- አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት “የእምነት አባቶች” የክህደቱ ተዋንያን ናቸው
“… ይህ ዜና በተገለበ መልኩ መሰማት ከጀመረ ሰነባብቷል። ዜናው በደባና በተቀነባበረ ሤራ የሚካሄድ ቢሆንም ዜናውን በገደምዳሜ የሚያሰራጩት ክፍሎች ስለ ጉዳዩ የተጨነቁ አይመስሉም። ቅርብ ሆኜ እንደምከታተለው ይህ ዜና አደገኛና ኢትዮጵያን ዳግም ክህደት የሚያከናንባት፤ እንደ አገር የመኖር ኅልውናዋን አደጋ ላይ የሚጥል ነው። ይህንን የሚያውቁ የሃይማኖት አባት መስቀል ተሸክመው የዚህ ሸፍጥ ተዋንያንና አስፈጻሚ መሆናቸው ያሳፍራል። ጉዳዩ በአጭሩ ህወሓት ከሻዕቢያ ጋር በኢትዮጵያ ስም ሊታረቅ ዓለምአቀፍ ዕውቅና የተሰጠው ድርድር መጀመሩ ነው…”
ይህ አጭር ሃሳብ ለጎልጉል ከተላከ የውስጥ አዋቂ ደብዳቤ የተቀነጨበ ነው። ደብዳቤውን የላኩት ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ በኢህአዴግ ውስጥ ከፍተኛ የሚባል ኃላፊነት ያላቸውና ኃይለማርያም ደሳለኝ በሚመራው የህወሓት ድቃይ ፓርቲ ውስጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ የደቡብ ክልል ተወላጅ ናቸው።
ሃሳቡ ሙሉውን የሚያተኩረው “ኤርትራና ኢትዮጵያን ለማስማማት” በሚል የተጀመረው የሃይማኖት መሪዎች የሰላም ድርድር አንድ መቶ ሺህ የሚጠጋ አገር ወዳድ ሕዝብ ያለቀበትን ባድመንና አካባቢውን ለኤርትራ ማስረከብን ዋና ዓላማ ያደረገ ነው። “ቁማሩ” እንደ ደብዳቤው “ከሰላሙ በኋላ ሁሉም ወደ ነበረበት ይመለሳል (ትግራይና ኤርትራ አንድ “አገር” ሲሆኑ ባድመም የሁለቱም ትሆናለች)። ኤፈርት በከፍተኛ ደረጃ ያከማቸውን ሃብት ኤርትራ ላይ ኢንቨስት በማድረግ ኢኮኖሚውን በመቆጣጠር ኤርትራን “ማልማት” ይሆናል። ይህንን ዕቅድ እውን ለማድረግ ባድመን አስመልክቶ ለሚነሳው ጥያቄ ወያኔ አይከራከርም። በዚህም ስልት ሻዕቢያ በአሸናፊነት ድርድሩን ይቀበላል”።
የጎልጉል መረጃ ምንጭ እንደሚሉት ደግሞ ህወሓት አሁን ኢትዮጵያ ላይ የሚጫወትበት የፖለቲካ ካርድ ስላለቀና ስለተቃጠለበት ከሻዕቢያ ጋር አስቸኳይ ዕርቅ ማድረግ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ዕርቁን እውን ለማድረግ ጉዳዩን ወደ ኃያላን አገሮች ወስዶታል። በባርነት የሚያገለግላቸው ኃያላን የሚባሉት አገሮች ለዚሁ ተግባር ደፋ ቀና እያሉ ነው።
የምስራቅ አፍሪቃን የፖለቲካ ቀጣና እንደ ምክንያት በመንተራስ አሜሪካ ሁለቱን ተገንጣይ የወንበዴ ቡድኖች (ወያኔና ሻዕቢያን) እንድታስታርቅ ህወሓት በወስዋሾቹ አማካይነት ወደ ፍጻሜው ተዳርሰዋል። ለዚህም ይመስላል የአንዳንድ ተቃዋሚ ኃይሎች ስም ከኤርትራ ጋር እየተነሳ ያለው።
ኸርማን ኮሆንም ቢሆኑ ፈራ ተባ እያሉ ሲጠቃቅሱ የነበረውን ሁለቱን “አገራት” የማስታረቅ ጉዳይ አንገብጋቢ መሆኑንን በይፋ አመላክተዋል። እኚሁ ለወንበዴው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን በገጸበረከትነት ያስረከቡ ሰው፤ በሃሳባቸው ምን ያህል እንደሚገፉበት ባይታወቅም በመርህ ደረጃ ሁለቱን አካላት ለማስታረቅ ከየአቅጣጫው አረንጓዴ መብራቶች መኖራቸውን የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ያረጋግጣሉ። በዓለምአቀፍ ደረጃ የሃይማኖት መሪ የሚባሉትም ሰዎች የዚሁ ፖለቲካ አካል ናቸው።
በተለይ ህወሓት የዓለምአብያተ ክርስቲያናት ምክርቤትን ጠጋ በማለት አጀንዳውን ካስጀመረ ቆይቷል። ም/ቤቱ በአገራት መካከል ሰላም ለማስፈን የሚጥርና ተገቢውንም ሁሉ የሚያደርግ በመሆኑ ጉዳዩን በዚሁ መልኩ መመልከቱ የሚያስጠረጥረው አይደለም። ሆኖም በኢትዮጵያና ኤርትራ ስም ህወሓት ከበስተጀርባው ስምምነቱንና ዕርቁን በትግራይና በኤርትራ መካከል ለማድረግ ደፋ ቀና እያለ እንደሆነ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። በምክርቤቱ ያሉቱ ከዓላማው ቅዱስነት አኳያ የህወሓት መሠሪነት ብዙም ትኩረት የሰጡት አይመስልም።
በአገር ውስጥ ያለው ሁኔታ እየተወሳሰበና መፍትሔው እየጠፋ ባለበት ባሁኑ ወቅት ህወሓት በማኒፌስቶው ላይ እንዳሰፈረው ትግራይን ሪፑብሊክ የማድረግ ዕቅዱ ከታሰበው ጊዜ የቀደመበት ይመስላል። ለኢትዮጵያ የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ሰጥተናል እያለ ሲፎክር የነበረው የህወሓት ፈጣሪና ጌታ ሻዕቢያም “ተስፋው” ግቡን አልመታለትም። ከዚያ አልፎ በኢትዮጵያ አንጡራ ሃብትና በህወሓት ተላላኪነት ኤርትራን ሲንጋፖር የማድረግ ሕልሙ ከህወሓት ጋር በከፈተው ጦርነት ቅዠት ሆኖ ቀርቷል። ከነዚህ ሁሉ ጉዳዮች በመነሳት ሁለቱ የወንበዴ ቡድኖች ስምምነት የማድረግ ፍላጎታቸው ባሁኑ ሰዓት ቢነሳሳ የሚገርም እንዳልሆነ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
ከበረሃ ጀምሮ ችግር ያልተለየው የወያኔና የሻዕቢያ ወዳጅነት ተበጠሰ ሲባል እየተቀጠለ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ የደረሰው በህወሓት ውስጥ ባለው መስመር የለቀቀ የኤርትራ ተቆርቋሪነት እንደሆነ ይታወቃል። የመለስ ዜናዊ ሬሣ ወደ ከርሰመቃብር በወረደበት ጊዜ አዲሱ ለገሰ በስንብት ስነ ስርዓቱ ላይ ስለ መለስ ባነበበው ሰፊ ጽሁፍ የኤርትራን ጉዳይ አንስቶ መለስን እንዲህ በማለት አወድሶት ነበር፤ “መለስ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት መካሄድ የለበትም” የሚል የጸና እምነት እንደነበረው ከገለጸ በኋላ “በድምጽ ብልጫ ተሸንፎ የገባበትን ጦርነት በብቃት መርቷል” በማለት የኤርትራና የመለስን ወዳጅነት ስንብቱ ላይም ህዝብ ልብ እንዲል መናገሩ ይታወሳል።
በባድመ ጉዳይ ከኢሳያስ ጋር ያልተፈለገ የከረረ ግጭት ውስጥ የገባው የመለስ ህወሓት፤ ኤርትራን ለዓለምአቀፉ ኅብረተሰብ በማሳጣት ለማዕቀብና ስቃይ ሲዳርጋት መቆየቱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። በሌላው በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ የኤርትራ ተቃዋሚ ድርጅቶችን አሰባስቦ ለኤርትራ የሽግግር መንግሥትና ሕገመንግሥት መለስ ሳይሞት አዘጋጅቷል። ይህንን የመለስ ሤራ ሻዕቢያና ኢሳያስ ጠንቅቀው የሚያውቁት ነው። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን የዝምድና ጉዳይ በማይበጠስ ገመድ ስላስተሳሰራቸው ነበር እነ ስብሃት ነጋ፤ ኤርትራ ጦርነት ቢነሳባት ከህዝቧ ይልቅ እኛ ቀድመን እንዋጋለን በማለት በአደባባይ ሲናገሩ የኖሩት።
“ኤርትራ የትግራይ ናት”፤ “ትልቅ ነበርን ትልቅ እንሆናለን” – ህወሃት በሚል ርዕስ የዛሬ ሁለት ዓመት ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ባወጣው ዘገባ ላይ ስለዚህ የህወሓትና የስብሃት አቋም ይህንን ማለቱ አይዘነጋም፤
“ስለ ኤርትራ ከተወላጆቹ በበለጠ በልበሙሉነትና ባለቤትነት መንፈስ በገሃድ የሚሟገተው የቀድሞው የህወሓት መሪና የነፍስ አባት ስብሃት ነጋ በወቅቱ ይመራው ስለነበረው የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ተቋም ሲናገር፤ “የሃገሪቱን ገፅታ ለመገንባት የኢትዮ-ኤርትራን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማድረስ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ” ነው በማለት ኢህአዴግ በፓርላማ ስም ለሚመራው የምክርቤት ኮሚቴ መናገሩን ሰኔ 5፣2007 የታተመው የኢቲቪ (ኢብኮ) ዘግቧል። የውጭ መከላከያና ደህንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮቴውም የስብሃትን ዘገባ ካደመጠ በኋላ “ኢንስቲትዩቱ የኢትዮ-ኤርትራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል” ማሳሰቡ ጨምሮ ገልጾዋል።”
ከዚህ ሁሉ የዓመታት የበስተጀርባ ሥራ በኋላ ነበር በኢትዮጵያ ስም በህወሓትና በሻዕቢያ መካከል ሊደረግ የታሰበው የሰሞኑ የዕርቅ ሃሳብ ይፋ የሆነው። በኅዳር ወር (2010/2017) መግቢያ ላይ ሪፖርተር እንደዘገበው የምሥራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባዔዎች ማኅበር (አሜሰያ)/Association of Member Episcopal Conferences in Eastern Africa (AMECEA)/፣ ዕርቁን እውን ለማድረግ ከሁለቱም ክፍሎች ይሁንታ አግኝቷል። ከዚህ አስቀድሞ (በየካቲት 18፤ 2007ዓም ወይም 25 February 2015 በታተመው የሪፖርተር ዘገባ ላይ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ካርዲናል ሆነው በቫቲካን የተሾሙት “ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦችን በማቀራረብ በሁለቱ አገሮች መካከል ዘላቂ ሰላምና ወንድማማችነት ዳግም ለመመለስ እንዲሠሩ” ከህወሓት ጥሪ እንደቀረበላቸው ይታወሳል። በዚህ የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት በተደረገ ጥሪ መሠረት ነበር የሰሞኑ የህወሓትና የሻዕቢያ ዕርቅ በኢትዮጵያ ሽፋን መካሄድ የጀመረው።
እገዛታለሁ የሚላትን አገር ፖለቲካዊ ፋይዳ አመናምኖ የገደለው መለስ ዜናዊ በዕቅዱ አለመሳካት “እብድ፣ ያበደ ውሻ፣ ተናካሽ ውሻ፣ አጉራ ዘለል፣ ዱርዬ …” እያለ ኢሳያስ አፈወርቅ ላይ ሲሳለቅ ቢቆይም ዛሬ ህወሓት በኢትዮጵያ ስም የሚጠየቀውን በማድረግ፣ ዳግም ድንበር ሰጥቶ (ባድመን) ለመታረቅ በመወሰኑ የ“ሃይማኖት መሪዎች” የሚባሉት ጉዳዩን ከዳር ለማድረስ እንደማይቸገሩ የዜናው ምንጮች ያስረዳሉ።
በኢትዮጵያ ህዝብ ሲረግፍ፣ ሲታሰርና፣ ሲገረፍ፣ አገሪቱ ወደ ጎሣ ጦርነት ስታመራ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ሲፈናቀሉ ከጥቂት ታይታዊና ልማታዊ እንቅስቃሴ በስተቀር ዝምታን የመረጡት የሃይማኖት መሪዎች ከሁሉም በላይ ያሳሰባቸው የሻእቢያና የህወሓት ዳግም መወዳጀት ነው። የሃይማኖት አባቶች ለእነ መረራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባ፣ አንዷለም አራጌ፣ ኦልባና ሌሊሣ፣ አህመዲን ጀበል፣ እስክንድር ነጋ እና ሥፍር ቁጥር ለሌላቸው የኢትዮጵያ ልጆች ከእስር መፈታት ግልጽ ጥያቄ ማቅረብ ጀምረው ካልተፈቱ ምግብ አንቀምስም በማለት የረሃብ አድማ እስከመምታት ሊደርሱ በተገባቸው ነበር። የሃይማኖት ስብዕናቸው ልዕልና ያጣ በመሆኑ የታዘዙትን የሚፈጽሙ “መንፈሳዊ ካድሬዎች” ሆነዋል በማለት አስተያየት ሰጪዎች ሲማርሩ በየጊዜው ይሰማል።
ካድሬዎች የወረሩት የሃይማኖት ተቋም መስቀል ይዞ ወደ አደገኛ የክህደት ጠረጴዛ ሲያመራ ሌሎች አካላት ዝም ማለታቸው በርካቶችን ያሳዘነ ጉዳይ ሆኗል። ይህንን ከላይ የተቀመጠውን ሃሳብ የላኩልን ተቆርቋሪ እንዳሉት የአገር ዕርቅ ከሆነ ጉዳዩን ህወሓት በምሥጢር ሊይዘው አይገባም። በሕዝብ መካከል ጸብ የሌለ በመሆኑ ገለልተኛ ወገኖች ዕርቁን ሊተገብሩት ግድ ነው። ዕርቁ በኢትዮጵያ ስም ከሆነ በዓለምዓቀፉ የእምነት ተቋማት ውስጥ ያሉት የህወሓት ሰዎች ከማስማማቱ ስራ ሊታቀቡ ይገባል። ለዕርቅ የቀረበው እጅ መንሻ ከህወሓት ብቸኛ መዘውር ወጥቶ ቢያንስ በኢህአዴግ ደረጃ ሊመከርበት ይገባል። ይህንን ሲያልፍ ደግሞ ጉዳዩ የሕዝብ እንደመሆኑ ሕዝብ በገሃድ ሊያውቀውና ሊመክርበት የግድ ይላል።
መቀሌ ላይ ሲሰዳደብ የከረመው የህወሓት ወንበዴዎች ቡድን የሚፈልጋቸውን ከመራረጠ በኋላ መግለጫ አውጥቶ ነበር። ለሕዝብ ይፋ ያደረገው ያቋም መግለጫ ላይ ከኤርትራ ጋር ሊያካሂድ ስላሰበው ስምምነትም ይሁን ግጭት ምንም ትንፍሽ ያለው ነገር አለመኖሩ አሁን በኢትዮጵያ ስም በህወሓትና ሻዕቢያ መካከል እየተሠራ ላለው “እኩይ ዕርቅ” አስረጅ ሆኖ ቀርቧል።
በማሕበር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ /ማገብት/ አዋላጅነት በሻዕቢያ የተደቀለው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር /ህወሃት/ በነጻ አውጪ ስም አገር መግዛት በጀመረበት ጊዜ ለእርሱ የበረሃ ራዕይ የሚለውን፤ ለኢትዮጵያ ግን ትውልድ የሚጨርስ ነቀርሳ የሆነውን ችግር ተከለ። ራሱን መሪ አድርጎ በሾመው መለስ ለማኝነት በዓለም እስካሁን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የተባበሩት መንግሥታት ፊት ቀርቦ አገር እንድትገነጠል በይፋ ለመነ፤ ሰዎችን እንደ እህል በዘር ጆኒያ ሰፈረ፤ በሰላም አብሮ የኖረን ሕዝብ እርስበርሱ አጋጨ፣ ነዋሪዎችን ከመኖሪያቸው አፈናቀለ፤ መሬት ነጠቀ፤ ዜጎችን አዋረደ፣ አሰረ፣ ገረፈ፣ አሰቃየ፣ ገደለ፣ ጨፈጨፈ፣ … በመላው ኢትዮጵያ የማይጠፋ እሳት ለኮሰ፤ አሁን እሳቱ ራሱን የሚበላበት ሰዓት ላይ ደረሰ! ስለዚህ የዘረፈውን ይዞ፣ ሱዳንና ኤርትራን ወዳጅ አድርጎ፣ አገር መስርቶ “በሰላም” ወደሚኖርበት የ“ዕርቅ” አቅጣጫ እየተጓዘ ነው። “የሚያሳዝነው” ይላሉ የጎልጉል መረጃ አቅራቢ “ለዚህ እኩይ ዕርቅ አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት የሃይማኖት አባቶች ሽፋን መሆናቸው ነው።”
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
Simir says
ጎልጉሎች የደርግ ቦሃቃ ሁሉ
ጎልጉሎች የደርግ ቦሃቃ ሁሉ
You guys are the dumbest creatures on the face of the earth and you need to be quarantined because you are infected with hate and twisted ideology. I bet G7 is probably your # 1 enemy not Shabia or woyane.
Scientific_Mind says
የሃይማኖት አባቶች ስራ የተጣላን ማስታረቅ ነው::ማንም ይሁን ማን ሰዉ ሲታወቅ የሚያመዉ ሰይጣን ቢቻ ነዉ::ኦፒዲኦ እና አንደም ባህር ዳር ባደባባይ ታርቀዉ ሲጨፍሩ እነሱንም በኢትዮጵያ ስም ንግድ ጀመሩ ማለት ይቻላል በእናንተ አገላለፅ ::ፕሮፌሰር ኤፍሬም አይዛቅ መለስ እያለ የጀመረዉ ግልፅ ጉዳይ ነዉ እናንተ እንደምትቀባጥሩት በሚስጢር የተጀመረ አይደለም::
mynameis says
Simir,
Buhaqa eko ye-injer lit yiyizal. People like you we call them Hodam as they can only think about their kerse. What is your hangup on G7? As much as tplf and other dummy parties are free to operate why not G7? Woyanei dyas are numbered – it isa case of when not if until, like Zenawi, it turns into ashes – it is digging its own grave as seen in the marathon meeting recently. It is literally surviving by the skin of its teeth.
Simir says
mynameis…,
I think you are misquoting my words. I am for G7. The writer of this article and the likes of him never get tired of preaching the identical nature of Shabia and Woyane…, Well that was history. they used to be but not any more. That was what prompted me to write such a comment. Based on your comment here. You sound like you are against G7. What is your point by calling all parties dummy? After all Woyane ….or tplf to use your own word can only operate in Ethiopia not in Eritrea. You don’t think G7 is dummy. Do you ?
Editor says
Simir
You said “…The writer of this article …” This is a news report and the writer is ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
And we do not have any problem with ግንቦት 7 (why should we have a beef in the first place?) and this news report is not written having ግንቦት 7 in mind. The reportage is clear and direct to the point: TPLF and EPLF are working to unite under the disguise of unity between Ethiopia and Eritrea. Got that?
ያልተጻፈ አታንብብ – we don’t let our readers to read between lines or to second guess. We have the media and we will say it as it is when needed.
ተግባባን?
Editor
Simir says
Dear Editor..,
Still your reportage is debatable but thank you anyway.
Editor says
Debatable it may be, we are open for any rejoinder.
Editor
messi says
Thank u !
Sam says
ጎልጉሎች ጥሩ ትንተና ነው፡፡
በቅርቡ የነ አባይ ወልዱ ከህውዋት የስልጣን ማማ ላይ መውረድ የአናንተን ትንተና ያጠናክረዋል፡፡ የእነ አባይ ቡድን ጸረ ኤርትራ አቋም የነበረው ሲሆን አሁን የመጡት ግን የኤርትራ ደጋፌዎች ናቸው፡፡ ህዝቡ ያልገባው ስብሰባቸው ረጅም ጊዜ ወስዶ ሲያጨቃጭቃቸው፤ ሲያባላቸው የሰነበተው ጉዳይ ከሙስና ጋር በተያያዘ፤ አንተ ሌባ፤ አንቺ ሌባ ሲባባሉ የከረሙ መስሎታል (ለሌብነቱማ ሁሉም አንድ ናቸው) የሌብነት ጥል ቢሆን ኖሮ ስብሰባው በአንድ ሳምንት ውስጥ ያልቅ ነበር፡፡ የስብሰባው ዋና አጨቃጫቂ አጀንዳ የነበረው የኤርትራው ጉዳይ ነበር፡፡ በአጀንዳው ላይ የታሪክ ተጠያቂ መሆን አንፈልግም፤ እንዴትስ ብለን የትግራይን ህዝብ እናሳምነዋለን የሚለው ቡድን በዚህ በመጨረሻው ስብሰባቸው ላይ ከጫወታው የወጣ ይመስለኛል፡፡ (የኤርትራ ጉዳይ ለየዋሆቹ ትግራዮች ሁልጊዜ አጨቃጫቂ ነው፡፡ በማንኛውም ባለስልጣኖች የተገኙበት የትግራይ ሰዎች ስብሰባ ላይ፤ ህዝቡና ባለስልጣኑ ተጣልተው ነው የሚለያዩት)፡፡
ሌላው ለዚህ ሀሳብ ማጠናከርያ የደብረጽዮን ወደ ትግራይ መመደብ ነው፡፡ ልብ በሉ እነዚህ እርኩሶች የኢትዮጵያን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የሚያታልሉት የትግራይንም ህዝብ ነው፡፡ የትግራይን ህዝብ ስለሚፈሩት በዘዴ ለማሳመንና ውስጥ ውስጡን ብዙ ነገር መሰራት ስላለበት ነው ደብረጽዮን ትግራይ ውስጥ የሚያስፈልገው፡፡
የትግራይም ሆንክ የኢትዮጵያ ህዝብ ንቃ! ጉድ ይጠብቅሀል
ምስጢራቸውን የሚያውቀው እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ
Bemikru says
ዶር ብርሃኑ ወያኔን ባልተናነሰ የኢትዮጵያ ጠንቅ ነው። ደብረጽዮን ራቅ መደረጉ ለምንድነው? ዶር ደብረጽዮንን መቀሌ የላኩት ከፕሬዚደንትነት ያነሱት ኣባይ ወልዱ ዝም እንደማይል ስለሚያውቁ ነው። ስብሃት ነጋ በሴራ ነው የኖረው። የወንድሙ የገብረ እግዚኣብሔር ነጋ ልጅ ፈትለወርቅ የደብረጽዮን ምክትል ሆና ኣዲስ ኣበባ ቀርታለች። ኣውራምባታይምስ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ጻድቃን ከኤርትራ ጋር እርቅ ለመደራደር ኣንድ ሆቴል ውስጥ ስብሰባ ጀምረዋል ብሎ ነበር፤ ኣሁን ግን ዜናውን ኣንስቶታል።
yoni says
you idoit G7 and thous of u living abroad try to distabilizing our great county with hate and ethinic separations go suck you fucking dick you always say weyane tigre. who is prime minister ,foreing minister the president with are the highst power b/c the fact is all ethiopia are ruling the country all have power. ethiopia needs a person who figth for his people not like you who sell his own country for the sake of green card (political dependecyor assaylom) norrow minded go clean the dirty ass of white people.