የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በተሿሚዎች፣ በተመራጮች ወይም በመንግሥት ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል። በ2002 ዓ/ም በወጣው የሀብት ማሳወቂያና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ድንጋጌ መሠረት፦* የአገሪቱ ፕሬዚዳንት፣* ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣* ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣* ሚኒስትሮች፣* ሚኒስትር ዴኤታዎች፣* ኮሚሽነሮች፣* ምክትል ኮሚሽነሮች፣* ዋና ዳይሬክተሮች፣* ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፣ እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ግዴታ ጥሎባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ ግለሰቦቹ ለኮሚሽኑ ያስመዘገቡትን ሀብት መረጃ በሚስጥር መያዝና ለሕዝብ ይፋ አለማድረግ ከአዋጁ ጋር የሚፃረር ድርጊት እንደሆነ … [Read more...] about “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “