• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የእግዚአብሔር መልእክት በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል

April 21, 2017 04:01 am by Editor 3 Comments

“ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደአለላ ብትሆን እንደአመዳይ ትጸዳለች እንደደምም ብትቀላ እንደባዘቶ ትጠራለች፤ እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እንቢ ብትሉ ግን ብታምጹም ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናገሮአልና፡፡” ኢሳ. 1/18.

በእግዚአብሔር ለሚያምን ሰው፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜም፣ ለዘለዓለም ሙሉና የማይወዳደሩት ኃይል እንዳለው ለሚያምን ሰው፣ ለእግዚአብሔር ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም አሁን መሆኑን ለሚያምን ሰው “ኑና እንዋቀስ” (በእንግሊዝኛው “come now let us reason together”) ማለት ለእግዚአብሔር ምን ያህል መውረድ እንደሆነ መገንዘብ የሚዳግት አይመስለኝም፤ የእንግሊዝኛው ትንሽ ሻል ያለ መስሎ “ኑና እንከራከር” የሚል ቢሆንም ከመጨረሻው የላይኛው ዳኛ ጋር መከራከር የሚችለው ማን ነው? እግዚአብሔር ነው፤ ትልቁ ነገር እሱ ፈቀደ፤ “እንዋቀስ” አለ!

መዋቀስ ዓላማ አለው፤ ለመግባባት ነው፤ ለመስማማት ነው፤ ለፍቅር ነው፤ ለሰላም ነው፤ ለመረዳዳት ነው፤ እንደመለስ ዜናዊ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ማለት ሲቻለው፤ ኑና እንዋቀስ የሚል ኃያል አምላክ ለእኛ ምን ያስተምረናል?

የእግዚአብሔር ቃል ኑና እንማከር በማለት አልቆመም፤ እሺ ብትሉ፣ ለእኔም ብትታዘዙ፣ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እንቢ ብትሉ ግን ብታምጹም ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና፡፡

እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ትሕትናንና መወያየትን፣ መወቃቀስና መስማማትን ለማስተማር በነቢዩ በኢሳይያስ በኩል መልእክቱን አስተላለፈ፤ ዛሬ ይህ መልእክት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ይመስለኛል፤ ዛሬ ይህ የእግዚአብሔር መልእክት ለወያኔ ይመስለኛል፤ ዛሬ ይህ መልእክት ለወያኔና ለአጋሮቻቸው ይመስለኛል፡፡
በኢሳይያስ በኩል የመጣው መልእክት ግልጽ ነው፤ ምርጫው “የምድርን በረከት መብላት” ወይም በሰይፍ መበላት ነው፡፡

የምድር በረከትን በሙሉ ሁሉ በጄ ሁሉ በደጄ ላለ ጥጋብ ላይ ነውና ይበልጥ አይታየውም፤ በዕብሪት ላበጠም ስለሰይፍ ቢወራ አያስፈራውም፡፡

እግዚአብሔር ‹‹እንዋቀስ›› ካለ እኛ፣ ገዢዎቻችንም ለሰላም ሲሉ ለፍቅር ሲሉ፣ ለልጆቸው ሲሉ፣ ለአገር ሲሉ “እንዋቀስ” ቢሉ ያስከብራቸዋል እንጂ አያዋርዳቸውም፤ ታሪካቸውን ያሳምርላቸዋል እንጂ አያጎድፍባቸውም፤ መንፈሳዊ ወኔ ያላቸው፣ ልበ-ሙሉ ጀግኖች ያደርጋቸዋል እንጂ ፈሪ አያደርጋቸውም፤ አርቀው የሚያስተውሉ ብልሆች ያደርጋቸዋል እንጂ ጊዜያዊ ጮሌነት አይሆንባቸውም፡፡

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ግንቦት/ 2009

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions, Social Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Tadesse says

    April 22, 2017 12:57 pm at 12:57 pm

    Great professor.God bless You,talak sew.

    Reply
  2. Dereje says

    April 25, 2017 10:42 pm at 10:42 pm

    Hey Anta Mesfin,
    Nayi balina mist tseb meselika hagerina?

    Reply
  3. Eunetu Yeneger says

    May 4, 2017 03:01 am at 3:01 am

    ፕሮፌሰር!!!

    ለምን ከኦርቶዶክስ፣ ከካቶሊክ፣ ከፕሮቴስታንት፣ ከሙስሊምና ከቤተ እስራኤል ቤተ እምነቶች በተውጣጡ ሀገር ወዳድ ሽማግሌ የሃይማኖት መሪዎች በኩል ከኢሕአዴግና ተቃዋሚች ጋር ከልብ መወቃቀሱ አይጀመርም????

    በዚህ የምንስማማ ከሆነ እነዚህ የተባሉትን ሰዎች መጠቆሙን እንጀምር ከዚያም ለስብሰባው የሚሆነውን በኢሜል እየተነጋገርን እናዘጋጅ???
    የእኔ ኢሜል: eunethiowt@gmail.com ነውና እስቲ ፕሮፌሰር የነቢዩ ኢሳያስን መጽሐፍ ጠቅሰው ኑ እንዋቀስ ያሉትን ተግባራዊ ለማድረግ ሁላችንም ለምን ድርሻችንን ለመወጣት አንሞክርም?ረጅሙ ጉዞ በአንድ ርምጃ አይደል የሚጀመረው?

    እግዜር ያስበን
    ለሥራም ያነሳሳን

    እውነቱ ይነገር ነኝ
    ካለሁበት

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am
  • የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው December 7, 2020 12:38 am
  • የቆሰሉ ወታደሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጎበኙ December 6, 2020 11:41 pm
  • “ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ December 2, 2020 12:24 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule