• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አዲሷ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬተሪ በዜግነት ካናዳዊት ናቸው

November 7, 2018 03:05 pm by Editor 3 Comments

በዚህ ሳምንት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ ሴክሬታሪ ሆነው የተሾሙት ወ/ሪት ቢልለኔ ስዩም ወልደየስ በዜግነት ካናዳዊት መሆናቸው ጥያቄ አስነስቷል። ሹመታቸውም በሥራ ላይ ያለውን ሕግ የሚጻረር ነው ተብሏል።

ወ/ሪት ቢልለኔ ለማስተርስ ዲግሪ ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሁፍ “Transformative Spaces: Enabling Authentic Female Leadership Through Self Transformation – the Association of Women in Business” ወደሚል መጽሐፍ ቀይረው ባሳተሙት ገጽ 16 ላይ በትውልድ ኢትዮጵዊት በዜግነት ግን ካናዳዊት መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ከዚህ አንጻር ከታየ ሹመታቸው የሕግ ጥያቄ እንደሚስነሳ የሪፖርተሩ ዳዊት እንደሻው ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያ ይናገራሉ፤ “አዋጅ ቁጥር 270/1994፣ ‹‹የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎች በትውልድ አገራቸው የሚኖራቸውን መብት ተጠቃሚነት ለመወሰን በወጣው ሕግ መሠረት፣ ማንኛውም የውጭ ዜግነት ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ በማናቸውም የአገር መከላከያ፣ የአገር ደኅንነት ወይም በውጭ ጉዳይና መሰል የፖለቲካ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በመደበኝነት ተቀጥሮ መሥራት እንደማይችል ተደንግጓል፤” ይላል።

“በዚህም አዋጅ መሠረት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትም እንደ አንድ ወሳኝ የፖለቲካ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የውጭ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መቀጠር እንደማይችሉ፣ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ይህ ጉዳይ መንግሥት ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባው ነው። ምክንያቱም ዜጎች ለየትኛው ፖስፖርት ነው ታማኝነታቸው የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል … ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ እንዲህ ዓይነት ቦታ ላይ መቀመጥ ካለባቸው፣ የያዙትን የውጭ አገር ዜግነት መመለስ ይገባቸዋል” ሲሉ አንድ የሕግ ባለሙያ ተናግረዋል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ሪፖርተር ፕሬስ ሴክሬታሪዋን በስልክ የጥሪና የጽሑፍ መልዕክት፣ እንዲሁም በትዊተር ገጻቸው መልዕክት በመላክ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል። አለቃቸውን አቶ ሽመልስ አብዲሣንም ለማግኘት ደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት ሪፖርተር ጠቅሷል።

ሪፖርተር ለቃል አቀባይዋ በስልክ የጥሪና የጽሑፍ መልዕክት፣ እንዲሁም በትዊተር ገጻቸው መልዕክት ቢልክም መልስ ማግኘት አልቻለም። በተጨማሪም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተደርገው የተሾሙትን አቶ ሽመልስ አብዲሳን ለማግኘት የተደረገው ሙከራም አልተሳካም።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: billene, Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    November 8, 2018 06:43 pm at 6:43 pm

    የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ ሴክሬታሪ ሆነው የተሾሙት ወ/ሪት ቢልለኔ ስዩም ወልደየስ በዜግነት ካናዳዊት መሆናቸው ጥያቄ አስነስቷል።
    አዋጅ ቁጥር 270/1994፣ ‹‹የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎች በትውልድ አገራቸው የሚኖራቸውን መብት ተጠቃሚነት ለመወሰን በወጣው ሕግ መሠረት፣ ማንኛውም የውጭ ዜግነት ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ በማናቸውም የአገር መከላከያ፣ የአገር ደኅንነት ወይም በውጭ ጉዳይና መሰል የፖለቲካ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በመደበኝነት ተቀጥሮ መሥራት እንደማይችል ተደንግጓል፤›› ይላል፡፡
    በዚህም አዋጅ መሠረት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትም እንደ አንድ ወሳኝ የፖለቲካ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የውጭ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መቀጠር እንደማይችሉ፣ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
    ‹‹ይህ ጉዳይ መንግሥት ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባው ነው፡፡ ምክንያቱም ዜጎች ለየትኛው ፖስፖርት ነው ታማኝነታቸው የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል፤›› ሲሉ አንድ የሕግ ባለሙያ ተናግረዋል፡፡
    **************
    የዚህ ጉዳይ አንሺዎችና(ጋዜጠኞች) ሕጉን ያብራራው ባለሙያ(ጠበቃ) የሕጉን ትክክለኛነትና ጉድለትን አይተቹም!?ልዩ ጥቅማጥቅም
    በመሠረቱ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ( አበበ አበባና አቦቦች) ማለትን አንድ ነው ብሎ የተቀበለ ይህንንም ሕገመንግስት የሚቃወም ይሁን ማሻሻል ወይንም አንድ ቃል ቢያወጣ አፈነዳለሁ! አፈርሳልሁ! እገነጥላለሁ! ለሚሉ ዲያስፐርስ ምንም አልተባሉም። አደለም እንዴ?
    ይህ ጫጫታ ምንድነው?
    “ኢትዮጵያውያንና ትወልደ ኢትዮጵያውያን” ለነገሩ ክልላዊ ማንነት እንጂ ሀገራዊ ዜግነት ዋጋ እንዳለው ሕዝቡ አሁን እንዴት ገባው? ለዚያውም ለጠ/ሚ ወሬ ተንታኝ ለመሆን? ሀገሪቷ አዲስ ነገር አይታይበሽ ተበላ እንደተረገመች አቃቂረኛና አሽሙረኛው አፉን አሹሎ ብቅ ይላል።
    ለምሳሌ የቻይና ቲቪ ጋዜጠኛ ግሩም ጫላ ጥያቄ መጀመሪያ የሥራ ቋንቋዬ እንግሊዘኛ ስለሆነ ጥያቂዬን በእንግሊዘኛ ላቅርብ ይላል” …ኢትዮጵያዊ ሆኖ በሥራ ቅጥር ቻይናዊ ሆኗል ማለት ነው። በአሜሪካ እና ካናዳ ሌሎችም ሀገር ያሉ የውጭ ጋዜጠኞች ስፓንሹም ፈረንሳዩም ትንታኔ የሚጠይቁት በሀገሩ ብሔራዊ ቋንቋ እንጂ በመጡበት ሀገር ወይም በተቀጠሩበት ሀገር ቋንቋ አደለም። ግሩም ጫላ ለምን ለየት ለማለት ፈለገ?
    ወ/ሪት ቢልለኔ ስዩም ወልደየስ በዜግነት ካናዳዊት መሆናቸው ለማሳጣት ወይስ እንግሊዘኛ ብቃታቸውን ለመፈታተን? (መሰሪነት!)
    ሌላው ያነሳው ነጥብ ” ከእናንተ ይልቅ ጠ/ሚ ኮ/ል አብይ አህመድ በወር አንድ ግዜ ከፈረሱ አፍ መስማት እንፈለጋለን” ይላል ይህ ሁለተኛው ጠለፋ ነው። (ግሩም ጫላ.አዲስ አበባ ኢትዮጵያ) ሲል በጣም ደስ የሚለኝ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ነው።
    ጠ/ሚ ኮ/ል አብይ ለአዳራሽ የሚበቃ ጥሩ የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም (ጋዜጠኛው አፋጠጣቸው፡ ታሪክ ሰራ) የሚያስብል አልባሌ ጥያቄ በመጣል አድናቆትን የሚያነፈንፉ ጋዜጠኞች ) አስተሳሰብ ነው። ዓብይ አሁን አንዳንዱ ጨዋታም ገብቷቸዋል ማለት ነው፡ ወይ ፀጥ ለጥ አድራጊ አፈቀላጤ መቅጠር አለዚያም ይህንን ጥያቄ አልፈዋለሁ ማለት። በበኩሌ ጠ/ሚ ኮ/ል አብይ በአሽሙር ከመለሰው መልስ ይልቅ…በተለይ ሕግ ነክ ጥያቄዎችን ሳያጨማልቅ ጥያቄዎችን የዘለለበት ዘዴዎች በጣም ተስማምቶኛል..የመለስን ራዕይ ቢከተል እንዲሁ የቻይና ተረት፡ የጫት ላይ ቀልድ ፓርላማ እየቀለደ በውሸት ጭብጫቦ ይደነቁር ነበር።
    ሌላው ቱማታ “ዜጎች ለየትኛው ፖስፖርት ነው ታማኝነታቸው የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል፤››
    ድንቄም! መጀመሪያ ግሎባላይዜሽን ሉዓላዊ ሀገርነትህን ገፎታል። የኢትዮጵያ ሕገመንግስትም ዳር ደንበር በክልሎቹ ይወሰናል ይላል እንጂ አዋሳኝ ሀገር ድንበር የለንም፡ጭራሽ አሁን አፍሪካን አንድ ማድረግ ሕልም በገዳ ሥርዓት ማስተሳሰር ሲባል አብረህ ታጨበጭባለህ ከፍተህ ምን ልትሰጥ፡ ምን ልትቀበል እንደሆን ይታያል!። ዛሬ የሚያበድሩንና የሚረዱን ሀገራት ፳፪ ቢሊየን ዶላር ዕዳ ሲቆሉሉብን የጋዜጠኛ ወሬን ሳይሆን ወርቅ፡ ነዳጅ፡ ቅርስ፡ ገንዘብ፡ብረትና ቡና የት እንዳለ ሥንት እንደሚያወጣ ከአየር ላይ እየተቆጣጠሩና እየመዘገቡ እንደሆነ ማወቅ ነው። ይህንን ለማድረግ ሳተላይት እንጂ ፓስፖርት(ዜግነት፡ቪዛ) አያስፈለጋቸውም ግድግዳ ላይ የተጻፈን ቆሞ ጋዜጠኛ ፊት ማውራት ምን ያህል የሀገር ድብቅ ሚስጠር ቢሆን ነው? ስንቱ የወጭ ዜግነት ይዞ ሚዲያ ከፍቶ ሁለተኛ መንግስት መስርቻለሁ ይል የለምን? የአንድን ደሃ ሀገር ዓመታዊ የትምህርት ፈተና ሰርቄ እኔነኝ መልስ የሰራሁትና መንግስትን ዕዳ የጨመርኩት የሚልን ጎረምሳ ቤተመንግስት አስገብቶ ያንፈላሰስ የለምን? ትውልደ ኢትዮጵያዊውን አደለም አንድ ዶላር ከቡና ቀንስ ሀገርህን ዕርዳ ተብሎ የሚለመነው? የትውልደ ኢትዮጵያዊው የቤተሰብ እርዳታ አደለም ከውጭ እርዳታ የሚበልጠው? ለመሆኑ ከነጭ እውቀት ከምንለምን የነጭ ዕውቀት ነጥቀው በሚመጡ ብንጠቀምበት ምንድነው ችግሩ? ለመሆኑ ጠ/ሚሩ በተለያዩ የውጭ ሀገራት ሲሄዱ ትምህርት፡ ጤና፡ መከላከያውን ለማጠናቀር እርዱኝ ብለው ሲለምኑ የሀገር ሚስጥር ሳይገለጥ ነው? እነኝህ ሰዎች ለመምከርና ለመርዳት ሲመጡ የክልል ዜግነትና ፓስፖርት ተሰጥቷቸው ነው? (ቂጥ ገልቦ ክንብንብ) አሉ
    **************
    ይህ ጉዳይ ኮ/ል አብይ አህመድ የአብዛኛውን ተቃዋሚ ተፎካካሪ ተደጋፊ ከበሮ ቀምቶ መደለቅ ሲጀምር ብዙው ሥራ ፈት ሆኗል። ከ፷፭ ፓርቲ ለምርጫ ውድድር የተመዘገበው እንኳ ፭ አልሆነም !? ሁሉንም ኢህአዴግ አድርጎ ደምሮታልና!!። ጋዜጠኛውንም..ሰበር ዜና፡ ሚስጥር፡ ሹክሹክታ፡ውስጥ አዋቂ የሚለውን በአንድ ቃል አቀባይ ለሁሉም ያወራዋል ስለዚህ ነገሮች ግልጽ እየሆኑ ይሄዳሉ የስሚ ስሚ የለም ቃል አቀባዮቹ ጠ/ሚስተሩንም ፓርቲውንም ይሞግቱለታል .. አሉ.. ተባለ አሉ.. መሰለኝ… ጠረጠርኩ የሚሉ እንቶፈንቶ ወሬ ይቀንሳል ይቀራልም። ስለዚህ ጅምሩን መተቸት፡ አለዚያም ማተራመስ ወይም መቀወጥ ስልታዊ መሸበርና ማሸበር ነው በለው!

    Reply
  2. አለም says

    November 8, 2018 07:22 pm at 7:22 pm

    ውድ ጎልጉል፣
    ለምን ይደንቃል? እንግሊዛዊው ግልክስ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ዋና አማካሪ ሆኖ ሲሠራ ይኸ ጥያቄ እንዴት አልተነሳም? ወ/ት ቢልለኔማ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ነች! አላሙዲ በእናቱ ኢትዮጵያዊ በአባቱ የመን የሳውዲ ዜጋ ሆኖ ከአንድ ኢትዮጵያዊ የበለጠ መብት አልነበረውም? ቢልለኔማ በእናትም ባባትም ኢትዮጵያዊት ነች። ፕሬስ ሰክሬተሪነት የሚጠይቀው ብቃት አለ፤ አንደኛው የውጭውን ኣለምና ያገር ቋንቋ አጥርቶ ማወቅ ነው።

    Reply
  3. demeke alamirew says

    November 9, 2018 11:40 am at 11:40 am

    አቶ ተወልደ አሜሪካዊ ሁኖ አይደል አየር መንገድን እፓርታይድ ያደረገው

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule