ከአራት ቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ለ“ካቢኔያቸው” ወደ ሁለት ሰዓት የሚፈጅ ሥልጠና ሰጥተዋል። ይህ በሥነአመራር ጥበብ ላይ ያተኮረው የጠ/ሚ/ሩ ገለጻ በኮሌጅ ደረጃ የሚሰጥ ትምህርት ተጨምቆ የቀረበበት ነው። በካቢኔ አባልነት የተቀመጡት ግለሰቦች አንዳንዶቹ በመደነቅ፣ ሌሎቹ በመገረም፣ አፋቸውን በመያዝ አንዳንዶች በመናደድ ሌሎች ደግሞ አልገባ ብሏቸው ግራ በመጋባት ሲያደምጡ ተስተውለዋል። በርካታዎቹ ከየ“ዲግሪ ወፍጮ ቤቱ” የከፍተኛ ትምህርት ምሩቃን ተብለው ከሚችሉት በላይ ዲግሪ ተሸክመው የሚንገዳገዱ በመሆናቸው የጠቅላዩ ንግግር አቅማቸውን የማይመጥን ሆኖ እንዳገኙት ከፊታቸው ላይ የሚታይ ነበር። ምክንያቱም እነርሱን ወደዚህ ዓይነት ማዕረግ እንዲመጡ ያደረጋቸው ራሱ ከዲግሪ ወፍጮ ቤቶቹ በአንዱ በፖሰታ ቤት ዲግሪውን የተቀበለው መለስ ዜናዊ ነበር። መለስ አካባቢውን … [Read more...] about ጠ/ሚ/ሩና ውቅር የማይገባው “የዲግሪ ወፍጮ” ምሩቃን ካቢኔ