በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሻ የተለያዩ ሽጉጦች እና ጥይቶች እንደተያዙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ::
በከተማዋ ጥቃት ለመፈፀም እና ሰላም ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ የሚያደርገውን ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ ሸንቁጤ እንደገለፁት ከቂርቆስ ወደ ቄራ አቅጣጫ በምሽት ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2A-41649 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ በክፍለ ከተማው ወረዳ 4 በተለምዶ 31 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲደርስ በፖሊስ አባላት ፍተሻ ሲደረግለት 4 የተለያዩ ሽጉጦች፣ 30 የክላሽ ጥይቶች ከነካርታው እና 39 የሽጉጥ ጥይቶች በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል፡፡
በህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ 3 ተጠርጣሪዎች ከነተሽከርካሪው ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ አስረድተዋል፡፡ ©የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply