
በኢትዮጵያ ያለው የደን መጠን ሽፋን ወደ 17 በመቶ ማደጉ ተገለጸ። ይህ የተነገረው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሦስተኛውን ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር መጠናቀቁን እሁድ ባሳወቁበት ጊዜ ነበር።
የመርሀግብሩን መጠናቀቅ አስመልክቶ ባሰራጩት አጭር መልዕክት፥ የሦስተኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ ያለን” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘንድሮው መርሀ ግብር 6.7 ቢሊየን ችግኞችን መተከላቸውን አሳውቀዋል፤ ይህም ከተቀመጠው ግብ ያለፈ መሆኑን ነው ያነሱት።
ከዚህ ከ2013 የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር መጠናቀቅ ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ የማጠቃለያ ስነስርዓት ዛሬ ተካሂዶ ነበር።
በዚህ ስነስርአት ላይ በሶስት ዓመታት ውስጥ ከ18 ቢሊየን የሚበልጡ ችግኞች መተከላቸው ተነግሯል ፤ በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በአራት ዓመታት ውስጥ 20 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ነበር የታሰበው።(tikvahethiopia)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ውሸታም አነሰ እንጂ በለጠ