• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ኦሮሞ የሞተላትን አገር ጥሎ ወዴትም አይገነጠልም! ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ውጭ አገር የለውም! አይኖረውም!” ዐቢይ አሕመድ

September 21, 2018 06:33 pm by Editor 1 Comment

ህወሓት የሰየመለትን ስም፣ ዓርማና መዝሙር በማስወገድ ራሱን ነጻ ያወጣው የቀድሞው ኦህዴድ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) የሚል ስያሜ በመውሰድ አዲስ ፓርቲ ሆኗል፤ የሚከተሉትን የኦዴፓ/ኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በማድረግ መርጧል 1. ዶክተር አብይ አህመድ፤ 2. አቶ ለማ መገርሳ፤ 3. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፤ 4. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ፤ 5. ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፤ 6. አቶ አዲሱ አረጋ፤ 7. አቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ 8. አቶ ፍቃዱ ተሰማ፤ 9. ዶክተር ዓለሙ ስሜ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚከተሉትን 55 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን መርጧል፤ እስካሁን ይፋ በሆነው የምርጫ ውጤት መሰረትም፦

    1. ዶክተር አብይ አህመድ
    2. አቶ ለማ መገርሳ
    3. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ
    4. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ
    5. ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
    6. ኢንጂነር ታከለ ኡማ
    7. አቶ ሽመልስ አብዲሳ
    8. አቶ ኡመር ሁሴን
    9. ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን
    10. አቶ አዲሱ አረጋ
    11. ዶክተር ግርማ አመንቴ
    12. ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ
    13. ዶክተር ሚልኬሳ ሚደጋ
    14. አቶ ተሾመ አዱኛ
    15. አቶ ታዬ ደንደአ
    16. ዶክተር አለሙ ስሜ
    17. ዶክተር ቶላ በሪሶ
    18. አቶ ደመላሽ ገብረሚካኤል
    19. አቶ ግርማ ሀይሉ
    20. አቶ ወርቁ ጋቸና
    21. አቶ ሻፊ ሁሴን
    22. አቶ ቶሎሳ ገደፋ
    23. አቶ ፍቃዱ ተሰማ
    24. አቶ ብርሃኑ በቀለ
    25. አቶ አወሉ አብዲ
    26. አቶ ጌቱ ወዬሳ
    27. አቶ ካሳሁን ጎፌ
    28. አቶ መላኩ ፈንታ
    29. አቶ ታረቀኝ ገለታ
    30. አቶ አበራ ወርቁ
    31. አቶ መኩዬ መሃመድ
    32. አቶ አህመድ ቱሳ
    33. አቶ አሰግድ ጌታቸው
    34. አቶ ደንጌ ብሩ
    35. አቶ ነመራ ቡሊ
    36. አቶ አብዱልአዚዝ መሃመድ
    37. አቶ ሮባ ቱርጬ
    38. አቶ ጀማል ከድር
    39. አቶ መሃመድ ከማል
    40. አቶ ከፍያለው ተፈራ
    41. አቶ መስፍን አሰፋ
    42. ወይዘሪት ሌሊሴ ነሜ
    43. አቶ ናስር ሁሴን
    44. አቶ ሞገስ ኢደኤ
    45. ዶክተር ደረጄ ዱጉማ
    46. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ
    47. ወይዘሮ ሎሚ በዶ
    48. ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ
    49. ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ
    50. አቶ ማሾ ኦላና
    51. ወይዘሮ አለምፀሀይ ሽፈራ
    52. አቶ አህመድ እድሪስ
    53. ወይዘሮ ሙና አህመድ እና
    54. አቶ ጥላሁን ፍቃዱ
    55. አቶ አብዱላኪም ሙሉ

ረቡዕ መስከረም 9፤2011ዓም በተጀመረው የኦዴፓ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢ የሆነ መልዕክት አስተላልፈው ነበር። የመልዕክታቸው ፍሬ ነገሮች ከዚህ በታች ሰፍረዋል። መረጃውን ከተለያየ የፌስቡክና የማኅበራዊ ሚዲያ በቅብብል ያገኘነው ነው።

  • “እሳት ውስጥ ቆመን፣ ስድቡን ሁሉ ችለን፣ ትግሉን ከዳር አድርሰነዋል። ኦሮሞ ከለቅሶ መውጣት አለበት። … ይህ አገር ያለ ኦሮሞ አገር መሆን አይችልም። ለኦሮሞ ኢትዮጵያ ብቻ ትጠበዋለች። አፍሪካንም መገንባት ይችላል ብለን ተነሥተናል። … ረጅም መንገድ እንድንሄድ ከፈለጋችሁ ይቺን አገር የመገንባት ኃለፊነት እንዳለብን እንወቅ። … አድዋ ላይ ማን ነው ያሸነፈው? … ይህንን አገር ለማን ትተን ነው የምንመለሰው? አንመለስም”
  • “ኢትዮጵያን እንገነባለን፣ አፍሪካን እንገነባለን፣ ማንም ኃይል ደግሞ ከዚህ ሊያቆመን አይችልም”
  • “ኦሮሞ ማቀፍን፣ ጉዲፈቻን እናት የሌላቸውን ልጆች ማሳደግን ነው ያስተማረን፣ ኦሮሞ ከተዋጋ ያሸንፋል እንጂ ሰውን መግደልን አላስተማረንም”
  • “የዚህ አገር አንድነት ለማስጠበቅ ኦሮሞ ኃላፊነት አለበት … ኢትዮጵያ ከጠላት ጋር ባደረገችው ጦርነቶች ውስጥ ኦሮሞ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል … አባጅፋር ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም ጭምር አርቀው የሚያስቡ ነበሩ … አሁን ባለንበት ዘመን በትናንትናው ስልት ማሸነፍ አይቻልም”
  • “ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም የሚሉን አሉ፤ ኦሮሞ አገር መምራት ብቻ ሳይሆን አገር መገንባት ይችላል፤ ኦሮሞ ገዳን ለዓለም እንደ ሰጠ ሁሉ፣ ኦሮሞ በቅርቡ አዲስ ፍልስፍና ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ሰጥቶ ሊያሳያቸው ይፈልጋል።
  • “ከዚህ በኋላ በኦሮሞ ህዝብ ስም መነገድ የለም። ኦሮሞ የሞተላትን አገር ጥሎ ወዴትም አይገነጠልም። ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ውጭ አገር የለውም፤ አይኖረውም። ኢትዮጵያ ብዙ አባቶቻችን ከአድዋ ጀምሮ ዋጋ የከፈሉባት አገራችን ነች። አንዳንዶች ጠዋት ስለ አንድነት ስለ አብሮነት እያወሩ ማታ አገር ስለማፍረስ ይዶልታሉ። መደመር እንደዚህ አይደለም። የኦሮሞ ህዝብ ወላዋዮችን ይጠየፋል። የምትበተን ኢትዮጵያ የለችም”

ስብሰባው ዛሬ ሲጠናቀቅ ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

(የተመራጮቹ ስምና አንዳንዶቹ ፎቶዎቹ የተወሰዱት ከፋና ፌስቡክ እና ከኢንተርኔት ነው)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Uncategorized Tagged With: abiy ahmed, Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    September 22, 2018 03:47 am at 3:47 am

    ከዚህ በኋላ በኦሮሞ ህዝብ ስም መነገድ የለም። ኦሮሞ የሞተላትን ሃገር ጥሎ ወዴትም አይገነጠልም።”
    +++++++++++++++++++++++++++++++++++
    **መቼም ኮ/ል ዓብይ አህመድ ዓሊ ይህንን ኮስታራ ፊት ሊያሳይ ይህንን መፈከር ሊያሰማ ያደፋፈረና ያስቆጣው በይቅርታና መደመር እሳቤ ያለ ቅድመሁኔታ ፈቶ የለቀቃቸው የውጭ ዜጎች እንጂ አማራና ትግሬ አደለም።
    ይህ ሰውዬ አምባገነን ሲሆን ታየኝ !
    ” በምሕረት በይቅርታና በመደመር መልካም ምኞት ለመግለፅ የመጣችሁ እንግዶቻችን ሆይ፤
    አሁን የጭፈራና የፈንጠዝያው ግዜ ስላለቀ ላደረጋችሁልን ትብብር እያመሰገንን ከድሃው ጉሮሮ *ተቀንሶ ለጤነነታችሁና ለደህንነታችሁ ያወጣነው ወጪ ሁሉ በይቅርታና በእንግዳ ተቀባይነታችን ኢትዮጵያዊ ባሕልና ጨዋነት ሂሳቡ በእኛ *ተደምሮ ለሕዝብ *ተካፍሎ ከዚህ በላይ የድሃ ገንዝብ ማባከንም ሆነ ጭፈራ ድህነት *ማብዛት ሆነብን። የእናንተም የሻንጣ ገንዘብ በጥቁር ገበያ ተለወጦ ለሀገር ምንም ያተረፈ ስላልሆነ፡ ለነበረን መልካም የፌሽታ ግዜ ከልብ ደስትኞች ነን ወደፊት በራሳችሁ ወጪ እየመጣችሁ የዲሞክራሲ ተቋዳሽ፡ የምሕዳሩ ተሽከካሪ እንድትሆኑ እየተመኘን ከሚቀጥሉት ቀናት በኋላ ምንም ስብሰባና የመንገድ ላይ ጭፋሮ አክሳሪ እንጂ አዋጪ ሆኖ ስላላገኘነው ቢቻል የውጭ ዜግነታችሁን በኢትዮጵያዊነት ለውጣችሁ በሰላምና በደስታ በእናት ሀገራችሁ ኢትዮጵያ ላይ በሰላም የጡረታ ዘመናችሁን እንድትገፉ፡ አለዚያም በጎብኝነት ወጥታችሁ ከሀገር ውጭ በመቆየት የውጭ ዜግነትና የጡረታ መብታችሁ፡ ከመሰርዙና የጤና የነጻ ሕክምና ካርዳችሁ ግዜው አልፎ ያለ ጧሪ ቀባሪ ያለ ዕድር በፓርቲ ምሥረታ ብቻ መንገድ ከምትወድቁ አማራጩን ትመረጡ ዘንድ ከወዲሁ እናሳስባለን!! ዲሞክራሲ ሂደት እንጂ በሻንጣ የሚመጣ ቁሳቁስ ስላልሆነ እኛው ባለን የተማረ ኅይልና ኅብረተሰብ ተሳትፎ እንድናዳብረው የወሰነን ስልሆነ እንደተለመደው የውጭ ሀገር ልምድ ሐሳብ ስንፈለግ እኛው በመልዕክተኛ ወይንም የእውቀት ሽግግር በሬዲዮና በቲሌቪዥን ጣቢያችሁ የቀጥታ ስርጭት የዲሞክራሲ ግንባታ ትምህርት እንድትሰጡ በማሰብ ወደመጣችሁበት ሀገር ትመለሱ ዘንድ የሰጠናችሁ የጥበቃ ዋስትና ብዙ ሂሳብ ስልጠየቀና የሀገራችን ጸጥታ መደፈረስ የፍቅርና የመደመር ምኖታችን የእርስ በእርስ ፉክክር ቁርሾና የዘር መተላለቅ ተከስቶ በዓለም ደረጃ ከርሃብተኝነትና ደንቁርና ተጭማሪ እሴት በዘር ማጥፋት ማፈናቀል ሀፍረትና ውርደትን ደምረናል!! ስለሆነም ከፖለቲካ ግርግር ይልቅ ቅድሚያ የምንሰጠው ለሀገሩ ዜጋ ሰላምና ደህንነት መልሶ ማቋቋም በመሆኑ፡ ከይቅርታ ጋር በሰላም ልንሸኛችሁ ወሰንን ይህም ሲባል ከመጣችሁበት ሀገር ተመልሳችሁ መንግስትን ማሳጣት፡ መወንጀል፡ ወይም ከሀገር ውስጥ በደል አለ የሚለው ጩኸት መሰማት አይኖርበትም!፡
    ምክንያቱም እናንተው እዚህ በአካል ተገኝታሁ ሀገር ሲረበሽ፡ ዜጋ ሲገደል፡ሲፈናቀል ሲሰለብ ንብረቱ ሲወድም ደጋፊዎቻችሁን እንኳ በወጉ ማስተባበርና ኅላፊነት መወሰድ አለመቻላችሁ ሀገርን ለናንተ መስጠት አለመቻሉን የመጣችሁባቸው ሀገራት ኤምባሲ ወኪሎች የዓለም አቀፉ ማኅበራት ሁሉ ዕለት ከዕለት እንቅስቃሴአችሁንና የሕዝቡን ተቃውሞ ያለውን የፀጥታ መደፈረስ መንስኤ ምን እና ማን ለም ተልዕኮ እንደሆነ የዓይን ምስክር ሆነዋል። ዜና መፍጠርና ማስተባበልም ሆነ ሌላውን መወንጀል አደጋ አለው።
    ስለሆነም በሕዝብ ወጪ በኢሕአዴግ ቤተመንግስት በነበራችሁ ልዩ መንስተንግዶና ሰላማዊ እንቀስቃሴያችሁ ደጋፊና ተደጋፊዎቻችሁን አግኝታችሁ ያሳላፋችሁት የተንፈላሰሰ ግዜ አጭር ቢሆንም በዘመነ የዲሞክራሲ የኢትዮጵያ ንጹሕ አየር እንዳስደሰታችሁ ከመግለጫና ከፎተግራፋችሁ፡ ከተለያዩ ባሕላዊ ልብስ ሽልማቶች፡ ጭፈራዎች ከምትወክሉት ባንዲራ ጋር ልዩ ደታና ፍቅር ትዝታ የሚያጭር ለትውልድ የሚተላለፍ ቅርስ እንደሆናችሁ የመጣችሁባቸው ዲፕሎማት ሀገሮች ሁሉ ደስተኛነታቸውን በመካከላችሁ ተገኝተው ፎቶ አብረዋችሁ በመነሳት አረጋግጠውልናል። ስለዚህ ቀሪው ዘመን ዜግነት ቀይራችሁ ኢህአዴግ ላይ ተደምሮ በሶስተኛ አማራጭነት ለመኖር ከሆነ ሀገራችሁ ነው….አትሂዱ አትገንጠሉ ተደመሩ….እኛ እንደፈለግነውና እንደመረጥነው ሥልጣን ተካፍለን ወይም ክልል ተቆርሶ ተሰጥቶን ካላስተዳደርን ዋ ! እናፈርሳለን! የሚሉ አስገዳጅ ሁኔታዎች ግን ቅድሚያ ለነዋሪው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ፍላጎትና ምርጫ ስለምንሰጥ፡ሕዝብ በመገንባት እንጂ በማፍረስ በመገደል በማፍረስ አላምንም ብሏልና ዓላማና ፍላጎታችሁን በምርጫ ባገኛችሁት ዜግነት ሀገር ላይ መተገበርን አንከለክልም! ኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲ ግለሰቦች ወይንም የአክቲቪስትና ሊህቃን ቡድን የግል ንብረት ሳትሆን ኢትዮጵያ የ ፻፭ ሚሊየን ሕዝብ ሀገር (እ)ናት ።አራት ነጥብ።”
    የመደመር ጽ/ቤት ዋና ኅላፊ ሌ/ኮ ዓብይ አህመድ አሊ
    ….ቢልና ይህንን ዲያስፐር ሁሉ በወታደር መኪና ጭኖ ቦሌ አየር ማረፊያ ቢያጉራቸውስ?
    የመጡበት ሀገር በረራ ሰዓት እስኪደረስ ቃለመጠይቅ ሲደረጉ፡ ወንበር ላይ ተጋድመው ማየት በራሱ ዲሞክራሲ ነው።
    ሰወዬው ሳይቸገረው በገዛ እግሩ ሄዶ መዘዝ ይዞ ይመጣል? አደለም እንዴ? ዋሸሁ እንዴ፧ ነን ሶቤ?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule