
ጋዜጣዊ መግለጫ
ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ ተደናቂ የሆነ የፍትሕ አገልግሎት በመፈጸማቸው ከዚህ ቀጥሎ ስማቸው ለተዘረዘሩት ሽልማት ያበረከተ መሆኑን ይገልጻል፤
- ቀሲስ/ዶር. ምክረ-ሥላሴ ገብረ አማኑኤል፤በፋሺሽት ኢጣልያ የኢትዮጵያ ወረራ ዘመን ስለነበረው የቫቲካን ሚና ግንዛቤ እንዲገኝ በደረሱት መጽሐፋቸው አማካኝነት ስላበረከቱት አስተዋጽኦ፤
- ሚር. ኢያን ካምፕቤል፤ ፋሺሽቶች በኢትዮጵያ ላይ ስለ ፈጸሙዋቸው የጦር ወንጀሎች በደረሱዋቸው መጽሐፎች ስላበረከቱት አስተዋጽኦ፤
- ሚር. ቫሌሪዮ ቺሪያቺ፤ ፋሺሽት ኢጣልያኖች፤ በኢትዮጵያ ላይ ስለ ፈጸሙት የጦር ወንጀልና ባሁኑ ወቅት በመኪያሔድ ላይ ስላለው የፍትሕ ጥረት ግንዛቤ እንዲገኝ ፊልም በማዘጋጀት ስላበረከተቱት አስተዋጽኦ፤
- አቶ ከባዱ በላቸው፤ ፋሺሽት ኢጣልያኖች፤ በቫቲካን የትብብር ድጋፍ፤ በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸሙት የጦር ወንጀል ለሚያስፈልገው የፍትሕ ጥረት ሕዝብን በማስተባበርና በማነቃቃት ስላበረከቱት አስተዋጽኦ።
ማሕበራችን ለተሸላሚዎቹ መልካም ምኞቱን እየገለጸ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ ለውድ ሐገራችን፤ ለኢትዮጵያ፤ ስለሚያስፈልገው ተመሳሳይ የፍትሕ አገልግሎት እንዲጥሩ ያሳስባል።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ።
AWARD FOR DISTINGUISHED SERVICE TO JUSTICE
PRESS RELEASE
This is to announce that the Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause has granted its award for distinguished service to justice to the following individuals:
- Rev/Dr. Mikre-SellassieGebre-Amanuel for his contribution, through his book, to the knowledge on the Vatican’s role during Fascist Italy’s invasion of Ethiopia;
- Ian Campbell for his contribution, through his books, to the knowledge on the Fascist war crimes in Ethiopia;
- Valerio Ciriaci for his contribution, through his documentary film, to the knowledge on the Fascist war crimes in Ethiopia and the current quest for justice;
- Kebadu Belachew for his contribution to the quest of justice,through his tireless public coordination and dissemination effort, with regard to the Fascist Italian war crimes on Ethiopia with the complicit support of the Vatican.
Our Alliance hereby expresses its compliments to the award winners and also calls on all Ethiopians and friends of Ethiopia to strive for a similar contribution to service for justice on behalf of our beloved country, Ethiopia.
God bless Ethiopia!
ዓለምአቀፍሕብረትለፍትሕ – የኢትዮጵያጉዳይ
4002 Blacksmith Drive, Garland, TX 75044; Tel: (214)703 9022
www.globalallianceforethiopia.org; E-mail: info@globalallianceforethiopia.com
Leave a Reply