• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአሜሪካ ምርጫ እንደ ኤርትራ ሕዝበ ውሳኔ

November 10, 2016 07:31 am by Editor 5 Comments

ለሁለት ዓመታት ያህል ሲካሄድ የቆየው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሪፓብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የምርጫው ውጤት ለሒላሪ ክሊንተን ድምጻቸውን የሰጡ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኗል፡፡ ምርጫው ለአንዳንዶች እንደ ኤርትራው ሕዝበ ውሳኔ “ነጻነት” ወይም “ባርነት” የመምረጥ ያህል ተሰምቷቸዋል፡፡ ይህ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተሻለ አማራጭ የጠፋበትና ከሁለት ገዳይ ካንሰሮች አንዱን የመምረጥ ያህል ነው ተብሏል፡፡

ገና ከጅምሩ በሚሰጡት ከፋፋይ መልዕክት የመመረጥ ዕድል እንደሌላቸው ሲገመቱ የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ ለዚህ መድረሳቸው በርካታ የሚዲያ ሰዎችንና የፖለቲካ ተንታኞችን ያስደመመ ነው፡፡ ትራምፕ ፓርቲቸውን ወክለው ለመወዳደር ዕድል ካገኙ በኋላ እንኳን በታዋቂ ሪፓብሊካን ድጋፍ ተነፍጓቸው ቆይተዋል፡፡ ከዴሞክራቲክ ፓርቲ ተወካይ ሒላሪ ክሊንተን ጋር በምርጫ ዘመቻ በነበሩበት ጊዜ አብዛኛው ትራምፕ ያደረጓቸው ንግግሮችና ያለፈው ታሪካቸው ያለመመረጥ ዕድላቸውን ያሰፋ መስሎ ታይቶ ነበር፡፡

ለሴቶች ያላቸው አመለካከት እስከ ማባለግ የደረሰ መሆኑ፤ በአብዛኛው በምርጫ ዘመቻና በፕሬዚዳንታዊ ክርክሩ ወቅት ከፖሊሲ ንግግሮች ይልቅ የዘለፋና የነቀፋ ንግግሮችን ማድረጋቸው፤ “አሜሪካንን እንደገና ታላቅ እናድርግ” ከሚለው የምርጫ መፈክር በስተቀር ይህ ነው የሚባል የአገር ውስጥና የውጪ ፖሊሲ አቋማቸውን ያላሳዩ መሆናቸው፤ አንዲት ቀን እንኳን በመንግሥት ተቋም ውስጥ ለሕዝብ አገልግሎት ሰጥተው የማያውቁ መሆናቸው፤ ወደ አሜሪካ ለገቡ እና ወደፊት ለሚገቡ ስደተኞች የሚናገሯቸው ጽንፈኛ አመለካከቶች፤ ወዘተ ትራምፕ የመመረጥ ዕድላቸው ያነሰ መሆኑን በተለይ በሚዲያው ሲስተጋባ ቆይቷል፡፡

ከዚህ በተጻጻሪ ደግሞ በአብዛኛው የሚዲያው ድጋፍ የተቸራቸው፣ የባራክ ኦባማና የትዳር ጓደኛቸው እንዲሁም የባላቸው ቢል ክሊንተን ድጋፍና የምርጫ ዘመቻ የተደረገላቸው፤ በሌሎች ታላላቅ የዴሞክራቲክ ፓርቲ አመራሮች ከፍተኛ ድጋፍ የነበራቸው፤ በሴትነታቸው የበርካታ ሴቶችን ድምጽ የማግኘት ዕድል እንዳላቸው የተነገረላቸው፤ እጅግ በርካታ ለሆኑ ዓመታት በመንግሥት ሥራ ላይ እንዲሁም የሕዝብ ተመራጭ በመሆን መሥራታቸው በሰፊው የተወራላቸው፤ ለዓመታት ያካበቱትን የአገር ውስጥና የዓለምአቀፍ ልምድ በፕሬዚዳንትነት ለከፍተኛ ጥቅም ያውሉታል ተብለው የተጠበቁት፤ በወንዶች ተይዞ የነበረውን የመስታወት የሥልጣን ጣሪያ በርቅሰው በመውጣት ለወደፊት ሴቶች ተስፋ ይሆናሉ ተብለው የተጠበቁት ሒላሪ ክሊንተን በፍጹም ያልጠበቁትን የሽንፈት ጽዋ ተጎናጽፈው ደጋፊዎቻቸውንም እጅግ አስለቅሰዋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ለመራጮቻቸው ምሥጢራዊ መልዕክት አስተላልፈዋል በማለት አስተያየታቸውን የሚሰጡ ፈርጀ ብዙ የሆነው “አሜሪካንን እንደገና ታላቅ ማድረግ” የሚለው የምርጫ መፈክራቸው ለደጋፊዎቻቸው ተገቢውን መልዕክት አስተላልፏል ይላሉ፡፡ ይህ አሜሪካንን እንደገና ታላቅ የማድረግ ዘመቻ በሥራ ማጣት፣ በኢሚግሬሽን፣ በኢኮኖሚ ድቀት፣ ሥራቸው ወደ ኢሲያ አገራት በመሄዱ በስቃይ ለሚገኙ፣ በኦባማ ጥላቻ ባደረባቸው፣ … ላይ ተስፋን የጫረ ብቻ ሳይሆን ክብርንም የሚመልስ ተደርጎ ታይቷል፡፡

እስከ ምርጫው ቀን በተካሄደው የሕዝብ አስተያየት በአብዛኛው ክሊንተን ሲመሩ ቆይተው ትራምፕ ማሸነፋቸው በተለይ የሚዲያ ሰዎችን ያነጋገረ ሆኗል፡፡ ከተሰጡት በርካታ ምክንያቶች መካከል አንዱ መራጮች ለሕዝብ አስተያየት (ፖል) ሲጠየቁ ትክክለኛ ምርጫቸውን አለመናገራቸው ነው ተብሏል፡፡ ምክንያቱም እንደ ትራምፕ ዓይነቱን ዕጩ በግልጽ እደግፋለሁ ብሎ መናገር ለብዙዎች በተለይም ክሊንተንን ለመምረጥ ላልወሰኑ መራጮች የሚያኮራ ባለመሆኑ ነው ተብሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ለወራት ሲወሰዱ የነበሩት የሕዝብ አስተያየቶች ትክክለኛ የሕዝቡን የምርጫ ፍላጎት ጠቋሚ እንዳልነበሩ ተነግሯል፡፡

በሌላ በኩል ከቢል ክሊንተን የአርካንሳስ አገረ ገዢነት ጀምሮ እስከ ኋይትሃውስ ከዚያም በውጭ ጉዳይ ሚ/ርነት ዘመን ድረስ ከባላቸው ጋር በመሆን ፈጸሟቸው የሚባሉ እስከ ነፍስ ማጥፋት የዘለቁ ሕገወጥ ተግባራት፤ በሊቢያ የነበሩት የአሜሪካ ዲፕሎማት መገደል፤ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር የሥልጣን ዘመናቸው ጠፉ ወይም ተሰረዙ የተባሉት የኢሜይል መልዕክቶች እና ከዚያ ጋር ተያይዞ የተናገሩት ውሸት እንዲሁም ለመራጮቻቸው በተለይም እርሳቸውን ለመምረጥ ላልወሰኑቱ ከዶናልድ ትራምፕ የተሻሉ ዕጩ መሆናቸውን በበቂ መረጃ ያለማቅረባቸው የመራጮቻቸውን በተለይ ትራምፕን ለመምረጥ ፍላጎት ያልነበራቸውን ድምጽ እንዳያገኙ ካደረጓቸው ጥቂቶቹ ናቸው፡፡clinton-trump

እንደ ቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ከቀድሞዎቹ አውሮጳ ነገሥታት ጋር ቀጥተኛ የደም ትስስር እንዳላቸው የተነገረላቸው ትራምፕና ክሊንተን ለዚህ የአሜሪካ ምርጫ የቀረቡበት ሁኔታ “ነጻነት” ወይም “ባርነት” ይል እንደነበረው የኤርትራ ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎ ታይቷል፡፡ በሌላ አነጋገር የአሜሪካ ሕዝብ ከሁለት ገዳይ የካንሰር በሽታዎች አንዱን እንዲመርጥ የተገደደበት ሁኔታ በሚል ይህንን ምርጫ የሚተቹ ይናገራሉ፡፡ ሁለቱም ብዙ የሚያስወቅሷቸው ተግባራት መኖራቸውና በተለይ ዶናልድ ትራምፕን ለመምረጥ ፍላጎት የሌላቸው ሒላሪ ክሊንተንን አሳማኝ ዕጩ ሆኖ አለማግኘታቸው ክሊንተንን የጎዳ ቢሆንም ከሁለቱም አንዱ ያነሰ ክፉ (lesser evil) እንዳልሆኑላቸው አስተያየት ሲሰጡ ተሰምተዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) ሥልጣን ከያዘ በኋላ እንደ መለስ ዓይነቱን የለየለት ኮሙኒስታዊ አምባገነን “የአፍሪካ የሕዳሴ መሪ” በማለት የሰየሙት የቢል ክሊንተን ባለቤትና ከባላቸው እምብዛም ያልተለየ ፖሊሲ እንደሚኖራቸው የተጠበቁትን ሒላሪ ክሊንተንን በርካታ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵውያን መደገፋቸው ለአንዳንዶች ያልተዋጠ ተግባር ሆኗል፡፡ በተለይ ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ዴሞክራቱ ኦባማ የህወሃትን ምርጫ “ዴሞክራሲያዊ” በማለት በህዝብ ላይ መቀለዳቸው እየታወቀ ኢትዮጵውያኑ ሒላሪን መደገፋቸውና መምረጣቸው ግራ ጋባ ሆኗል፡፡ አሁንም የዚህ ምክንያት እንደ ኤርትራው ሕዝበ ውሳኔ ጉዳዩ የ“ነጻነት” ወይም የ“ባርነት” ዓይነት ስለሆነባቸው ነው የሚል አስተያየት ይሰጣል፡፡

የትራምፕ በፕሬዚዳንታዊ መንበሩ ላይ መቀመጥ የአሜሪካንን የውጪ ፖሊሲ በተለይ በአፍሪካ ላይ የሚኖረውን እምብዛም እንደማይቀይር ይነገራል፡፡ “አዲስ የዓለም ሥርዓት” በሚል የፖለቲካ አመለካከት ህወሃትን በሥልጣን ላይ እንዲቀመጥ ካደረጉት ሪፓብሊካኑ 41ኛው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ጀምሮ ቀጥሎም በነሱዛን ራይስ አማካሪነት ህወሃትን ሲያቀማጥሉ የነበሩት ቢል ክሊንተን በኋላም ጆርጅ ደብሊው ቡሽ አሁን ደግሞ ህወሃትን “ዴሞክራሲያዊ” እስካሉት ኦባማ ድረስ የአሜሪካ የውጪ ፖሊሲ በኢትዮጵያ ላይ ሲለወጥ አልታየም፡፡ በትራምፕ ፕሬዚዳንታዊ ዘመንም ይለወጣል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ነገር ግን ህወሃትን ልክ እንደ አድዋ ልጅ የሚደግፉት የዴሞክራቲክ ፓርቲ አመራሮች፣ እንደነ ሱዛን ራይስ ዓይነት ባለሥልጣናትና ሌሎች የህወሃት አቀማጣዮች ከኦባማ ጋር አብረው ጥር ወር ላይ መውጣታቸውና በትራምፕ ሠራተኞች መተካታቸው ለህወሃት አሁን አገር ውስጥ ካለው ሕዝባዊ ተቃውሞ ጋር ተዳምሮ የማገገሚያውን ጊዜ ያስረዝምበታል ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሞ ህወሃትን በማንገሳቸው ቁጭት ላይ የሚገኙ የቀድሞ ባለሥልጣናት ጋር በመተባበር የውትወታ (የሎቢ) ሥራ የማከናወኑ ጉዳይ ካሁኑ መጀመር እንዳለበት አንዳንድ ወገኖች ሃሳባቸውን ይሰጣሉ፡፡  trumpweddingyayclintons

ሕዝብ የፈለገውን መርጧል፤ ትራምፕ መራጮቻቸውን ለማስደሰት ይሁን ከልባቸው ለሕዝብ እጅግ በርካታ ተስፋዎችን ገብተዋል፡፡ በሥልጣን መንበሩ ላይ ከተቀመጡ ከ100 ቀናት በኋላ ያደረጓቸው ወይም ለማድረግ የሚያቅዷቸው ነገሮች የቀጣዩ አራት ዓመታት ጉዟቸውን የሚተነብዩ ይሆናሉ፡፡ ከዚያ በፊት ግን ባራክ ኦባማ አሜሪካዊ ዜግነታቸውን ለተጠራጠሩትና በይፋ በዚህ ጉዳይ ላይ ሲናገሩ ለነበሩት ለዶናልድ ጄ. ትራምፕ ሥልጣናቸውን በይፋ ያስረክባሉ፡፡ ከኦባማ የማንነት ጥያቄ ጀምሮ እስከ “አሜሪካንን እንደገና ታላቅ ማድረግ” ድረስ ታላቅ ተስፋ የገባው የትራምፕ አመራር ጥር 12፤ 2009 ሥራውን ይጀምራል፡፡ ከዚያ በፊት ግን በትራምፕ ዩኒቨርሲቲና በሌሎች ጉዳዮች ዶናልድ ትራምፕ ፍርድቤት ይቀርባሉ፡፡

አሜሪካ እጅግ በርካታ የፖለቲካ ድራማ የሚካሄድባት አገር ናት፡፡ ዴሞክራሲ፣ ምርጫ፣ የሕዝብ ድምጽ፣ … የሚባሉት ነገሮች እንዳሉ ሆነው 32ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ስለ ፖለቲካ ያሉትን ማስታወሱ ተገቢ ይሆናል፡፡ ፍራንክሊን ዲ. ሩዝቨልት እንዲህ ነበር ያሉት፤ “በፖለቲካ ዓለም በድንገት የሚከሰት ነገር የለም፤ ካለም የተከሰተው እንደዚያ እንዲሆን ታቅዶ ስለመሆኑ መወራረድ ይቻላል”፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    November 10, 2016 05:24 pm at 5:24 pm

    የሃበሻ ፓለቲከኞችና የየጊዜው አለቆቻችን ፍርፋሪ ለቃሚዎች አስተሳሰብ በየጊዜው ይገርመኛል። ገና ትራምፕ መወዳደድር ሲጀምርና የከረረ አቋሙን ለዓለም ይፋ ሲያደርግ በየድህረ ገጽ ነዳያን ፓለቲከኞች የቁጡን የባጡን ይቀባጥሩልን ነበር። በየስማቸው ስር ዶክተር፤ የተቃዋሚ የፓለቲካ መሪ፤ ጋዜጠኛና ተራ ዜጎችም አእምሮአችን ሲያጨናንቁን ሰንብተዋል። በቃ አለቀ ስንል ደግሞ አሁንም የመነጋገሪያና የንትርክ መንስኤ መሆኑ ሥራ ማጣት ነው። የሞተን ነገር ከመበስበስ የሚያስቀረው የለም! ህይወት ካለው ዘር ያፈራል፡፡ ህይወት አለባ ከሆነም የመሬት ገጸ በረከት ማዳበሪያ ይሆናል።
    በመሰረቱ ተጨፈኑና ላሞኛቹሁ የሚለው የአሜሪካ ፓለቲካ ዲሞክራሲያዊነት የለውም። ዲሞክራሲ ለበስ ነገሮችን ግን ተከናንብዋል። ገና ከጅምሩ ትራምፕ ለሥልጣን ሊበቃ እንደሚችል የሚያመላክቱ ነገሮች ነበሩ።
    1. የአሜሪካ የሰዎች የኑሮ ደረጃ ዝቅ ማለት
    2. የህዝብ እስከ ህልፈተ አለም ፓለቲከኞችን መጥላት
    3. የአሜሪካ ኩባኒያዎች ለስደት መዳረግና ሥራ ማጣት
    4. የማያቋርጠው የስደተኞች ጎርፍ የፈጠረው ውጥረት
    5. የሚበልጠው የአሜሪካ ህዝብ የቀን ተቀን ፈንጣዥና የነገን የማያስብ በመሆኑ ዲሞክራቶች ቢመረጡ ጾም አላድርም በሚል ቀቢጻዊ ተስፋ መታሰርና በአፍ ብቻ ለፍልፎ የምርጫ ቀን በቦታው ተገኝቶ ድምጽ አለመስጠት ዛሬ የአሜሪካ የፓለቲካ ላለበት ውጤት ደርሰናል። ይሁን እንጂ የኤርትራን ከኢትዮጵያ መገንጠል ከአሜሪካው ምርጫ ጋር ማነጻጸር ድንቁርና ነው። የኤርትራ ህዝብ ጠበንጃ ባነገተ፤ የዘር ጥላቻን በተጋተ እሳት ተፍቶ ከእሳት ተርፎ በእሳት ላይ ተጫምቶ ሌላውን እኔ የምላቹሁን ካልሰማቹሁ ዋ በማለት ባርነት/ነጻነት የሚል ምርጫ የሰጠ አረመኔ መንግስት ነው። ለዚህም ዋና ምስክር የሚሆነው አሁን ኤርትራ ያለችበት ሁኔታ ነው። አፍሪቃዊትዋ ሰሜን ኮሪያ! ነጻነት ጥቂቶች የሚፈነጩበት ዓእላፍ ሃበሳ የሚቆጥሩበት እንደ ኤርትራና ኢትዮጵያ አይነት ከሆነ ባፍንጫየ ይውጣ! እንደዛም በመሆኑ የአሜሪካን ምርጫ ከሻብያ የመገንጠል መርጫ ጋር ማወዳደር ተገቢ አይደለም። እኔ በአሜሪካ የፓለቲካ የምርጫ ውጤት እንቅልፍ አጥቼ አላውቅም። መስሎን ነው እንጂ ሁለቱም የፓለቲካ ፓርቲዎች ሥራቸው አንድ ነው። ለሃገር ቅድሚያ መስጠት። አሜሪካን እንደ ሰብአዊ መብት ተከራካሪ፤ ለአለም ዘብ እንደቆመች አርጎ መመልከት ራስን ማጃጃል ነው። ዛሬ በሶሪያ፤ በሊቢያ፤ በኢራቅና በሌሎችም ሃገሮች በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ነገሮችን የሚያፋልሱት እነርሱ ናቸው። ታዲያ ጥቁሩ ዓለም ራሱን ፈትሾ፤ የህዝብን ሰላምና ነጻነት ዘር፤ ጎሳና ሃይማኖት ሳይለዪ ሃገርን እንደመገንባት በድንጋይ ዘመን አስተሳሰብ ዛሬም እኔ ኢርትራዊ ነኝ፤ እኔ ኦሮሞ ነኝ፤ እኔ አማራ ነኝ ስንል ጀንበር ወጥታ ትገባለች። የጠባቦች በሽታ መርፌ አያድነውማና! ይልቅስ ከእጣት እጣት ይበልጣል በማለት እራስን ከመደለል አንድ በሚያደርገን ነገር ላይ ትኩረት በመስጠት የጥቁር ህዝቦችን ነጻነት እናስከበር። የአሜሪካ ምርጫ እንደ ኤርትራ ህዝብ ውሳኔ በማለት በዚህ ድህረ ገጽ ላይ የሰፈረውም ሀተታ ጌሾ አልባ ጠላ ነው። አክ እንትፍ ሊባል የሚገባው። የኤርትራ ህዝብ ምርጫ አልተሰጠውም ትእዛዝ እንጂ!

    Reply
    • Editor says

      November 10, 2016 09:41 pm at 9:41 pm

      Tesfa

      ስለ አስተያየትዎ ቀጥተኛ ስለሆነው ትችትዎ ከልብ እናመሰግናለን – እንደዚህ ዓይነት በጉዳዩ ላይ ትኩረት የሰጠና በሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ትችት አስፈላጊና ገንቢ ነው::

      ምርጫውን ከኤርትራ ሕዝበ ውሳኔ ጋር ያነጻጸርነው ጉዳዩ በቁሙ ሲታይ ስለሚመሳሰል ነው – “ነጻነት” ወይም “ባርነት” የሚለው አነጋገር ልክ በራሱ ነጻነትም ባርነትም የሚያመጣ አልነበረም:: በመሰረቱ ሕዝበ ውሳኔም ምርጫም ሊባል የማይገባው ነው:: ሕዝቡን ምርጫ ያሳጣ ሕዝበ ውሳኔ ነው:: የአሜሪካውም ምርጫ ሕዝቡን ምርጫ አሳጥቶት ከሁለት ገዳይ ካንሰሮች አንዱን እንዲመርጥ አስገድዶታል:: የኤርትራ ሕዝብ “ነጻነት” ብሎ መምረጡ ነጻ አላደረገውም – የአሜሪካ ሕዝብም ትራምፕን መምረጡ መረጠ አያስብለውም ነው የኛ ሃሳብ – የኤርትራው ሕዝበ ውሳኔ የተሻሉ ምርጫዎች ሊሰጡት ይገባ ነበር – የአሜሪካውም ምርጫ የተሻሉ ብቁ መሪዎች ሊወዳደሩበት እና ለሕዝቡ እውነተኛ ምርጫ ሊሰጠው ይገባ ነበር – እርስዎ እንዳሉት ለበርካታ የዓለማችን ችግሮች (የኛንም ጨምሮ – በጽሁፋችን እንዳልነው ህወሃትን ያነገሱብን እነሱው ናቸውና) ቀዳሚ ተጠያቂ አሜሪካ መሆኗን ያልተስማማን አይደለንም:: ሁኔታውን በዝርዝር ያልገለጽነው ጉዳዩ የሚታወቅ ነው በሚል ነው::

      ስለ አስተያየትዎና ቀጥተኛ ትችትዎ ልባዊ ምስጋናችን ይድረስዎ

      የጎልጉል አርታኢ

      Reply
  2. tesfai habte says

    November 11, 2016 02:17 pm at 2:17 pm

    በኢትዮጵያ ኣይደለም የኤርትራ ነጻነት የተቀማ፡ በኣመሪካ እንጂ! ብዙ የኢትዮጵያ ህዝብ የኤርትራ ነጻነት በኢትዮጵያ ሃይል የተቀማ ይመስለዋል። ነገር ግን ኢትዮጵያ የአመሪካ ተላላኪ እንቺ ራስዋ ችላ ለመኖር ያልታደለች አገር መሆንዋ እናውቃለን። የኤርትራ ህዝብ ናጽነቱ በሪፈረንደም ሳይሆን ብመስዋእት ብረታዊ ተጋድሎ የረጋገጠው ነጽነት ነው። አሁን ከትራምፕና ከምርጫው ኣመሪካ የሚያስመሳስለው ምንም ነገር የለውም። አንድ ነገር ግን ኣለ። የትራምፕ ፖሊሲ ”እኛ ለተለያዩ ሃገሮች ፖሊስ ኣይደለምን” ብለዋል። የወራበሎች የክሊንተን ጉሩብ ከኣይስስ፡ አልቃኢዳ፡ ቦኮሃራም፡ ኣልሸባብ ከሚያዋፍሩ፡ እና ዕጸፋርስ ከሚነግዱ ሰዎች ኣመሪካ መላቀቅዋ፡ እንደ ትራምፕ ወደ ስልጣን መምጣቱ፡ እንደ ኤውሮጵ፡ ጃፓን፡ ኮርያ፡ ዩክሬን፡ ፖላንድ፡ ኢትዮጵያ የመሳሰሉ በአመሪካ ትክሳ የሚነሩ አገሮች፡ ብውግያ እንደ ውሻ ትርፍ የሚያገኙ ደም ፍላት እና ተቅማጥ መያዝ መጀመሩ ታይተዋል። እኛ ድሮም አልነበርንም ዛሬም አይኖረንም!—ለወያኔ ኢትዮጵያ አሳዝነዋል!—-ምን ይደረግ አመሪካ፡ አመሪካ ብቻ የሚል ሰው መርጠዋል!—-በቃ! ትራምፕ ለአመሪካ ብልጽግና ብቻ የተመረጠ፡ የውሸታሞች፡ ወረቦላዎ፡ የውግያ ነጋዴዎች ገቢ ዝግ ሆነዋል!

    Reply
  3. tesfai habte says

    November 16, 2016 02:50 pm at 2:50 pm

    በCNN Media ፍርሃት የመፍጠር ዘመቻ እና የፍርሃት (Fear) ጨወታ!
    የፍርሃት (Fear) ሰርሳሪዎች የሚሉት ነገሮች ኣለ። እንደ ኩባ፡ በኒዝወላ፡ ኮርያ፡ ኤርትራ፡ ዝንባብወ፡ ሶማል፡ ኢራቅ፡ ሊብያ፡ ወዘተ የመሳሰሉ አገሮች በአመሪካ መንግስትና ዜና (Media) በሚፈጥሩት የፍርሃት (Fear) ዘመቻ ለብዙ አመታት በስቃይና በትግል ላይ ናቸው። የአመሪካ ፕረሲደንት ነበር ቡሽ ለኢራቁ ሳዳም ለመጥላላትና ሰይጣይናዊ ባህርይ ያለው ለመምሰል ሺ የሚያክሉ ኩርዲስታን ገደለ፡ ኒኩለር (nuclear) ሊጠቀም ይችላልና፡ ለዓለማችን ስጋት (Fear) ነው በማለት፡ የተፈጠረው ቀውስ ኣይተናል። ብአፍጋኒስታት ኣልቃዒዳ እና ጣሊባት ራሳቸው በፈጠሩት ሃገርን ዘመቱት። በሶማል ኣልሸባብ፡ ብሊብያ ሶርያ አይሲስ፡ በናይጀርያ፡ ማሊ፡ ማእከላይ ኣፍሪቃ ቦኮሃራም በመሰልጠን እና በማስታጠቅ ሃገሮች በመበታተን ናቸው። የዩኮዝላብያና ደቡብ ሱዳንን ኣይተናል።
    ዓለማችን በፍርሃት ላይ እየኖረች፡ መጀመርያ ተጠቃሚዎች የሆኑ ኣገሮች፡ የፊር (fear) ፍራፍሬዎች (ኔቶ፡ ኢትዮጵያ ወያኔ፡ ከንያ፡ ጀርመን ማርከል፡ ኮርያ፡ ጃፓን፡ ኤውሮፓ፡ የሽብር ከፋሊ ኣረቦች፡ ዩክሬን፡ ጆርጅያ፡ መድያ፡ ወዘተ ናቸው።) ከምዕራቡ ዓለም የተውጣጡ አክቲቪስቶች (Activists)፡ ወደ ሶርያ በነጨ ሰራዊት ተብሎ በመላክ ኣለፖ (Alepo) በመግባት ሃገር ወደ ቀውስ ውስጥ ገብታለች። ከ2.5 ሚልዮን ሰው ወደ ኤውሮፓ ወደ ስደት ሲያመራ፡ ህጻናትና ሰቶች የተገደሉ በተሰባቸው ይቁጠራቸው። ከምዕራቡ ዓለም የተውጣጡ በሶርያን መሪ ፍርሃት ለማሳደር፡ የራሻ መሪ ብላድሚር ፑቲን ስጋቱ ቀልብሰዋል። የበንጋዛ ኣክቲቪቲስ ብቃዛፊ ሊብያ በማመጽ ሃገር ወደ የጦር ኣውድማ ተለውጣለች። ሄሌሪ በሊብያና ኢመይል በፈጸሙት ቕጥ ያጣ ጣጣ ከፕረሲደንታዊ ምርጫ ማስወገዳቸው አይተናል።
    የፍርሃት (Fear) ለአፍሪቃ መሪዎችም በኣዲስ ኣበባ ስብሰባ ሲገኙ፡ የመድያ የፍርሃት መሳርያ የኤች.ኣይቪ.ኤድስ (HIV.AIDS)፡ ማላርያ (malaria)፡ ሁሉ ግዜ ብሞስኮት ቲቪ (TV) እየሳየ፡ የአፍሪቃ ህዝብ ለመፍራት፡ የድህነት እና ርሃብ የቅብብሎች ጨወታ ያሳያል። የኣፍሪቃ መሪዎች በምዕራቡ ዓለም ትክሻ ስለሚኖሩ፡ የመድያ ፍርሃት ከጥቅማቸው ጋር ስለሚያቋሩኑ ፍርሃቱ ኣይጠሉቱም። ስለዚ የፍርሃት (Fear) ለኣፍሪቃ መሪዎች የሚያዋጣ ሃብት ነው። ንግድ ነው። የአመሪካ ባለስልጣን ለመድያ ለፍርሃት ነው የሚጠቀሙበት። የኣመሪካ መንግስትና መድያ በኤርትራ ላይ ፍርሃት በመፍጠር፡ የየመን፡ የጅቡቲ፡ የኢትዮጵያ፡ በኤርትራ ድንበር ወተሃደራዊ ውጥረት ለማፍጠር ሞኩረዋል። የሱማል ኣልሸባብ፡ ራሳቸው በኣከባብያችን ስጋት የፈጠሩት፡ ለኤርትራ የማእቀብ ፍርሃት ኣሳድረዋል። ለወያኔ ድጋፍ እየሰጡ በኦሮማ ኣማራም ፍርሃትና ስጋት ፈጥረዋል።
    ኣመሪካኖች ልክ እንደ በኤርትራ የተደረገው በመስኮ ፍርሃት ለመፍጠር፡ ለጆርጅያ እና ለዩክሬን መንግስታት በስውር ድጋፍ በመስጠት፡ ሩስያ ላይ ወተሃደራዊ ጦርነት ለመፈጸም ተነስተዋል። ይሁን እንጂ የሩስያ ሃይል ለፍርሃት ወደ ጀብደንነት ቀልሰባል። ሩስያ ከዩክሬንና ጆርጅያ ሃገሮች ሰፊ መሬት ወስደዋል። አስፊሪዎች በጣም ተቆጡ። ግን ምን ይደረግ፡ የሩስያ ጥንካሬ ከዶላር ዓቅም በልጦ ተገኘ ማለት ነው። ዛሬ እንደትላንት ኣይደለም። ዛሬ የመድያ ፍርሃት ወደ ጉድጓድ ቆፋሪው ኣመሪካ ገብተዋል። የፍርሃት ፈጣሪ ኣሸባሪ ኣክቲቭስትስ (Activists) ከኢራቅ፡ ሶርያ፡ ሊብያ፡ ማሊ፡ ናይጀርያ፡ ዩክሬን፡ ኢትዮጵያ ለቆ እየወጣ ነው። በትራምፕ ሰላማዊ ሰልፍ በማካየድ ላይ ነው።
    በትራምፕ ላይ ፍርሃት (Fear) ለመፍጠር፡ ቅድመ ምርጫው ክሊንተን 46 በ 42 እስከ መጨረሻው ስዓት ለትራምፕ ቀድማ እንደነበር፡ ኋላ በተፈጠርው ውጤት ሰዎች እስከማመን (መቀበል) ያቃተው፡ የመድያ ጨወታ ነው። ከምርጫው ውጤት ብኋላም ፕሮፎሽናል ሰልፈኛች እየተመሩ የአመሪካ ፍርሃት ወደ ሰማይ እሽቅብ ኣውጡት። ምክንያቱም ትራምፕ የፍርሃት ኣቀንቃኝ የሚጠቀሙበት የባንክ፡ ዕጸፋርስ፡ ጦርነት፡ ሽብር፡ የብረት መሸጣ ወዘተ እንደሚያጠፋ በገለጠበት ስዓት፡ ከነዚህ ጥቅማ-ጥቅም የሚያገኙ የነበሩ የባንክ ሕሳብ ስለሚዘጋቸው ነው። እንደ ወያኔ ኣጋፋሪ፡ በሌላ ትክሻ የሚኖሩ ተላላኪዎች፡ የዶላር ቕጥረኛች፡ ስጋት ውስጥ መግባታቸው የታወቀ ነው።
    ኣንድ የፍርሃት (Fear) ጨውታ ልንገራቹ። ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት (መለስ እና ኢሰያስ) በኣልጀርስ የሰላሙ ንግግር ወይም ስምምነት ላይ በነበሩበት ስዓት፡ ኤርትራ ከመሬትዋ 40 ኪ.ሜ ወደ ኋላ እንድትመለስ በስምምነቱ ገብቶ ነበረ።
    የኤርትራ ፕረሲደንት ኣቶ ኢሰያስ ኣፈወርቅ የስምምነቱ ጉዳይ መቀበሉና ኣለመቀበሉ ለመግለጽ ንግግሩ ቅድሚያ እንዲሰጥና ለዚህ ስምምነት እንደማይቀበል ኣመሪካኖች በሰሩት ኣሻጥር ጽኑ እምነት ስለነበራቸው፡ ኢሰያስ የማይቀበለው መሆኑን የፍርሃት ሓሳብ እንደጠነሰሱት ኣረጋግጠው ነበር። ግን ከዚህ የፍርሃቱ ጥንስ መውጣት፡ የሚመጣው የዓለም መድያ የወንበዴ ስራ የተረዳ ኢሰያስ፡ ስምምነቱ የለመወላወል ተቀብለዋል። የጥንሱ ሓሳብ ያላወቀው የአፍሪቃ መሪ በደስታ ጨብጨባው ቤቱን አናወጠው። ውስጠ-ነገሩ ፍርሃቱ ለወያኔ ተሰጠ ማለት ነው። ኣመሪካኖች ያለማመን ዝም ኣሉ። ‘’ኤርትራ ሰምምነቱ መቀበል ከፈነገጠች’’ ብኋላ ወያኔዎች በአመሪካ የተሰጣቸው የመናገርያ ጽሁፍ ወድቅ በመሆኑ ወረቀቱን ወደ እሳት ወረወሩት፡ የማፋራርያ ጽሑፍ ተቃጠለ። ወያኔዎች በመድረክ በመውጣት ‘’ለኤርትራ ኣትመኑ። ይህ ሃሰት ነው። ነጭ ሃሰት’’ በማለት የማዳናገርያ አዝማምያ ለአፍሪቃ መሪዎች ፍርሃት ለማሳደር ሞኮሩ። ነገር ግን ፍርሃቱ ፍጹም ለአንዴና ለመጨረሻ በነዋል። ምክንያቱም የሰላም ንግግሮች የተካነ እውቀት ያላቸው የኤርትራ መሪዎች ፍርሃት ወደ ወያኔ እና አመሪካኖች ወርውረው ዓረፉ። የፈሪዎች ጨወታ እየቀጠለ ነው። እንግሊዝ ከኤውሮፓ መውጣትዋ፡ ኣመሪካ ለትራምፕ መምረጡ፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ለወያኔ እምቢ ኣልገዛ ብሎ ማመጹ፡ የሚያሳየው ምልክቱ ህዝባዊ ዓመጽ ብዓለማችን እየገነፈለ ነው። እስከ መቸ ነው ሰዎች በ1% elite Secret Societies የሚመራው። ብፍርሃትና በጦርነት የምንኖረው?
    Conspiracy secret societies of new world order illuminati, or the world blood cancer & Global fascist like Nazi & criminal politics who are they: –
    1. The secret of Skull and Bones (322) the elite blood lines societies
    Member this network is: – most active Bush family, Clinton, Kerry,
    Secretary of CIA
    Secretary Council foreign relation
    Secretary General of NATO
    Secretary state of US
    Head of IMF
    Head of World Bank
    Prime minister Britain Tony Blair

    2. The secret of Bilderberg the elite global domination power full societies
    Member this network is: –
    The Washington post
    The Financial post
    CNN
    BBC
    Chancellor German
    Prime minister of Japan
    Prime minister Britain Tony Blair
    Prime minister Ethiopia
    Prime minister Nigeria
    Secretary General of NATO
    Secretary of US
    Head of IMF
    Head of World Bank
    Holly wood
    Queen of Britain
    Secretary of UN

    3. The Trilateral commission to abound by president Carter’s
    North America member
    Western European member
    Japanese member

    Reply
  4. tesfai habte says

    November 17, 2016 10:43 am at 10:43 am

    New world order lead by secret elite’s illuminati means
     order to destroy nationality (Iraq, Libya, Syria, Afghanistan, Somali………)
     order to destroy Humanity, community, culture, religions, families——-
     order to accept homosexuals, drugs transactions (cocaine), fantasia, Satanism…
     order to accept only lead by secret elite’s illuminati & refuse own leader, country
     order to accept war, kill people, division with each other, global disorder & lies
     order to accept crime, fascist, racist (kill black mater), sanction on other……
     order to accept money laundering, human traffic, lobbyist, gangster leaders, ….
    now what is going & seen in the world order? After invasion Iraq, Libya, Syria, Afghanistan & Somali many people are killed & displaced. Now what are we needs, must be we defend our self. Because the past learns for present. The future builds up our self-defenses like Korea. Even a nuclear! —- no fear with nuclear! —-all thing the world balance with nuclear! —–no more fear & no more war! But must eliminate the secret societies elite’s the cancer of the world. Than future all nuclear arms are be free! —–free for fears! Free for sanction, and free for war! —always is free!
    Ethiopia is a multi-religions country, but Meles zenawi (weyane) accepted one of the order of elite’s homosexual, war, kill people……. Than,
    Flow us for free societies, dignity, true democracy! & keep our values!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule