• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መከላከያ በአዲሱ አወቃቀር በኮሚቴ (ወታደራዊ ካዉንስል) ሊመራ ነው

May 21, 2018 08:41 pm by Editor 3 Comments

  • በሶማሌና በአፋር ክልል አዲስ ዕዞች ይቋቋማሉ፤ ለምን?

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር /ህወሓት ሊያጣው የማይፈልገውን የመከላከያና የደኅንነት ሥልጣንን አስጠብቆ ለመኖር ፍትጊያ እያደረገ መሆኑ በተደጋጋሚ የሚገለጽ ቢሆንም ብወዛው እንደማይቀር የጎልጉል የአዲስ አበባ መረጃ አቀባይ ጠቁሟል። መከላከያ በኮሚቴ (ካውንስል) ሊመራ ነው። አራቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች አንድ አንድ ወኪል አላቸው። በሶማሌና አፋር ክልል ሁለት አዲስ ዕዞች ይቋቋማሉ፤ በማን እንደሚመሩ ለጊዜው አልታወቀም።

ይህንን አዲስ አወቃቀር ተግባራዊ ለማድረግ አዲሱ ጠ/ሚ ዓቢይ አህመድ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮችን የሥራ ኃላፊነት የሚመለከት ብወዛ ለማካሄድ ብሎም በጡረታ ለመሸኘት በደመቀ መኮንንና በአባዱላ ገመዳ የሚመራ የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖችን ያካተተ አንድ ግብረ-ኃይል (ታስክፎርስ) እንዲቋቋም አድርገዋል። እንደ ጎልጉል ዘጋቢ የመረጃ ምንጮች ከሆነ ግብረኃይሉ በዋናነት የሚከተሉትን ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ ይገኛል።

  • ሁለት አዳዲስ ዕዞች ያቋቁማል፤

አሁን ካሉት አራት ዕዞች፣ ሰሜን ዕዝ (መቀሌ)፣ ደቡብ ምስራቅ ዕዝ (ሐረር)፣ ምዕራብ ዕዝ (ባህር ዳር) ማዕከላዊ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ (አዲስ አበባ ጃንሜዳ) በተጨማሪ ሁለት ዕዞችን ለማቋቋም የቅድመ ዝግጅት ሥራዉ ተጠናቋል። በዚህም መሠረት አዲስ የሚቋቋሙት ሁለት ዕዞች፤ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ (አፋር) እና የምስራቅ ዕዝ (የኢትዮጵያ ሶማሌ) ላይ እንደሚቋቋሙ ከመረጃው ለማረጋገጥ ተችሏል።

ቀደም ሲል በነበረዉ አሠራር አሁን አዲስ ዕዝ እንዲመሠረት የታሰበባቸው ክልሎች ውስጥ በክፍለ ጦር ደረጃ ሠራዊት ነበር። መረጃው በዝርዝር እንዳሰፈረው የአፋርና ኤርትራ አዋሳኝ ቦታዎች የህወሓቱ ሌ/ጄ ገብራት አየለ በሚያዘው የሰሜን ዕዝ ሥር ባለ አንድ ክፍለ ጦር የሚመራ ሲሆን የኢትዮጵያ ሶማሌው ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ሌላኛው የህወሓት ጄኔራል አብርሃ ወ/ማርያም ሐረርን ማዕከል ባደረገው የደቡብ ምሥራቅ ዕዝ ሥር ባለ ክፍለጦርና ተወርዋሪ ቃኝ ሻለቃዎች ይመራ ነበር። በዚሁ መሠረት በአዲሱ አወቃቀር በአፋር ክልል የሰሜን ምስራቅ ዕዝ፤ በኢትዮጵያ ሶማሌ ደግሞ የምስራቅ ዕዝ ተብሎ በአዲስ መልኩ ይቋቋማሉ።

  • የኤታማዦር ሹመትን የተመለከቱ ዝርዝር ነጥቦችን ይፈትሻል፤

ከዚሁ ጋር ተያይዞ አስራ ሰባት አባላት ያሉት የወታደራዊ ካዉንስል በአዲስ መልኩ ስለሚቋቋምበት ሁኔታ ቅድመ ዝግጅትች በመካሄድ ነው። ከዚህ ቀደም በሳሞራ የኑስ የበላይነት ተጠርንፎ ተይዞ የነበረዉ የኤታማዦር ሹም ኃላፊነት ቦታ እንደ ቀድሞው በአንድ ጄኔራል የሚመራ ቢሆንም፣ የዉሳኔ አሰጣጥ በተመለከተ “የኤታማዦር ኮሚቴ” እንዲሆን ይደረጋል። በዚህም መሠረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተነሳ ወይም ከተጠናቀቀ በኋላ ባሉ ጥቂት ጊዜያት ዉስጥ የሳሞራ የኑስ ጡረታ መዉጣት በአገዛዙ ሚዲያ ይፋ ተደርጎ አዲሱ የቡድን ወይም የኮሚቴ ውሳኔ አሰጣጥ የሚመራው አሠራር ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ሳሞራን ይተካል ተብሎ የሚጠበቀዉ በአሁኑ ሰዓት የመከላከያ የሥልጠናና ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ የሆነዉ ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ይመር እንደሚሆን ተጠቁሟል። ሰዓረ በአዲሱ ኢታማዡር ኮሚቴ ኢታማዦር ተብሎ የሚሾም ይሆናል። ቀሪዎቹ የኮሚቴዉ አባላት እንዲሆን የተመለመሉት፤

1 – ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለልቻ (የሰላም አስከባሪ ግዳጅ ኃይል ዋና ኃላፊ – ኦህዴድ)

2 – ጄኔራል አደም መሐመድ ሟህመድ (የአየር ኃይል ዋና ኃላፊ – ብአዴን)

3 – ሌ/ጄኔራል ሞላ ኃይለማርያም አለማየሁ (የኮር አመራር የነበረ- ከደኢህዴን)

ሰዓረን ጨምሮ ብርሃኑን እና አደምን የምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹመት በመስጠት የሙሉ ጄኔራልነት ማዕረግ ጥር 26፤ 2010ዓም ያጎናጸፋቸው ሃይለማርያም ደሳለኝ ነበር። በዚሁ ዕለት ሞላም የሌ/ጄኔራልነት ማዕረግ ተሰጥቶታል።

  • ወታደራዊ ካውንስል ያደራጃል፤

አስራ ሰባት አባላት ያሉበት የመከላከያ ወታደራዊ ካዉንስል ሲደራጅ በዋናነት የኤታማዦር ኮሚቴዉን፣ የዕዝ ኃላፊዎችን እንዲሁም የወታደራዊ ደህንነት፣ የሎጀስቲክስ፣ የልዩ ኃይል፣ የመስመር ኃይል ኮር አመራር የበላይ ኃላፊዎችን ባካተተ መልኩ እንደሚሆን የጎልጉል ዘጋቢ አመልክቷል። የኤታማዦር ቦታዉ እንደማይነካበት ቃል የተገባለት ህወሓት በወታደራዊ ካዉንስሉ በኩል ቁጥሩ የላቀ አባላቱን ለማስመልመል የሚችለውን ሁሉ እያደረገ መሆኑንም መረጃ አቀባዮቹ አስታውቀዋል።

ሱሪ ረጃጅሞቹ የህወሓት ጄኔራሎች ጥር 26፤ 2010ዓም ሹመት የተሰጣቸው ዕለት

በዚሁ መሠረት ህወሓት በመከላከያ ወታደራዊ ካዉንስል ዉስጥ ወሳኝ  ሚና እንዲጫወቱለት  ወደፊት ያወጣቸዉ ዋና ዋና አመራሮቹ የሚከተሉት ናቸው፤

  1. ሜ/ጄኔራል አታክልቲ በርሀ ገብረማርያም
  2. ሜ/ጄኔራል ያይኔ ስዩም ገብረማርያም
  3. ሜ/ጄኔራል ሙሉ ግርማይ ገ/ህይወት
  4. ሜ/ጄኔራል ፍሰሃ ኪ/ማርያም ወ/ሂወት
  5. ሜ/ጄኔራል ገብራት አየለ
  6. ሜ/ጄኔራል ፍስሓ አዳነ
  7. ሌ/ጄኔራል መሐሪ ዘውዴ ገ/ማሪያም
  8. ጄኔራል አብረሃ ወ/ማርያም ገንዘቡ
  9. ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ናቸዉ። (በተራ ቁጥር 5 እና 6 ከተጠቀሱት በስተቀር ሌሎቹ በሙሉ ሃይለማርያም ደሳለኝ በጥር ወር ለፕሬዚዳንቱ አስቀርቦ ሹመት ያሰጣቸው ናቸው፤ ይህም የሚያሳየው ህወሓት የፖለቲካ ሥልጣኑን ማጣቱ እውን እየሆነ ሲሄድ የመከላከያውን ጉዳይ ከእጁ እንዳይወጣ አስቀድሞ የቤት ሥራውን ሲያከናውን እንደነበር ጠቋሚ ነው)

በዝርዝሩ እንደተመለከተው ከአስራ ሰባቱ ወታደራዊ ካዉንስል አባላት ውስጥ ዘጠኙ የህወሓት ነባር ታጋዮች እንዲሆኑ ህወሓት የሞት ሽረት ትንቅንቅ በማድረግ ላይ ይገኛል። እንደ ጎልጉል ምንጭ ከሆነ ሳሞራ “ጥቂት ጊዜ ስጡን” ያለበት ምክንያትም ከዚሁ ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ግምታቸውን ሰጥተዋል። የጻድቃን ገብረትንሳኤ መከላከያውን እና ደኅንነቱን ሳንነካ የፖለቲካ ተሃድሶ እናድርግ ዕቅድም ከዚሁ ጋር እንደሚያያዝ አስተያየት ይሰጥበታል።

በሶማሌ ክልል ህወሓት አለው ከሚባለው ልዩ ፍላጎትና አሁን ካለው ችግር አኳያ፣ እንዲሁም ለትግራይ አጎራባች ከሆነውና ሰፊ ክልሉ የተወሰደበት አፋር ላይ አዳዲስ የጦር ዕዞች ለማቋቋም የተያዘው ዕቅድ ዓላማው በተለይ ከህወሓትም ሆነ ከትግራይ ጥቅም አንጻር ምን እንደሆነ የመረጃው ምንጮች እየመረመሩ እንደሆነ የጎልጉል ዘጋቢ አመልክቷል። የኃላፊዎች ምደባ ይፋ ሲሆን ጉዳዩ ይበልጥ ግልጽ እንደሚሆንም አክለዋል። የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል በህወሓት ጄኔራሎች የሚመራና እንዳሻው የሚፈነጭ፣ የክልሉም ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ኢሌይ ከልካይ የሌለው በደም የተጨማለቀ አምባገነን መሆኑን የሚጠቅሱ በሁለቱ ክልሎች ህወሓት የራሱን ሰዎች እንደሚያስቀምጥ ከወዲሁ አስታውቀዋል።

ኦህዴድና ብአዴን በመከላከያና በደኅንነት ውስጥ ያለው ውክልና ሙሉ በሙሉ ሚዛን የሳተ እንደሆነ በግምገማ ወቅት ቁርጠኛ አቋም ይዘው ሲሟገቱበት እንደነበር የሚታወስ ነው። በተለይም ኦህዴድ በያዘው የፈረጠመ አቋም የተነሳ ግምገማው መራዘሙና በመቋጫው ህወሓት አምኖ ማስተካከያ እንዲደረግ ስምምነቱን መግለጹ አይዘነጋም። አስራ ሰባት አባላት በሚኖሩት ካውንስል ውስጥም ዘጠኙን የህወሓት ጄኔራሎች ከወሰዱት ቀሪው ስምንት በኦህዴድ፣ በብአዴንና በደኢህዴን መካከል እንዲሆን የመደረጉ ጉዳይ በተለይ ኦህአዴድና ብአዴን ለመቀበል የሚቸግራቸው ከመሆኑ አንጻር አሁን ያለው አካሄድ ተለዋጭ አሠራር ሊቀርብበት ይችል ይሆናል የሚል ግምት አለ። ህወሓት ግን ከዘጠኝ ያነሰ ድምፅ ሰጪዎች በሚኖሩበት ካውንስል ውስጥ የሚፈልገውን አጀንዳ በድምፅ ብልጫ ማስፈጸም የማይችልበትን አካሄድ ለመቀበል የተዘጋጀ አይመስልም በማለት የመረጃው ምንጮች ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የአዲስ አበባ መረጃ አቀባይ አስረድተዋል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Politics Tagged With: defence council, Full Width Top, generals, Middle Column, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Ayu says

    May 27, 2018 05:11 pm at 5:11 pm

    Selam Wendimoche,
    Please add FB link so I can post or share this article to my FB page

    Thank you

    Reply
    • Editor says

      May 30, 2018 06:44 am at 6:44 am

      Ayu

      Thanks for your suggestion. There is some tech issue and we are working on it.

      Regards,
      Editor

      Reply
  2. Zewdu says

    July 11, 2018 01:56 am at 1:56 am

    ትግሬዎች 5% ሆነው እንዴት ከ ግማሽ በላይ ፣ ማለትም ከ 17 ወንበር 9 ኙ፣ ለ እኛ ይሰጠን ይላሉ? አሳፋሪ እና መሆን የማይገባው ነው። ይህን መፍቀድ የ27 አመቱን ግፍ አገዛዝ ቀጥሉ ማለት ነው። ሊኖራቸው የሚገባቸው አንድ ብቻ ነው። እዚህ ላይ ምንም አይነት ድርድር ማድረግ አይገባም።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule