
ላለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት በዘረኛው የትግሬ ነፃ አውጪ የአገዛዝ መዳፍ ሥር የታፈነውን ሕዝባችንን ወደ ነፃነትና የዴሞክራሲ ምዕራፍ ለማሸጋገር የጋራ ትግል ለማድረግ ሲሞከር ቆይቷል።
ሆኖም በእነዚህ ዘመናት ውስጥ የተፈጠሩት የፖለቲካ ኃይሎች ትብብር፣ ቅንጅት፣ ኅብረት እና ውህደት አንዱም ከዳር ሳይደርስ እንዲሁ ሲሰበሰብና ሲበተን ከርሟል። እንደ አባባልም እንደ መታወሻም “ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ” የሚለው የዶ/ር መረራ ጉዲና መፈክር አንዱም ገቢራዊ ሳይሆን አብዛኞቹ የፖለቲካ ተቋማት በአገዛዙ ጫናና በራሳቸው ደካማ አደረጃጀት ህልውናቸው እየጠፋ ለሐገር የሚተርፍና ትውልድ የሚረከበው አንድም አግባቢ የጋራ ማዕከል ሳይመሰረት በኪሳራ የታጀቡ ዓመታትን አሳልፈናል።
ትብብር የጉልበት ምንጭ ነው።ትብብር ድልን ማቅረቢያ ዘለቄታዊና ሠላማዊ ሽግግርን ማሳለጫ መሳርያ ነው።ትብብር ከሚከሰረው የሚያተረፈው የሚበዛበት የሕዝብን አብሮነት ማጠናከርያ፣ልዩነትን ማጥበቢያና የቅራኔ ማርገቢያ ጠቃሚ ዓላማ ነው።
አበው“ድር ቢያብር አንበሣ ያስር ” እንዲሉ የተበታተነን ትግል አቀናጅቶ ለውጤት በማብቃት የትብብር አስፈላጊነት ላይ ማንም ጥያቄ ባይኖረውም ይህንን ጠቃሚ መሳርያ ተጠቅሞና ኃይልን አጠናክሮ ጠላትን ለመርታት የሚያስፈልገውን ሰጥቶ የመቀበል፣የመቻቻልና የሰለጠነ ፖለቲካዊ ባህል ባለመኖሩ በተደጋጋሚ በሕዝብ ተነሳሽነት የተገኙ ወሳኝ ድሎች የተባበረ አመራር በመጥፋቱ ለቅልበሳ ሲዳረጉ ቆይተዋል።
ባለፈው ሰሞን የተለያዩ ወገኖች በተለያየ ጽንፍ ቆመው በአወዳሽነትና በነቃፊነት በየመገናኛ ዘዴዎቹ ሲናጩ የከረሙበት የአድዋ ድል በዓል ከአሸናፊነት የስነ ልቦና ውርስነቱና ፤ የክብር ልዕልናው ባሻገር ለዓለም ጭቁን ሕዝቦች ተምሣሌት የሆነ የመተባበር ውጤታማነት ማሳያ መሆኑን “ የራስ ወርቅ አያደምቅ” እንዲሉ እኛ ባለቤቶቹ ልንጠቀምበት ባንችልም በደቡብ አፍሪካ ፀረ-አፓርታይድ ትግል እና በሠሜን አሜሪካ የቆዳ ቀለም {ጭቆናን} ለመሰባበር ያስቻለ ተምሣሌት ለመሆኑ የትግሉ ባለቤቶች የመሰከሩትን ማየት ብቻ በቂ ይሆን ነበር።
ይህን የመሰለ ታሪክ አባቶቻችን ዘር፣ ቀለም፣ፆታና የብሔር ማንነት ሳይገድባቸው በሐገር ውስጥ የነበራቸውን ልዩነት አቻችለው በተባበረ ኃይል የአውሮፓ ወራሪን አሳፍረው በመመለስ ያቆዩልንን ሐገርና ዝንተ ዓለም በዓለም ጭቁን ሕዝቦች ታሪክ እንዳበራ የሚኖረውን ታሪክ ልንመራበት ቀርቶ ልንማርበት አለመቻላችን እጅጉን ያሳዝናል።
ከዚህ የተነሳ ሊያቀራርበን የሚችለውን ትተን ዘመን የሻረው አሮጌ ታሪክ ላይ ተቸክሎ፤ ማላዘን ተቋማዊና ሕብረተሰባዊ ባህል ወደ መሆን የደረሰ እስኪመስል ድረስ በሺህ ዘመናት ውስጥ ተገንብተው የኖሩ በጎና ተወራራሽ የጋራም የተናጥልም፤ የድል፣ የአብሮነትና የመቻቻል ታሪካችን ላይ ትኩረት ሰጥተን ያንን እንደማዳበር ከመቶ አምስት ዕጅ በማይሞላው የንትርክ አጀንዳ ላይ ኃይላችንን በማዋላችን ለሕዝባዊ ውድቀትና ለሃገራዊ ኋላ ቀርነት ተዳርገን ቆይተናል።
ሕወሃት ባሰማራቸው ቅጥረኞ፤ ባዶ ዝና ያናወዛቸው ዋልጌዎ፤ በጽንፈኛ ብሄረተኞች አቀጣጣይነት በሶሻል ሚዲያው በኩል የሚራገበው አሳፋሪ፤ አደገኛና ሗላቀር የጥላቻ ቅስቀሳ ተጠናክሮ ከቀጠለ ሕብረት መፍጠር አይደለም የሰላም ተስፋም እይኖርም። ከዚህም በላይ በሃገር ውስጥ ከእለት ወደ እለት እየተባባሰ የመጣው ድህነትና የአገዛዝ ጫና ሕዝባችንን ተስፋ ቆርጦ ወደ ለየለት አመጽ ገብቶ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ ከሆነ በሗላ ለሕዝቡም ሆነ ለሃገሪቷ ልንደርስ የምንችልበት እድል በቀላሉ ስለማይኖር፤ ቀኑ ሳይመሽ ባለን እድል መጠቀሙ ለሁሉም የሚበጅ ይሆናል (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
እኔን ግን ከሁሉ ከሁሉ የገረመኝ አቶ ኃይለገብርኤል አያሌው ይህችን ፎቶ የለጣፋት ምን መልዕክት ለማስተላለፍ ፈልጎ እንደሆ ነው። ትልቅ ሰው ነኝ ለማለት ነው? ትልቅ ስለሆንኩ የኔ ውሎ ከፕ/ሮች ጋር ነው ለማለት ነው? በጣም የሚገርም ብቻ ነው።
ለማንኛም ኮሜንት ልሰጥ ወደተነሳሁበት ዋናው ቁም ነግር ልግባ።
አቶ ኃይለገብርኤል አያሌው አንተ ተስፋ የምትለው “የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ ” የሚባለውና ግንቦት 7 በበላይነት ሞተር ሆኖ የሚያሽከረከረው ንቅናቄ ለአማራው ምን እንደሆነ አማራው ጠንቅቆ ያውቃል። አንት ግን ስልጣንና በየመድርኩ እየተገኘህ ስምህንና ፎቶ መንሳትን ብቻ ስለምትወድና ስለተሸፈነብህ ግንቦት 7 ስለ አማራው ያለውን አመለካከት አታውቅም። ብታውቀም ስለተሸፈነብህ አይታይህም።
አንት አማራው ተሎ ተደራጅቶ አንተ ተስፋ የምትለውን “የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ” እንዲቀላቀል ትላላል። ግንቦት 7 ግን አማራው ተሎ ተደራጅቶ እንኳን ድርጅቱን እንዲቀላልቀል ቀርቶ እራሱን ብቻውን ቆም እንዲታግል አይፈልጉም። ለዚህ ማስረጃ የሚሆነው የሚከተለውን የከንቦት 7 ከፍተኛ አመራ የሆነው አቶ አበበ ቦጋ የተናገረውን ማዳመጥ ብቻ በቂ ነው። ሙሉን ማዳመጥ ጥሩ ነው። እኔ ግን እንድታዳምጠው የምፈልገውና አንተ ለጻፍከው የአማራ መደርጃት ለሚለው ጽሁፍ ግንቦት 7 ያለውን መለካከት ብቻ እጠቅሳለሁ።
https://www.youtube.com/watch?v=eI7ZkWy3gyo
ከቪድዮው ከ1:21፡00 (ከ1 ሰዓት 21 ደቂቃ ጀምሮ አዳምጥ)
የኢትዮትዮብ ጠያቂ ጋዜጠኛ ዮሴፍ፤ ግን እኮ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በስብሰባው ላይ ተጠይቀው በአሁን ሰዓት በአማራ ስም የተደራጁ ብዝህ ድርጅቶች ስላሉ ሁሉንም መጥራት ስላቻልን ወደፊት ለብቻ ሰርተን አንደ የተጠናከረ የአማራ ድርጅት ወደ “ሐገራዊ ንቅናቄ” እናመጣለን ብለው መስልስ ሰጥተዋል። ብሎ ሲጥይቀው
መልስ የሚሰጠው የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አቶ አበበ ቦጋለ፤ እኔ ሻለቃ ዳዊትን ብሆን ኖሮ ይህ አይነት ነገር ትክክል አይደለም ብየ ነበር የምናገረ። {አማራ ተደራጅቶ ወደ ንቅናቄ ይምጣ የሚለውን ነገር አልደግፍም ማለቱ ነው። ገባህ???}
ስለዚህ አቶ ኃይለገብርኤል አያሌው ባጭሩ አንተ አማራው ተደርጅቶ ብትፈልግም የድርጅቱ አለቃና ሞተር ግንቦት 7 አይፈቅድም ማለት ነው።
ከዚህ ላይ ግልጽ ላደርግልህ የምፈልገው ግን አማራው ተደራጅቶ የራሱ ስራ እየሰራ ነው። የተደራጀው ግን ከማንም ጋር ተቀላቅየ ስራ እስራለሁ ብሎ ሳይሆን በወያኔ እየደርሰበት ያለውን ጥቃት ለመመክት መደራጀት ስላለበትና መመከትም ስለምችል ነው። አማራ ከሆንህ አማራ ምን ማድረግ እንደሚችል ታውቃለህ።