የአጼ ምኒሊክን መቶኛ የሙት አመት መከበር ምክንያት በማድረግ በ DW ሬድዮ በተደረገው ጥያቄና መልስ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፣ ዶ/ር ሓይሌ ላሬቦና ዶ/ር ሹመት ሲሳይ (የታሪክ ተመራማሪዎች) ቃለ መጠይቅ ተደርጎ በሚሰጠው መልስ ላይ ስለ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በተናገሩት ላይ አስተያየቴን አቀርባለሁ። አንባቢያንን ቃለመጠይቁን ቢያዳምጡ ጥሩ ነው ባይ ነኝ፤ ሁለቱ የታሪክ ምሁራን ትምህርታዊ ትንተና ይሰጣሉና፡፡ ውሸት ሲደጋገም እውነት ሊመስል ይችላል፤ በተለይም የአገራችንን የኢትዮጵያን ታሪክ ለማያውቁ እውነታው ምን እንደሚመስል መረጃ ለማቅረብ እሞክራለሁ። አቶ ቡልቻ ኦሮሞ ከባሌ እየተስፋፋ ሲመጣ ልብነ ድንግል እንዳይስፋፋ አቆሙት ይላሉ፡፡ ለምን ይህን ምሳሌ እንዳቀረቡም ግልጽ አይደለም ለሳቸው ትንታኔ የማይመች በመሆኑ፤ ለዛውም በአጼ ልብነ ድንግልና በኦሮሞች መሀከል ስለነበረው ግኑኝነት … [Read more...] about አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ስለምኒሊክና ስለኢትዮጵያ
Uncategorized
ሰማያዊ ፓርቲ በአሜሪካ
በሳውዲ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ቀጥሏል
ሪያድ አሚራ ኑራ ዩኒቨርስቲ በሚገኝ ጊዜያዊ መጠለያ ሜዳ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል በተነሳ ግጭት አንዲት ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት በአውቶብስ ተገጭታ ህይወቷ አለፈ። ሪያድ መንፉሃ እየተባለ ከሚጠራ አካባቢ ሰሞኑንን በሳውዲ ፖሊሶች ታፍሰው ከከተማይቱ 120 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኝ፡ በተለምዶ ሚንዛህሚያ እየተባለ የሚጠራ እስርቤት ተወስደው ከነበሩ 10 ሺህ ኢትዮጵያውያን መሃከል ግማሽ ያህሉ በ17 አውቶብስ ተጭነው ማምሻውን ሪያድ ከተማ አሚራ ኑራ እየተባለ የሚጠራ ዩኒቨርስቲ ሜዳ ላይ መጣላቸውን ተከትሎ ከባድ ሁከት መቀስቀሱን ከሪያድ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህን ተከትሎ በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ በኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል ከባድ ግጭት መከሰቱን የሚገልጹት እነዚህ ምንጮች አዲት ነፍሰጡር ሴት ከድንጋይ ውርወራው … [Read more...] about በሳውዲ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ቀጥሏል
በሳዑዲ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት ለማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ
ከጥቅምት 26 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን የኃይል ጥቃት ለማውገዝ በአዲስ አበባ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠራ። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አባል ፓርቲዎች ትናንት በመድረክ ጽ/ቤት በስራ አስፈፃሚ ደረጃ ባካሄዱት አስቸኳይ ስብሰባ በሳዑዲ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሳዑዲ ፖሊስ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት መፈፀሙን፣ አልፎ ተርፎም እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን በመግለፅ ሁኔታውን አውግዟል። የችግሩ ክብደትና አሳዛኝነት በመቀጠሉ ድርጊቱን በመግለጫ ከማውገዝ ባለፈ ሁኔታውን በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ከመድረክ የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ በኋላ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንዳረጋገጡት መድረክ የጉዳዩን … [Read more...] about በሳዑዲ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት ለማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ
በታሪክ ውስጥ የሚሰሩ ስትራቴጂያዊ ስህተቶች
አምስተርዳምጉባዔላይለጥናትየቀረበጽሁፍ! 1.0 መግቢያ የታሪክ ግዴታ ሆኖ የሰው ልጅ እንደማህበረሰብ ከተደራጀና፣ ስልጣንና ሀብት በጥቂት ሰዎች ቁጥጥር ስር መውደቅ ከጀመረ ወዲህ የአንድ ህዝብ ዕድልና የወደፊት ጉዞው፣ ታሪክ የመስራትና ያለመስራት ችሎታው በመጀመሪያ ደረጃ ሊወሰን የሚችለው ስልጣንን በቁጥጥራቸው ውስጥ ባስቀመጡ ጥቂት ሰዎች አማካይነት ነው። በታሪክ ውስጥ አንድ ህዝብ ከአንድ አገዛዝ ቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ የራሱን ህይወት በነፃ ያደራጀበትና ታሪክ የሰራበት በተለይም ቀደም ብለው በነበሩ ስርዓቶች ውስጥ አልነበረም። እንደሚታወቀው የአንድ አገዛዝ ምንነት የሚታወቀው ታሪክ ለመስራት ባለው ችሎታና አገርን ጥበባዊ በሆነ መልክ በማስተዳደር ረገድ ነው። አንድ አገዛዝ ታሪክን እንዲሰራ ከፈለገ ደግሞ ንቃተ-ህሊናው በጣም ወሳኝ ነው። በታሪክ ውስጥ በአንድ ማህበረሰብ … [Read more...] about በታሪክ ውስጥ የሚሰሩ ስትራቴጂያዊ ስህተቶች
ኢትዮጵያን እንደገና ማነጽ
መግቢያ የዛሬው የመወያያ ሃሳብ ኢትዮጵያን እንደገና ለማነጽ ኣዲስ የማህበራዊ ፖለቲካ መዋቅር በማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ ነው። ይህ መዋቅር ኢትዮጵያን ወደ ኣዲስ ኪዳን የሚጋብዝ ነው። ኢትዮጵያ የገጠማት የከፋ ችግር በኣብዛኛው ከታችኛው የማህበራዊ ፖለቲካ (socio politics) መዋቅር ጋር የተገናኘ በመሆኑ በዚህ ላይ ኣማራጭ ሃሳብ ማምጣት በተለይ ይህ የኣሁኑ ትውልድ የሚጠበቅበት ይመስላል። ያለፉትን ችግሮች ኣስር ጊዜ እያወጣን ብናወርዳቸው ድካም ብቻ ይሆንብናልና። በተለምዶ ያ ትውልድ እያልን የምንጠራው ቀዳሚው ትውልድ ኣንድ የሆነ ሼል ሰብሮ የወጣ ነበር። ያ ትውልድ ለዘመናት የነበረውን ዘውዳዊ ኣገዛዝ ደፍሮ የጠየቀ፣ የፍትህና የእኩልነትን ጥያቄዎች ኣንግቦ ግንባሩን ለጥይት የሰጠ በመሆኑ ታሪክ ሁልጊዜም ያ ትውልድ..........እያለ ሲያስታውሰው እንዲሁ ይኖራል። (ሙሉውን … [Read more...] about ኢትዮጵያን እንደገና ማነጽ
ከአንድነቶች ሶስት ወር ዘመቻዎች የተማርናቸው!
የህውሃት/ኢህአዴግ ጠንካራ ጎኑ እስከ ጥርሳቸው ድረስ የታጠቁት ፖሊስ፣ ድህንነት፣ ምድር ጦር፣ አየር ኃይል፣ አየር ወለድ፣ ካድሬ እና ቅጥረኛ ወርበሎችን ያካትታል። የሚያውቀው የፖለቲካ ትግል ዘዴ በጫካ መገዳደልን እንጂ በከተሞች ሰላማዊ ትግሎች ማድረግ አይደለም። ስለዚህ ሰላማዊ ትግል ህውሃት/ኢህአዴግን በማያውቀው የትግል ሜዳ፣ የትግል ዘዴ እና በደካማ ጎኑ እንዲታገል እንደሚያስገድደው እና የህዝብ ድጋፍ የሚያሳጡ ስህተቶች እንደሚያሰራው የአንድነቶች የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ወለል አድርጎ አስተምሮናል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ) … [Read more...] about ከአንድነቶች ሶስት ወር ዘመቻዎች የተማርናቸው!
ዲሲ 2013
ስለ ኢትዮጵያውያን ብዙ የሚያውቁ ፈረንጆች ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ጠንቀቆ ማወቅ በጣም አስቸጋሪ እና ከባድ እንደሆነ ይናገራሉ። "ስለ ሕዝቡ ለመጻፍ የሚፈልግ አንድ ሰው ኢትዮጵያ በገባ ማዕግስት አንድ መጽሃፍ ሊጽፍ ይችላል፤ ይህ ሰው ሳምንት ሲቆይ አንድ መጣጥፍ ይጽፋል፣ ወር ሲቆይ ግን የሚጽፈው ይጠፋበታል።" ይላሉ። ይህ አባባል በከፊል ትክክል ይመስለኛል። ኢትዮጵያ የብዙ ባህል፣ የብዙ ቋንቋና የበርካታ እምነት ሃገር ስብስብ በመሆንዋ ታሪኳን ጠለቅ እያልን ለማወቅ በሞከርን ቁጥር ሊወሳሰብ ስለሚችል እጅግ ብዙ ጥናት ማድረግ ይገባል ለማለት ነው። ጸሃፊው ለረጅም ጊዜ በቆየ ቁጥር የሚጽፈው ጠፍቶት ሳይሆን ግራ ተጋብቶ መጻፉን ያቆማል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ዲሲ 2013
የሙስና ምርመራ እየተወሳሰበ ነው!
በጉምሩክና ገቢዎች ባለስልጣን የተጀመረው የጸረ ሙስና ዘመቻ ተከትሎ እየተካሄደ ያለው ምርመራ እየተወሳሰበ መሔዱ ተሰማ። በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ተከሳሾች የሚሰጡት መረጃ መበላላት ያስነሳል የሚል ፍርሃቻ እያስነሳ ነው። “ሰፈር የለየው” የጸረ ሙስና ዘመቻ የፈጠረው ስጋት የሃይል ሚዛን የያዙትንም ስጋት ውስጥ ከትቷል። በኢትዮጵያ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ የታየው የውስን ሰዎች በድንገት በመበልጸግ ከባለስልጣኖችና ከከፍተኛ የስርዓቱ ሰዎች ቤተሰቦች ጋር በሚከናወን መተሳሰር አማካይነት እንደሆነ ከህዝብ የተሰወረ አይደለም። ሰሞኑንን ይፋ የተደረገው የባንክና የንብረት እግድ እንዳመለከተው የዝርፊያው ሰንሰለት በቤተሰብ የታጠረ መሆኑን ነው። አቶ መለስ ከድነው ያቆዩትና የሳቸውን ሞት ተከትሎ ከፖለቲካው ልዩነት ጋር በተያያዘ እንደተጀመረ የሚነገርለት የጸረ ሙስና ዘመቻ፣ … [Read more...] about የሙስና ምርመራ እየተወሳሰበ ነው!
የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን አረጋገጠ
ከ፩፯ አመት የደርግ የጭቆና አገዛዝ ማብቂያና ስርአቱ ካበቃበት ከ፩፱፰፫ ወርሐዊ ግንቦት ጀምሮ ለ፪፪ አመታት የስርአቱን ለዉጥ ተከትሎ ስልጣንላይ በሀይል ተቆናጦ ያለዉ የህወሐት መንግስት አምባገነንነቱ ወደ አፓርታይድ ስርአት ተቀይሮዋል። ለዚህም ማሳያዉ ላለፋት ፪፩ አመታት በሙዋቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ መሪነት በሐገሪቱዋ ዉስጥ እጅግ ኢሰብአዊ ድርጊት ዘርንና ክልልን መሰረታዊ ያደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል አሁንም እየተፈፀመ ነዉ። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን አረጋገጠ









