ቁጥራቸው 16 የሆኑ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ የነበሩ የህወሃት መኮንኖች ወደ ጅቡቲ ቢኮበልሉም ጅቡቲ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው እንደተሰጡ ተነገረ። የጅቡቲ ዜና ወይም Les Nouvelles de Djibouti በድረገጹ ይፋ ያደረገው ዜና ርዕስ “የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወታደሮችን ጅቡቲ ለኢትዮጵያ አሳልፋ ልትሰጥ ነው” የሚል ነበር። ይህ አሳልፎ የመስጠት ስምምነት የተፈረመው እኤአ በመጋቢት ወር 2017 ነበር። በወቅቱ ኢትዮጵያን ይጎበኙ በነበሩት ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህና ጠቅላይ ሚኒስትር በነበረው ኃይለማርያም ደሳለኝ መካከል ነበር። በስምምነቱ መሠረት ማንኛውም “ወንጀለኛ፣ አሸባሪ” ተብሎ የተጠረጠረና ከአንዱ አገር ወደሌላው ጥገኝነት ለመጠየቅ የሄደ አገራቱ አሳልፈው እንዲሰጡ የሚያደርግ ነበር። ይህንን ስምምነት በዋንኛነት የፈለገው ራሱን … [Read more...] about ጅቡቲ በህወሃት ዘመን በፈረመችው ውል መሠረት 16 የህወሃት ወታደሮችን አሳልፋ ሰጠች