ባንኮች በኢኮኖሚው ላይ እያደረጉ ካሉት አስተዋጽኦ ባሻገር ዘመናዊ ህንጻ በመገንባትም የላቀ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ተናገሩ። ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በ2 ቢሊየን ብር ያስገነባውን ዘመናዊ ህንጻ ዶ/ር ይናገር ደሴ በተገኙበት ዛሬ አስመርቋል። ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች ውጤታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የተናገሩት ገዥው ቢዘገይም የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸው ስለማይቀር ከአሁኑ ጠንካራ መሆንና ተወዳዳሪ ለመሆን መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል። ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በፋይናንሥ ዘርፉ የሚጠበቅበትን ለማበርከት የጀመረውን ፕሮጀክት በታሠበው ጊዜና ወጭ ማጠናቀቁን የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ገነነ ሩጋ ተናግረዋል። የተገነባው ባለ 37 ወለል ዘመናዊ ህንጻ የንብ ባህላዊ ቀፎና የማር እንጀራን ቅርጽ እንዲኖረው … [Read more...] about ባንኮች ከኢኮኖሚው አበርክቶ ባለፈ በህንጻ ግንባታም የላቀ ሚና እየተጫወቱ ነው ተባለ