“ሕገመንግሥቱ ያልፈለገ በሰላም ይሰናበታል” ብለው አለቆች ባስተማሩት መሠረት ትግራይ ከፌዴሬሽኑ መቀጠል አልፈልግም ስትል ይህንኑ ለምን ተግባራዊ አላደረገችም? ለምን ጦርነት ውስጥ ገባች? ምን ተፈልጎ ነው ወደ ጦርነት የተገባው? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ አለመኖሩ የኬሪያ ኢብራሒም ጥያቄ ነው። አንቀጽ 39 ተጠቅሶ መገላገል እንደሚቻል በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ የነበረ ድርጅት፣ ለዚሁ ህግ ጠበቃና ብቸና ሞግዚት ሆኖ የኖረ ፓርቲ ለምን ይህን ሁሉ ወጣት በነጻነት ሰበብ አስጨረሰ? ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ ምላሽ መስጠት ለማይፈልጉና ለሚያድበሰብሱ ኬሪያ “አስቡና መልሱን ወዲህ በሉኝ” የሚል እንደምታ ያለው መረጃ ሰንዝረዋል። ጦርነቱን አስመልክቶ የትህነግ ጠበቃና ተከላካይ ሆኖ የዘለቀው ጠያቂያቸው ዝም ብሎ ተጨማሪ ማብራሪያ ሳይጠይቅ ያለፈው ይህ አንኳር ነጥብ ውሎ አድሮ አጀንዳ እንደሚሆን … [Read more...] about የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል”

