• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሽመልስ አብዲሳ አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ

November 5, 2018 02:23 am by Editor 2 Comments

ለበርካታ ወራት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ፍጹም አረጋ ወደ ቀድሞ መሥሪያ ቤታቸው የኢንቨስትመንት ጽ/ቤት እንደሚመለሱ ከተነገረ ወዲህ ቦታቸውን የሚተካው ማን እንደሚሆን እስካሁን አልታወቀም ነበር።

ዛሬ ከተለያዩ ምንጮች የተሰራጨው መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ ሽመልስ አብዲሣ የፍጹም አረጋን ቦታ ተክተው እንደሚሠሩ ታውቋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በአዲስ መልክ በተደራጀው “ፕሬስ ሴክሬተሪ” ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀኑ በ8:00 ላይ በጽ/ቤቱ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን ሹመቱም በዚሁ ጊዜ ይፋ እንደሚገለጽ ይነገራል።

አቶ ሽመልስ አረጋ በቡድን ለማ (ቲም ለማ) ውስጥ ቁልፍ ቦታ የነበራቸው የለውጡ አካል ሲሆኑ የኦዴፓ እና ኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባል ናቸው።

አቶ ሽመልስ በኦሮሚያ ክልል የኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ፤ በመቀጠልም የከተማና ቤቶች ልማት ምክትል ኃላፊ በመሆን የኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮትን የመሩ ናቸው።

አቶ ፍጹም በቲዊተርና በፌስቡክ መረጃዎችን በመልቀቅ በጥሩ ሁኔታ ግንኙነት ሲያደርጉ እንደቆዩ ቢነገርላቸውም ከጠ/ሚ/ር ዐቢይ ጋር ለመገናኘት የሚያዙ ቀጠሮዎችን በማዛባት ብቻ ሳይሆን እጅግ በተደጋጋሚ የሚደወልላቸውን ስልክ ባለመመለስ፣ ለሚላክላቸው አጭር የጽሁፍ መልዕክት (ቴክስት) ምላሽ ባለመስጠት ወዘተ ኃላፊነታቸውን ባግባቡ እንዳልተወጡ በግል ሳይሆን በድርጅት ደረጃ ጠ/ሚ/ሩን ለማግኘት ጥረት ያደረጉ ምሬታቸውን ይገልጻሉ። ከአቶ ሽመልስም ከዚህ የተሻለ እንደሚጠብቁ ይናገራሉ።

አቶ ሽመልስ የኦዴፓ እና የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ መሆናቸው የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በፌዴራል መንግሥት ውስጥ ከሚገኙት ዐቢይ አህመድ፣ ወርቅነህ ገበየሁ፣ አዳነች አቤቤ፣ ወዘተ ቀጥሎ ተጨማሪ የኦዴፓ ኃይል ሆነው  መምጣታቸው አንዳንዶች የህወሓት የበላይነት በኦዴፓ የመተካት ሁኔታን ያሳያል ይላሉ።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. gi Haile says

    November 6, 2018 06:24 am at 6:24 am

    Any party or leaders need trusted officials this not just in Ethiopia any where in the world for the last 2000 years. That is why TPLF deligated thousands of TPLF members in all regions to spy over all regions and violayed the Federal stature . Ptess secretary and PM office chief of staff can be anybody when itcomes to trust and confidentiality. Nothing wrkng with such appointment. TPLF feferal appointment totally invasion of all region and forign affairs department. PM Abiy appointement fare and based on skills and professionalism. Way to go!

    Reply
  2. Sergute Selassie says

    November 7, 2018 02:43 pm at 2:43 pm

    እስኪ መጀመሪያ ተግባራቸውን እንይ። አብሶ ከኦነጋውያን መንፈስ ጋር ካልተጋቡ፤ ለለውጡ ታማኝ ከሆኑ ለዜግነታቸው ከማለት ያለፈ መሆንን ካሳዩ ስጋቱ ይደረስበታል። ኦህዴድ እራሱ ፈተና ውስጥ ስለሆነ ብሄራዊ ግዴታውን እንዲወጣ ካስቻለው በአደብ መከታተል ይበጃል። አብሶ ኮነሬል ጎሹ ወልዴ የጠ ሚኒስትሩ አማካሪ ከሆኑ ወጣ ገቦች መልክ ይይዛሉ ብየ አስባለሁኝ። በወሮ አዳነች አቤቤ በኩል ጥንካሬ እንዳላቸው ተከታትያለሁኝ፤ ከዞጋቸው ጋር ዜግነታቸውን እንዴት አጣጥመው እንደሚጓዙ ለማዬት ጊዜ ያስፈልግ ይመስለኛል። ምስክርነት መስጠት ዛሬ ላይ አስፈሪ እየሆነ ነው።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule