በዚህ ሳምንት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ ሴክሬታሪ ሆነው የተሾሙት ወ/ሪት ቢልለኔ ስዩም ወልደየስ በዜግነት ካናዳዊት መሆናቸው ጥያቄ አስነስቷል። ሹመታቸውም በሥራ ላይ ያለውን ሕግ የሚጻረር ነው ተብሏል። ወ/ሪት ቢልለኔ ለማስተርስ ዲግሪ ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሁፍ “Transformative Spaces: Enabling Authentic Female Leadership Through Self Transformation - the Association of Women in Business” ወደሚል መጽሐፍ ቀይረው ባሳተሙት ገጽ 16 ላይ በትውልድ ኢትዮጵዊት በዜግነት ግን ካናዳዊት መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ከዚህ አንጻር ከታየ ሹመታቸው የሕግ ጥያቄ እንደሚስነሳ የሪፖርተሩ ዳዊት እንደሻው ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያ ይናገራሉ፤ “አዋጅ ቁጥር 270/1994፣ ‹‹የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎች በትውልድ … [Read more...] about አዲሷ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬተሪ በዜግነት ካናዳዊት ናቸው