ጊዜ ገድቦ መናገር ይከብድ ካልሆነ በቀር በኢትዮጵያ የስርዓት ለውጥ አይቀሬ ስለመሆኑ ክርክር የለም (አንዳንድ የወያኔ አንጋሽ ምዕራባውያን ባለሙያዎች በጥቂት ወራት ይተምኑታል)። ይህ እውነት ቢሆንም አንዳንድ “የፖለቲካ መክለፍለፎች” ሊወድቅ የተቃረበውን አገዛዝ እንዲውተረተር ዕድል ሊሰጠው ይችላል የሚል ስጋት ያላቸው ወገኖች ከያቅጣጫው ብቅ እያሉ ነው። የስጋታቸው መንስኤ ደግሞ በዋናነት የግልጽነት፣ ያለመተማመን፣ የውድድርና “ጊዜን” የመጠቀም ተራ እሽቅድምድም እንደሆነ እነዚሁ ስጋት የገባቸው ክፍሎች ይናገራሉ።
ከየአቅጣጫው የሚሰሙት የ“ሽግግር” ዜናዎች፣ ዳር ዳሩን በለሆሳስ ይሰማ የነበረው “የሃሜት በሽታ” ገልጠውታል። በዚሁ መነሻ ይመስላል ለኦሮሚያ የሽግግር ሰነድ እንደሚዘጋጅ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ሰፊና ግልጽ ያለ መልስ ከሚመለከታቸው የእነ በቀለ ገረባ ወኪሎች ህዝብ እየጠበቀ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ “የቱ መቀደም ነበረበት?” የሚሉ አሉ።
የኢትዮጵያን አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ ይዞ የሚታገለው “አማራ”፣ በብሔር ደረጃ ወይስ በብሔራዊ ደረጃ ቻርተር ሊያረቅ? በሚል ግራ የተጋባ ጥያቄ የሚያቀርቡ ክፍሎች፣ “ሁሉም ብሔረሰቦች በግል ሊሮጡ?” ሲሉ ይጠይቃሉ። ሁሉንም የሚያገባባ ሰነድ ማዘጋጀትና ውሳኔውን ለህዝብ መተው እንደሚሻል በመጠቆም ያገባናል የሚሉ ወገኖች በአንድነት መክረው አንድ የመሸጋገሪያ ሰነድ ለማዘጋጀት አለማሰባቸው ያስገረማቸውም አሉ። ሁሉም ያለውን ቢል አሁን ይፋ የሆነው የኦሮሚያ የሽግግር ቻርተር ጉዳይ አንኳር ጉዳይ ለመሆን በቅቷል።
ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ ቢቢኤን ያነጋገራቸው በኬተሪንግ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር የሆኑት ሕዝቅኤል ገቢሳ ግልጽ ያለ ምላሽ ሰጥተዋል። እንደ እሳቸው አባባል ዛሬ “አማራ የለም ለምን ትላላችሁ?” የሚሉ ክፍሎች ተነስተዋል። “የጎንደር ትግል” እየተባለ ትግሉን የማሳነስ ጉዳይ አግባብ እንዳልሆነ የሚናገሩት ክፍሎች “ትግሉን የአማራ ትግል” እንዲባል እየወተወቱ ነው። ዶ/ር ሕዝቅኤል አያይዘውም “ተወደደም ተጠላም አሁን ውጤት እያመጣ ያለው በብሔር እየተደራጁ ያሉ ሃይሎች ናቸው። ስለዚህ በብሔር ደረጃ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ግድ ነው” ሲሉ ቀዳሚው ተግባር ሁሉም በ“የቤቱ” ስራውን ሰርቶ በአገር ደረጃ አንድ ማዕድ ላይ መቅረቡ አማራጭ መሆኑን ጠቅሰዋል።
እንዲህ ያለውን ዝግጅትና ውይይት ማድረግ አግባብነት ያለው፣ ዴሞክራሲያዊና ህጋዊ የሆነ መሆኑንን ያመለከቱት ሕዝቅኤል በኢትዮጵያ ደረጃ የሚደረግ ውይይት ስለመኖሩም ጠቁመዋል። ይህ አካሄድ ስርአት የጠበቀ ሆኖ ሳለ የተለያየ ስም መስጠት፣ ጥርጣሬን፣ አለመተማመንን ማንገስና መፈራራትን መስበክ አግባብ አለመሆኑንን አስረድተዋል። አያይዘውም አሁን በተቀጣጠለው የሕዝብ ትግል “ኦሮሚያ ትገንጠል” የሚል አላማ የሚያራምዱ ሃሳቦች ጭራሹኑ እንደማይሰሙ ነው ያመለከቱት።
የታሪክ ምሁሩ ሕዝቅኤል ገቢሳ ኦሮሞ የኢትዮጰያ መሰረት መሆኑን፣ ከጣሊያን ወረራ ጀምሮ ኦሮሞዎች አገርን ከወራሪ ሃይል ለመታደግ ህይወታቸውን መከስከሳቸውን፣ በኤርትራ፣ በሶማሌ ወረራና አሁን በቅርቡ በባድመ ህይወታቸውን መክፈላቸውን አንስተው እንዴት ይህ ህዝብ አይታመንም የሚል እንደምታ ያለው ማሳያ አቅርበዋል። እሳቸው እንደሚሉት ተራ ጥርጣሬና አለመተማመን ካልሆነ በስተቀር ተከባበሮ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር አይቸግርም።
በዚሁ ቃለ መጠይቅ ላይ ሌላ ተጋባዥ የነበሩት አቶ ጃዋር መሐመድ በበኩላቸው “ቅድመ ዝግጅት ካልተደረገ አደገኛ ነው” ሲሉ ግብጻውያን አብዮት ካካሄዱ በኋላ ሌላ አምባገነን እጅ ላይ መውደቃቸውን፣ የቱኒዚያ የለውጥ ሃይሎች አስቀድመው ዝግጅት በማድረጋቸው የተሳካ ሽግግር ማድረጋቸውን ዋቢ ያደርጋሉ። ሊቢያ መተራመሷንም ያወሳሉ። ስለዚህ ሁሉም፣ አማራዎችን ጭምር የራሳቸውን ዝግጅት አድርገው ስምምነቱ “በብሔራዊ ደረጃ መሆን አለበት” የሚሉት ጃዋር፣ በአገር ደረጃ ያለውና በብሔር ደረጃ ያለው አስተሳሰብ መጥራት እንዳለበት ማሳሰቢያ አዘል ሃሳብ ሰንዝረዋል።
ከለውጡ መጋጋል ጋር ግንባር የሆኑት ጃዋር መሐመድ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ሃላፊ ከመሆናቸው በዘለለ የትኛውን ተቋምና የፖለቲካ ድርጅት ወክለው መግለጫ እንደሚሰጡ ግልጽ አይደለም። አቶ ጃዋር ራሳቸውን ስልጣን የማይፈልጉ አክቲቪስት መሆናቸውን በተደጋጋሚ ቢናገሩም፣ በወሳኝነትና በሙሉ ስልጣን የሚሰጧቸው መግለጫዎችና አስተያየቶች ብዙ ጊዜ አነጋጋሪ ናቸው።
በርካቶች ሲሉ እንደሚሰማው አንዳንዴ ሰፊ ምክክርና ማስተዋል የሚሹ ጉዳዮችን ጃዋር መሐመድ እንደ ቀላል ጉዳይ ይናገራሉ። እነዚሁ ክፍሎች ጃዋር አሁን ያላቸውን የነቃ ተሳትፎ ባይነቅፉም እንደ በሰለ ሰው ንግግራቸውና አቀራረባቸው የሰሚዎችንና የጉዳዩን ባለቤቶችን ቀልብ ሊስብ ይገባል ባይ ናቸው። እንዲያውም አካባቢያቸው ያሉ ፖለቲከኞች በቁልፍ ጉዳዮች ላይ እሳቸው ስለሚሰጡት መግለጫዎች ምክክርና ጥንቃቄን እንዲያደርጉ ይመክራሉ። እንደ መሪም ማብራሪያቸውን በተዋበ መንገድ እንዲያስተላልፉ እንዲመክሯቸው የሚያሳስቡም አሉ። ጃዋር ከስሜት በራቀ መልኩ በግልጽ የቀረበላቸውን ምክር ቢቀበሉ የእነ በቀለ ገርባን አሻራ ሊከተሉ የሚችሉ ሰው እንደሚሆኑም ያመለክታሉ።
ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት እሳቸው በሚመሩት ሚዲያ የሚቀርቡ የኦሮሞ ምሁራን በርጋታና በፍጹም ሊደመጥ በሚችል መልኩ የሚያቀርቡት ገለጻ የተዛነፉ የሃሳብ ሚዛኖችን እያስተካከሉ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ህዝብ ወደፊት መክሮና ዘክሮ ውሳኔ በሚሰጥባቸው ጉዳዮች ላይ አስቀድሞ በስልጣን መናገር አድሮ ከውስጥም ከውጭም አደጋ ሊጋብዝ እንደሚችል አስተያየት እየተሰጠ ነው። ለህወሃት የፕሮፖጋንዳ ፍጆታ የሚዳርግና ጅምራቸው መልካም የሆኑ አካሄዶችንም የሚጎዳ ሊሆን እንደሚችል ግንዛቤ ሊወሰድ እንደሚገባ የሚያሳስቡ ጥቂት አይደሉም።
በቅንጅት የፖለቲካ ወቅት ሁሉም አመራሮች እንዳሻቸው መግለጫ እንዲሰጡ መፈቀዱ መጨረሻ ላይ ለህወሃት ቅስቀሳ ተጋላጭ እንዳደረጋቸው፣ ሚዲያዎችም አጀንዳ ከማስያዝ፣ ሁኔታዎችን ከመዘገብ፣ ከመተቸትና ሚዛናዊ ዘገባ ከማቅረብ በዘለለ የትግሉ ስትራቴጂ ነዳፊ የመሆን ጣለቃገብነት ማሳየታቸው ትግሉን እንደጎዳው ያስታወሱ ክፍሎች፣ አሁንም ተመሳሳይ ጥፋት እንዳይሰራ ይፈራሉ። ፍርሃቻቸውንም ሲገልጽ የሚዲያ መሪዎች “ከመክለፍለፍ ፖለቲካ” ራሳቸውን በማግለለ የፖለቲካ ውሳኔዎችን ለፖለቲከኞች እንዲተውና የህዝብን ሃሳብ በነጻነት እንዲያራምዱ ይመክራሉ። ክርክሮችን በማዘጋጀት ህዝብን ግራ የሚያጋቡ ጉዳዮችን ማጥራት ላይ ቢያተኩሩ እንደሚሻል ይጠቁማሉ። በሌላም በኩል ጃዋር እንዳሉት የሰዎችን ወይም የድርጅቶችን ሃሳብ ካለመረዳት ውስን ሃረጎችን በመምዘዝ ማጸጽ አደጋው የከፋ ስለሚሆን ጥንቃቄ ሊወሰድበት የሚገባ አቢይ ጉዳይ ስለመሆኑ ይናገራሉ፤ ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብት እንዳለ ሆኖ አስተያየት ሰጪዎችም ይህንኑ አመለካከት ይጋራሉ!!
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ውክልና ሳያገኙ አገርና መጪውን ትውልድ ችግር የሚያወረሱ ልሂቃኖች እንደሆኑ ባለፉት የለውጥ ሂደቶች ላይ ታይቷል። ሁሉንም ወደኋላ ብንተወው እንኳን ህወሃት የቅርብ ምሳሌ ሊሆን ይችላል። በራሳቸው የልደት ታሪክ ህወሃት ዱር ቤቴ ያለው ደርግ ወደ ስልጣን በመጣ በዓመቱ አካባቢ ነበር። ደርግ አዲስ አገዛዝ ሆኖ ሳለ እነሱ “የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር” ብለው በረሃ ሲገቡ ህዝብ ስለመገንጠል ጉዳይና አጀንዳ የሚያውቀው ነገር አልነበረም። የራሳቸው አባላት በተለያዩ ጊዜያት እንደመሰከሩት ሁሉም የሆነውና የተጠነሰሰው ህዝብ ውክልና ሳይሰጥ፣ ህዝብ ሳይጠየቅ፣ ከጥቂት ቅጥረኞች በስተቀር የሸፈቱት ራሳቸው በቂ ግንዛቤ ሳይዙ ነበር። ዛሬም ለዚህ ነው ያለፈውን ስህተት ላለመስራት ጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባል የሚባለው። ሁሉንም ጉዳይ በጥቅሉ በአገር ደረጃ አዘጋጅቶ ቀሪውን ጉዳይ ለህዝብ መተው ከታሪክም፣ ከኪሳራም፣ በተለይም ከኅሊና ህመም ያድናል በሚል ርጋታና ማስተዋል እንደሚያሻ በስፋት እየተነገረ ነው።
የኦሮሚያ ቻርተር – መሠረታዊ ሃሳቦች
አሁን በኦሮሚያ ትግሉ ያመረረበት ደረጃ ደርሷል። ይህ ትግል መሰባሰብና ወደ አንድ የዕዝ ቋት /ኮማንድ ፖስት/ መግባት እንዳለበት ታምኗል። ይህንን ለማድረግ ደግሞ አንድ ሁሉንም በኦሮሚያ ክልል ላይ ያገባኛል የሚሉትን ድርጅቶች ሊገዛና ሊመራ የሚችል ቻርተር ማዘጋጀት ግድ ሆኗል። ጥያቄው ያለው ይህ ቻርተር ከሌሎች ህብረ ብሔር ድርጅቶች ጋር ግንባር/የጋራ መድረክ ፈጥረው የሚሰሩትን የኦሮሞ ድርጅቶች እንዴት ያስተናግዳቸዋል? የሚለው ነው። ምክንያቱም ለጎልጉል መረጃ እንዳቀበሉ ክፍሎች ግርድፍ ሃሳብ፤ ቻርተሩ ማንም ድርጅት በቻርተሩ ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ፣ በግሉ ከማዕቀፉ ውጭ ካሉ የፖለቲካ ተቋማት ጋር ስምምነት ማድረግን በተመለከተ ድርጅታዊ ነጻነቱ ላይ ገደብ የማድረግ ሃሳብ ስላለበት ነው።
የቻርተሩ “ነፍስና ልብ” የሚባሉትን ሁለት ጉዳዮች እንያቸው። ለጎልጉል መረጃ የሰጡና ከጉዳዩ ጋር ቅርብ ግንኙነት ያላቸው የብሔሩ ተወላጅ እንዳሉት መሳሪያ ያነገቡና በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ድርጅቶችን በሁለት ከፍሎ የሚያየው ቻርተር ሁለቱንም ዓይነት ሃሳቦችን እንደ ፍጥረታቸው በጋራ ይገምዳቸዋል። አገር ውስት በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉት ህወሃት እንዲታዘዙ ከሚያስገድዳቸው አንጻር ጉዳያቸው በልዩ መንገድ የሚታይ ይሆናል፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉት ግን በአጠቃላይ የኃይል አማራጭ በመያዝ ትግል ሜዳ ያሉትን በአንድ፣ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉትን በሌላ ከፍሎ የሚገምዳቸው ይህ ቻርተር ጊዜያዊ ይሆናል።
መሳሪያ ያነገቡ ሁሉ ጠላታቸው ወያኔ ከሆነ፣ እሱን ለማውረድ የሚታገሉ ከሆነ የማያስማማቸው ነጥብ ለኦሮሞም ሆነ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ግልጽ አይደለም። ሁሉም በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉት የኦሮሞ ድርጅቶች በሙሉ ሃሳባቸውና እምነታቸው ወያኔን በሰላማዊ መንገድ መጣልና ህዝብን የሥልጣን ባለቤት ማድረግ ከሆነ እነርሱንም የማያስማማቸው ጉዳይ ግልጽ አይደለም። በዚህ መነሻ ቻርተሩ እነዚህን ሁለት ዓይነት ኃይሎች ባንድ ገምዶ ለቻርተሩ እንዲገዙ ያደርጋቸዋል። ሌላ አጀንዳ እስከሌላቸው ድረስ!
በዚሁ መሰረት ቻርተሩ አንድ ድንበር ያለው ጊዜያዊ መግባቢያ ይሆናል። ይህንን ድንበርና ገደብ የሚያበጀውን ቻርተር መቀበልና ፈርሞ አባል መሆን ማለት በተቀመጠው ገዢ ህግ መመራት ማለት ይሆናል። ቻርተሩ መተዳደሪያ ደንብ ሆኖ ሲተከል ከሁሉም ድርጅቶች የሚውጣጡ አስፈጻሚ አካላት ይኖሩታል። ተግባራዊ ሲሆን ማንኛውም ዓይነት ኅብረብሔራዊም ሆነ ብሔር ተኮር የፖለቲካ ድርጅት ከኦሮሞ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት ግንኙነቱ በቻርተሩ ደንብ መሰረት ቻርተሩን እንዲጠብቁ ከሚሰየሙት ክፍሎች ጋር ይሆናል ማለት ነው።
ዝርዝሩን ለጊዜው በጥልቀት መተንተን ቢያስቸግርም ይህ ቻርተር የድርጅቶችን ውስጥዊ ነጻነት እንዳያንቅ ፍርሃቻ ስለሚኖረው ሊያከራክር እንደሚችል ይገመታል፤ እንደ መረጃው ሰው ግን በአገር ቤት በ“ህግ” ተመዝግበው የሚሰሩትንም ሆኑ ከሌሎች ኅብረብሔርና የብሔር ድርጅቶች ጋር ግንባር የፈጠሩ የኦሮሞ ድርጅቶች ጉዳይ ባግባቡ የሚስተናገዱበት አግባብ እንደሚኖር ይጠቁማሉ። እሳቸው ይህን ቢሉም ታዛቢዎች ይህ ጉዳይ አዳጋች እንደሚሆን ከወዲሁ እየተናገሩ ነው። በዚህም መነሻ ቻርተሩ ጠብመንጃ ያነሱት ላይ ቢያተኩር እንደሚሻል ይጠቁማሉ።
ሌላኛውና ዋናው ጉዳይ አገር ቤት ያሉትም ሆነ፣ በውጪ አገር ሆነው በትጥቅ ለመፋለም የወሰኑ ክፍሎች ሠራዊታቸው ወደ አንድ የዕዝ ማዕከል /ኮማንድ ፖስት/ እንዲካተቱ መታሰቡ ነው። ጃዋር መሐመድ ለቢቢኤን እንዳሉት ተመጣጣኝ ኃይል ያላቸው ክፍሎች ወደፊት ችግር ውስጥ እንዳይገቡ አስቀድመው ሃይላቸውን ሁሉ ወደ አንድ ዕዝ ማዕከል ማስገባታቸው አደጋን ያስቀራል። ይህ አስተሳሰብ ኦሮሚያ “መከላከያ ሠራዊት የመገንባቱን ሥራ ከወዲሁ አጠጠናቅቃ፤ አለያም ወጥ ሠራዊት ማደራጀት ትጀምር” እንደማለት ይሆናል።
በዚህ ጉዳይ ላይ አስመራ የከተሙት የኦነግ /ብዙ ኦነጎች አሉ/ አመራሮች ይፋ አስተያየት ባይሰጡም ቻርተሩን ከተቀበሉ ወታደራዊ ኃይሉ ወደ አንድ ቋት ሲገባ የኃይል አሰላለፍ ላይ ስምምነት ለመድረስ ቀላል እንደማይሆን የሚገምቱ አሉ። እዚህ ላይ በኦሮሚያ ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ በአገሪቱ የተቀናቃኝ ፖለቲካ ደርጅቶች ዘንድ ያለው ልብ የሚያደማ ጉዳይ ይነሳል። የፖለቲካ ፕሮግራማቸው ካንዱ የተገለበጠ የሚመስለው የተቃዋሚ ድርጅቶች እርስ በእርስ ሲላተሙና ህዝብን ተስፋ ሲያስቆርጡ የመኖራቸው ምሥጢራዊ ምክንያት ለማንም ዜጋ ግልጽ አይደለም። እንደውም ተስፋ አስቆራጮች ሆነው የኖሩ አሉ። አንዳንዶቹም ቲተርና ማህተም፣ በየወቀቱ የማይታደስ ድረገጽ ይዘው ከመንከላወስ ሳያልፉ መኖራቸውን የሚያውጁት ለመስራት የሚንቀሳሰቀሱትን ሲያወግዙና ሲኮንኑ ነው።
ዛሬም ኦሮሚያ ላይ ይህን “መበታተን” ያሉትን ጉዳይ ለማስወገድ የሚዘጋጀው ጉዳይ ከወዲሁ እንከን እንዳይገጥመው ፍርሃቻ አለ። አንድም “ከመክለፍለፍ”፣ አለያም ዓላማን ግልጽ ካለማድረግ የሚነሱ ጉዳዮች ግማሹን በጥርጣሬ፣ ግማሹን በግል የሥልጣን ስካር እንዳይከፋፍሉት የሚፈሩ፣ አሁን ብቅ ያሉና የረጋ ስብዕና ያላቸው ክፍሎች ጉዳዩን በጥንቃቄ እንዲመሩት ይመክራሉ። በተለይም ዶ/ር ሕዝቅኤል ገቢሳ፣ ዶ/ር ጸጋዬ አራርሣ፣ ዶ/ር አወል ቃሲም አሎና እነሱን መሰል ዜጎች ጉዳዩን በጥንቃቄ እንዲይዙት የሚወተውቱ ጥቂት አይደሉም።
“ከመክለፍለፍ ፖለቲካ ክስረት፣ እንዲሁም የማይነሱበት ውድቀት እንጂ ሌላ ትርፍ የለም” የሚሉ ክፍሎች ይህ አሁን እየፈሰሰ ያለውን ደም፣ የእናቶች እምባ፣ የንጹህ ዜጎች ሰቆቃ የሚያሽር ታሪክን የሚቀይር ሃሳብ ከዚህ ትውልድ እንደሚጠበቅ እምነት አለ። አገራችን በደም ታጥባለች። ትኩስ ቁስል ላይ ነች። ወገን፣ ዘር፣ ጎሣ፣ ብሔር ሳይለይ ሐዘን ሁሉንም ስብሮታል። ታላቅ የሆነ ብሔራዊ መግባባት አለ። እዚህ የተደረሰው በቀላሉ አይደለም። እንደ ህወሃት መሠሪ አሠራር ሳይሆን ባጭሩ ሊባል በሚችል ጊዜ ይህንን ዓይነት መግባባት ላይ መደረሱ እንደ ታላቅ ድል ሊቆጠር ይገባል። ከዚህ ወደ ኋላ መመለስ በሕዝብ ደም መቀለድ ነው። ውጤቱም የዜሮ ድምር ጨዋታ ነው።
ባለፉት 25 ዓመታት ለመታዘብ እንደተቻለው በኢትዮጵያ የተመሠረቱና እስካሁንም እየተመሠረቱ ያሉት ድርጅቶች (በተለይ ጎሣዊ ትኩረት የያዙት) ሕዝብ “ተመሥረቱልኝ” ብሎ ጠይቆ ወይም ከሕዝብ ጋር ተማክረው ሳይሆን “እናውቅልሃለን” በሚል አስተሳሰብ ነው ራሳቸውን ያቋቋሙት። በዚህ እሳቤ ላይ በመመርኮዝ ተመሥርተው ሃሳባቸውን በፕሮፓዳንዳ መልክ በሕዝብ ላይ በመጫን ሕዝብ ያላሰበውን እንዲያስብ፤ ያልተመኘውን እንዲመኝ፤ ያልሆነውን እንዲሆን አድርገውታል፤ ስያሜና መጠሪያም ሰጥተው አሳንሰውታል። ከመተለቅ ማነስን አጀንዳቸው በማድረግ ድብልቁን ሕዝብ መኖሪያ አሳጥተውታል፤ ኢትዮጵያዊነትን አመናምነውታል። ይህ አሁንም እየሆነ ያለ ሃቅ ነው። በዘር መደራጀት የሚሠጠው የግል ጥቅም ቢኖርም ውጤቱን ግን እንደገና መመለስ እጅግ ሲከብድ ተመልክተነዋል። ትልቅን ነገር ማሳነስ ሊቀል ይችላል፤ ያነሰን ነገር መልሶ ማተለቅ በጣም ከባድ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በሰብዓዊ ፍጡር፣ በአገር፣ በትውልድ፣ … ላይ ሲደረግ ማንነትን፣ ኅልውናን ያጠፋል።
ጎንደር ላይ በተሰማው “በኦሮሚያ የሚደረገው የወንድሞቻችን ግድያ ይቁም” በሚል መፈክር ከ40 ዓመት በላይ በፓርቲዎች፣ በአርነት ንቅናቄዎች፣ በጎሣ ድርጅቶች፣ … ያልተሳካ ጉዳይ በህዝብ በቀላሉ ተፈታ። ሕዝብን ማዳመጥ አሁንም ለበርካታ ጉዳዮች መልስ ይሠጣልና የኦሮሞው መብት፣ የአማራው መብት፣ የ… መብት የሚለው አስተሳሰብ ወደ “ሕዝብ ምን ይላል” አስተሳሰብ ቢለወጥ በርካታ ችግሮች መፍትሔ ያገኛሉ።
የፖለቲካ ድርጅቶች በዓላማነት የሚያስቀምጡት፤ አመራሮቻቸው የሚናገሩትም ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ማድረግ ነው። ወደ ሥልጣን መንበር እየተቀረበ ሲመጣ ግን የትግል ዲስኩር ይቀየራል። ሕዝብ በደሙ ታሪክ እየጻፈ ድል እያስመዘገበ ሲመጣ ከጀርባ ያሉት ኃይሎች “የመክለፍለፍ ፖለቲካ” ውስጥ የመግባት ሁኔታ እያሳዩ ነው። ይህ ከቀጠለ ደግሞ ወያኔ አፈር ልሶ እንደገና እንዲነሳ በር ይከፍታልና፤ ጥንቃቄና ስክነት ያስፈልጋል። ሕዝብን ከፖለቲካ ክስረት መታደግ ያስፈልጋል። ሕዝብን ተስፋ ከማስቆረጥ መታቀብ ያስፈልጋል። ሕዝብን ውዥንብር ውስጥ አለመክተት ያስፈልጋል። ሁኔታዎች በወጉ ተመክሮባቸው ሳይበስሉ ለማኅበራዊ ሚዲያ ፍጆታ ማዋል አንዳች የሚረባ ነገር የለውም። በርን ዘግቶ፤ ጉዳይን እዚያው ወቅጦ፤ ሲያልቅ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ እጅግ አዋቂነት ነው።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
GETACHEW REDA says
Freom GETACHEW REDA (editor Ethio Semay)
“እሳቸው እንደሚሉት ተራ ጥርጣሬና አለመተማመን ካልሆነ በስተቀር ተከባበሮ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር አይቸግርም።
ግማሹን በግል የሥልጣን ስካር እንዳይከፋፍሉት የሚፈሩ፣ አሁን ብቅ ያሉና የረጋ ስብዕና ያላቸው ክፍሎች ጉዳዩን በጥንቃቄ እንዲመሩት ይመክራሉ። በተለይም ዶ/ር ሕዝቅኤል ገቢሳ፣ ዶ/ር ጸጋዬ አራርሣ፣ ዶ/ር አወል ቃሲም አሎና እነሱን መሰል ዜጎች ጉዳዩን በጥንቃቄ እንዲይዙት የሚወተውቱ ጥቂት አይደሉም።”
You guys are collective of journalists (if true). And yet, you are telling us “…ዜጎች ጉዳዩን በጥንቃቄ እንዲይዙት የሚወተውቱ ጥቂት አይደሉም።” (I guess you are talking about the secessionists and narrow Oromo elements and their charter issue and the organizers)- who are the ጥቂት አይደሉም who are the advisors you are referring to? We wish you tell us who these advisors are. In fact you are telling us the so called ጥቂት አይደሉም advisors are advising the Oromo secessionist agenda (call it ‘Charter’ to make you happy) to be lead or guided by the same nihilist group who wave the secessionist OLF flag and same group who advice and argue and vow Latin the colonialist language alphabet to be implemented in ten future Oromia (I can’t say Ethiopia- because they have no agenda for Ethiopia to begin with- their agenda is Oromia first agenda)- these elements are “ዶ/ር ሕዝቅኤል ገቢሳ፣ ዶ/ር ጸጋዬ አራርሣ፣ ዶ/ር አወል ቃሲም አሎና እነሱን መሰል ዜጎች “ . You got to be kidding us!
Do you know these elements? Particularly the two most vicious nihilist whom their office and shelve books is decorated by the secessionist OLF flag? They honored this criminalist flag as credited and respected flag—are they? Was not this flag hoisted when thousands of Amhara perhaps millions were murdered or chased out of “Oromiya” ? These nihilist elements are still hoisting the same flag and yet your ጥቂት አይደሉም advisors are referring the Oromo mission to be guided these people? What is the different between the Mencha revolutionary SheiKK/Mulah Jawar Mohammod and these elements? Have you ever read their writings/books, interviews before?
‘ታላቅ የሆነ ብሔራዊ መግባባት አለ።እዚህ የተደረሰው በቀላሉ አይደለም።’ Please!!!!! What is that mean? ‘ታላቅ የሆነ ብሔራዊ መግባባት አለ። Really? Where?
“ባጭሩ ሊባል በሚችል ጊዜ ይህንን ዓይነት መግባባት ላይ መደረሱ እንደ ታላቅ ድል ሊቆጠር ይገባል።” seriously I am puzzled and lost here. Where and whose whome and who are these groups you are talking about ?
“ሕዝብን ማዳመጥ አሁንም ለበርካታ ጉዳዮች መልስ ይሠጣልና የኦሮሞው መብት፣ የአማራው መብት፣ የ… መብት የሚለው አስተሳሰብ ወደ “ሕዝብ ምን ይላል” አስተሳሰብ ቢለወጥ በርካታ ችግሮች መፍትሔ ያገኛሉ።” I thought you said “‘ታላቅ የሆነ ብሔራዊ መግባባት አለ” if there is why then there is የአማራው መብት፣ የ… መብት የሚለው አስተሳሰብ…..concerns you if indeed there is ‘ታላቅ የሆነ ብሔራዊ መግባባት አለ። ?
“የፖለቲካ ድርጅቶች በዓላማነት የሚያስቀምጡት፤ አመራሮቻቸው የሚናገሩትም ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ማድረግ ነው። ወደ ሥልጣን መንበር እየተቀረበ ሲመጣ ግን የትግል ዲስኩር ይቀየራል።” here I agree with you. Unless, criminals persecuted in thee international court (OLF/TPL and others for the crime they did) and unless as you mentioned above የኦሮሞው መብት፣ የአማራው መብት፣ የ… መብት የሚለው አስተሳሰብ abandoned as this is itself Fascism tendency, there will not be healthy Ethiopia. What you will see is Oromia and Tigria, Amharia sloganeers and their flag destroying themselves and thee country. All these groups are nihilists and dangerous snakes who kipoison the people of Ethiopia.
Good luck with Fascism coming and reborn in the future of Ethiopia after the current Tigrayan fascism is removed.
Getachew Reda (Editor Ethio- Semay)
Getachew Reda says
Dear Editors;
Thanks for posting my comment. The so called opposition media as you excellently described it on your commentary above “የሚዲያ መሪዎች “ከመክለፍለፍ ፖለቲካ” ራሳቸውን በማግለለ የፖለቲካ ውሳኔዎችን ለፖለቲከኞች እንዲተውና የህዝብን ሃሳብ በነጻነት እንዲያራምዱ ይመክራሉ” is the right description. As you have been perhaps reading me for many, many years over and over that my commentaries are not welcome on any of the so called opposition media- this is due to their involvement in what you excellently described it “ከመክለፍለፍ ፖለቲካ”. They do not want me to expose or being critique of their political leaders as they are their cults. These media are ridiculous and shameful media who simply do
not know what they were doing for the last many years. Their media is still serving the subversive groups or the old establishments who are politically corrupt, visionless and many of them are criminals who were involved in ethnic atrocity or mass murder. Therefore those opposition media are proud to be tools for these subversive criminals who used politics to hide their crime. This is why I was confronting the so called “opposition media” who are deeply involved in the ከመክለፍለፍ ፖለቲካ serving few and refuse to post my message to my people. Is there any crime in media than closing doors for some patriotic Ethiopians from reaching their people while they serve criminals and subversive nihilists? Ethiopians need to confront criminals who have been hiding themselves in political organizations from getting prosecuted. All they do is subvert so justice will not served, all they do is derail the direction of Ethiopianism from reaching its goal. If Ethiopia stays as a proud nation- they know they will be accountable in the court of law for the ethnic cleansing and mass murder they committed. Atrocity upon millions of our people was carried by these elements – and yet no one seemed to care or concern or want to talk about these criminals. The media, the politicians, the elites, activists are al playing in the same house as if nothing happen in the last 25 years. They shake and laugh and sleep talk and drink hug with these criminals. The people who got murdered are inside grave screaming for justice and yet they ignored them. How pathetic!!!! Look, how many times was Mulah Jawar Mohammed vowed openly to evict Ethiopians out from his Oromia? and yet, none VOA, Ethiomedia, Zehabesha, Heber radio, (ESAT – though no one expect them such will come out from them , since they are the first promoters of this young ‘Mulah’) you name them scores of radios and TV media – none of them asked him to apologize for his Fascistic and nihilist crime for vowing Ethiopia out of Oromia before he opens his filthy politics on their media!
To demand Ethiopians to be evicted from their own country is a big crime. And yet, as he said it openly “The Habeshaa media will not function without me’- said Jawar – ‘that is exactly why they keep coming to me to interview me. They have no politician to talk, but me” said Jawar.
I do not blame him for boasting on them. These are useful idiots calling themselves journalists or media owners bringing him twice a week as if there is no politician on the land of Ethiopia. It is a great corruption on those Diaspora opposition media (including the media in Ethiopia who calls him YE-POLETICA TENTANG”. Shame on these ignorant opposition media. You are right to say የሚዲያ መሪዎች “ከመክለፍለፍ ፖለቲካ” ራሳቸውን በማግለለ…….’
Any way,what I like to say is thanks for posting my comments. You are good. Take care!!!!!!
Thanks again Getachew Reda (Editor Ethio Semay)
Mulugeta Andargie says
እንደ ዛሬ ሲስቶዲን ሳይሰራጭ:ያገር መዳኒት ለኮሶ ትል
ከዛፍ ተሸምጥጦ: ተጭቶ: በውሃ ተበጥብጦ:ጣፋጭ ሳይን መረር የሚል
እንደ ዠግና የሚያስፎክር:ኮስተር ኮስተርተር የሚያስብል
መረር የሚል!!
እንጂ: የሚጣፍጥ ሳይሆን: የሚመር:ግን ገዳይ የኮሶ ትል
የውጭ ክኒን ሳንሻ:ምን ቢመር:ከጉረሮ አንቆርቁረን:“ዶሮ ማታ!“ ብለን
ነበር:ያኔ ወግ ሲለን:ወግ ብለን::
ዛሬ ግን ለይቶልን!የኮሶ ፍሬ ላንሸመጥጥ
በታብሌት መገላገል:ሳይመር ሳይሰነፍጥ
በቀላሉ መገላገል!
እንዲያ ነበር የስጋ ትል!!
ደርሶ ሳይጣባኝ:
ወዳጅ ሆኖ ሊግተኝ!?
አጉል አሳቢ ሆኖኝ
ሊያስጎነጨኝ?
እየመረረኝ?
ያውም ላያሽረኝ??
ጠጣ ሊለኝ?
ከጀለኝ??
አንድ የድሮ ወዳጄ የሚያውቀኝ
የጥንት ወግ አንስቶ ቢያወጋኝ
የማውቀው ሆኖ ሲያየኝ
መደጋገም ሆኖ ታይቶት! ታይቶኝ!
ኤጭ!ተሰለቻቸን መሰለኝ
የማውቀውን ሊጠርቀኝ!?
ምነው አቴ!ኧረ በቃኝ!
እንደ ባቡር ወደ ኋላ አትንዳኝ!
እንደ ካሮት ስር ወደ ታች አታፋፋኝ!!
ኧረ በቃኝ! ያጼነት ዘመን ይብቃኝ!!!!
በለው! says
__ “ዘመኑ የትብብርና አጋርነት ነው…ኢትዮጵያዊ ማንነት (አንድነት) የሚባል ነገር የለም! ኢትዮጵያዊነት የትግር እና አማራ ነው ለእነ ፓስፖርት ብቻ ነው” የሕግ ምሁር ዶ/ር ጸጋይ አራርሳ…. ድንቅ ቪዥን (ምድረ ደንባራ!) በለው!
*** ከሁሉ አስቀድሞ እንደተለመደው ጋዜጠኛ ካሳሁን ስቦቃን በጣም አደንቃለሁ አመሠግናለሁ:: በእውነትም በሙያው ተክኗል: አይፈራም! ያለውን አወዛጋቢ ብዥታ : በጥርጣሬ የሚባለውን ሐሚትና ተቃውሞ ሕዝብን በሚያነጋግሩም ሆነ በሚያደናብሩ ሐሳቦችን በሚገርም ሁኔታ እንደወረዱ ያቀርባቸዋል::
~~ ዶ/ር ፀጋዬ ረጋሳ ሙያቸውን በተመለከተ የተምታታና የተወሳሰበ ፍላጎትና መሪ ያለው ኦሮሞ ሥርዓቶች ከበደሉት በባሰና በከፋ መልክና ቅርጽ በነጻ አውጭ አመራሮቹ መብዛትና መጓተት አያት ቅድም አያቶቹ ደሙን አፍሶ አጥንቱን ከስክሶ ያቆማትን ኢትዮጵያ እንደጭራቅ ምድር አስበርግገው ከልለውና ከልክለው የበይ ተመልካች ያደርውጉትን ሰብስቦ በማነጋገር በአንድ የሐሳብ ውሳኔ በግልጽ አቋምና በሕግ ማዕቀፍ ለውጭውም ገላጋይ ለውስጡም ደጋፊ ያመች ዘንድ የቤት ሥራው ባልከፋ ነበር ::
~~~ የግለሰቡ ችግር የመጣው ከሙያቸውና ከባሕሪያቸው ውጭ የታሪክ ድሪቶ: ሌሎችን የፖለቲካ ተንታኝ (በታኝ) ወይም ታሪክ ገልባጮችንን ላለማስከፋት የተጓዙበት የ5 ደቂቃ መንገድ ሁሉንም በአስቀያሚ መልኩ ገደል ከተውት ሄዱ::
” ዘመኑ የትብብር : የአጋርነት ዘመን ነው::” ይህ ማለት ከዚህ በፊትም ጠቅሰውታል “አንድነት” የሚባል ነገር የለም አንድ አደለንም ብለዋል:: እሳቸው እንዳሉት ኢትዮጵያ የትግሬና የአማራ ማንነት ነው:: ዳቦ: ጠላ: ዶሮ: ወጥ: ነጠላና ጋቢ: የአማራና የትግሬ ነው? ለመሆኑ የሌሎችን ሀገር ኦሮሞዎች ባሕላቸውን ምግባቸውን አላውቅም የኢትዮጵያ ኦሮሞዎች በግድ ጋቢ ተጫነብኝ ዶሮ ወጥ ብላ ተብዬ ተገረፍኩ ሲሉ አልሰማሁም አላየሁም ብዙ ጥበበኛ ሸማኔ ለአማራና ትግሬ ሸጦ ግብር ከፍሎ እናንተን እዚህ ያደረሰው ከዚያው ከኢትዮጵያ በተገኘ ፍራንክ እንጂ በአውስትራሊያና አሜሪካ ዶላር አደለም::አራት ነጥብ::
** ኦነግ ስም: ባንዲራ ቦታ እየቀያየረ በህወአት /ኢህአዴግ ጥላ ሥር እጅግ በጣም ተጠቃሚ ቡድን ነው ችግራቸው ሥልጣን እንጂ ዓላማቸው አንድና አንድ ነው:: ትብብርና አጋርነት ሥልጣንና መከላከያውን እስክንይዝ አዳርሱን ማለት ነው:: ሜ/ር ጀ አበበ ተክለሃይማኖት ሕገመንግስታችንን ክሚያደንቁልን የኦሮሞ የሕግ ምሁራን ተብለው ከተጠቀሱት ዶ/ር ጸጋዬ ከብዙዎች አሮሞ አንዱ ናችው:: ዶ/ር ጸጋዬ እና ጆቤ እንደ እርሾ ይጠቅመናል ያሉት ሕገመንግስት በጥቅማጥቅም (መደለያ) እንጂ በሙሉ መብት አለመሆኑን አያውቁም? ግን ይህ ነቄ ትውልድ የአድርባይ ቦልጥቀኛ የ43 ዓመት ቁማር ገብቶታል..በቅርቡ ኢትዮጵያ ኬኛ ይላል::
** የኦሮሞ ልሂቃን ፓርቲና ባንዲራ አበዛዝ ሳሙናው ጁንዲን ሰዶ” በህወአት ባለሥልጣናት እየተገረፍኩ: እየተሰደብኩና እየተዋረድኩ ከ1983 ዓ.ም ወዲህ ግን ማንነቴ ታውቆ: በቋንቋዬ ተናግሬ: ባሕሌና ማንንቴ ታውቆ ኖሬአለሁ: የኦሮሞን ልጅ ከሌላው ወገኑ እንዳይግባባ በቁቤ ጠርንፎ : ባሕሉን እንዳይወራረስ: እንዳይጋባ ግራ አጋብቶ:ሌላው እንዱስትሪ ሲገነባ ለኦሮሞና አማራ ተከልካዮች እስታዲየምና ቢራ ፋብሪካ ሲገነባ ድመት ሆኖ ኖረ የፌደራል ሥርዓት ሳይገባው ዛሬም በሲቭል ሰርቭስ ሥራ ውስጥ ብዙ የአማራ ልጅ መኖሩ ይቆጨኛል” ይለናል ‘የሕዝብ ዓይንና ጆሮ?’ ነኝ በሚለው ኢሳት ላይ ተጥዶ!! አሁን እንደ ዶ/ሩ እብደት በባህል:በዘፈን: እንጀራና ዶሮ ወጥ:ነጠላና ጋቢ: ትግሬና አማራ ኢትዮጵያዊነት መገለጫቸው ከሆኑ አኤርትራም እኔም ኩታ ገጠም ነኝ ካለችስ? ሚስኪን ኦሮሞስ? ወይ ‘ለትብብርና አጋርነት ብቻ አብሮ ማሸቋለጥ’ ከዚያስ? ዘ ይገርም አሉ