ደግሞ፤ “አማራውን መቃብር ውስጥ ማስገባት አለብኝ!” ብሎ በመርኀ-ግብሩ አስፍሮ ነው። እንግዲህ ይህ የትግሬዎች ቡድን የተነሳው፤ በአማራው መቃብር ላይ፤ የትግሬዎችን ሪፑብሊክ ለመመሥረት ነው። አንዱ ጠፍቶ ሌላው መኖር አለበት! የሚል የፖለቲካ መርኅ አንግቶ ነው። በተግባርም ያደረገው ይሄንኑ ነው። ለአማራዎች፤ ይሄን የትግሬዎች ቡድን፤ “ተው! እሱን አታድርግብን!” ብሎ ልመና ወይንም ለዚህ አካል አቤቱታ ማቅረብ ወይንም ለክስ መነሳት፤ ጹም የማይታሰብ ነው። ስለዚህ፤ አማራዎች ራሳቸውን ከጥፋት ለማደን፤ ተደራጅተው መከላከል አለባቸው። ይሄን ማንም ሊነግራቸው፤ ወይንም አድርጉ! አታድርጉ! ብሎ ሊያዛቸው አይችልም። ይሄን ካላደረጉ፤ ራሳቸው ይጠፋሉ። የወደፊት ትውልድም አይኖራቸውም። ታሪክ ይጠይቃቸዋል!

ይህ የትግሬዎቹ ገዥ ቡድን እስካለ ድረስ፤ አማራው ሕልውናው አደጋ ላይ ነው። ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹ የተለየ የሕልውናውኃላፊነት አለበት። ይሄን ጠቅጥቆ ሊሄድ አይችልም። ስለዚህ አማራው በአማራነቱ ብቻ ተደራጅቶ፤ ራሱን ከመጥፋት ማዳን አለበት። ይህን በማድረግ ላይ ነው። ሀገሩን አልካደም። ሰንደቅ ዓላማውን አልካደም። ነገር ግን፤ በአማራነቱ እንዲደራጅና እንዲታገል፤ ያለንበት የፖለቲካ ሀቅ ግድ ብሎታል። ስለዚህ አማራው በአሁን ሰዓት፤ ያላማራጭ፤ በአማራነቱ መደራጀት አለበት።

ሌሎችስ? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ተገቢም ነው። ሌሎችም በአማራው ደረጃ አይሁን እንጂ፤ ለትግሬዎች መጠቀሚያ ሲባል፤ በተጠቂነት ላይ ያሉ ናቸው። ስለዚህ፤ እነሱም መነሳት ግዴታቸው ነው። አነሳሳቸው እንደ አማራው አይሆንም። ከአማራ ጋር ግን፤ ጎን በጎን መነሳት ይችላሉ፤ አለባቸውም። አማራው አጋራቸው ነው። እነሱም የአማራው አጋር ናቸው። አማራው እንዳልጠፋ ብሎ ሲነሳ፤ ሌሎች አማራው እንዳይጠፋ ብለው ማበሩ፤ ለነገው አንድነታቸው ይረዳቸዋል። በተቃራኒው ደግሞ፤ ከገዥው ትግሬዎች ቡድን ጋር አብረው፤ አማራውን በማጥፋት የተባበሩ አሉ። ይህ የፖለቲካ እርምጃ ነው። ተጠያቂነት አለበት። ወንጀለኛው የትግሬዎችን የበላይነት አቀንቃኙ የትግሬዎች ገዥ ቡድን፤ በርግጥ በነሱም ላይ የሚያደርገው በደል ትክክል ስላልሆነ፤ የዚህን መርዘኛ ገዥ ቡድን ማጥፋት፤ የራሳቸውም ተልዕኮ ነው።እናም መታገላቸው ለነሱም ግዴታቸው ነው።

በጎንደር ከተማ የአማራ ወጣቶች፤ እጆቻቸውን አስተሳስረው፤ “የኦሮሞ ደም የኛ ደም ነው! የእስልምና ተከታዮች መሪዎች የኛ ናቸው!” እያሉ የጮኹ ጊዜ፤ ሌሎችን የትግል አጋር አድርገው መነሳታቸውን አብሳሪ ነበር። የአንድነቱን ሰንደቅ ከማንም በላይ ከፍ አድረገው መያዛቸው ነው። በዚህ የአማራውች ትግል ምንነቱንና አቅጣጫውን መመልከት ይቻላል።

እዚህ ላይ፤ ባንድ በኩል፤ የትግሬዎችን ገዥ ቡድን የማውደም ተልዕኮ አለ። በሌላ በኩል ደግሞ ተከትሎ የሚመጣውን ሥርዓት መለየትና ማወቅ አለ። የሚከተለውን ሥርዓት አስመልክቶ፣ አማራው፤ “በደረሰብኝ የዘር ማጥፋት ሂደት፤ ተጠያቂ አለና፤ ይታሰብልኝ። ለወደፊቱም ይሄን የመሰለ እንዳይደገምብኝ፤ ማስተማመኛ እፈልጋለሁ!” ይላል። አኙዋኩ ደግሞ ተቀርRቢ ጉዳይ ይዟል። ኦሮሞውም ሆነ ኦጋዴኑ ከዚህ አይርቅም። አዎ! መገንዘብ ያለብን፤ አሁን ያለው ሀቅ ይህ መሆኑንነው። ይሄን አደባብሰን፤ “የአንድነት ትግል ብቻ ነው ማካሄድ ያለብንና፤ በአንድነት ወደፊት እንሂድ!” ብንል፤ በመካከላችን መጠምዘዣዎችን ማበጀትና ርስ በርሳችን ሳንተማመን መጓዝ ስለሚሆን፤ የትግሬዎቹን ገዥ ቡድን ዕድሜ ከማርዘም በስተቀር፤ የምናደርገው ሌላ ፋይዳ የለም።

በዚህ በፖለቲካው ትግል፤ ሁለቱ መሠረታዊ የሆኑት ጉዳዮች በፊት ለፊት ቀርበው፤ በታጋዩ ክፍል መካከል፤ ስምምነት መገኘት አለበት። ለየብቻ የምናደርገው ግልቢያ፤ ተቃውሞ ከማቅረብ የተለየ አይደለም። በርግጥ ለየብቻ ትግሉ ለየብቻ መጥፋት እንደሆነ ማንም አይስተውም። እናም፤ ትግሉን በአንድነት ለማድረግ፤ የአንድነት መሠረቱንና ሂደቱን ከወዲሁ መነጋገርና፤ አንድ ቦታ ላይ መድረሱ፤ ቅድሚያ ቦታ ይይዛል።

አንድነት ስል፤ በሥልጣን ላይ ያለውን የትግሬዎች ገዥ ቡድን ለማስወገድና፤ ከድሉ በኋላ በሚመሠረተው መንግሥት፤ አብሮነት እንዲከተል፤ ትግሉን አሁን በአንድነት ማካሄድ የሚል ግንዛቤ ይዤ ነው።

የአንድነቱን ትግል ለማድረግስ፤ መነጋገር ያለባቸው እነማን ናቸው? ይህ ደግሞ ራሱን የቻለ ጉዳይ ነው። በኔ እምነት፤ መጀመሪያ አማራው በአንድ ላይ ሆኖ፤ አንድ አማራውን የሚወክልና የአማራው ትግል ተጠሪ አካል ማበጀት አለበት። ይህ አጠያያቂ አይደለም። እየተደረገም ነው። በርግጥ በምመኘው ፍጥነት እየሄደ አይደለም። አማራው የያዘውን ትግል ምንነት፣ የትግሉን ዕሴቶች፣ የትግሉን ግብ፣ የትግሉን የጉዞ መስመር፣ ከሌሎች ጋር ሊኖረው የሚፈልገውን የትብብርና የአብሮነት መሰላል፤ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት።

በዚህ ቅንብሩ፤ ሌሎችን ወደ ትግል መጋበዝ ይጠበቅበታል። ሌሎች ደግሞ፤ ቀድመው የተደራጁ እንዳሉ ግልጽ ነው። ያልተደራጅ ወይንም በተለያየ የተቃውሞ ግቢ ያሉት ደግሞ፤ ወደ ፖለቲካ ትግል ስብስብ ተዋቅረው፤ በዚህ ትግል በባለቤትነት መሰለፍ መቻል አለባቸው። በትግሉ አብረው በመሰለፍ፤ የነገ ሕልውናቸውን አስተማማኝ ማድረግ ይችላሉ። አሁንም ይህ በገዥነት ያለው የትግሬዎቹ ቡድን ቢወድም፤ “እኛ ጠበቃ ሆነን ትግሬዎችን እናድናለን!” በማለት፤ መሰሪ የሆኑ የዚሁ አጥፊ የትግሬዎቹ ገዥ ቡድን መስራቾች በሆኑትበግደይ ዘርዓፅዮንና በአረጋዊ በርሄ የሚመራ፤ ትግሬዎችን ብቻ ያካተተ የትግሬዎች ጠበቃ ድርጅት አቋቁመው፤ በታጋዩ ሕዝብ መካከል፤ አለሁ እያሉ ያወናብዳሉ።ተመልከቱ፤ “አሁንም የትግራይ ሕዝብ ተበድሏልና፤ ከናንተ ብዙ እንፈልጋለን!” ነው የሚሉን። እኒህን መንጥረን እናውጣቸው፤ ወይንም በኋላ የሠሩትን ሠርተው፤ በጎን አጥንታችን ውስጥ የሰላ ሰይፋቸውን ሰክተው ወደ ጓዶቻቸው ሲሄዱ፤ ምርር ብለን፤ ከዱን ብለን እናልቅስ።

እንግዲህ የአንድነት ውይይቱ፤ አማራው ባንድ ገጽ፤ የኦሮሞ ወጣቶች ደግሞ በአንድ ገጽ፤ ሌሎች የተደራጁ የተጨቆኑ ወገኖች በአንድ ገጽ እያሉ፤ ወደ አንድ ስብስብ በመምጣት፤ ማድረግ ይቻላል። ይህ ብቻ አይደለም መንገዱ። የተለያየ መንገድ ሊኖር ይቻላል። እኔ የማቀርበው መፍትሔ ብዬ ያየሁትን ነው። አማራው አንድ ደረጃ ላይ ደርሷል። አኙዋኩም ሆነ ኦጋዴኑ፣ ሲዳማውም ሆነ አፋሩ፣ የተደራጀውን የአማራ ክፍል ቢቀርብና ቢያነጋግር፤ አጋር ማራቱ ነው። በአሁኑ ሰዓት፤ የኢትዮጵያ ድርጅት ብሎ ማንም ቢዘላብድ፤ ግአንዘብ ከመሰብሰብና ታጋልኩ እያለ ከመፎከር ሌላ፤ አንዲት ቅንጣት እርምጃ ወደፊት አይሄድም። ወሳኙ፤ የአማራ ወጣቶችና፤ አሁን በቦታው ያሉ ሌሎች ታጋይ ወጣቶች ናቸው። እኒህን የሉም ብሎ ወይንም በኔ ሥር ሆናችሁ ታጋሉ ብሎ የሚነሳ፤ በጀርባው የያዘውን ማወቁ ይጠቅማል።

አንዱዓለም ተፈራ  – የእስከመቼ አዘጋጅ

(eske.meche@yahoo.com)

አርብ፣ መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓመተ ምህረት


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule