• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የመለስ ሞትና የኤርትራ ዝምታ

September 13, 2012 02:06 pm by Editor 3 Comments

የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር የአቶ መለስን ሞት አስመልክቶ ሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራም (ሻዕቢያ) ሆነ መሪው አቶ ኢሳይያስ የሚያስተዳድሩዋቸው መገናኛዎች ዝምታን መምረጣቸው እያነጋገረ መሆኑ ተገለጸ። በአገር ውስጥና በውጪ ለሚኖሩ የተለያዩ ኅብረተሰብ ክፍሎች መጠይቅ በመበተን ባሰባሰብነው መረጃ የኤርትራ ዝምታ የአቶ መለሰንና የኤርትራን ቁርኝት አደባባይ ያወጣ እንደሆነ የሚስማሙት ቁጥር አብላጫ ነው።

“አቶ መለስ ቀድሞውንም ለኤርትራና ለኤርትራ ተወላጆች ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ የነበሩ መሪ መሆናቸውን ለምንረዳ የሻእቢያ ዝምታ አያስገርምም” የሚሉት አስተያየት ሰጪ “አቶ መለስ ለኤርትራ ያሳዩትን ከልብ የመነጨ ፍቅርና የተቆርቋሪነት ስሜት ለሚመሩት ህዝብና አገር አሳይተው አያውቁም። የኤርትራ ተወላጆችም ሆኑ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ሃዘን ቢቀመጡ ከኢትዮጵያዊያን በላይ አግባብነት አላቸው” ብለዋል።

አቶ አዲሱ ለገሰ በአስከሬን ስንብት ስነ ስርዓት ላይ ስለ አቶ መለስ ባነበቡት ሰፊ ጽሁፍ የኤርትራን ጉዳይ አንስተው መለስን አወድሰው ነበር። “መለስ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት መካሄድ የለበትም” የሚል የጸና እምነት እንደነበራቸው ከገለጹ በኋላ “በድምጽ ብልጫ ተሸንፎ የገባበትን ጦርነት በብቃት መርቷል” በማለት የኤርትራና የመለስን ወዳጅነት ስንብቱ ላይም ህዝብ ልብ እንዲል አሳስበዋል።

ከበረሃ ጀምሮ ችግር ያልተለየው የወያኔና የሻዕቢያ ወዳጅነት ተበጠሰ ሲባል እየተቀጠለ እዚህ የደረሰው በአቶ መለስ ወገንተኛነት እንደሆነ የሚጠቁሙ የቀድሞ የህወሓት አባል የኤርትራን ዝምታ ከዚሁ ከቆየው የመለስ ውለታ አንፃር እንደሆነ አመልክተው የአቶ ኢሳይያስ አገዛዝ ፍርሃት ውስጥ እንዳለ ይጠቁማሉ። በአቶ መለስ ትዕዛዝ በቅርቡ ሁለት ከፍተኛ የተባለ ጥቃት ሲሰነዘረበት እጁን አጣጥፎ የተቀመጠው ሻዕቢያ ኢትዮጵያ ላይ የሚከተለው አቋሙ ዝምታ እንዲመርጥ እንደሚያስገድደው የቀድሞ የህወሃት ሰው ያስረዳሉ።

በበረሃው ትግል ወቅት “ሻዕቢያ ከደርግ በላይ ቀንደኛና ቁልፍ ጠላታችን ነው፤ ከሻዕቢያ ጋር ያለን ግንኙነት ሊበጠስ ይገባል” በሚል የከረረ አለመግባባት ተፈጥሮ ሶስት ወራት የፈጀ ስብሰባ መደረጉን ያወሱት እኚሁ የቀድሞ የህወሃት ሰው “አሁን የቀረው የህወሃት አመራር የሻዕቢያን ጉዳይ በጥብቅ ስለሚመለከተውና በመካከላቸው የሃሳብ ልዩነት ስለሌለ ሻዕቢያን የሚያስታምመው የለም፤ በዚህም ድንጋጤ ውስጥ ነው” ብለዋል።

በዓለምአቀፍ ጫና ሰበብ በ1991 ያከተመለትን የአቶ ኢሳይያስ አገዛዝ እንዲያንሰራራ ያደረጉት አቶ መለስ በባድመ ጦርነት ያለ ምንም ፋይዳ ለሞቱት የኢትዮጵያ ልጆች ደም ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ እግረ መንገዳቸውን የጠቆሙት ሌላ አስተያየት ሰጪ አቶ መለስ በኤርትራ ላይ ይከተሉት የነበረው የተንሸዋረረ ፖሊሲ ኢትዮጵያዊያንን እጅግ ከፍተኛ የሞራልና የቁስ ዋጋ አስከፍሏቸዋል። የዚያኑ ያህል ሻዕቢያ በአገራችንና በኢኮኖሚው ላይ እንዲፈነጭና ልዩ ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጎታል። ሃዘኔታው የሚመነጨው በበርካታ ምክንያቶች ነው።

ፕሬዚዳንት ኢሳይያስን “አጉራ ዘለል፣ ያበደ ውሻ፣ ጋጠወጥ፣ ዱርዬ…” በማለት እሳቸው በፈጠሩት ፓርላማ፣ በአፍሪካና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች መሳቂያና መሳለቂያ አደርገው ከዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ ያሽቀነጠሩዋቸው መለስ ሲሞቱ ኤርትራ በአገር ደረጃ ዲፕሎማት በመላክ ለቅሶ መድረሷ እንዳስገረማቸው አብዛኞች ተናግረዋል።

መለስ የኤርትራን ተቃዋሚዎች በማደራጀት ኢሳያስን ጥለው የሚፈልጉትን መንግስት ለማቋቋም በግልፅ እንደሚሰሩ ሻዕቢያ ጠንቅቆ ያውቃል፣ ኢሳያስ ሞቱ በተባለበት ወቅት ስልጣን ለመረከብ ኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመውና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቅስቀሳ ሰዓት ተፈቅዶለት ኢሳያስን እያወገዘ ያለው የተቃዋሚዎች ህብረት የመለስን ይሁንታ አግኝቶ መሆኑ ሚስጥር አይደለም። ኢሳያስ የተደገሰላቸውን ድግስ ቢያውቁም በመለስ ህልፈት የተፈጠረውን ቀዳዳ ለመጠቀም አለመሞከራቸው ለኢትዮጵያዊን ተቃዋሚዎች የማንቂያ ደወል ስለሆነ አጋጣሚው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚጋብዝ ነው። በጽሁፍ ከአውስትራሊያ መልዕክታቸውን ያደረሱን አስተያየት ሰጪ በጥቅሉ ኤርትራ የመሸጉ ተቃዋሚዎችን ከማሳሰብ በስተቀር በስም አልጠሯቸውም።

በአደራዳሪነት ሽምግልና ሰበብ የኦነግን ሰራዊት በሰላም ስምምነት አግባብቶ የተለያዩ የማሰልጠኛ ካምፖች በመክተት በወያኔ ሰራዊት እንዲከበቡና ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ያደረገው ሻዕቢያ መሆኑን ያመለከቱት አስተያየት ሰጪ፣  በተመሳሳይ መሰረታቸውን ኤርትራ አድርገው ለዓመታት የሚንቀሳቀሱ ወገኖች ሂደቱን ሊመረመሩት እንደሚገባ ጠቁመዋል። ሻዕቢያ የተረጋጋችና አንድነቷን የጠበቀች ኢትዮጵያ እንድትኖር ከእውነተኛ ኢትዮጵያኖች ጋር ሊሰራ ይችላል? የሚለውን መሰረታዊ ጉዳይ እነዚሁ ክፍሎች በጥንቃቄ በማገናዘብ እንዲገመግሙ መክረዋል። ኤርትራን ማመን ከቶውን እንደማይቻል አሳስበዋል። ከኤርትራ መውጣት የተከለከሉ የነጻነት ታጋዮች መኖራቸውንም አመልክተዋል።በአደራዳሪነት ሽምግልና ሰበብ የኦነግን ሰራዊት በሰላም ስምምነት አግባብቶ የተለያዩ የማሰልጠኛ ካምፖች በመክተት በወያኔ ሰራዊት እንዲከበቡና ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ያደረገው ሻዕቢያ መሆኑን ያመለከቱት አስተያየት ሰጪ፣  በተመሳሳይ መሰረታቸውን ኤርትራ አድርገው ለዓመታት የሚንቀሳቀሱ ወገኖች ሂደቱን ሊመረመሩት እንደሚገባ ጠቁመዋል። ሻዕቢያ የተረጋጋችና አንድነቷን የጠበቀች ኢትዮጵያ እንድትኖር ከእውነተኛ ኢትዮጵያኖች ጋር ሊሰራ ይችላል? የሚለውን መሰረታዊ ጉዳይ እነዚሁ ክፍሎች በጥንቃቄ በማገናዘብ እንዲገመግሙ መክረዋል። ኤርትራን ማመን ከቶውን እንደማይቻል አሳስበዋል። ከኤርትራ መውጣት የተከለከሉ የነጻነት ታጋዮች መኖራቸውንም አመልክተዋል።

በሌላ ተመሳሳይ ዜና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ገዳዮች መወያያ መድረክ ድረገጽ ላይ “አስገራሚው መግለጫ እንደሚከተለው ተተርጉሟል” በሚል በህይወት የሌሉት የአቶ መለስ ወላጅ እናት ወ/ሮ አለማሽ ገብረልዑል የስጋ ዘመዶች ከኤርትራ በአይጋ ፎረም አማካይነት የላኩትን የሃዘን መግለጫ አስነብቧል። ትርጉሙን ያቀናበሩት ኢየሩሳሌም አርአያ መሆናቸውን አስታውቋል። “የሃዘን ማፅናኛ መግለጫ” ደብዳቤው እንደሚከተለው ይነበባል።

“በኤርትራ ምድር እና በመላው አለም የምንገኝ የደጃዝማች ገብረልኡል ተስፋማርያም እና የአቶ ካህሱ መላ ቤተሰቦች የሆንን፤ በሞት በተለየን በምናፈቅረው፣ ልጃችን እና ወንድማችን፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማን መሪር ሃዘን እየገለጽን፤ ለዘመዶቹ ለቤተሰቡ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጽናቱን ይስጠን እንላለን። አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ እና አፍሪካ ታሪክ ረሃብን ከሰፊው ህዝብ ለመንቀል፣ የታመመው እንዲፈወስ፣ መሃይሙ እንዲማር፣ መብቱ የተገሰሰው ፍትህ እና ነጻነት እንዲከበርለት እና እንዲረጋገጥለት፣ ለአንድ ቀን እና ሰአት ሳያርፍ እና እፎይ ሳይል፣ ተወዳዳሪ የሌለው ዘላለማዊ የታሪክ ሃውልት ማኖሩ፣ ለህዝቡ እና ለቤተሰቡ የማይረሳ የድል ችቦ፣ የማይናድ ቅርስ፣ የማይጠፋ መብራት፣ ተጠብቆ የሚኖር ዘላለማዊ ክብር፣ … ትቶ በማለፉ፣ የተሰማንን ትልቅ ኩራት እየገለጽን፤ በተለይ ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ ህዝብ በተለይም ደግሞ ለመላው ቤተሰቡ የጀመረውን ስራ ሳይጨርስ፣ ገና በ57 አመት እድሜው ማለፉ ሃዘናችንን ጥልቅ መሪር እና በጣም ከባድ ሸክም አድርጎታል። አቶ መለስ ዜናዊ እድሜውን ሙሉ ሲያከናውነው የቆየው ፣መልካም እና የተቀደሰ ተግባራት ባይኖር ያለምንም ማጋነን እና አድሎ የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት አሁን ላለበት ደረጃ ሊበቃ እንደማይችል በማመን፣ እርሱ የጀመረው ወደር የሌለው የአገር እና ህዝብ ግንባታ አጠናክረው እንደሚገፉበት እና እንደሚያጎለብቱት ያለንን እምነት እና ተስፋ በዚህ አጋጣሚ እንገልጻለን። ለአቶ መለስ ደግሞ ያንን ሁሉ የህዝብ እና ቤተሰቡ ጸሎት እና መሪር ሃዘን ፈጣሪ አምላክ ሰምቶለት በመንግስተ ሰማያት ያኑረው ።”

በሌላም በኩል  ነሐሴ 20/2004 የታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ በፖለቲካ አምዱ “ሳያርፍ ያረፈ መሪ በሚል ርዕስ” “ በአቶ መለስ ሞት የፈነጠዙ ኢትዮጵያዊያን ብቻም አይደሉም፡፡ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በኤርትራ ውስጥ ሲሰቃዩ፣ ኤርትራውያን በኢትዮጵያ የተለየ መብት በመስጠት፣ ኤርትራን በማስገንጠልና ኢትዮጵያን ወደብን በማሳጣት የሚተቹት አቶ መለስ መሞታቸውን ተከትሎ፣ በውጭ እየጨፈሩና መንግሥት ለመመሥረት እየተሯሯጡ ካሉት ጋር ኤርትራዊያን እንዳሉበት መስማቱ የበለጠ አሳዛኝ አድርጎታል፡፡ ምንጮች እንደሚጠቁሙት፣ በኢትዮጵያ መንግሥት አማካይነት ወደ ውጭ አገሮች የወጡ ኤርትራዊያን ወጣቶች የዚሁ እንቅስቃሴ አካል መሆናቸው እየተሰማ ነው፡፡ ብስራት የተባለ የአዲስ አበባ ነዋሪ ወጣት፣ መንግሥት አሁንም በኤርትራና በኤርትራዊያን ላይ የሚከተለውን ፖሊሲ እንደገና እንዲገመግም የሚጠይቀው ይህንን ከሰማ ወዲህ ነው” ሲል አስነብቧል። ከሪፖርተር ወገናዊነት አንጻር በመለስ ሞት ማግስት ይህ መጻፉ መለስ ሲጫኑት የኖረው ህወሃት/ኢህአዴግ ኤርትራ ላይ የሚከተለውን ፖሊሲ ይቀይራል የሚሉትን ክፍሎች ሃሳብ ያጠናክራል። በዚሁ መሰረት የኤርትራ ዝምታ ይህንኑ የፖሊሲ ለውጥ ፍርሃቻ ሳይሆን እንደማይቀር ግምታቸውን ሪፖርቱ አስፍቶታል። ይህ ዜና አስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በአቶ መለስ ህልፈት ዙሪያ ኤርትራ በገሃድ የተነፈሰችው ባሉታዊ መልኩ የሚጠቀስ ዜና የለም።

(በጎልጉል ሪፖርተር)

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Feeko says

    September 12, 2012 05:40 am at 5:40 am

    It is true that Eritrea lost a dedicated son who has been leading Ethiopia for over two decades doing ground work for the break up of Ethiopia into several small ethnic states so no powerful entity remains that can reclaim Assab, etc and challenge Eritrea for ever. No wonder Eritreans and their govt are in secret mourning while we Ethiopians are relieved of bottomless hopelessness and insecurity as a state. But God came to the rescue of Ethiopia even though its people are still in deep sleep. However, there are still a bunch of Eritreans (who pose as Tigray) still left in EPRDF govt. We still have long long way to go.
    Wake up people. Wake up the people of Tigray from deep sleep. Wake up the people of Ethiopia from half death. Wake up oppositions working with Eritrean govt from excessive naivety and madness.
    Thanks

    Reply
  2. gelanew kirar says

    September 12, 2012 06:39 am at 6:39 am

    Congratulations!
    What a great news! Welcome to the world of media!
    I also like to say “የሚወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል” b/s I at least scanned the articles and it is a very professional start! Specially I have read this one and is very balanced with a lots of truth in it.

    Reply
  3. Tesfay says

    September 15, 2012 06:21 pm at 6:21 pm

    Very well said. Eritreans have so many reasons to mourn for the death of PM Melles. My mother used to say ” until you go blind you don’t realize how your eyes are important ”. This is to say that I don’t know if Eritreans knew the late PM was concerned for Eritrea and Eritreans as much as he concerned for Ethiopia if not more, but I’m sure that today Isayas and his people are worried to their death, and they now know how important the PM was for Eritrea. They know after Melles there’s no one in Ethiopia who holds umbrella over Eritrea like Melles did.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule