• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“በመንግሥታችን ምክንያት አገራችን ተከፋፍላለች” ቴዲ አፍሮ

July 14, 2017 04:12 pm by Editor 2 Comments

  • ቴዲ “የአማራ ሙዚቀኛ በመሆን ቀጥሏል” ዘ ጋርዲያን
  • “ወቅቱ አደገኛ ነው፤ አሁን እኔ ቅድሚያ የምሰጠው ለኢትዮጵያ ነው” ቴዲ

የፍቅር፣ የዕርቅና አንድነትን መልዕክት በማንገብ ዘፈን ዘፍኖ ገንዘብ ከመሰብሰብና ታዋቂ ከመሆን በላይ የሚለፋው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አዲሱ አልበሙ ከወጣ በኋላ ከእንግሊዙ ጋዜጣ ዘ ጋርዲያን ጋር ባደረገው ቃለምልልስ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ቁልጭ አድርጎ ተናግሯል፡፡ “በመንግሥታችን ምክንያት አገራችን ተከፋፍላለች” ያለው ቴዲ “የአፍሪካ ሞዴል ነበርን” በማለትም የቀደመውን የኢትዮጵያን ታላቅነትና ክብር አስታውሷል፡፡

በቅርብ የተለቀቀውን “ኢትዮጵያ” አልበም በተመለከተና ስለ አገሩ እንዲሁም ስለ ራሱ የህይወት ፍልስፍና የዜና ዘገባ ያወጣው ዘ ጋርዲያን ቃለ ምልልሱን ያደረገው በቴዲ የመኖሪያ ቤት በመገኘት ነበር፡፡ ስለ ቴዲ የቀድሞ ሥራዎች፣ ሰው ገጭተህ ገድለሃል በሚል ክስ ተመሥርቶበት በእስር ስላሳለፈው ህይወቱ፣ አዲሱ አልበሙ በሽያጭ ቀዳሚነትን የያዘ ስለመሆኑ ወዘተ በርካታ ጉዳዮችን በዘገባው አካትቷል፡፡

“ወጣቱ ትውልድ ያለፈውን ታሪኩን በተመለከተ አጣብቂኝ ውስጥ ነው ያለው፤ (የአገራችንን) መልካም ታሪክ የማስተማር ኃላፊነት እንዳለብኝ ይሰማኛል፤ (ወጣቱ) ስላለፈው ታሪክ ስኬት ኩራት ሊሰማው ይገባል” በማለት የተናገረው ቴዎድሮስ ካሳሁን አዲሱ አልበሙ ይህንኑ የኢትዮጵያን የቀድሞ ገናናነት እንደገና በማስታወስ ለአንድነት ጥሪ የሚያደርግ ሥራ መሆኑን ተናግሯል፡፡

በእነዚህና ሌሎች የቴዲ ሥራዎች ላይ ጋዜጣው ትንታኔ ከሰጠ በኋላ ኢትዮጵያን ለመከፋፈል የኖረ ምኞት እንዳላቸው አውሮጳውያን አቅጣጫውን በመቀየር ቴዲ አፍሮን ከአጼ ቴዎድሮስ፣ ምኒልክና ኃይለሥላሴ ጋር በአንድ የዘር ቋት ውስጥ መድቦ ሲያበቃ ሁሉንም አማራ በማለት ከመሰየም አልፎ ቴዲንም የአማራ ብሔረተኝነትን ናፋቂ አድርጎ አቅርቦታል፡፡ ለዚህ አስተሳሰቡ ደጋፊ ማስረጃ ለማድረግም በቴዲ ክፍሎች ውስጥ የምኒልክ ጎራዴ፣ የኃይለሥላሴ ዘመን ሠንደቅ ዓላማና የሳቸው ፎቶ መኖሩን አብሮ አስፍሯል፡፡ ለዚህ መሰሉ ፍረጃ ቴዲ የሰጠው መልስ “ወጣቱ ትውልድ አባቶቹ ለዚህች አገር ምን እንዳደረጉ ማወቅ አለበት፤ ምኒልክ ለዚህች አገር፣ ለአንድነት እና ለጸረ ቅኝአገዛዝ መዋጋታቸው ግልጽ ነው” በማለት ኢትዮጵያዊ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ዓላማ ይዞ የተነሳ የሚመስለው ጋዜጣ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ 88 ቋንቋዎች የሚነገሩ ቢሆንም ቴዲ ግን “የአማራ ሙዚቀኛ በመሆን ቀጥሏል” በማለት ቴዲን በዘር ሣጥን ውስጥ ከቶታል፡፡ በመቀጠልም “ከታዋቂዋ የአማራ ድምጻዊት ሒሩት በቀለ” ጉልበቶች ላይ ቁጭ ብሎ እሷ ስትዘፍን ያዳምጥ እንደ ነበር ማስታወሱን ዘግቧል፡፡ ይህ የጋዜጣው ዘገባ አገላለጽ የቀደሙትንም ሆነ አዲሶቹን የኢትዮጵያ ድምጻዊንን በህወሓት/ኢህአዴግ የዘር መስፈሪያ ውስጥ አስገብቶ ለማጥበብ የሞከረ ሆኖ ማግኘታቸውን ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ ገልጸዋል፡፡

ጋዜጣው በማጠቃለያው የቴዲ ሙዚቃ ቅንብሮች ከኢትዮጵያና ከዳያስፖራው ባለፈ መልኩ በዓለምአቀፍ መድረክ ላይ የማይሰሙ መሆናቸውን ከገለጸ በኋላ ምክንያቱንም ሲያስረዳ ቋንቋውም ሆነ የሙዚቃው ስልት ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ነው ብሏል፡፡ ከዚህ አልፎም ቴዲን ከሙላቱ አስታጥቄና መሐሙድ አህመድ ጋር በማነጻጸር የቴዲ ሥራዎች እንደ ሁለቱ አርቲስቶች ለምዕራባውያን አድማጮች ቅቡል አለመሆናቸውን ላነሳው ሃሳብ እንደ ተጨማሪ ማድመቂያ አቅርቧል፡፡ ለዚህ ግን የቴዲ ምላሽ “ወቅቱ አደገኛ ነው፤ አሁን እኔ ቅድሚያ የምሰጠው ለኢትዮጵያ ነው” ብሏል፡፡

እንደ ሃሳብ፤ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ቴዎድሮስ ካሳሁን ኢትዮጵያዊ ድምጻዊ እንደሆነ ያምናል፡፡ በዚህ የ “ዘ ጋርዲያን” ዘገባ ላይ ቴዲን የአማራ አርቲስት ተድርጎ የቀረበው ሃተታ አግባብነት አለው ብለን አናምንም፡፡ የቴዲ አፍሮ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለዚህ የተዛባ አቀራረብ ማስተካከያ ይሆን ዘንድ በተለይ ለ “ዘ ጋርዲያን” ምላሽ ቢሰጥ ሃሳብ እናቀርባለን፡፡ (Photograph: Mulugeta Ayene AP)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News, Politics Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. አለም says

    July 15, 2017 04:17 pm at 4:17 pm

    ውድ ጎልጉል፣ ቶም ለተሰኘ ለ”ዘ ጋርድያን” ጸሐፊ ሁለት ጊዜ ማብራርያ ጽፌ ሁለቱንም ጊዜ ሠርዞታል። የመጀመሪያ ቅሬታዬ በሙዚቃው ዓለም ጥላሁንን አለማንሳት አይቻልም የሚል ነው። ሁለተኛው የአገራችንን ታሪክ አለማወቁ መሐሙድ አማራ ሙዚቀኛ አይደለም፤ በአማርኛ ግን ይዘፍናል። በትግርኛ ቢዘፍን አድማጭ 100 ሺህ ሰው አይሞላም [ከትግራይ 4 ሚሊዮን ሕዝብ ሁሉም ሬዲዮ አለው ሁሉም ያደምጣል ካላልን በስተቀር]። በወላይትኛም፣ ወዘተ። አማርኛ ብዙ ሰው የሚሰማው ስለሆነ፣ ከገበያም አንጻር። በበአንጻሩ ዴጃቩ እና አባዲ ለተባሉት ሠፊ መድረክ ሰጥቶአቸዋል። ለ ዘ ጋርድያን ዋና አርታኢ ቅሬታ ማቅረብ ይኖርብናል።

    Reply
    • Editor says

      July 15, 2017 04:57 pm at 4:57 pm

      መልካም ብለዋል አለም። ሌሎችም የርስዎን አርአያነት ቢከተሉ የሚበጅ ይመስለናል። ከሁሉ በላይ ግን የቴዲ አፍሮ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ጋዜጣውን ቢያነጋግር የተሻለ መፍትሔ ያመጣል ብለን እናምናለን።

      ጊዜዎን ወስደው ስለላኩልን አስተያየት እናመሰግናለን።

      የጎልጉል አርታኢ

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule