• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የበሰበሱት” ህወሃት እና ሻዕቢያ

September 16, 2013 08:13 am by Editor 6 Comments

አምባገነነኖች ከሚታወቁበት አንዱና ዋንኛ መለያቸው መካከል ሁለተኛ ሰው አለማዘጋጀታቸው ነው። አቶ መለስ በድንገት ሲስፈነጠሩ በውል የታየው አስከሬን ደብቆ ድብብቆሽም የዚሁ ውጤት ነው። ኢሳያስ ከስልጣን ቢወገዱ ማን ይተካቸዋል? የሚለው ችግርም ጎልቶ የሚታየው ከዚሁ የአምባገነኖች በሽታ አንጻር ነው።

ግጭትና ችግር ከመፈጠሩ በፊት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ደወል የሚያንጫርረው ዓለምአቀፉ የግጭት ቡድን (International Crisis Group) ፍርሃቻም ከዚሁ የመነጨ ይመስላል። በኤርትራ ህዝቡ በቃኝ ወደ ማለቱ ደረጃ መቃረቡን የሚጠቁመው የዘንድሮው ዓመት ሪፖርት ኤርትራ በቅርቡ መንግስት አልባ የመሆን እድሏ ሰፊ እንደሆነ ያወሳል። በቅርቡ “የሚከሽፉ መንግስታት” በሚል ስማቸው ከተዘረዘሩት ውስጥ አገሮች መካከል ኢትዮጵያም ተመልክታለች።

እኩል ወደ ስልጣን የመጡት ሻዕቢያና ወያኔ ደረጃቸው ቢለያይም ሊድኑ በማይችሉበት ደረጃ መበስበሳቸው በገሃድ የሚታይ እውነት እንደሆነ አብዛኞች ይስማማሉ። ከበሰበሱበት ባህርና ችግር ለመውጣት አግባብ ያለውን መንገድ ከመከተል ውጪ አንዱ ሌላውን ቀድሞ ለማጥፋት እሽቅድድም መርጠዋል። የዚሁ የእሽቅድድማቸው መድረሻ መሰረት ደግሞ አንዱ ለሌላው ተቃዋሚ ምርኩዝና አጋር የመሆንና አንዱ በሌላው መንኮታኮት የግል ትርፍን አስጠብቆ ለመዝናናት እንጂ ህዝብን ማዕከል ያደረገ አይደለም።

ኤርትራ “በነጻ” ምድሯ ላይ “አቅፋና ደግፋ” የያዘቻቸው የኢህአዴግ ተቃዋሚዎች የሚታይ ውጤት ባለማስመዝገባቸው ተግባር ለሚናፍቁ ወገኖች ጉዳዩ “ከበሰበሰ ባህር” አይነት ሆኖባቸው ዓመታት ተቆጥረዋል። ሰሞኑንን ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የግንቦት7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይፋ ያደረጉት መረጃ አዲስ የውይይት አጀንዳ ዘርግቷል።

በኤርትራ መንግስት በኩል የሚደረገው ድጋፍ “ባለ አራትና አምስት ኮከብ ሆቴል ውስጥ ተቀምጦ የመታገል ያህል ነው” በማለትandargachew ያሞካሹት አቶ አንዳርጋቸው “ታይቶ የማይታወቅ፣ ከሚገባው በላይ የበዛ” ሲሉ የገለጹት የኤርትራ ድጋፍ አስቀድሞም ቢሆን ውጤት ማስመዝገብ ያልቻለው ኤርትራ በከተሙ ተቃዋሚዎች ችግር እንጂ በኤርትራ መንግስት እንዳልሆነ በቅርብ ሆነው ማየትና መረዳታቸውን በመግለጽ ምስክርነት ሰጥተዋል።

ይህ መረጃ ከተሰራጨ በኋላ ከኢህአዴግ ወገን ሁለት አንኳር ጉዳዮች ተሰምተዋል። በኤርትራ ላይ መከላከልን መሰረት ያደረገው ፖሊሲ “ተመጣጣኝ ርምጃ መውሰድ” በሚል በመቀየሩ ኢህአዴግ ባልተጠበቀ ወቅትና ጊዜ አስቀድሞ ጥቃት ለመሰንዘር እንደሚችል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለኤርትራ ያዘጋጀላትን አዲስ የአስተዳደር ቅርጽ ተግባራዊ የሚያደርጉ ድርጅቶችን ወደ ግንባር መግፋት የሚሉት የመጀመሪያዎቹ ሲሆኑ ሁለተኛው ግን ከወትሮው ለየት ያለ ሆኖ ተገኝቷል።

አዲስ ራዕይ የሚባለው የኢህአዴግ ልሳን ይፋ እንዳደረገው ወደ ጎረቤት አገራትም ሆነ ሌሎች አካባቢዎች የሚሰደዱ ዜጎች በተቃዋሚ ወገን ለውትድርና እየተመለመሉ እንደሆነና ይህ ሁኔታ በዝምታ ከታየ ስርዓቱ ችግር ሊገጥመው እንደሚችል አመላክቷል። ከዚህም ጋር ተያያዥነት ባለው መልኩ ሌሎች ወገኖች ግብጽ እጇን የዘረጋችላቸው ክፍሎች ስለመኖራቸው መረጃዎች እንዳሉ ለማሳበቅ ሲሞክሩ ሰንብተዋል። ከዚህ አንጻር ቀደም ሲል ከነበሩት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በተለየ መልኩ ኢህአዴግ ስጋት ውስጥ ስለመሆኑ ይሰማል።

ከላይ የቀረቡት ሁለቱ አንኳር ጉዳዮች መላምት ሳይሆኑ በውል የተቀመጡ እውነታዎች ናቸው። ኢህአዴግ አደራጅቷቸው የስደት ፓርላማ የመሰረቱ የኤርትራ ተቃዋሚዎች ዝግጅታቸውን ተያይዘውታል። እነዚህ የብሔር ድርጅቶች የሚበዙበት ጥምረት ህወሃት እንደሚያስበው ወደ ስልጣን ከደረሱ ኤርትራን ቢያንስ በስምንት “ብሔር ተኮር” ክልል ይከፍሏታል። በአሜሪካ ኒው ጀርሲ ጠቅላይ ግዛት ሮዋን ዩኒቨርስቲ የማርኬቲንግ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር በርሀ ሃብተጊዮርጊስ በ9/8/2010 ለጀርመን ሬዲዮ እንደገለጹት “ኢትዮጵያ በራሷ ልክ የተሰፋ መንግሥት ነው ለማቋቋም የምትፈልገው፤ ይህ አይሳካም” በማለት ተናግረው ነበር። መምህሩ አያይዘው በቋንቋና በብሔር ኤርትራን የመተልተል እቅድ መያዙንም አጥብቀው ተናግረዋል። ህወሃት ይህንኑ አላማውን ለማሳካት ሲል ከሰላማዊ ድርድር ማፈግፈጉን አመልክተዋል።

ኤርትራ ጨለመች – “ከወያኔ ይልቅ ጨለማ !!”

በበርካታ የኤርትራ ተወላጆች ዘንድ አንድ ትልቅ ስጋት አለ። በኤርትራ ቆላማ ክፍል የሚኖሩ ሙስሊሞች ቋንቋቸው አረቢኛ እንዲሆን ምኞት አላቸው። ቁጥራቸው ከክርስቲያኑ ስለሚበልጥ ይህንኑ የብሔር ጥያቄ ላይ የተንጠለጠለ በራስ ቋንቋ የመስራት መብት እንዲከበር ይፈልጋሉ። ከዚህም በላይ በደገኞች እጅ የተያዘውን የስልጣን ሞኖፖሊ አጥብቀው ይቃወሙታል።

ከሐምሌ 24 – ነሃሴ 3 ቀን 2010 ዓ ም ድረስ “ብሔራዊ ጉባኤ ለዴሞክራሲ ለውጥ” በሚል ርዕስ አዲስ አበባ ተደርጎ በነበረው ጉባኤ ጥምረት የፈጠሩት አስር ተቃዋሚዎች ከበርካታ ጭቅጭቅ በኋላ አቋም አድርገው የወሰዱት “የቋንቋና የብሔር መብት ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ነው” በሚል ነው። በወቅቱ የተያዘውን አቋምና የጉባኤው የመጨረሻ ውሳኔ ይፋ ሲሆን የተገለጸው ኢሳያስ ሲወገዱ ስልጣን ተረክቦ ኤርትራን የሚያስተዳድር የስደት ፓርላማ ለማቋቋም ነበር።

eritrea-opposition-conferenceከ330 በላይ ተወካዮች ከተገኙበት ስብሰባ ውስጥ 55 አባላት ያሉበት አደራጅ ኮሚሽን በማቋቋም የተጠናቀቀውን ጉባኤ አስመልክቶ ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ “ተቃዋሚዎች አቋማቸው ግልጽ አይደለም” በማለት ለመቃወም ጊዜ አልወሰዱም። ከእርሳቸው በተለየ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ትምባሆ ሞኖፖል ዋና ስራ አስኪያጅና የንግድ ምክር ቤት ጸሐፊ የነበሩት አቶ ረዘነ ሃብቱ በበኩላቸው ህግና ህገ መንግስት እንደማያውቅ የጠቀሱት ስርዓት አሁን ባሉት ተቃዋሚዎች ሊተካ እንደሚችል እምነታቸውን ያስቀምጣሉ።

በኮታ የሚሸጥ ቁራሽ ዳቦ ለመግዛት ሌሊት የሚሰለፉት የኤርትራ ተወላጆች፣ ኑሮ ቢግልባቸውም፣ የመኖር አቅም ቢያጡም፣ ውትድርናና የነጻ አገልግሎት ቢያንገሸግሻቸውም፣ በነጻነት የመደራጀትና በሰውነት ብቻ ሊያገኙት የሚገባቸው መብቶች ባይኖሩዋቸውም፣ ከሁሉም በላይ አሁን መብራት በሳምንት በፈረቃ አንድ ጊዜ ቢደርሳቸውና በሳምንት ስድስት ቀን በጨለማ ቢቀመጡም “ወያኔ” ያበጀው ስርዓት እንዲመሰረትላቸው አይመኙም።

አስገራሚው አቋማቸው ሁሌም የሚመዘነው ከ”ወያኔ” ጋር እንጂ ከጥቅል የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዳልሆነ በይፋ ይናገራሉ። የህወሃት ሰዎችና ደጋፊዎችም ይህንን አቋም ይረዱታል። ኢሳያስን ለማስወገድ የሚደረገው ጥረት በተፈለገው ፍጥነት ሊተገበር ያልቻለበት አንዱና ትልቁ ምክንያት ይህ በመሆኑ “ኢሳያስን ከአህጉርና ከዓለም ኣቀፍ ፖለቲካ በመነጠል አስልሎ ማጥፋት” የሚለውን ሁለተኛው ስልት ኢህአዴግ ዘግይቶም ቢሆን ለመጀመር መገደዱንና በስተመጨረሻ ውጤት እንዳገኘበት ይገልጻሉ።

በዚሁ የማስለል ስልት ወንበራቸው የተፈረካከሰው አቶ ኢሳያስ “የኤርትራ ወጣቶች እንዲሰደዱ የአሜሪካ የስለላ ድርጅት እየሰራ ነው” በማለት በጃንዋሪ 2013 የፈረንጆች አዲስ ዓመት ተናግረዋል። ችግር የሚቆላውን ህዝብ “የኤርትራ ህዝብ ችግር የለበትም ቀልማጣ ነው” ሲሉም አሙቀውታል። ኤርትራ በውጪ አገር መንግስታትና በኢትዮጵያ አማካይነት ጫና እንደተደረገባት መሆኑና መሸሸግ አልተቻላቸውም። ሰሞኑንን ለቅዱስ ዮሐንስ በቃለ ምልልስ መልክ ለህዝባቸው የደሰኮሩት ኢሳያስ የአገሪቱ ወጣቶች ለመኮብለላቸው ምክንያቱ ችግር ሳይሆን ኢትዮጵያንና አሜሪካንን ግንባር ቀደም ተጠቃሽ አድርገዋል። የኢሳያስ ደጋፊ ምሁራን ሳይቀሩ ህወሃት ኤርትራን ከዓለምአቀፍ መድረክ በመነጠል እንደጎዳቸው ማመናቸውን የሚገልጹ እንደሚሉት ህወሃት “የኤርትራን መንግስት በሚገባ አስልሎታል። አቅም አልባና የቀጣናው ተራና ውዳቂ፣ ህግና ወግ የማያውቅ ዱርዬ መንግስት ተደርጎ እንዲሳል አድርጎታል” ይላሉ። አያይዘውም “ህወሃት በግብሩ ከሻዕቢያ ባይሻልም በጉዳይ አስፈጻሚነትና አፍሪካ ህብረትን በወጉ መቆጣጠር በመቻሉ የውጭ ገጹን ማሳመር በመቻሉ ከሻዕቢያ የተሻልኩ ነኝ ብሎ ማሳመን ችሏል፡፡”

eritreans in line
በኤርትራ የዳቦና ወተት ወረፋ (ፎቶ: ኒው ዮርክ ታይምስ)

በዚሁ መነሻና በውስጥ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ቀውስ እየወላለቁ አሉት ኢሳያስ ከስጋትና ከፍርሃቻ እንደሆነ በሚያስታውቅ ጎልዳፋ ፍልስፍና “ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ግዢ ስር ነበረች ተብሎ በተደጋጋሚ ሲወራ ለወያኔዎች ኩራት ሆኗቸዋል” ሲሉ ለተደገሰላቸው ድግስ የኤርትራ ተወላጆችን እልህ ውስጥ የሚከትት ንግግር አሰምተዋል። በርካቶች ኢትዮጵያን ዝቅ አድርገው የተመለከቱ መስሏቸው ቢናደዱም አቶ ኢሳያስ ግን በሳቸው ዘመን ኤርትራ በህወሃት ቅኝ ግዢ እንዳትያዝ ማስጠንቀቂያ ማስተላለፋቸው እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ለጎልጉል ተናግረዋል። ጳጉሜን 2፤ 2005ዓም (በሴፕቴምበር 7፤ 2013) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ኤርትራ ለኢትዮጵያዊያን ነጻ መውጣት ሊታመን የማይችል ድጋፍ እየሰጠች ነው ባሉበት ማግስት ኢሳያስ “ለመሆኑ ኢትዮጵያ የተፈጠረችው መቼ ነው?” በማለት እንደ አንድ ታሪክ አልባ አገር አበሻቅጠው ማቅረባቸው ቀደም ሲል የነበረውን ቅሬታና ጥርጣሬ እንዲያገረሽ አድርጎታል የሚሉ ወገኖችም አልታጡም።

ህወሃት ልክ እንደነ ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደኢህዴን እና መሰል ድቃይ ድርጅቶች ኤርትራን እንዲመሩ ያደራጃቸውን ክፍሎች አስተምሮና አንቅቶ ከመዘጋጀቱ ጋር ተዳምሮ ኢሳያስን ጤና የነሳቸው ጉዳይ ዓለምአቀፉ የግጭት ቡድን (International Crisis Group) በዝርዝር ያስቀመጣቸው መሰረታዊ ጉዳዮች የኤርትራን መንግሥት በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ስለከተቱት ነው። በጦር አመራሮችና በፖለቲካ ክንፎች ውስጥ የተከሰተ አለመተማን፣ ተሞክሮ ከሸፈ የተባለው መፈንቅለ መንግሥት፣ የማስታወቂያ ሚኒስትር የነበሩት አሊ አብዶን ጨምሮ የቅርብ ታማኞች መክዳት፣ የወጣቶች አገር ጥሎ መኮብለል፣ እስር፣ የኑሮ ውድነት፣ የምንዛሬ ችግር መባባስ ህወሃት ለሚወስድባቸው ማንኛውም ርምጃ መቋቋም የሚችሉበት ትከሻ ስለሌላቸው እንደሆነ ከግምት በላይ አስተያየት የሚሰጥበት እውነት ነው። በስንቅና ትጥቅም ደረጃ አይመታጠኑም የሚሉ ባለሙያዎችም ካላይ በቀረበው ሃሳብ ይስማማሉ።

ምንም ሆነ ምን ህወሃት ኢሳያስን አስወግዶ አሻንጉሊት መንግስት ከሚያስቀምጥላቸው ይልቅ የኤርትራ ተወላጆች ከኢሳያስ ጋር በመሆን መሰቃየትን እንደሚመርጡ ቀደም ሲል ታጋይ የነበረችና አሁን በስደት ላይ የምትገኝ የኤርትራ ተወላጅ ትናገራለች። ባልደረባዋም ሃሳቧን ይጋራታል። “በየትኛውም መመዘኛ ህወሃት (ወያኔ) ኤርትራ ላይ አሻንጉሊት መንግስት አስቀምጦ አይገዛንም። ኢሳያስ ይሻለናል። በብሄር ሊበጣጥሱንና እኛ በማያቋርጥ ችግር ውስጥ ስንኖር እነሱ ሊስቁብን ነው” በማለት አንገቱን እያወዛወዘ አስተያየቱን ሰጥቷል። ሁለቱም ስማቸው እንዳይገለጽ ጠይቀዋል።

ሻዕቢያ ኢትዮጵያ ጠንካራ ሉአላዊ አገር እንድትሆን ይፈልጋል?

“ለኢትዮጵያዊያን አገራቸው ክብራቸው ናት። ማንም በታሪካቸውና በማንነታቸው እንዲሳለቅ አይወዱም። መለስ የሚባሉት ክፉ መሪ ህዝብ እንደረገማቸው ያለፉት ኢትዮጵያንና ታሪኳን ከፍ ዝቅ በማድረግ በማራከሳቸው ነው። ታሪካችንን ወደ 100 ዓመት በማኮሰስ፣ ሰንደቃችንን ከተራ “የመገነዣቸው እራፊ” ጋር በማመሳሰላቸው ሲተፉና ሲወገዙ ኖረው መሞታቸውን በማውሳት  ኢሳያስ ደፍረውና ታብየው “ለመሆኑ ኢትዮጵያ ማን ናት?” ለማለት የተነሱበትን ምክንያት በማስቀደም አስተያየታቸውን ይጀምራሉ።

“በስብሶ ሊወድቅ የደረሰ ስርዓት የሚመራ፣ በልመናና ከስደት በሚገኝ ቀረጥ የምትተዳደር፣ ዳቦ በራሽንና በወረፋ የሚሸጥበት አገር እየመሩ፣ በ20ኛው ክፍለዘመን በኩራዝ የምትበራ አገር ይዘው  ራሱን ችሎ የሚኖርን ህዝብ መተንኮስ አግባብ አይደለም” በሚል ኢሳያስን የተቃወሙ ጥቂት አይደሉም። የኢሳያስ ንግግር በስደት “መብታቸው ተከብሮ” አዲስ አበባና የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የራሳቸውን አገር ሰዎች ጭምር የሚያስደስት እንዳልሆነ፣ ይልቁኑም የሚያሸማቅቅ እንደሆነ ነው የሚሰማው። የዚያኑ ያህል “ጨንቋቸው ነው። ምን ይበሉ? አዲስና ለህዝብ ጥቅም ያለው ወሬ ሲጠፋ ከታሪክና ከምኞት ጋር መጣላት የጊዜው አማራጫቸው ነው” በማለት ያጣጣሏቸውና ምላሽም እንደማያስፈልጋቸው የገለጹ ጥቂት አይደሉም።

አቶ ኢሳያስ ሲፈልጋቸው “ኢትዮጵያ በቅኝ ስትገዛን ኖራለች፤ ነጻነት እንፈልጋለን” በሚል በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን ህይወትን የገበሩት ሳያንስ ዛሬ፣ “ለመሆኑ ኢትዮጵያ መቼ ነው የተፈጠረችው” ሲሉ ጠይቀው “ኢትዮጵያ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ድል የተቀዳጁ ለጥቅማቸው ማስጠበቂያ ሲሉ የፈጠሯት አገር መሆኗን ነው እኔ የማውቀው” ማለታቸው ኢሳያስ መቼም ቢሆን ኢትዮጵያ ላይ ያላቸው አመለካከት የጸዳ እንዳልሆነ የሚያረጋግጥ ይሆናል። ከዚህ አንጻር ብቻ ሳይሆን በበርካታ ጉዳዮች ችግር ቢኖርብንም “ኢሳያስን ጠንቀቅ” የሚሉ ወገኖች ለክብር ቅድሚያ እንዲሰጥ ይመክራሉ።

“አ–ያ ሆ ሆ ማታ ነው ድሌ” ማን?

“ሻዕቢያና ኢህአዴግ ተመሳሳይ ፖሊሲ መከተል ጀምረዋል” የሚሉ የጎልጉል የዘወትር አስተያየት ሰጪ “ኢህአዴግ ሶማሊያ ላይ የሚከተለውን ፖሊሲ ሻዕቢያም እየተገበረው ነው” ይላሉ። አያይዘውም “ኢህአዴግ በሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር መስራትና፣ ኢትዮጵያ የምታስቀምጠውን አጀንዳ የሚሸራርፍ መንግስት በማዕከላዊ መንግስትነት እንዲቀመጥ እንደማትፈልግ ሁሉ፣ አሁን አሁን ኤርትራም የጀመረችው የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች በዚሁ መልኩ የማደራጀት ስራ ነው” በማለት ይዘረዝራሉ።

በሶማሊያ ከኢህአዴግ ሃሳብ ውጪ ለመንቀሳቀስ የሚያስብ ማዕከላዊ መንግስት ብቅ ቢል ወዲያው መብራቱን ያጠፉበታል። በደቡብ ሱዳን ያለው እውነታ ተመሳሳይ ነው። ደቡብ ሱዳን እየተመራች ያለችው በኢህአዴግ፣ በተለይም በህዋሀት ሰዎች መሆኑንን የሚያመለክቱት አስተያየት ሰጪ፣ “ያለ ምንም ማመንታት ኤርትራ ከውስጥ ያለባት ችግሯ፣ በዓለምአቀፍ ደረጃ የደረሰባት ኪሳራና በመንግሥቱ ውስጥ ከተፈጠረው መፈረካከስ ጋር ተዳምሮ የጎረቤቶቿ እድል ይገጥማታል። ኢሳያስ ያበቃላቸዋል። ኢህአዴግ የሰራው መንግስት ይቋቋማል” ብለዋል።

ኢህአዴግ በአገር ውስጥ ያለበት ቀውስ ቀኑን ጠብቆ የሚፈነዳ እንደሆነ ያመለከቱት አስተያየት ሰጪ “የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር ኢሳያስ አሁን ባሉበት ደረጃ ለኢህአዴግ ስጋት አይሆኑም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ኢህአዴግ በግፍ፣ በኑሮ ውድነት፣ ፍትሃዊ ባልሆነ የሃብት ክፍፍል፣ በሙስና፣ ወዘተ የፈጠረው ምሬት ከመጠን ያለፈ ቢሆንም እንደ ሻዕቢያ በቀላሉ የሚናድበት ደረጃ ያለ እንደማይመስላቸው የገለጹት አስተያየት ሰጪ “ኢህአዴግን ከምንም በላይ የሚያሰጋውና የሚያስጨንቀው የከረረ ሰላማዊ ትግል ነው። በትክክለኛ መርህ ላይ የተመሠረተ እውነተኛ ሰላማዊ ትግልና ሕዝባዊ እምቢተኝነት ስለማይገባውና በጉዳዩ ላይ በቂ ተሞክሮ ስለሌለው የሚያሸብረውና አስገድዶ ወደ ድርድር የሚያመጣው እሱ ብቻ እንደሆነ አምናለሁ” ሲሉ አስተያየታቸውን አጠቃለዋል። በሌላ ወገን ደግሞ የተቃዋሚዎች አቅም ከቀድሞው በተለየ የተጠናከረና የፕሮፓጋንዳውን ዘመቻ በማሳደጋቸው ምን አልባት መከላከያ ሰራዊቱ አካባቢ የመከፋፈል ችግር ሊፈጠር ይችላል የሚል ግምት ያላቸውም ብቅ እያሉ ነው።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. epheno says

    September 16, 2013 09:03 am at 9:03 am

    mejemeria yerasehen (ethio ) chegr lemeftat mokr … ezih lai Sle Eritrea yesafkew neger (ane sle eritrea menem endematawq new yemiasredaw) lemehonu ethiopia dabo teselfeh algezahem … yewelon rehab resahew … (tawqaleh once upon a time … ke andit egyptian set gar egyptian chat room gebche where r u from ? alechign … am from Eritrea selat … i don’t know Eritrea alechign then do u know Ethiopia ? alkuat … yeah yeah … i know i know .. ethiopia is famous in “hunger” alechign … ena zem beleh atakabd ante yepagume Gazetegna … free honeh … ewnetegna journalist lemehon moker … this is not journalism … just enatat entat bebado qit new yemibalew …

    Reply
  2. washeraw says

    September 16, 2013 11:58 am at 11:58 am

    የኤርትራ ችግር ዘላቂ መፍትሔ የሚሆነው ከኢትዮጵያ ጋር በሆነ መንገድ ተመልሳ መገናኘት ከቻለች ብቻ ይመስለኛል። ይህን የምናምንበት ከሆነ ቁልፉ እርምጃ የኢትዮጵያን ፌዴሬሽን እንደገና ማዋቀር ነው። ከብሔረሰብ ይልቅ አስተዳደራዊ አመቺነትን መሠረት ያደረገ፣ የሁሉንም ብሔረሰቦች በቋንቋቸው የመጠቀም መብት ያለገደብ የሚያከብር ተደርጎ እንደገና ቢሠራ ኤርትራዊያንን ለመጋበዝ ችግር አይሆንም። አሁን ባለው ቅርጹ የሚቀጥል ከሆነ ግን ኤርትራ ቢያንስ ከሦስት ተቆርጣ ነው ከኢትዮጵያ ጋር የምትዋሃደው ማለት ነው።

    ህወሃትም ሆነ ሻዕቢያ ይህን ስለማይፈልጉ የመጀመሪያው እርምጃ እነሱን ማስወገድ መሆን ይኖርበታል። ህወሃት ቀድሞ ቢወገድ ሁሉም ይቀልልናል።

    Reply
  3. Dekedeku YeBerale says

    September 16, 2013 05:37 pm at 5:37 pm

    The case of Ethiopia and Eritrea will remain problematic as long as the ruling parties are in power. The reasen for that both parties are using the barel of the gun as a prerequsit to hold power. As long as there is no democratic governement out of the peoples voting box, this status quo remains there.
    A case in point is to take in to account the coming of a poletical power in Ethiopia that holds a an intention to be nationalistc. There will be a great danger for the government of Eritrea.
    Either it will be removed via direct or indirect interfirance of that Ethiopian Government or Ethiopia will get by hoke or crucke its legitmate see gate, where EPRDF fails to realise it.
    As far as the people of Eritrea and Ethiopia is concerned, regardles of all negetive factors, they remain a mamber of one family as it used to be since time immorial. There is blode, culture, tradition as well as spritual conection between the two peace loving people that are forced to be separated to fulfil the interest of two power mongering, unpopular dictators who are through and throug leftists.
    When will this happen will be your question but the answere is simple that will be “Time will tell us itself when it will be”.
    Peace to the peace loving people !!

    Reply
  4. Musie says

    September 16, 2013 11:05 pm at 11:05 pm

    werenga hula

    Reply
  5. በለው! says

    September 22, 2013 05:38 pm at 5:38 pm

    ፩)”የሬድ ሲ አፋር ዲሞክራቲክ ኦርጋናይዜሽንና የሳሆ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ባደረጉት ጉባዔ፣ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን መንግሥት አገዛዝ ለመገርሰስና የኤርትራን ሕዝብ ነፃነት
    ለመመለስ ወደ ትጥቅ ትግል ለመግባት ከስምምነት ደርሰዋል”፡፡
    **የአቶ መለስ ህገመንግስት አብሮ ሞተ ማለት ነው?”በሰው ሀገር ፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ለህወአት/ወያኔ/ኢህአዴግ ይፈቀዳል ማለት ነው?የኢህአዴግ ሕገመንግስት “ሁሉም ሰው በአንድ ፖለቲካ ጥላ ሥር ሊሰባሰብ በሚወክለው ሕዝብ ሥም ተጘኝቶ አፀደቀው ይህም ተፎካካሮ፣ አማራጭ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አያስፈልግም የሚለው” እንደተጠበቀ ሆኖ መድብለ ፓርቲ ተፈቀደ ከሚለው የደንቆሮ ተወዳዳሪ ምሁራን ትርጓሜ ጋር ሲጣረስ…ማናቸውም ተቃዋሚ ባይ ነን ሚሉ ትናውም ጎረቤት ሀገር ገብተው ሲደራጁ ሕገመንግስቱን መናድ ሥርዓቱን ለመገርሰስ ማቀድ ተብሎ ሲያስወነጅል የጌረቤት ሀገር ተቃዋሚ የጦርና የፖለቲካ ውልጠና ተሰጥቶአቸው የኤርትራን መንግስት ለመጣል ከዘመቱ ወያኔ ኢህዴግ ህወአት የበሉበትን ወጭት ሰባሪ ናቸው፡፤ አሁን የሚከላከሉት መከላከያቸው፣ ኢፈርትን፣ ፋውንዴሽኑን፣መከላኬአው የገነባውን ኢንዱስትሪና የሙሰኛ ካድሬ ኪራይ ሰብሳቢነታቸው የሆድአደሩ ምሁር ባይ ሥልጣን፣የዲያስፖራው ከውጭ ተዘርፎ በኢህዴግ ጠባቀነት ተቀበረን ገንዘብ በኤርትራ መንግስት እንዳይወሰድ እንጂ የኢትዮጵያን ብሔር ብሄረሰብ የሚነካ ጥቅማቸውንም አያስቀርም።፵ዓመት ልጅህን ንብረትህን ገበርክ ድሃ ሞኝ የዋህ መሃይምን ገበሬ ሄደህ እንዳትሞት በርህን ዝጋ!። ሻቢያ፣ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ህወአት፣ የአንድ ኮብል እስቶን ጥርብ ድንጋይ ናቸው በለው!
    ፪)ድርጅቶቹ ወታደራዊ ጥቃቱን የመጀመር ዕቅዳቸው ከዚህ ቀደም የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይሎች በኢትዮጵያ በፈጠሩት ኅብረት ጀምረውት እንደነበረው በዕቅድ እንደማይቀርና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር እንደሚሸጋገር እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
    **ለመሆኑ መሳሪያ ከየት መጣ? የኢህአዴግ ሠራዊት የጦር ማሳረያ ከማምረትም በላይ መሸጥ ጀምሯልን?እዚህ ላይ ነው መንግስትና ሠራዊቱ ተለያይተዋል የምንለው ኅኢለመልስ ውሃ በላው ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ኢትኦጳአን አስወርሮ የኤርትራ ቡድን ኢትዮጵያን ልትመራ ነው ወይንም ኢህአዴግ በደብረፂዮን ተሀድሶ ልታደርግ ነው!?ነገር አለ በለው!!!!!!!

    Reply
  6. Truly says

    October 25, 2013 02:03 am at 2:03 am

    Pls. Don’t be the mouthpiece of Woyane junta. The main enemy for the horn of Africa is woyane but not Shaebia. Isias is brutal dictator but has no destructive agenda than woyane. Isias is a nationalistic, non tribal, and brutal totalitarian dictator. But woyane is a crooked, racist, corrupted ethnic based regime. In Eritrea , whether woyane has a dream of ethinic based puppet government or not, it won’t be happen any day. Above 80% of the Eritrean people & oppositions mistrust woyane. That is why you see a few hundred of armed opposition fighters compare to those who flee from the country. Anyway I can forecast that EPLF can fight anywhere ( even by doing the usual strategic retreat techniques ) . But the demise of woyane will be happen sooner.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am
  • የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ? February 19, 2025 06:00 pm
  • አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?! February 19, 2025 12:29 am
  • የአሜሪካ ድምፅ/ቪኦኤ ይዘጋ ተባለ  February 12, 2025 03:37 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ሹመኛ ካድሬዎች February 3, 2025 11:07 am
  • ትግሉን የጎዳው የእስክንድር ነጋ አካሄድ February 3, 2025 10:29 am
  • ኤሊያስ መሠረት “ጭምብሉ ዛሬ ወለቀ”፤ ተከፋይ ነው! February 2, 2025 05:32 pm
  • የፋሲል ግንብ እድሳት እንዴት ተካሄደ? የመንጣቱ ምክንያት? January 23, 2025 03:41 pm
  • ታሪካዊዉ የፋሲል ቤተመንግሥት ለምን ነጣ? January 23, 2025 03:04 pm
  • የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተወልደ አስተዳደር ዘመን ለተሠራ ስህተት 425ሺ ዶላር ተቀጣ December 14, 2024 01:44 am
  • በትግራይ ከሞትና ከአካላዊ ጉዳት የተረፉት ለስደት ተዳርገዋል November 27, 2024 12:09 pm
  • የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሠራሩን እንዲያርም ጥብቅ መመሪያ ተሰጠው November 27, 2024 11:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule