በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከመሬት ምዝበራ ጋር በተያያዘ ሁለት አመራሮችና ስድስት ባለሙያዎች በጥቅሉ ስምንት በሙስና የተጠረጠሩ አመራሮችና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በቁጥጥር ስር የዋሉ አመራሮች፦
1. አቶ መለሰ ጋሻው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ
2. አቶ ፍቃዱ መለሰ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የመሬት ማኔጅመንት ፅ/ቤት ሃላፊ ሲሆኑ
በቁጥጥር ስር የዋሉ ፈፃሚዎች ደግም
3. አቶ ሄኖክ ፍቃዱ (የመሬት አገልግሎት መሻሻያ ዘርፍ አስተባባሪ)
4. ሜሮን ማህረይ (የቤዝ ማፕ ባለሙያ)
5. አቶ በላይህ ተፈሪ (የቤዝ ማፕ ባለሙያ)
6. አቶ ፍቅሬ ብርሃኑ (ፋይል አደራጅ)
7. ወ/ሮ ዘላለም በዛብህ (የሲአይ ኤስ ባለሙያ)
8. አቶ ሃጎስ በርሄ (የሰነድ አጣሪ ባለሙያ) ናቸው፡፡
የተጀመረው ህግን የማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ የፀረ ሙስና ኮሚቴ ማስታወቁን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። (አዲስ ሚዲያ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply