የጎልጉል ማሳሰቢያ፡ ይህንን ጽሁፍ የላኩልን ሰላማዊት አሰፋ ይባላሉ፡፡ ስለጽሁፉ ይዘት እኛ ከምንናገር ይልቅ አንባቢዎች የራሳቸውን ግንዛቤ እንዲወስዱ ለንባብ አትመነዋል፡፡ ጸሐፊዋን በግል ለማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ በቀጥታ በዚህ አድራሻ ለመጻፍ ይችላሉ (a_selamawit53@yahoo.com) ይህንን ጽሁፍ አስመልክቶ በጨዋነት የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት የሚፈልጉ ሁሉ የሚልኩልንን ጽሁፍ እንደምናትም ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ! ሀገራችን ኢትዮጵያ በጠባብ ዘረኞች መዳፍ ስር ከወደቀች እነሆ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ተቆጠሩ። ህዝባችንም ቢሆን በዋነኛነት በዘር እንዲከፋፈል ተደርጎ እርስ በርሱ እንዳይተማመን ይልቁንም በጠላትነት እንዲተያይ ከመደረጉም ባሻገር በፖለቲካና በማህበራዊ ጉዳይ በገዛ ሀገሩ ባዕድ እንዲሆን ተደርጓል።በኢኮኖሚውም ቢሆን ኑሮው … [Read more...] about አካፋን አካፋ እንላለን!!!
ኦባማ አርፍደው ወደ ኢትዮጵያ?
በአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ከሚገኙት የተለያዩ እንግዶችና ባለስልጣናት በተጨማሪ አራት ታላላቅ መሪዎች እንደሚገኙ እየተነገረ ነው። በዋናነት የሚጠቀሱት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ኦባማ ሲሆኑ፣ የቻይና አቻቸውም ዋናውና ታላቁ እንግዳ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ባለፈው ረቡዕ ለአሜሪካ ኮንግረንስ ኮሚቴ የተናገሩትን በመጥቀስ ዜናውን የላኩልን ክፍሎች እንዳሉት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ሊያመሩ ይችላሉ። ውጪ ጉዳይ ሚ/ሩ ኦባማ ኢትዮጵያ ስለመሄዳቸው ፍንጭ ቢሰጡም ስለጉዞው ዝርዝር አለመናገራቸው ታውቋል። የቻይና በአፍሪካ ሚና መጉላት ውሎ አድሮ የጠዘጠዛት አሜሪካ፣ በመጪው ወር በሚካሔደው የአህጉሩ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ በፕሬዚዳንቷ ለመወከል መወሰኗ "ጉባኤ አድማቂ" አሰኝቷታል። "በአፍሪካ ብዙ የምንሰራው ስራ አለን" ሲሉ የተናገሩት ኬሪ … [Read more...] about ኦባማ አርፍደው ወደ ኢትዮጵያ?
50 Ethiopian immigrants sentenced to lengthy jail term with hard labor in Zambia.
Victims of human smugglers . . . Kembatta Ethiopians flocking south in search of better life. Although the word “hard labour” sounds brutal and primitive, Zambian magistrate Shadreck Chanda was merciless in passing judgment when he sent 50 destitute Ethiopians to jail for entering the landlocked nation illegally on 29 March 2013. The Ethiopians aged 11 to 37 were caught by Zambian police at Nakonde Border post, according to the Post online website, an online Zambian paper April 21st … [Read more...] about 50 Ethiopian immigrants sentenced to lengthy jail term with hard labor in Zambia.
ግንባር፣ ትስስረ-ትውልድ እና የኢትዮጵያ ስነ-አስተዳደር
እስከመቼ ለተለያዩ ድርጅቶችና የሚዲያ አካላት የጻፈው ደብዳቤ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡ ንጥር ዘገባ “የሚሠራ ምንም አያወራ” በሀገራችን ውስጥ ከግማሽ ምዕት ዓመት በላይ የስነ-አስተዳደር ትግል በተለያየ መልክና ቦታ ሲካሄድ ቆይቷል። በዚህ ወቅት በተደረጉትና አሁንም እየተደረጉ ባሉት ትግሎች፤ የተለያዩ ድርጅቶች ከመሰሎቻቸው ጋር ጊዜያዊም ሆነ ረጅም ዕድሜ ያለው ትብብር መሥርተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ፤ ዘለቄታ ያለው ግንባር መሥረቶ አብሮ የመሥራት፤ አልፎም መዋኀድ ጎልተው አይታዩም። ይልቁንም አንድ የነበረ*፫ ድርጅት ሲከፋፈል ማየቱ የተለመደ ሆኗል። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) ፡ … [Read more...] about ግንባር፣ ትስስረ-ትውልድ እና የኢትዮጵያ ስነ-አስተዳደር
ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ
“ኢሳታዊ ሐረካት???” ምን? ጉድ ፈላ። ግዕዙን አረብኛ ተካው ልበል?! ቅዱስ ሚካኤል ወይም ቅዱስ ገብርኤል ሳይሆን፣ ወያኔ ሰሞኑን ክንፉን የዘረጋላቸው የሎንደን ደብረጽዮን ቅድስት ማርያም ጥቂት “ካህናት” በየውሸት መነኲሴው አመራር፣ ጭራሹኑ ሐፍረታቸውን ጥለው፣ ቤተክርስቲያኒቱን በዚህ ዓቢይ ጾም ጥርቅም አድርገው መዝጋታቸው ሳያንስ ወያኔ ብብት ውስጥ ለመሸሸግ ተጥግተው ገና የእግራቸው ጢዛ ንእንኳን ጠፈፍ ሳይል፣ ቋንቋውን አቀላጥፈው መናገር ጀመሩ። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ
The Economy of Renaissance – An African Perspective
This article is presented in power point but we have converted it to PDF and attached it here. … [Read more...] about The Economy of Renaissance – An African Perspective
ከእሁድ እስከ እሁድ
በሲዳማ ህዝብ እያመጸ ነው ሚያዚያ 6 ቀን 2005 ዓ ም ኢህአዴግ ብቻውን ሊያካሂደው የነበረውን ምርጫ አንቀበልም በማለት ከተለያዩ ወረዳ በትስስር የተቃወሙ የሲዳማ ብሔረሰብ አባላት መታሰራቸውን የጎልጉል ምንጮች አስታውቀዋል። ምንጮቹ እንዳሉት በአካባቢው ከፍተኛ ድጋፍ ያለው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ከምርጫው ራሱን ማግለሉ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንዳገኘም አመልክተዋል። በቀበሌ የመሰብሰቢያ አዳራሾች የታጎሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው የብሔረሰቡ አባላት እንዲፈቱ በሚጠይቁና በታጣቂ ሃይሎች መላከል የተካረረ ግጭት ይነሳል የሚል ፍርሃቻ እንደነበር ያመለከቱት ምንጮች የሲዳማ ተወላጆች የታጠቁ ስለሆነ ኢህአዴግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ አንጋቾችን ማሰማራቱን አመልክተዋል። ለምርጫው አንድ ቀን ሲቀረው እጩዎቼ፣ ታዛቢዎቼና አባላቶቼ በእስር፣ በድብደባና ከሥራ በመባረር እየተንገላቱ ነው … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
“ማፈናቀሉ የሚካሄደው በመንግሥት ትዕዛዝ ነው፤ ወደ ክስ እናመራለን”
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ2000 ሺህ በላይ ትግሬዎች ባለይዞታ መሆናቸውንና ማንም ሳይነካቸው በሰላም እንደሚኖሩ፣ በቶጎ ወረዳ ከስልሳ በላይ ነባር የህወሃት ታጋዮች ሰፋፊ የእርሻ መሬት ወስደው በባለሃብት ደረጃ እንደሚገኙ የመኢአድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አስታወቁ። ከሌሎች ብሔረሰቦች ተለይቶ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ያለውን የአማራ ብሔረሰብ በድጋሚ ለማስወጣት መታቀዱንም በመረጃ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል። በቦታው በመገኘት አስፈላጊውን መረጃ እንደሰበሰቡ ለአሜሪካ ሬዲዮ የገለጹት የመኢአድ ስራ አስፈጻሚ በክልሉ ከሚኖሩት የተለያዩ ብሔረሰቦች ተለይቶ የአማራ ብሔረሰብ እንዲፈናቀልና እንዲሰቃይ የሚደረገው በማዕከላዊ መንግስት ትዕዛዝ እንደሆነም አመልክተዋል። መኢአድ ያሰራጨውን መግለጫ ተከትሎ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ሃይሉ ሻወል፣ ድርጊቱ በበታች … [Read more...] about “ማፈናቀሉ የሚካሄደው በመንግሥት ትዕዛዝ ነው፤ ወደ ክስ እናመራለን”
Land Grab Destroy Lives and Futures of Africans
I would like to thanks Congressman Christopher Smith, Chairman of the U.S. House Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights and International Organizations and members of the subcommittees for making this briefing on land grabs in Africa possible. I am honored to be among those invited to talk about the impact of these land and resource grabs on the people of Africa. It is a vitally important issue that needs to be confronted. To me, this is not just about land grabs, but it is … [Read more...] about Land Grab Destroy Lives and Futures of Africans
ኢህአዴግን በጓሮ ድርድር የጠየቀበት ሰነድ ተተረጎመ!
በልማትና ኢንቨስትመንት ስም ኢህአዴግ ለውጪና ለራሱ ሰዎች እየቸበቸበ ያለውን መሬት አስመልክቶ የኦክላንድ ተቋምና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በጋራ ያዘጋጁት ጥናታዊ ዘገባ አማርኛ ትርጉም በሳምንቱ መጨረሻ ይፋ ይደረጋል ተባለ። የመሬት ነጠቃ ዜጎችን እያፈናቀለና ውድ የተፈጥሮ ሃብትን እየበላ ነው። እመራቸዋለሁ ለሚለው ህዝብና አገር ደንታ የሌለው ኢህአዴግ፣ በመረጃ ለሚያጭበረብራቸው ዜጎች የተሟላና የተመጣጠነ ዘገባ እንደሚያቀርብ የተነገረለት ይህ ሰነድ በአማርኛ ተተርጉሞ ይፋ እንደሚሆን የገለጸው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ዴስክ ነው። የጋራ ንቅናቄው የህዝብ ግንኙነት ዴስክ በተለይ ለጎልጉል በሰጠው መረጃ በጥናቱ ሰለባዎች፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ ኢንቨስተሮች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ክፍሎች፣ የቅርብ ምስክሮች፣ የተለያዩ ከዓለምአቀፍ ተቋማት … [Read more...] about ኢህአዴግን በጓሮ ድርድር የጠየቀበት ሰነድ ተተረጎመ!