በሶማሌና በአፋር ክልል አዲስ ዕዞች ይቋቋማሉ፤ ለምን? የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር /ህወሓት ሊያጣው የማይፈልገውን የመከላከያና የደኅንነት ሥልጣንን አስጠብቆ ለመኖር ፍትጊያ እያደረገ መሆኑ በተደጋጋሚ የሚገለጽ ቢሆንም ብወዛው እንደማይቀር የጎልጉል የአዲስ አበባ መረጃ አቀባይ ጠቁሟል። መከላከያ በኮሚቴ (ካውንስል) ሊመራ ነው። አራቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች አንድ አንድ ወኪል አላቸው። በሶማሌና አፋር ክልል ሁለት አዲስ ዕዞች ይቋቋማሉ፤ በማን እንደሚመሩ ለጊዜው አልታወቀም። ይህንን አዲስ አወቃቀር ተግባራዊ ለማድረግ አዲሱ ጠ/ሚ ዓቢይ አህመድ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮችን የሥራ ኃላፊነት የሚመለከት ብወዛ ለማካሄድ ብሎም በጡረታ ለመሸኘት በደመቀ መኮንንና በአባዱላ ገመዳ የሚመራ የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖችን ያካተተ አንድ ግብረ-ኃይል (ታስክፎርስ) እንዲቋቋም … [Read more...] about መከላከያ በአዲሱ አወቃቀር በኮሚቴ (ወታደራዊ ካዉንስል) ሊመራ ነው